Angetamabo -አንገታም አቦ

Angetamabo -አንገታም አቦ የገጠር አብያተ ክርስትያን ህዝበ-ክርስቲያኑ እንዲያሰራ ለማስተባበር እነዲሁም እኛም የድርሻችንን በመወጣት በረከተ ነፍስ ለማግኘት ነው፡፡

††† እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እና ለጻድቁ አባ ዮሐንስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††...
06/19/2026

††† እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እና ለጻድቁ አባ ዮሐንስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት †††

††† ቅዱስ ገብርኤል :-
¤በራማ ከሚኖሩ ሊቃናት አንዱ::
¤አርባብ በሚባሉ አሥር ነገዶች ላይ አለቅነትን የተሾመ::
¤የስሙ ትርጓሜ "እግዚእ ወገብር" (ጌታና አገልጋይ) አንድም "አምላክ ወሰብእ" (የአምላክ ሰው መሆን) ማለት የሆነ::
¤በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን ዘጠና ዘጠኙን ነገደ መላእክት ያረጋጋ::
¤ብርሃናውያን መላእክትን የሚመራ::
¤በብሉይም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት አብሣሪነቱ በስፋት የተነገረለት::
¤በተለይ ደግሞ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው የመሆን ዜና ይሸከም ዘንድ ያደለው::
¤ከድንግል ማርያም ጎን በፍጹም የማይርቅ::
¤በፈጣን ተራዳኢነቱ ብዙ ቅዱሳንን ያገለገለ ታላቅ ቀናዒ መልአክ ነው::

በዚሕች ዕለት እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ባቢሎን ልኮታል:: ሊቀ መላእክት ነቢዩ ዳንኤልን ከአናብስቱ ጥርስ እንዳዳነው መጽሐፍ ነግሮናል::

ይልቁኑ ታላቁ ነቢይ ዳንኤል የተማረኩ ወገኖቹን መመለስ እያሰበ በሃዘን ሲጸልይ በዚሕ ቀን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ዳስሶታል:: ባርኮታል:: አጽናንቶታል:: ለዳንኤል በዋነኛነትም ሦስት ምሥጢራትን ገልጾለታል:-

1.የቤተ እሥራኤልን ከሰባ ዘመን በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ::

2.የክርስቶስን ሰው መሆንና መሞት::

3.የሐሳዌ መሲሕን በመጨረሻ ዘመን መምጣት ነግሮታል:: ስለዚህም እኛ ቅዱስ ገብርኤልን እንድናከብረው : በጸሎትም እንድንጠራው አባቶቻችን አዝዘውናል::

††† አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም †††

††† ጻድቁ ሃገራቸው መካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ ሲሆን የታላቁ ሊቅ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ባልንጀራ ናቸው:: ከሕፃንነታቸው ጀምሮ በክርስትና አድገው : ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምረው ወደ ገዳም መንነዋል::

ከታላቁ ኮከበ ገዳም አባ ኢላርዮን ሥርዓተ መነኮሳትን አጥንተው አባ ኤስድሮስን በረድዕነት አገልግለዋል::

ከብዙ ዓመታት ትሕርምትና ገዳማዊ ሕይወት በኋላ የቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም ጳጳስ ሆነው ተሹመዋል:: በጵጵስናቸው ዘመን አንድ ከባድ ስሕተት ሠርተው ነበር::

እርሱም ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ከምእመናን የተሠበሠበውን ገንዘብ ለግል ጉዳያቸው አውለው ልብሳቸውና ቤታቸው ወርቅ በወርቅ ሆኖ ነበር:: ፈጣሪ ግን ይሕንን ብክነት ከእርሳቸው ያርቅ ዘንድ ቅዱስ ኤጲፋንዮስን ላከው::

እርሱም በምክንያት ከቆጵሮስ ኢየሩሳሌም ገባ:: ጓደኛ ናቸውና አሳምኖ የወርቅ ንብረቶቹን ሁሉ ወሰደ:: ለነዳያንም ሰጣቸው:: አባ ዮሐንስ ሊቁን "እቃየን ካልመለስክ" ብለው ቢይዙት ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ጸልዮ ዐይናቸው እንዲታወር አደረገ:: አንዳንዴ የታወረ ልብ የሚገለጠው እንዲሕ ነውና::

በደቂቃዎች ልዩነት ዐይነ ስውር የሆኑት አባ ዮሐንስ አለቀሱ:: ሊቁንም "ራራልኝ : አማልደኝ?" አሉት:: እርሱም ጸልዮ አንድ ዐይናቸውን ብቻ አበራላቸው:: "ለምን?" አሉት:: "ተግሳጽ ነው" አላቸው::

ከዚያች ቀን በኋላ አባ ዮሐንስ ወደ ልቡናቸው ተመለሱ:: ቤታቸውን ገዳም አደረጉት:: በሚደነቅ ቅድስና : ፍቅርና ሐዋርያዊ አገልግሎት ምዕመናንን አገልግለው በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፈዋል::

††† የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ረድኤት : የአባ ዮሐንስ በረከት አይለየን::

††† ሰኔ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት (ወደ ዳንኤል የወረደበት)
2.አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
3.አባታችን ቃይናን (ከአዳም አራተኛ ትውልድ)
4.አባ ማትያን ጻድቅ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
3.ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5.አሥራ ሦስቱ ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

††† " . . . በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም: ተናገረኝም:: እንዲህም አለ:- "ዳንኤል ሆይ! ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ::" †††
(ዳን. ፱፥፳-፳፪)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

‹‹ሰኔ 12›› በዚህች ቀን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል አፎምያን ከሰይጣን እጅ ያዳነበት ቀን ነው።ቅድስት አፎምያ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክር ታዘክር ነበር ለድሆችም አብዝታ ትረዳ ነበር፤ በዚህ ...
06/19/2026

‹‹ሰኔ 12›› በዚህች ቀን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል አፎምያን ከሰይጣን እጅ ያዳነበት ቀን ነው።

ቅድስት አፎምያ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክር ታዘክር ነበር ለድሆችም አብዝታ ትረዳ ነበር፤ በዚህ ሰይጣን ቀናባት በመነኩሴ ተመስሎ ሊያስታት ሞከረ በቅዱስ ሚካኤል ስዕል አሳፍራ መለሰችው ከ 3 ወራት በኃላ ሰኔ 12 ቀን ዳግመኛ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ ብሎ ሊፈትናት መጣ።

ሚካኤል ከሆንክ መስቀልህ የት አለ? አለችው ከዚህ በኃላ አፉን ከፍቶ አይኑን አጉረጥርጦ አንገቷን አነቃት “ቅዱስ ሚካኤል ድረስልኝ” ብላ ተጣራች ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ፈጥኖ ወረደ በበትረ መስቀሉም መታው ጊዜዬ ሳይደርስ አታጥፋኝ ስዕልህ ባለበት፤ ስምህ በተጠራበት፤ ድርሳንህ በሚነበብበት፤ ፈጽሞ አልደርስም ብሎ ማለ፤ ተገዘተ ሸሸም።

ከዚህ በኃላ ቅዱስ ሚካኤል ቅድስት አፎምያን “ወዳጄ አፎምያ ባነቺ ደስ አለኝ ዋጋሽ በሰማይ ታላቅ ነው” ብሎ ባርኳት አርጓል።

ዳግመኛም በእዚህ ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ባሕራንን የሞቱን ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረበት ዕለት ነው። ጻድቁ ንጉስ ቅዱስ ላሊበላ ያረፈበት ቀን ነው።

አፎምያን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ የታደጋት ቅዱስ ሚካኤል እኛንም በጥበቃው አይለየን አሜን 🙏

  ፲፪ ሰኔ ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት የከበረ   በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር የተሾመበት፣ መታሰቢያው የሚከበርበት በዓል እና   የረዳበት ዕለት ነው፡፡ ዳግመኛም በዚህች ቀ...
06/19/2026

፲፪

ሰኔ ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት የከበረ በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር የተሾመበት፣ መታሰቢያው የሚከበርበት በዓል እና የረዳበት ዕለት ነው፡፡ ዳግመኛም በዚህች ቀን የዕረፍቷ መታሰቢያ ሆነ፣ የተባረከና የተመሰገነ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ፣ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት አረፈ፣ ስልሳ ሰባተኛ የሆነው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

ሰኔ ዐሥራ ሁለት በዚህች ዕለት እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር ሾመው። ይህም የከበረ መልአክ ክብር ይግባውና በጌታችን ፊት ስለ ሰው ልጆችና ስለ ፍጥረትም ሁሉ ይለምናል ይማልዳልም።

ዳግመኛ በዚች ዕለት የከበረ የመላእክት አለቃ የመልአኩ የሚካኤል የመታሰቢያውን በዓል ያከብራሉ።

የሚያከብሩበትም ምክንያት እንዲህ ነው። እስክንድርያ በምትባል ከተማ አክላወባጥራ የተባለች ንግሥት የንጉሥ በጥሊሞስ ልጅ ዙሐል በሚባል ኮከብ ስም ያሠራችው ታላቅ ምኲራብ ነበረና። በየዓመቱ ሰኔ በባተ በዐሥራ ሁለት ቀን በዚያ ምኲራብ ሕዝቡ ተሰብስቦ ታላቅ በዓል ያደርጉ ነበር። በዚያም ምኩራብ ውስጥ ዙሐል የሚሉት ታላቅ የነሐስ ጣዖት ነበረና በዓሉ በሚከበርበት ዕለት ብዙ ፍሪዳዎችን ያርዱለት ነበር።

