ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ "

  • Home
  • Qatar
  • Doha
  • ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ "
Directions Contact the organization

ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው  " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ " 💚💛❤️ አምላኬ ኳታር ቅድስት ሥላሴን ሳልጨርስ የትም አትውሰደኝ ::

21/10/2026

ለኢምግሬሽን አድርሱልኝ

20/10/2026

ይህ የብዙዎቻችን ችግር ነው ::

14/10/2026

🚨 በኳታር ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ 🚨
ፓስፖርትዎ ሊያበቃ ከ6 ወር በታች ቀርቶታል? እንግዲያውስ ነገ ዛሬ ሳይሉ አሁኑኑ ያሳድሱ!
የፓስፖርትዎ ጊዜ ካለቀ :

🪪 የመኖሪያ ፈቃድ (QID) ለማደስ ወይም ለማዛወር ይቸገራሉ፣

✈️ ወደ ሀገር ቤት ለመጓዝም ሆነ ለድንገተኛ ጉዞ በረራ ይስተጟጎላሉ ፣

💵) ያልታሰበ ቅጣት ወይም አላስፈላጊ ውጣ ውረድ ውስጥ ይገባሉ።

ስለዚህ ጭንቀትና ወረፋ ሳይኖርቦት፣ ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎት እንሰጥዎታለን።

📞 ለበለጠ መረጃ እና ቀጠሮ አሁኑኑ ይደውሉልን፦
👉 +974 66706055
💬 WhatsApp: wa.me/97466706055

🚉 አስተማማኝ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ከእኛ ዘንድ ያገኛሉ!

📍አድራሻችን ሜዘር ከፖልምስ ሞል ፊት ለፊት

05/10/2026

🛂አዲሱን ኢ ፓስፖርት ይፈልጋሉ ?

ላሊበላ ሰርቪስ አዲሱን የ ኢ ፓስፖርት እድሳት ቅጾችን መሙላት ክፍያዎችን መፈፀም እና ተያያዥ ሂደቶችን በፍጥነት እና በጥራት እናከናውናል።

📝ቢሮአችን ዘወትር ክፍት ሆኖ እርስዎን ለማስተናገድ ዝግጁ ነው።

📲ስልክ፡ 66706055 በዋትስአፕ ይፃፉልን
📍አድራሻ ሜዘር ከፓልምስ ሞል ፊት ለፊት

🌟 በመላው አለም የምትኖሩ ውድ ቤተሰቦቼ እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ :: የመስቀሉ ብርሐን በቤታችን በልባችን ይግባ ::መልካም በዓል ይሁንልን !!
27/09/2026

🌟 በመላው አለም የምትኖሩ ውድ ቤተሰቦቼ እንኳን ለብርሐነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ ::

የመስቀሉ ብርሐን በቤታችን በልባችን ይግባ ::
መልካም በዓል ይሁንልን !!

🕊️💍 እንኳን ለዚህ ታላቅ የክብርና የበረከት ቀን አበቃችሁ! 💍🕊️«እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው» እንዲል ቃሉ፤ በሊቃነ ጳጳሳት እጅ ተባርካችሁ፣ በካህናትና በሊቃውንት ጸሎት ታጅባች...
20/09/2026

🕊️💍 እንኳን ለዚህ ታላቅ የክብርና የበረከት ቀን አበቃችሁ! 💍🕊️

«እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው» እንዲል ቃሉ፤ በሊቃነ ጳጳሳት እጅ ተባርካችሁ፣ በካህናትና በሊቃውንት ጸሎት ታጅባችሁ፣ በቅድስት ቤተክርስቲያን የተፈጸመው ሥርዓተ ተክሊላችሁ እጅግ ያማረና ልብን በሐሴት የሞላ ድንቅ መንፈሳዊ በዓል ነበር።

የቤተክርስቲያናችን የዕውቀት ብርሃን የሆንከው ወንድሜ መምህሬ መጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ እና ውድ ባለቤትህ ወ/ት ሣምራዊት መልአኩ፤ ያደረጋችሁት የፍቅር ቃል ኪዳን የተባረከ፣ አዲሱ ቤታችሁም የሰላምና የደስታ ይሁንላችሁ።

🌿 ልዑል እግዚአብሔር ትዳራችሁን እንደ አብርሃምና እንደ ሣራ ያድርግላችሁ፣
🕊️ ቤታችሁን በፍቅር፣ ይሙላው፣ የተቀዳጃችሁት አክሊል ለዘላለም በደስታና በሰላም አብቦ ይኑር! መልካም፣ የተቀደሰና የተባረከ የትዳር ዘመን ይሁንላችሁ! 🤍🥂

20/09/2026

የ10ኛ ዓመት መታሰቢያ የአባቴን የገብረማርያምን ነፍስ ይማርልኝ !!