አባ እለእስክንድሮስም እስከተሾመበት ዘመን ድረስ ለዚያ ጣዖት እንዲህ ሲያደርጉ ኖሩ። ይኸውም ሦስት መቶ ዓመተ ምሕረት ተፈጽሞ በአራተኛው ምዕት ውስጥ ነበር። አባ እለእስክንድሮስ በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ጻድቅ ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ የክርስትና ሃይማኖት ስለ ተስፋፋች ያን ጣዖት ሊሠብረው ወድዶ ሳለ ጐስቋሎች ሰዎች ከለከሉት እንዲህም አሉት እኛ በዚህ ቦታ ይህን በዓል ማክበርን ለምደናል እነሆ ከአንተ በፊት ዐሥራ ስምንት ሊቃነ ጳጳሳት አልፈዋል ይህን ልማዳችንንም አልለወጡብንም ።

አባ እለእስክንድሮስ ግን ገሠጻቸው አስተማራቸውም ስሕተታቸውንም በመግለጥ እንዲህ ብሎ አስተማራቸው ይህ ጣዖት የማይጎዳና የማይጠቅም ነው እርሱንም የሚያመልክ ሰይጣናትን ያመልካቸዋል ምክሬንስ ብትሰሙ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ ይህን በዓል እሠራላችኋለሁ ይኸውም ጣዖቱን እንድንሰብረው ምኵራቡንም እንድንባርከውና በከበረ መልአክ በመላእክት አለቃ በሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን አድርገን እንድንሰይመው ነው እኛም ይህን ታላቅ በዓል እንሠራለን። የሚታረዱትም ላሞችና በጎች ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ለችግረኞችም በከበረው መልአክ ስም ምግብ ይሁኑ። እርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነት ያለው ስለሆነ ስለእኛ ይማልዳልና ይህንንም ብሎ በዚህ በጎ ምክር አስወደዳቸው እነርሱም ታዘዙለት።

ከዚህም በኋላ ያንን ምኵራብ አድሰው በዚህ የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን አደረጉት በዚችም ዕለት አከበሩዋት። እርሷም የታወቀች ናት። እስላሞችም እስከ ነገሡበት ዘመን ኑራ ከዚያ በኋላ አፈረሱዋት። ይህም በዓል ተሠራ እስከ ዛሬም ጸንቶ ይኖራል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

በዚህችም ቀን የከበረ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ለቅዱስ ባሕራን ቀሲስ ተአምራቱ ያደረገበት ነው። እግዚአብሔርን የሚፈራ አንድ ሰው ነበረ አርሱም የከበረ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ይልቁንም በሰኔና በኅዳር ወር አብልጦ ያከብር ነበር፡፡ በጐረቤቱም ርኅራኄ የሌለው አንድ ባለጠጋ ሰው ነበረ። ይህን እግዚአብሔርን የሚፈራውን ሰው የከበረ መልአክ የሚካአልን በዓል በሚያደርግበት ጊዜ ይጠላውና ያቃልለው ነበር ለድኆች ስለ መራራቱም ይዘባበትበት ነበረ። የሕይወቱ ዘመንም ተፈጽሞ የሚሞትበትና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ድካምም የሚያርፍበት ጊዜ ሲቀርብ የክቡር መልአክ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ታደርግ ዘንድ ምጽዋት ሰጭም ትሆን ዘንድ ሚስቱን አዘዛት።

ከዚህም በኋላ አረፈና ገንዘው ቀበሩት ሚስቱም ፀንሳ ነበረች የመውለጃዋ ጊዜም ደርሶ ምጥ ያዛት በታላቅ ጭንቀት ውስጥ ሳለችም እንዲህ ብላ ጸለየች የእግዚአብሔር መልአኩ ሆይ ራራልኝ በእርሱ ዘንድ ባለሟልነት አለህና በእግዚአብሔር ዘንድ ስለ እኔ ለምንልኝ። ይህንንም በአለች ጊዜ በቤቷ ውስጥ ብርሃን በራ ከችግርም ዳነች መልኩ ውብ የሆነ ወንድ ልጅንም ወለደች የእግዚአብሔርም መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን እንዲህ ብሎ ባረከው ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት ጥሪቱንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዝዟል ባለጸጋውም በቤቱ በዐልጋው ላይ ሳለ ጌታ ጆሮውን ከፍቶለት ይህን ነገር ከመልአኩ ሰማ።

ይህንንም በሰማ ጊዜ ታላቅ ኀዘን ደረሰበት ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመረ ነገር ግን ክብር ይግባውና ጌታ ይጠብቀው ነበር። ከዚህም በኋላ ያ ባለጸጋ ምክንያት አዘጋጅቶ የሚያገለግለኝ ልጅ ይሆነኝ ዘንድ ልጅሽን ስጪኝ እኔም እየመገብኩና እያለበስኩ አሳድገዋለሁ ለአንቺም ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሻለሁ አላት።

ይህንንም ነገር ከባለጸጋው በሰማች ጊዜ ስለችግሯ እጅግ ደስ አላት ልጅዋንም ሰጠችው እርሱም ሃያውን ወቄት ወርቅ ሰጣት ልጅዋንም ወሰደው የምሻው ተፈጸመልኝ ብሎ ደስ አለው።

ከዚህም በኋላ በልጁ ቁመት ልክ ሣጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አስገብቶ ዘጋበት እስከ ባሕርም ተሸክመው ወስደው በባሕር ጣሉት ክብር ይግባውና በጌታችን ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሠጥም ከዚያች አገር የሃያ ቀን መንገድ ያህል ርቃ ወደምትገኝ ወደ አንዲት አገር ወደብ እስከሚደርስ በባሕሩ ላይ ተንሳፈፈ።

በባሕሩም አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበረና ሣጥኑን በውኃ ላይ ተንሳፎ አየው እርሱም ከባሕሩ አውጥቶ ወደ ቤቱ ወሰደው ይህንም ሣጥን እንዴት እንደሚከፍተው ያስብ ጀመረ ይህንም ሲያስብ ወደ ባሕሩ ይሔድ ዘንድ ጌታችን በልቡናው ኃሳብ አሳደረበት ወዲያውኑም ተነሥቶ ወደ ባሕሩ ሔደና አንድ ዓሣ የሚያጠምድ ሰው አገኘ።

ዓሣ አጥማጁንም መረብህን በኔ ስም ጣል ለሚያዘውም ዓሣ ዋጋውን እሰጥሃለሁ አለው አጥማጁም እንዳለው አደረገ ያን ጊዜም ታላቅ ዓሣ ተያዘ ዋጋውንም ሰጥቶ ዓሣውን ተቀበለ ዓሣውንም ይዞ ወደቤቱ ሔደ ለራትም ይጠብሰው ዘንድ አረደው በሆዱም ውስጥ መክፈቻ አገኘ። በልቡም ይህ መክፈቻ ይህን ሣጥን ይከፍተው ይሆን አለ በሣጥኑ ቀዳዳም በአስገባው ጊዜ ፈጥኖ ተከፈተ በውስጡም ይህን ታናሽ ብላቴና አገኘ። ልጅ የለውም ነበርና ታላቅ ደስታ ደስ አለው ጌታችንንም አመሰገነው። ሕፃኑንም በመልካም አስተዳደግ አሳደገው ሕፃኑም አድጎ ጐልማሳ ሆነ።

ከብዙ ዘመናትም በኋላ ያ ባለ ጸጋ ተነሥቶ ወደዚያ አገር ሔደ በመሸም ጊዜ ወደ በግ ጠባቂው ደጅ ደረሰ በግ ጠባቂውን እስከ ነገ የምናድርበት ማደሪያ በአንተ ዘንድ እናገኛለን ኪራዩንም እሰጥሃለሁ አለው በግ አርቢውም እንዳልክ ይሁንና እደር አለው ባለጸጋውም በዚያ አደረ።

ራት በሚቀርብም ጊዜ ሕፃኑን ባሕራን ብሎ ጠራው ባለጸጋውም ሰምቶ ልጅህ ነውን ብሎ ጠየቀው በግ ጠባቂውም አዎን ታናሽ ሕፃን ሆኖ ሳለ ከባሕር አግኝቼዋለሁና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጄ ነው አለው ባለጸጋውም በምን ዘመን አገኘኸው አለው እርሱም ከሃያ ዓመት በፊት ብሎ መለሰለት። ያን ጊዜም እርሱ ወደ ባሕር የጣለው መሆኑን አውቆ እጅግ አዘነ።

በማግሥቱም ጎዳናውን ሊጓዝ በተነሣ ጊዜ ሰይጣናዊ ምክንያት አመካኝቶ በግ ጠባቂውን እንዲህ አለው ዕገሊት ወደምትባል አገር በቤቴ የረሳሁት ጉዳይ ስለ አለ እንድልከው ልጅህን ትሰጠኝ ዘንድ እሻለሁ እኔም የድካም ዋጋውን ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሃለሁ አለው። የብላቴናውም አባት ስለ ገንዘቡ ደስ ብሎት ልጁ ባሕራንን ሰጠው እንዲህም ብሎ አዘዘው ልጄ ባሕራን ይህ የከበረ ሰው ስለ ጉዳዩ ወደ ቤቱ ይልክህ ዘንድ ና ወደ ቤትህም በሰላም ትመለሳለህ። ባሕራንም አባቴ ሆይ እሽ በጎ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ አለ።

ያን ጊዜም ባለጸጋው ወደ መጋቢው እንዲህ ብሎ ደብዳቤ ጻፈ ይችን ደብዳቤ በምታነባት ጊዜ ደብዳቤዋን ይዞ የመጣውን ገድለህ በጉድጓድ ውስጥ ጣለው ማንም አይወቅ በመካከላቸውም የሚተዋወቁበትን ምልክት ጽፎ አሸጋት። ለባሕራንም ሰጠው ለመንገዱም የሚሆነውን ስንቅ ሰጠው ባሕራንም ተነሥቶ ጉዞውን ጀመረ ሲጓዝም ሰንብቶ የአንዲት ቀን ጐዞ ሲቀረው እነሆ የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ሚካኤል በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ አንተ ጐልማሳ የያዝኸው ምንድነው አለው ወደ ዕገሌ አገር ወደ ቤቱ ለማድረስ ከአንድ ባለጸጋ የተጻፈች መልእክት ናት አለው ያቺን ደብዳቤ አሳየኝ አለው እርሱም ስለ ፈራ ሠጠው።

በዚያን ጊዜም የከበረው መልአክ ሚካኤል ያቺን የሞት መልእክት ደመሰሳት በእርሷ ፈንታም በንፍሐት ለውጦ እንዲህ ብሎ ጻፈ ይቺን ደብዳቤ ይዞ ለመጣ ባሕራን ለሚባል ሰው ይቺ ደብዳቤ ደርሳ በምትነበብበት ጊዜ ልጄ እገሊትን አጋቡት በውስጥና በውጭ ያለ ንብረቴንና ጥሪቴን ወንዶችና ሴቶች ባሮቼን ጠቅላላ ንብረቴንም አውርሼዋለሁና የፈለገውንም ሊያደርግ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና እኔን አትጠብቁኝ። እኔ ብዙ እዘገያለሁ የኔ ሹም ዕገሌ ሆይ በእኔና በአንተ መካከል ይቺ ምልክት እነኋት ከዚህ በኋላ አሽጐ ለባሕራን ሰጠውና ወደ ባለጸጋው ቤት ሒደህ ይቺን ደብዳቤ ለሹሙ ሰጠው በጎዳናም እኔ እንደ ተገናኘሁህ አትንገረው እንዳይገድልህም ይህን የሞት ደብዳቤ ለውጬልሃለሁ አለው። ባሕራንም እሺ ጌታዬ ያዘዝኽኝን ሁሉ አደርጋለሁ አለ።

ባሕራንም ወደ ባለጸጋው ቤት በደረሰ ጊዜ ያቺን ደብዳቤ ለሹሙ ሰጠው በአነበባትም ጊዜ በመካከላቸው ያለውን ምልክት አገኘ አስተውሎም አርግጠኛ እንደሆነ አወቀ። ከዚህም በኋላ ለባሕራን ሠርግ አዘጋጅቶ እንደሚገባ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በተክሊል የባለጸጋውን ልጅ አጋቡት። አርባ ቀን ያህልም ደስታና ሐሴት እያደረጉ ኖሩ።

ከዚህ በኋላ ባለጸጋው ከሔደበት መመለሻው ጊዜ ሁኖ በደስታ የሆነውን የመሰንቆና የእንዚራ ድምፅ ሰምቶ ይህ የምሰማው ምንድነው ብሎ ጠየቀ እነርሱም ስሙ ባሕራን ለተባለ የአንተን ደብዳቤ ላመጣ ጐልማሳ ሰው ልጅህ ዕገሊትን አጋቡት እነሆ ለአርባ ቀናት በሠርግ ላይ ነው። ገንዘብህንና ጥሪትህን ሁሉ ወንዶችና ሴቶች ባሮችህን አንተ እንዳዘዝክ ሰጥተውታል አሉት። ይህንንም በሰማ ጊዜ ደንግጦ ከፈረሱ ላይ ወደቀ በድንገትም ሞተ።

ባሕራንም በጎ ሥራዎችን የሚሠራ ሆነ የተገለጸለትና ከመገደል ያዳነው የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ሚካኤል እንደሆነ ሊገድለው የሚሻውን የባለጸጋውን ጥሪቱን ሁሉ ያወረሰውም እርሱ እንደ ሆነ ተረዳ የዚህንም የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን መታሰቢያ በየወሩ ያደርግ ጀመረ ቤተ ክርስቲያንም ሠራለት የቅዱስ ሚካኤልንም ሥዕሉን አሥሎ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ አደረገው ከእርሱም ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ ባሕራንም ቅስና ተሹሞ እስከ ዕለተ ሞቱ በዚያች ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ሁኖ ኖረ በዚህ በከበረ የመላእክት አለቃ ሚካኤል አማላጅነት ከእናቱና ከአባቱ ከልጆቹም ጋራ የዘላለም ሕይወትን ወረሰ።

መድኃኒታችን በተነሣበትም ቀን ይህ ክቡር መልአክ ሚካኤል ከውስጠኛው መጋረጃ ውስጥ ገብቶ በክብር ባለቤት ፊት እንዲህ እያለ ይለምናል እውነት ስለሆነ ቃል ኪዳንህ በምድር መታሰቢያዬን የሚያደርጉትን ትምርልኝ ዘንድ ፈጣሪዬ ሆይ እኔ አገልጋይህና መልእክተኛህ ከቸርነትህ እለምናለሁ አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህና።

የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ ብሎ ይመልስለታል የመንፈሳውያን ሰማያውያን መላእክት አለቃቸው ሚካኤል ሆይ መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ መሸከም እንደምትችል ከሲኦል ሦስት ጊዜ በክንፎችህ ተሸክመህ እንድታወጣ እነሆ እኔ አዝዤሃለሁ።

ይህንንም ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት የበዓሉን መታሰቢያ ከሚያደርጉት በክንፎቹ ተሸከሞ የእሳቱን ባሕር አሳለፋቸው እነርሱንም ከብቻው ጌታ በቀር የሚቆጥራቸው የለም። ስለዚህም የዚህን ታላቅ የከበረ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ለማድረግ መታገል ይገባናል እርሱ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን ዘንድ በዘመናችን ሁሉም ይጠብቀን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይ ዘንድ መከራችንንም ያርቅ ዘንድ የምድራችንንም ፍሬ ይባርክ ዘንድ ፈቃዱንም ለመሥራት ይረዳን ዘንድ ከእኛ ወገን የሞቱትን ዕረፍተ ነፍስ ይሰጥ ዘንድ ወደ መንገድ የሔዱ አባቶቻችንና ወንድሞቻችንን ወደ ቤቶቻቸው በሰላም በጤና ይመልሳቸው ዘንድ በመካከላችንም ፍቅር ያደርግልን ዘንድ እስከ መጨረሻዪቱም ሕቅታ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ ይለምናልና።

የክርስቶስ ወገኖች የሆኑ መኳንንቶቻችንንም ጠብቆ በወንበሮቻቸው ላይ ያጸናቸው ዘንድ የሳቱትንም ወደ ቀናች ሃይማኖቱ ይመልሳቸው ዘንድ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

ዳግመኛም በዚህች ቀን እግዚአብሔርን የሚፈራ አስተራኒቆስ የሚስቱ የቅድስት አፎምያ የዕረፍቷ መታሰቢያ ሆነ። ይህም ሰው በየወሩ ሦስት በዓላቶችን እያከበረ ኖረ እሊህም ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ መታሰቢያ በየወሩ በሃያ ዘጠኝ፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል መታሰቢያ በየወሩ በሃያ አንድ፣ የከበረ የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያም በየወሩ በዐሥራ ሁለት ናቸው።

የሚሞትበትም ጊዜው ሲቀርብ እርሱ ሲሠራው የነበረውን ምጽዋት ይልቁንም እሊህን ሦስቱን በዓላት እንዳታስታጉል ሚስቱን ቅድስት አፎምያን አዘዛት። አርሷም የከበረ የመልአኩ የሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባሏን ለመነችው እርሱም አሠርቶ ሰጣትና በቤቷ ውስጥ በክብር አኖረችው።

ባሏም ከአረፈ በኋላ ባሏ ያዘዛትን መሥራት ጀመረች ሰይጣን ግን ቀናባት በመበለት ሴት መነኲሲት ተመስሎ ከእርሷ ጋራ ተነጋገረ እንዲህም አላት እኔ አዝንልሻለሁ እራራልሻለሁም ገንዘብሽ ሳያልቅ የልጅነትሽም ወራት ሳያልፍ አግብተሽ ልጅ ትወልጂ ዘንድ እመክርሻለሁ ባልሽም መንግሥተ ሰማያትን ወርሷል ምጽዋትም አይሻም።

አፎምያም እንዲህ ብላ መለሰችለት እኔ ከሌላ ሰው ጋራ ላልገናኝ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አድርጌያለሁ ርግቦችና መንጢጦች እንኳ ሌላ ባል አያውቁም በእግዚአብሔር አርአያ ከተፈጠሩ ሰዎች ይህ ሊሆን እንዴት ይገባል። ምክሩንም ባልሰማች ጊዜ አርአያውን ለውጦ በላይዋ ጮኸባት እንዲህም አላት እኔ በሌላ ጊዜ እመጣለሁ እርሷም የከበረ የመልአኩ የሚካኤልን ሥዕል ይዛ አሳደደችው።