10/09/2026

ውድ ቤተሠቦቼ እንኳን ለ2019 ዓመተ ምሕረት ለአዲሱ ዓመት በሠላም እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን !!

ዘመኑ የሠላም የፍቅር የበረከት እንዲሆን እመኛለሁ መልካም በዓል ይሁንልን !!

እንዲህም ዓይነት ክብር አለ ለካ... 🥹🙏🏽የጀርመን ክሮንበርግ ደብረ ኃይል ቅድስት በዓታ ለማርያም፣ ቅዱስ ኡራኤል ወቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን "ልጃችን እንኳን ተወለድክ" ብለው እጅግ ባል...
22/08/2026

እንዲህም ዓይነት ክብር አለ ለካ... 🥹🙏🏽
የጀርመን ክሮንበርግ ደብረ ኃይል ቅድስት በዓታ ለማርያም፣ ቅዱስ ኡራኤል ወቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን "ልጃችን እንኳን ተወለድክ" ብለው እጅግ ባልጠበቅኩት መንገድ ልደቴን ሁለት ጊዜ አከበሩልኝ!
አንደኛ፦ በዕለተ ቀኑ ላይቭ ላይ ረጅም ሰዓት ብቆይባቸውም፣ እስክወጣ በትዕግስት ጠብቀው የማይረሳ ትዝታ እንዲኖረኝ አደረጉኝ።
ሁለተኛ፦ በደብሩ ተገኝቼ «ዛቲ ይእቲ ማርያም» ብለን የዕለቱን መዝሙር አንስተን፣ የእመ አምላክን ፍቅር እና እናትነትን ተምረን ስንወጣ... ፍጹም ባልጠበቅኩት ሁኔታ ዳስ ተጥሎ፣ ህጻናት እና ማዕከላውያን ሰንበት ተማሪዎች ከቅዱስ ያሬድ ማኅበርተኞች ጋር ተጣምረው፣ መዝሙር አዘጋጅተውና ኬክ አስደፍተው ስጦታ አዘጋጅተው ያልተጠበቀ ፈንጠዝያ ፈጠሩብኝ! 🎉🎂

ምን ማለት እንዳለብኝ ራሱ አላውቅም። እኔ ለራሴ አድርጌው የማላውቀውን ነገር በዚህ ልክ እና ክብር አድርገው ማክበራቸው በእጅጉ አስደንቆኛል። ምን እላለሁ... በእውነት ቃላት ያጥሩኛል!

ልዩ እና ከልብ የሆነ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፦
ለደብሩ አስተዳዳሪ ለመልአከ ፀሐይ የኔታ ኢሳኢያስ፦ የኔ ትሑት እና እጅግ የሚያሳሱ አባት ከነልጆቻቸው ክብር ያድልልኝ።

ለቄሰ ገበዝ ግሩም፦ የኔ ብርታት ሁሌም ፍቅርዎ አይለየኝ።
ለመልአከ ህይወት ነቅአጥበብ እና ለመልአከ ሰላም መሠረት።

ለምስኪኑ እና ቅኑ ወንድሜ ለመሪጌታ ዳንኤል ከነእህቱ።
ለዘማሪት ማኅሌት፣ ለቅዱስ ያሬድ ማኅበር ሞተር ለሆነችው ፍርዬ እና ለመምህር ቃልአብ እና ለደብሩ ሰበካ ጉባኤ።
ለጽጌ ሀይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች።
እንዲሁም ዙሪያዬን ከባችሁ በደስታ እና በሳቅ ላደመቃችሁኝ ማኅበረ ምዕመናን በሙሉ... እግዚአብሔር ያክብርልኝ! 🙏🏽✨

እህቶቼ ኤሚዬ ፍርቲ እና ዊዊዬ ከነ ባለቤቶቻችሁ አትጠገቡም

Address

Doha
90945

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ " posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ ":

Shortcuts

Share