ከዚህም በኋላ ሰኔ ዐሥራ ሁለት የከበረ የመልአኩ የሚካኤል በዓል በሚከብርበት ዕለት እርሷም የበዓሉን ዝግጅት ስታዘጋጅ ሳለች ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ አፎምያ ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እኔ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነኝ ጌታ ወደ አንቺ ልኮኛልና እርሱም ይህን መመጽወትሽን ትተሽ ለአንድ ምእመን ሚስት ትሆኚ ዘንድ ጌታ አዞሻል ባል የሌላት ሴት መልሕቅ የሌለውን መርከብ እንደምትመስል ዕወቂ እንደ አብርሃምና ያዕቆብ እንደ ዳዊትም እንደእነርሱ ያሉ ብዙ ሴቶችን እንዳገቡ እግዚአብሔርንም ደስ እንዳሰኙት ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጥቅሶችን ያመጣላት ጀመረ።

ቅድስት አፎምያም መልሳ አንተ የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ የመስቀል ምልክት ከአንተ ጋራ ወዴት አለ የንጉሥ ጭፍራ የሆነ ሁሉ የንጉሡን ማሕተም ሳይዝ ወደ ሌላ ቦታ አይሔድምና አለችው። ሰይጣኑም ይህንን በሰማ ጊዜ መልኩ ተለወጠና አነቃት እርሷም ወደ ከበረው መልአክ ወደ ሚካኤል ጮኸች ወዲያውኑም ደርሶ አዳናት። ያንንም ሰይጣን ይዞ ይቀጣው ጀመረ ሰይጣኑም ጮኸ ማረኝ ያለ ጊዜዬ አታጥፋኝ እግዚአብሔር እስከ ዓለም ፍጻሜ ታግሦናልና እያለ ለመነው ከዚያም ተወውና አበረረው።

የከበረ መልአክ ሚካኤልም እንዲህ አላት ብፅዕት አፎምያ ሆይ ሒደሽ የቤትሽን ሥራ አዘጋጂ አንቺ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ትለዪአለሽና እነሆ እግዚአብሔርም ዐይን ያላየውን ጆሮም ያልሰማውን በሰው ልብም ያልታሰበውን አዘጋጅቶልሻል። ይህንንም ብሎ ሰላምታ ሰጣት ወደ ሰማያትም ዐረገ። የበዓሉንም ዝግጅት እንደሚገባ ከፈጸመች በኋላ ወደ ኤጲስቆጶሱና ወደ ካህናቱ ሁሉ ላከች ወደርሷም በመጡ ጊዜ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ይሰጧቸው ዘንድ ገንዘቧን ሁሉ አስረከበቻቸው።

ከዚህም በኋላ ተነሥታ ጸለየች የከበረ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤልንም ሥዕል አንስታ ታቅፋ ሳመችው ያን ጊዜም በሰላም አረፈች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

(ንጉሠ ኢትዮዽያ)

ዳግመኛም በዚህች ዕለት የተባረከና የተመሰገነ በሰማያት ያለ ምሥጢርን ያየ የኢትዮጵያ ንጉሥ ላሊበላ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ።ይህንንም ቅዱስ ወላጆቹ በወለዱት ጊዜ እግዚአብሔርን በመፍራትና በበጎ ሥራ ሁሉ አሳደጉት። አድጎ አካለ መጠን በአደረሰ ጊዜ ታላቅ ወንድሙ ንጉሥ ቀናበት መልእክተኞችንም ልኮ ወደርሱ አስመጣው ምክንያትም ሽቶ ከሦስት ሰዓት እስከ ሰባት ሰዓት እንዲገርፉት አዘዘ።

ከዚህም በኋላ በፊቱ እንዲአቆሙት አዘዘ በአቆሙትም ጊዜ የደረሰበት ጉዳት እንደሌለ አይተው ንጉሡና መኳንንቶቹ ሁሉ አደነቁ የእግዚአብሔር መልአክ ከግርፋት ሠውሮታልና። ከዚህ በኋላም ወንድሙ ንጉሥ በአንተ ላይ ስለአደረግሁት ክፉ ሥራ ወንድሜ ሆይ ይቅር በለኝ ብሎ ለመነውና እርስ በርሳቸው ታረቁ።

ከዚህ በኋላም እግዚአብሔር መንግሥትን አወረሰው። መንግሥትንም በያዘ ጊዜ እግዚአብሔርን በሚያገለግልበት ሥራ በረታ ሁልጊዜም ለድኆች ለምስኪኖችና ለችግረኞች ይመጸውት ነበር።

ክብር ይግባውና ጌታችንም የፍቅሩን ጽናት በአየ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት ወደ እርሱም ወደ ሰማያት አወጣው ዐሥሩን አብያተ ክርስቲያንም እንዴት እንደሚሠራቸው አሳየው እነርሱም ሥራቸው የየራሳቸው የሆነ ልዩ ነው ተመልሶም መንፈስ ቅዱስ እንደአራቀቀው በአስደናቂ ጥበብ አነፃቸው። እሊህንም አብያተ ክርስቲያናት አንፆ በፈጸመ ጊዜ መንግሥቱን ለወንድሙ ልጅ አወረሰ።

ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በብርሃን ሠረገላ ተቀምጦ የሚአስፈራ መብረቅን የተጐናጸፉ አእላፋት ሠራዊቶቹ ዙሪያውን ሁነው ወደርሱ መጥቶ እንዲህ አለው ወዳጄ ላሊበላ ሆይ ሰላም ይሁንልህ እኔ በማይታበል ቃሌ እነግርሃለሁ ማደሪያህ በክብር ሁሉ ከከበሩ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያቶቼ ጋራ ይሁን። በጸሎትህና በቃል ኪዳንህ ለሚታመን እምነቱ እንደ ጴጥሮስና ጳውሎስ ደም መፍሰስ ይሆንለታል።

ወደ ቤተ መቅደስህም የሔደ በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደሴ እንደ ሔደ ይሆንለታል መቃብርህንም የተሳለመ የሥጋዬን መቃብር እንደ ተሳለመ ይሆንለታል በዓመታቱ ወሮች ሁሉ የተራቡትን እያጠገበ የተጠሙትንም እያጠጣ መታሰቢያህን ለሚያደርግ እኔ የተሠወረ መና እመግበዋለሁ የሕይወት ጽዋንም አጠጣዋለሁ። በመታሰቢያህ ቀንም ዕጣን ወይም ስንዴ የሚያገባውን እኔ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት በውስጠኛው መጋረጃ አስቀምጬ ከተቆረሰው ሥጋዬ አቆርበዋለሁ በአማላጅነትህም እየታመነ የገድልህንና የቃል ኪዳንህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ያንተ ስም በተጻፈበት ቦታ እኔ ስሙን እጽፋለሁ በፍጹም ልቡ ለሚያምን ይህን የማይታበል ቃል የተናገርኩ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እኔ ኢየሱስ ነኝ አለው።

ላሊበላም ይህን ቃል ኪዳን ስለ አጸናለት ክብር ይግባውና ጌታችንን እያመሰገነ በምድር ላይ ወድቆ ሰገደ። ጌታችንም ሰላምታ ሰጥቶት በክብርና በምስጋና ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚህም በኋላ ጥቂት ሕማም ታሞ በሰላም አረፈ። ነፍሱንም የብርሃን መላእክት ተቀብለው የዘላለም ሕይወት ማደሪያ ወደሆነ ማረፊያው አስገቡት።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

በዚህችም ዕለት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስድስተኛ የሆነ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮስጦስ አረፈ። ይህም የከበረ አባት ከእስክንድርያ አገር ሰዎችም የተማረ አዋቂ ሰው ነበረ። እርሱንም ከእናትና አባቱ ከሌሎችም ብዙዎች ሰዎች ጋራ የክርስትና ጥምቀትን ወንጌላዊ ማርቆስ አጠመቀው። ከዚህም በኋላ አናጉንስጢስነት ሾመው ከአናጉንስጢስነትም በኋላ ዲቁና ሾመው በቅዱስ አንያኖስ ዘንድ እያገለገለው የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን በመማር አደገ።

ሕዝቡንም ሁልጊዜ ይመክራቸውና ይገሥጻቸው ያስተምራቸውም በቀናች ሃይማኖትም ያጸናቸው ነበር። አባ አብርምዮስም በአረፈ ጊዜ ያለ ፈቃዱ ወስደው በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በግብጽ አገር ያለች ቤተ ክርስቲያንንም በመልካም አጠባበቅ እንደሚገባ ጠበቃት። በወንጌላዊው ማርቆስ ወንበርም ዐሥራ ሁለት ዓመት ከኖረ በኋላ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

በዚህችም ዕለት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ ሰባተኛ የሆነው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቄርሎስ አረፈ። ከእርሱ አስቀድሞ የነበረ አባ ገብረ ክርስቶስ በአረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶሳትና የሕዝብ አለቆች ተስማምተው ወደ አስቄጥስ ወደ አባ መቃርስ ገዳም ወጡ ለዚች ለከበረች ሹመትም የሚገባውን እየመረመሩ ሁለት ወር ያህል ኖሩ።

በአባ ዮሐንስ ሐጺር ገዳም የትንቢት መንፈስ ያደረበት ስሙ ገብረ ኢየሱስ የሚባል አንድ ሰው ነበር ለእርሱም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾለት እንዲህ አለው። ለኤጲስቆጶሳቱ ለዚች ለከበረች ሹመት የሚገባ ስሙ ገዐርጊ የሚባል በመካከላችሁ አለና አትዘኑ በላቸው አለው።

ያን ጊዜም ቅዱስ ገብረ ኢየሱስ ይህን ነገር ነገራቸው ከዚህም በኋላ ይህን አባት ይዘው ያለፈቃዱ በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት እርሱም እጅግ አዋቂ ነበረና በሹመቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ደስ ተሰኘች። ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመ ብዙዎች አብያተ ክርስቲያናትንም አደሰ።

ከዚህም በኋላ ለኢትዮጵያ አገር አንድ ጳጳስ ሾመ በዕውቀቱና በደግነቱ እጅግ ደስ ተሰኙበት ብዙዎችን ከክፉ ሥራ ወደ በጎ ሥራ መልሶአቸዋልና እግዚአብሔርንም የሚፈሩ ሆነዋልና በበጎ ሥራም ጸንተዋልና።

ለንጉሡ እንዲሁም ለመኳንንቶቹ ብዙ ሚስቶች ነበሩአቸውና እርሱ ስለ አስተማራቸውና ስለገሠጻቸው ሚስቶቻቸውን አሰናብተው እንደ ሕጉ በየአንዳንዲት ሴት ጸኑ።

የከበረ አባ ቄርሎስም ዐሥራ አንድ ዓመት ከሦስት ወር ተኩል ሲፈጸምለት ሥጋውንና ደሙን ተቀብሎ በሰላም አረፈ ሥጋውንም ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደ አባ መቃርስ ደብር ተሸክመው ወስደው ከከበሩ ሊቃነ ጳጳሳት ዐፅም ጋራ አኖሩት።

† ሰኔ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅድስት አፎምያና ባለቤቷ ቅዱስ አስተራኒቆስ
4.ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ
5.ቅዱስ እለ እስክንድሮስ ሊቅ
6.አባ ዮስጦስ ሊቀ ዻዻሳት (የሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ደቀ መዝሙር)
7.አባ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት

† ወርሐዊ በዓላት

1.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ድሜጥሮስ
3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
6.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን፤ የከበረ መልአክ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን።

( )

  በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነትና ሥርዓት መሠረት፥ መላእክት የእግዚአብሔር የክብሩ መግለጫዎች፣ የፈቃዱ ፈጻሚዎችና የሰው ልጆች ረዳቶች ናቸው።  #መላእክት....
06/19/2026

በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነትና ሥርዓት መሠረት፥ መላእክት የእግዚአብሔር የክብሩ መግለጫዎች፣ የፈቃዱ ፈጻሚዎችና የሰው ልጆች ረዳቶች ናቸው።

#መላእክት...

💠 #ያድናሉ (ይታደጋሉ)፦ መላእክት እግዚአብሔርን በሚፈሩት ዙሪያ ሰፍረው ከመከራ ያድኗቸዋል።
“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” (መዝ. 33፥7)

💠 #ይለምናሉ / ያማልዳሉ፦ መላእክት ስለ ሰው ልጆች ምሕረትንና ይቅርታን ወደ እግዚአብሔር ይለምናሉ።

“የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ... የምትቆጣቸውን እነዚህን ሰባ ዓመት የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ።” (ዘካ. 1፥12)

💠 #ይደሰታሉ፦ በአንድ ኃጢአተኛ መመለስና ንስሐ መግባት በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆንባቸዋል።
“እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።” (ሉቃ. 15፥10)

💠 #ያዝናሉ፦ የሰው ልጅ ከፈጣሪው ሲርቅና ኃጢአት ሲሠራ መላእክት ያዝናሉ።
“እነሆ፥ ኃያላኖቻቸው በሜዳ ይጮኻሉ የሰላምም መልእክተኞች መራራ ልቅሶ ያለቅሳሉ።” (ኢሳ. 33፥7)

💠 #ያውቃሉ፦ መላእክት እግዚአብሔር በገለጠላቸው መጠን ረቂቅና ሰማያዊ እውቀት አላቸው።
“ጌታዬ ግን የእግዚአብሔር መልአክ እንደሚያውቅ በምድር ያለውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ጥበበኛ ነው።” (2ሳሙ. 14፥20)

💠 ፦ ድኅነትን (ሕይወትን) ለሚወርሱት ሁሉ ለአገልግሎት ይላካሉ።
“ሁሉ ድኅነትን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉ መናፍስት አይደሉምን?” (ዕብ1፥14)

💠 #ያበስራሉ፦ ለሰው ልጅ መልካሙንና የምሥራቹን
ቃል ያደርሳሉ።
“መልአኩም አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ።
” (ሉቃ. 2፥10)

💠 #ይቀጣሉ፦ እግዚአብሔርን በሚበድሉና በትዕቢተኞች ላይ የእግዚአብሔርን የፍርድ ቅጣት ይፈጽማሉ።
“ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው፥ በትልም ተበልቶ ሞተ።” (ሐዋ. 12፥23)

💠 ይበልጣሉ፦ መላእክት በባሕሪያቸው ረቂቃንና ብርቱዎች በመሆናቸው ከሰው
ልጅ በኃይል እጅግ ይበልጣሉ።
“ኃይለኞችና የበረቱ፥ የቃሉን ድምፅ ሰምታችሁ ትእዛዙን የምታደርጉ መላእክቱ
ሁሉ...”
(መዝ. 102፥20)

“ዳሩ ግን መላእክት በኃይልና በብርታት ከእነርሱ ይልቅ ምንም ቢበልጡ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብን ፍርድ አያመጡም።”
2ኛ ጴጥሮስ 2፥11

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በእነዚህ ቅዱሳን መላእክት ክብርና ጥበቃን የሰጠን አምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን። የቅዱሳን መላእክት አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን። አሜን!

 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስምሰኔ ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት የከበረ   በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር የተሾመበት፣ መታሰቢያው የሚከበርበት በዓል እና...
06/19/2026

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት የከበረ በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር የተሾመበት፣ መታሰቢያው የሚከበርበት በዓል እና የረዳበት ዕለት ነው፡፡ ዳግመኛም በዚህች ቀን የዕረፍቷ መታሰቢያ ሆነ፣ የተባረከና የተመሰገነ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ፣ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት አረፈ፣ ስልሳ ሰባተኛ የሆነው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

ሰኔ ዐሥራ ሁለት በዚህች ዕለት እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር ሾመው። ይህም የከበረ መልአክ ክብር ይግባውና በጌታችን ፊት ስለ ሰው ልጆችና ስለ ፍጥረትም ሁሉ ይለምናል ይማልዳልም።

ዳግመኛ በዚች ዕለት የከበረ የመላእክት አለቃ የመልአኩ የሚካኤል የመታሰቢያውን በዓል ያከብራሉ።

የሚያከብሩበትም ምክንያት እንዲህ ነው። እስክንድርያ በምትባል ከተማ አክላወባጥራ የተባለች ንግሥት የንጉሥ በጥሊሞስ ልጅ ዙሐል በሚባል ኮከብ ስም ያሠራችው ታላቅ ምኲራብ ነበረና። በየዓመቱ ሰኔ በባተ በዐሥራ ሁለት ቀን በዚያ ምኲራብ ሕዝቡ ተሰብስቦ ታላቅ በዓል ያደርጉ ነበር። በዚያም ምኩራብ ውስጥ ዙሐል የሚሉት ታላቅ የነሐስ ጣዖት ነበረና በዓሉ በሚከበርበት ዕለት ብዙ ፍሪዳዎችን ያርዱለት ነበር።

አባ እለእስክንድሮስም እስከተሾመበት ዘመን ድረስ ለዚያ ጣዖት እንዲህ ሲያደርጉ ኖሩ። ይኸውም ሦስት መቶ ዓመተ ምሕረት ተፈጽሞ በአራተኛው ምዕት ውስጥ ነበር። አባ እለእስክንድሮስ በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ጻድቅ ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ የክርስትና ሃይማኖት ስለ ተስፋፋች ያን ጣዖት ሊሠብረው ወድዶ ሳለ ጐስቋሎች ሰዎች ከለከሉት እንዲህም አሉት እኛ በዚህ ቦታ ይህን በዓል ማክበርን ለምደናል እነሆ ከአንተ በፊት ዐሥራ ስምንት ሊቃነ ጳጳሳት አልፈዋል ይህን ልማዳችንንም አልለወጡብንም ።

አባ እለእስክንድሮስ ግን ገሠጻቸው አስተማራቸውም ስሕተታቸውንም በመግለጥ እንዲህ ብሎ አስተማራቸው ይህ ጣዖት የማይጎዳና የማይጠቅም ነው እርሱንም የሚያመልክ ሰይጣናትን ያመልካቸዋል ምክሬንስ ብትሰሙ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ ይህን በዓል እሠራላችኋለሁ ይኸውም ጣዖቱን እንድንሰብረው ምኵራቡንም እንድንባርከውና በከበረ መልአክ በመላእክት አለቃ በሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን አድርገን እንድንሰይመው ነው እኛም ይህን ታላቅ በዓል እንሠራለን። የሚታረዱትም ላሞችና በጎች ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ለችግረኞችም በከበረው መልአክ ስም ምግብ ይሁኑ። እርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነት ያለው ስለሆነ ስለእኛ ይማልዳልና ይህንንም ብሎ በዚህ በጎ ምክር አስወደዳቸው እነርሱም ታዘዙለት።

ከዚህም በኋላ ያንን ምኵራብ አድሰው በዚህ የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን አደረጉት በዚችም ዕለት አከበሩዋት። እርሷም የታወቀች ናት። እስላሞችም እስከ ነገሡበት ዘመን ኑራ ከዚያ በኋላ አፈረሱዋት። ይህም በዓል ተሠራ እስከ ዛሬም ጸንቶ ይኖራል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

በዚህችም ቀን የከበረ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ለቅዱስ ባሕራን ቀሲስ ተአምራቱ ያደረገበት ነው። እግዚአብሔርን የሚፈራ አንድ ሰው ነበረ አርሱም የከበረ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ይልቁንም በሰኔና በኅዳር ወር አብልጦ ያከብር ነበር፡፡ በጐረቤቱም ርኅራኄ የሌለው አንድ ባለጠጋ ሰው ነበረ። ይህን እግዚአብሔርን የሚፈራውን ሰው የከበረ መልአክ የሚካአልን በዓል በሚያደርግበት ጊዜ ይጠላውና ያቃልለው ነበር ለድኆች ስለ መራራቱም ይዘባበትበት ነበረ። የሕይወቱ ዘመንም ተፈጽሞ የሚሞትበትና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ድካምም የሚያርፍበት ጊዜ ሲቀርብ የክቡር መልአክ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ታደርግ ዘንድ ምጽዋት ሰጭም ትሆን ዘንድ ሚስቱን አዘዛት።

ከዚህም በኋላ አረፈና ገንዘው ቀበሩት ሚስቱም ፀንሳ ነበረች የመውለጃዋ ጊዜም ደርሶ ምጥ ያዛት በታላቅ ጭንቀት ውስጥ ሳለችም እንዲህ ብላ ጸለየች የእግዚአብሔር መልአኩ ሆይ ራራልኝ በእርሱ ዘንድ ባለሟልነት አለህና በእግዚአብሔር ዘንድ ስለ እኔ ለምንልኝ። ይህንንም በአለች ጊዜ በቤቷ ውስጥ ብርሃን በራ ከችግርም ዳነች መልኩ ውብ የሆነ ወንድ ልጅንም ወለደች የእግዚአብሔርም መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን እንዲህ ብሎ ባረከው ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት ጥሪቱንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዝዟል ባለጸጋውም በቤቱ በዐልጋው ላይ ሳለ ጌታ ጆሮውን ከፍቶለት ይህን ነገር ከመልአኩ ሰማ።

ይህንንም በሰማ ጊዜ ታላቅ ኀዘን ደረሰበት ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመረ ነገር ግን ክብር ይግባውና ጌታ ይጠብቀው ነበር። ከዚህም በኋላ ያ ባለጸጋ ምክንያት አዘጋጅቶ የሚያገለግለኝ ልጅ ይሆነኝ ዘንድ ልጅሽን ስጪኝ እኔም እየመገብኩና እያለበስኩ አሳድገዋለሁ ለአንቺም ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሻለሁ አላት።

ይህንንም ነገር ከባለጸጋው በሰማች ጊዜ ስለችግሯ እጅግ ደስ አላት ልጅዋንም ሰጠችው እርሱም ሃያውን ወቄት ወርቅ ሰጣት ልጅዋንም ወሰደው የምሻው ተፈጸመልኝ ብሎ ደስ አለው።

ከዚህም በኋላ በልጁ ቁመት ልክ ሣጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አስገብቶ ዘጋበት እስከ ባሕርም ተሸክመው ወስደው በባሕር ጣሉት ክብር ይግባውና በጌታችን ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሠጥም ከዚያች አገር የሃያ ቀን መንገድ ያህል ርቃ ወደምትገኝ ወደ አንዲት አገር ወደብ እስከሚደርስ በባሕሩ ላይ ተንሳፈፈ።

በባሕሩም አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበረና ሣጥኑን በውኃ ላይ ተንሳፎ አየው እርሱም ከባሕሩ አውጥቶ ወደ ቤቱ ወሰደው ይህንም ሣጥን እንዴት እንደሚከፍተው ያስብ ጀመረ ይህንም ሲያስብ ወደ ባሕሩ ይሔድ ዘንድ ጌታችን በልቡናው ኃሳብ አሳደረበት ወዲያውኑም ተነሥቶ ወደ ባሕሩ ሔደና አንድ ዓሣ የሚያጠምድ ሰው አገኘ።

ዓሣ አጥማጁንም መረብህን በኔ ስም ጣል ለሚያዘውም ዓሣ ዋጋውን እሰጥሃለሁ አለው አጥማጁም እንዳለው አደረገ ያን ጊዜም ታላቅ ዓሣ ተያዘ ዋጋውንም ሰጥቶ ዓሣውን ተቀበለ ዓሣውንም ይዞ ወደቤቱ ሔደ ለራትም ይጠብሰው ዘንድ አረደው በሆዱም ውስጥ መክፈቻ አገኘ። በልቡም ይህ መክፈቻ ይህን ሣጥን ይከፍተው ይሆን አለ በሣጥኑ ቀዳዳም በአስገባው ጊዜ ፈጥኖ ተከፈተ በውስጡም ይህን ታናሽ ብላቴና አገኘ። ልጅ የለውም ነበርና ታላቅ ደስታ ደስ አለው ጌታችንንም አመሰገነው። ሕፃኑንም በመልካም አስተዳደግ አሳደገው ሕፃኑም አድጎ ጐልማሳ ሆነ።

ከብዙ ዘመናትም በኋላ ያ ባለ ጸጋ ተነሥቶ ወደዚያ አገር ሔደ በመሸም ጊዜ ወደ በግ ጠባቂው ደጅ ደረሰ በግ ጠባቂውን እስከ ነገ የምናድርበት ማደሪያ በአንተ ዘንድ እናገኛለን ኪራዩንም እሰጥሃለሁ አለው በግ አርቢውም እንዳልክ ይሁንና እደር አለው ባለጸጋውም በዚያ አደረ።

ራት በሚቀርብም ጊዜ ሕፃኑን ባሕራን ብሎ ጠራው ባለጸጋውም ሰምቶ ልጅህ ነውን ብሎ ጠየቀው በግ ጠባቂውም አዎን ታናሽ ሕፃን ሆኖ ሳለ ከባሕር አግኝቼዋለሁና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጄ ነው አለው ባለጸጋውም በምን ዘመን አገኘኸው አለው እርሱም ከሃያ ዓመት በፊት ብሎ መለሰለት። ያን ጊዜም እርሱ ወደ ባሕር የጣለው መሆኑን አውቆ እጅግ አዘነ።

በማግሥቱም ጎዳናውን ሊጓዝ በተነሣ ጊዜ ሰይጣናዊ ምክንያት አመካኝቶ በግ ጠባቂውን እንዲህ አለው ዕገሊት ወደምትባል አገር በቤቴ የረሳሁት ጉዳይ ስለ አለ እንድልከው ልጅህን ትሰጠኝ ዘንድ እሻለሁ እኔም የድካም ዋጋውን ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሃለሁ አለው። የብላቴናውም አባት ስለ ገንዘቡ ደስ ብሎት ልጁ ባሕራንን ሰጠው እንዲህም ብሎ አዘዘው ልጄ ባሕራን ይህ የከበረ ሰው ስለ ጉዳዩ ወደ ቤቱ ይልክህ ዘንድ ና ወደ ቤትህም በሰላም ትመለሳለህ። ባሕራንም አባቴ ሆይ እሽ በጎ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ አለ።

ያን ጊዜም ባለጸጋው ወደ መጋቢው እንዲህ ብሎ ደብዳቤ ጻፈ ይችን ደብዳቤ በምታነባት ጊዜ ደብዳቤዋን ይዞ የመጣውን ገድለህ በጉድጓድ ውስጥ ጣለው ማንም አይወቅ በመካከላቸውም የሚተዋወቁበትን ምልክት ጽፎ አሸጋት። ለባሕራንም ሰጠው ለመንገዱም የሚሆነውን ስንቅ ሰጠው ባሕራንም ተነሥቶ ጉዞውን ጀመረ ሲጓዝም ሰንብቶ የአንዲት ቀን ጐዞ ሲቀረው እነሆ የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ሚካኤል በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ አንተ ጐልማሳ የያዝኸው ምንድነው አለው ወደ ዕገሌ አገር ወደ ቤቱ ለማድረስ ከአንድ ባለጸጋ የተጻፈች መልእክት ናት አለው ያቺን ደብዳቤ አሳየኝ አለው እርሱም ስለ ፈራ ሠጠው።

በዚያን ጊዜም የከበረው መልአክ ሚካኤል ያቺን የሞት መልእክት ደመሰሳት በእርሷ ፈንታም በንፍሐት ለውጦ እንዲህ ብሎ ጻፈ ይቺን ደብዳቤ ይዞ ለመጣ ባሕራን ለሚባል ሰው ይቺ ደብዳቤ ደርሳ በምትነበብበት ጊዜ ልጄ እገሊትን አጋቡት በውስጥና በውጭ ያለ ንብረቴንና ጥሪቴን ወንዶችና ሴቶች ባሮቼን ጠቅላላ ንብረቴንም አውርሼዋለሁና የፈለገውንም ሊያደርግ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና እኔን አትጠብቁኝ። እኔ ብዙ እዘገያለሁ የኔ ሹም ዕገሌ ሆይ በእኔና በአንተ መካከል ይቺ ምልክት እነኋት ከዚህ በኋላ አሽጐ ለባሕራን ሰጠውና ወደ ባለጸጋው ቤት ሒደህ ይቺን ደብዳቤ ለሹሙ ሰጠው በጎዳናም እኔ እንደ ተገናኘሁህ አትንገረው እንዳይገድልህም ይህን የሞት ደብዳቤ ለውጬልሃለሁ አለው። ባሕራንም እሺ ጌታዬ ያዘዝኽኝን ሁሉ አደርጋለሁ አለ።

ባሕራንም ወደ ባለጸጋው ቤት በደረሰ ጊዜ ያቺን ደብዳቤ ለሹሙ ሰጠው በአነበባትም ጊዜ በመካከላቸው ያለውን ምልክት አገኘ አስተውሎም አርግጠኛ እንደሆነ አወቀ። ከዚህም በኋላ ለባሕራን ሠርግ አዘጋጅቶ እንደሚገባ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በተክሊል የባለጸጋውን ልጅ አጋቡት። አርባ ቀን ያህልም ደስታና ሐሴት እያደረጉ ኖሩ።

ከዚህ በኋላ ባለጸጋው ከሔደበት መመለሻው ጊዜ ሁኖ በደስታ የሆነውን የመሰንቆና የእንዚራ ድምፅ ሰምቶ ይህ የምሰማው ምንድነው ብሎ ጠየቀ እነርሱም ስሙ ባሕራን ለተባለ የአንተን ደብዳቤ ላመጣ ጐልማሳ ሰው ልጅህ ዕገሊትን አጋቡት እነሆ ለአርባ ቀናት በሠርግ ላይ ነው። ገንዘብህንና ጥሪትህን ሁሉ ወንዶችና ሴቶች ባሮችህን አንተ እንዳዘዝክ ሰጥተውታል አሉት። ይህንንም በሰማ ጊዜ ደንግጦ ከፈረሱ ላይ ወደቀ በድንገትም ሞተ።

ባሕራንም በጎ ሥራዎችን የሚሠራ ሆነ የተገለጸለትና ከመገደል ያዳነው የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ሚካኤል እንደሆነ ሊገድለው የሚሻውን የባለጸጋውን ጥሪቱን ሁሉ ያወረሰውም እርሱ እንደ ሆነ ተረዳ የዚህንም የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን መታሰቢያ በየወሩ ያደርግ ጀመረ ቤተ ክርስቲያንም ሠራለት የቅዱስ ሚካኤልንም ሥዕሉን አሥሎ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ አደረገው ከእርሱም ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ ባሕራንም ቅስና ተሹሞ እስከ ዕለተ ሞቱ በዚያች ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ሁኖ ኖረ በዚህ በከበረ የመላእክት አለቃ ሚካኤል አማላጅነት ከእናቱና ከአባቱ ከልጆቹም ጋራ የዘላለም ሕይወትን ወረሰ።

መድኃኒታችን በተነሣበትም ቀን ይህ ክቡር መልአክ ሚካኤል ከውስጠኛው መጋረጃ ውስጥ ገብቶ በክብር ባለቤት ፊት እንዲህ እያለ ይለምናል እውነት ስለሆነ ቃል ኪዳንህ በምድር መታሰቢያዬን የሚያደርጉትን ትምርልኝ ዘንድ ፈጣሪዬ ሆይ እኔ አገልጋይህና መልእክተኛህ ከቸርነትህ እለምናለሁ አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህና።

የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ ብሎ ይመልስለታል የመንፈሳውያን ሰማያውያን መላእክት አለቃቸው ሚካኤል ሆይ መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ መሸከም እንደምትችል ከሲኦል ሦስት ጊዜ በክንፎችህ ተሸክመህ እንድታወጣ እነሆ እኔ አዝዤሃለሁ።

ይህንንም ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት የበዓሉን መታሰቢያ ከሚያደርጉት በክንፎቹ ተሸከሞ የእሳቱን ባሕር አሳለፋቸው እነርሱንም ከብቻው ጌታ በቀር የሚቆጥራቸው የለም። ስለዚህም የዚህን ታላቅ የከበረ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ለማድረግ መታገል ይገባናል እርሱ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን ዘንድ በዘመናችን ሁሉም ይጠብቀን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይ ዘንድ መከራችንንም ያርቅ ዘንድ የምድራችንንም ፍሬ ይባርክ ዘንድ ፈቃዱንም ለመሥራት ይረዳን ዘንድ ከእኛ ወገን የሞቱትን ዕረፍተ ነፍስ ይሰጥ ዘንድ ወደ መንገድ የሔዱ አባቶቻችንና ወንድሞቻችንን ወደ ቤቶቻቸው በሰላም በጤና ይመልሳቸው ዘንድ በመካከላችንም ፍቅር ያደርግልን ዘንድ እስከ መጨረሻዪቱም ሕቅታ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ ይለምናልና።

የክርስቶስ ወገኖች የሆኑ መኳንንቶቻችንንም ጠብቆ በወንበሮቻቸው ላይ ያጸናቸው ዘንድ የሳቱትንም ወደ ቀናች ሃይማኖቱ ይመልሳቸው ዘንድ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

ዳግመኛም በዚህች ቀን እግዚአብሔርን የሚፈራ አስተራኒቆስ የሚስቱ የቅድስት አፎምያ የዕረፍቷ መታሰቢያ ሆነ። ይህም ሰው በየወሩ ሦስት በዓላቶችን እያከበረ ኖረ እሊህም ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ መታሰቢያ በየወሩ በሃያ ዘጠኝ፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል መታሰቢያ በየወሩ በሃያ አንድ፣ የከበረ የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያም በየወሩ በዐሥራ ሁለት ናቸው።

የሚሞትበትም ጊዜው ሲቀርብ እርሱ ሲሠራው የነበረውን ምጽዋት ይልቁንም እሊህን ሦስቱን በዓላት እንዳታስታጉል ሚስቱን ቅድስት አፎምያን አዘዛት። አርሷም የከበረ የመልአኩ የሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባሏን ለመነችው እርሱም አሠርቶ ሰጣትና በቤቷ ውስጥ በክብር አኖረችው።

ባሏም ከአረፈ በኋላ ባሏ ያዘዛትን መሥራት ጀመረች ሰይጣን ግን ቀናባት በመበለት ሴት መነኲሲት ተመስሎ ከእርሷ ጋራ ተነጋገረ እንዲህም አላት እኔ አዝንልሻለሁ እራራልሻለሁም ገንዘብሽ ሳያልቅ የልጅነትሽም ወራት ሳያልፍ አግብተሽ ልጅ ትወልጂ ዘንድ እመክርሻለሁ ባልሽም መንግሥተ ሰማያትን ወርሷል ምጽዋትም አይሻም።

አፎምያም እንዲህ ብላ መለሰችለት እኔ ከሌላ ሰው ጋራ ላልገናኝ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አድርጌያለሁ ርግቦችና መንጢጦች እንኳ ሌላ ባል አያውቁም በእግዚአብሔር አርአያ ከተፈጠሩ ሰዎች ይህ ሊሆን እንዴት ይገባል። ምክሩንም ባልሰማች ጊዜ አርአያውን ለውጦ በላይዋ ጮኸባት እንዲህም አላት እኔ በሌላ ጊዜ እመጣለሁ እርሷም የከበረ የመልአኩ የሚካኤልን ሥዕል ይዛ አሳደደችው።

ከዚህም በኋላ ሰኔ ዐሥራ ሁለት የከበረ የመልአኩ የሚካኤል በዓል በሚከብርበት ዕለት እርሷም የበዓሉን ዝግጅት ስታዘጋጅ ሳለች ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ አፎምያ ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እኔ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነኝ ጌታ ወደ አንቺ ልኮኛልና እርሱም ይህን መመጽወትሽን ትተሽ ለአንድ ምእመን ሚስት ትሆኚ ዘንድ ጌታ አዞሻል ባል የሌላት ሴት መልሕቅ የሌለውን መርከብ እንደምትመስል ዕወቂ እንደ አብርሃምና ያዕቆብ እንደ ዳዊትም እንደእነርሱ ያሉ ብዙ ሴቶችን እንዳገቡ እግዚአብሔርንም ደስ እንዳሰኙት ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጥቅሶችን ያመጣላት ጀመረ።

ቅድስት አፎምያም መልሳ አንተ የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ የመስቀል ምልክት ከአንተ ጋራ ወዴት አለ የንጉሥ ጭፍራ የሆነ ሁሉ የንጉሡን ማሕተም ሳይዝ ወደ ሌላ ቦታ አይሔድምና አለችው። ሰይጣኑም ይህንን በሰማ ጊዜ መልኩ ተለወጠና አነቃት እርሷም ወደ ከበረው መልአክ ወደ ሚካኤል ጮኸች ወዲያውኑም ደርሶ አዳናት። ያንንም ሰይጣን ይዞ ይቀጣው ጀመረ ሰይጣኑም ጮኸ ማረኝ ያለ ጊዜዬ አታጥፋኝ እግዚአብሔር እስከ ዓለም ፍጻሜ ታግሦናልና እያለ ለመነው ከዚያም ተወውና አበረረው።

የከበረ መልአክ ሚካኤልም እንዲህ አላት ብፅዕት አፎምያ ሆይ ሒደሽ የቤትሽን ሥራ አዘጋጂ አንቺ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ትለዪአለሽና እነሆ እግዚአብሔርም ዐይን ያላየውን ጆሮም ያልሰማውን በሰው ልብም ያልታሰበውን አዘጋጅቶልሻል። ይህንንም ብሎ ሰላምታ ሰጣት ወደ ሰማያትም ዐረገ። የበዓሉንም ዝግጅት እንደሚገባ ከፈጸመች በኋላ ወደ ኤጲስቆጶሱና ወደ ካህናቱ ሁሉ ላከች ወደርሷም በመጡ ጊዜ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ይሰጧቸው ዘንድ ገንዘቧን ሁሉ አስረከበቻቸው።

ከዚህም በኋላ ተነሥታ ጸለየች የከበረ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤልንም ሥዕል አንስታ ታቅፋ ሳመችው ያን ጊዜም በሰላም አረፈች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

(ንጉሠ ኢትዮዽያ)

ዳግመኛም በዚህች ዕለት የተባረከና የተመሰገነ በሰማያት ያለ ምሥጢርን ያየ የኢትዮጵያ ንጉሥ ላሊበላ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ።ይህንንም ቅዱስ ወላጆቹ በወለዱት ጊዜ እግዚአብሔርን በመፍራትና በበጎ ሥራ ሁሉ አሳደጉት። አድጎ አካለ መጠን በአደረሰ ጊዜ ታላቅ ወንድሙ ንጉሥ ቀናበት መልእክተኞችንም ልኮ ወደርሱ አስመጣው ምክንያትም ሽቶ ከሦስት ሰዓት እስከ ሰባት ሰዓት እንዲገርፉት አዘዘ።

ከዚህም በኋላ በፊቱ እንዲአቆሙት አዘዘ በአቆሙትም ጊዜ የደረሰበት ጉዳት እንደሌለ አይተው ንጉሡና መኳንንቶቹ ሁሉ አደነቁ የእግዚአብሔር መልአክ ከግርፋት ሠውሮታልና። ከዚህ በኋላም ወንድሙ ንጉሥ በአንተ ላይ ስለአደረግሁት ክፉ ሥራ ወንድሜ ሆይ ይቅር በለኝ ብሎ ለመነውና እርስ በርሳቸው ታረቁ።

ከዚህ በኋላም እግዚአብሔር መንግሥትን አወረሰው። መንግሥትንም በያዘ ጊዜ እግዚአብሔርን በሚያገለግልበት ሥራ በረታ ሁልጊዜም ለድኆች ለምስኪኖችና ለችግረኞች ይመጸውት ነበር።

ክብር ይግባውና ጌታችንም የፍቅሩን ጽናት በአየ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት ወደ እርሱም ወደ ሰማያት አወጣው ዐሥሩን አብያተ ክርስቲያንም እንዴት እንደሚሠራቸው አሳየው እነርሱም ሥራቸው የየራሳቸው የሆነ ልዩ ነው ተመልሶም መንፈስ ቅዱስ እንደአራቀቀው በአስደናቂ ጥበብ አነፃቸው። እሊህንም አብያተ ክርስቲያናት አንፆ በፈጸመ ጊዜ መንግሥቱን ለወንድሙ ልጅ አወረሰ።

ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በብርሃን ሠረገላ ተቀምጦ የሚአስፈራ መብረቅን የተጐናጸፉ አእላፋት ሠራዊቶቹ ዙሪያውን ሁነው ወደርሱ መጥቶ እንዲህ አለው ወዳጄ ላሊበላ ሆይ ሰላም ይሁንልህ እኔ በማይታበል ቃሌ እነግርሃለሁ ማደሪያህ በክብር ሁሉ ከከበሩ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያቶቼ ጋራ ይሁን። በጸሎትህና በቃል ኪዳንህ ለሚታመን እምነቱ እንደ ጴጥሮስና ጳውሎስ ደም መፍሰስ ይሆንለታል።

ወደ ቤተ መቅደስህም የሔደ በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደሴ እንደ ሔደ ይሆንለታል መቃብርህንም የተሳለመ የሥጋዬን መቃብር እንደ ተሳለመ ይሆንለታል በዓመታቱ ወሮች ሁሉ የተራቡትን እያጠገበ የተጠሙትንም እያጠጣ መታሰቢያህን ለሚያደርግ እኔ የተሠወረ መና እመግበዋለሁ የሕይወት ጽዋንም አጠጣዋለሁ። በመታሰቢያህ ቀንም ዕጣን ወይም ስንዴ የሚያገባውን እኔ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት በውስጠኛው መጋረጃ አስቀምጬ ከተቆረሰው ሥጋዬ አቆርበዋለሁ በአማላጅነትህም እየታመነ የገድልህንና የቃል ኪዳንህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ያንተ ስም በተጻፈበት ቦታ እኔ ስሙን እጽፋለሁ በፍጹም ልቡ ለሚያምን ይህን የማይታበል ቃል የተናገርኩ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እኔ ኢየሱስ ነኝ አለው።

ላሊበላም ይህን ቃል ኪዳን ስለ አጸናለት ክብር ይግባውና ጌታችንን እያመሰገነ በምድር ላይ ወድቆ ሰገደ። ጌታችንም ሰላምታ ሰጥቶት በክብርና በምስጋና ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚህም በኋላ ጥቂት ሕማም ታሞ በሰላም አረፈ። ነፍሱንም የብርሃን መላእክት ተቀብለው የዘላለም ሕይወት ማደሪያ ወደሆነ ማረፊያው አስገቡት።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

በዚህችም ዕለት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስድስተኛ የሆነ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮስጦስ አረፈ። ይህም የከበረ አባት ከእስክንድርያ አገር ሰዎችም የተማረ አዋቂ ሰው ነበረ። እርሱንም ከእናትና አባቱ ከሌሎችም ብዙዎች ሰዎች ጋራ የክርስትና ጥምቀትን ወንጌላዊ ማርቆስ አጠመቀው። ከዚህም በኋላ አናጉንስጢስነት ሾመው ከአናጉንስጢስነትም በኋላ ዲቁና ሾመው በቅዱስ አንያኖስ ዘንድ እያገለገለው የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን በመማር አደገ።

ሕዝቡንም ሁልጊዜ ይመክራቸውና ይገሥጻቸው ያስተምራቸውም በቀናች ሃይማኖትም ያጸናቸው ነበር። አባ አብርምዮስም በአረፈ ጊዜ ያለ ፈቃዱ ወስደው በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በግብጽ አገር ያለች ቤተ ክርስቲያንንም በመልካም አጠባበቅ እንደሚገባ ጠበቃት። በወንጌላዊው ማርቆስ ወንበርም ዐሥራ ሁለት ዓመት ከኖረ በኋላ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

በዚህችም ዕለት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ ሰባተኛ የሆነው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቄርሎስ አረፈ። ከእርሱ አስቀድሞ የነበረ አባ ገብረ ክርስቶስ በአረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶሳትና የሕዝብ አለቆች ተስማምተው ወደ አስቄጥስ ወደ አባ መቃርስ ገዳም ወጡ ለዚች ለከበረች ሹመትም የሚገባውን እየመረመሩ ሁለት ወር ያህል ኖሩ።

በአባ ዮሐንስ ሐጺር ገዳም የትንቢት መንፈስ ያደረበት ስሙ ገብረ ኢየሱስ የሚባል አንድ ሰው ነበር ለእርሱም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾለት እንዲህ አለው። ለኤጲስቆጶሳቱ ለዚች ለከበረች ሹመት የሚገባ ስሙ ገዐርጊ የሚባል በመካከላችሁ አለና አትዘኑ በላቸው አለው።

ያን ጊዜም ቅዱስ ገብረ ኢየሱስ ይህን ነገር ነገራቸው ከዚህም በኋላ ይህን አባት ይዘው ያለፈቃዱ በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት እርሱም እጅግ አዋቂ ነበረና በሹመቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ደስ ተሰኘች። ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመ ብዙዎች አብያተ ክርስቲያናትንም አደሰ።

ከዚህም በኋላ ለኢትዮጵያ አገር አንድ ጳጳስ ሾመ በዕውቀቱና በደግነቱ እጅግ ደስ ተሰኙበት ብዙዎችን ከክፉ ሥራ ወደ በጎ ሥራ መልሶአቸዋልና እግዚአብሔርንም የሚፈሩ ሆነዋልና በበጎ ሥራም ጸንተዋልና።

ለንጉሡ እንዲሁም ለመኳንንቶቹ ብዙ ሚስቶች ነበሩአቸውና እርሱ ስለ አስተማራቸውና ስለገሠጻቸው ሚስቶቻቸውን አሰናብተው እንደ ሕጉ በየአንዳንዲት ሴት ጸኑ።

የከበረ አባ ቄርሎስም ዐሥራ አንድ ዓመት ከሦስት ወር ተኩል ሲፈጸምለት ሥጋውንና ደሙን ተቀብሎ በሰላም አረፈ ሥጋውንም ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደ አባ መቃርስ ደብር ተሸክመው ወስደው ከከበሩ ሊቃነ ጳጳሳት ዐፅም ጋራ አኖሩት።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን፤ የከበረ መልአክ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን።

( )

100 የቅዱስ ሚካኤል ስምና ክብር ፦1) ሊቀ መላእክት2) የሰማይ ሰራዊት አዛዥ3) የጌታ ሰራዊት መሪ4) የሰማይ ኃይላት ልዑል5) ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት መካከል የመጀመርያው 6) የገነት  ...
06/18/2026

100 የቅዱስ ሚካኤል ስምና ክብር ፦
1) ሊቀ መላእክት
2) የሰማይ ሰራዊት አዛዥ
3) የጌታ ሰራዊት መሪ
4) የሰማይ ኃይላት ልዑል
5) ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት መካከል የመጀመርያው
6) የገነት ጠባቂ
7) ታማኝ ጠባቂ
😎 የሰይጣን ያሸነፈ
9) የቤተክርስቲያን ተከላካይ
10) የሕዝብ ጠባቂ
11) የክብር አብሳሪ
12) የጽድቅ ተዋጊ
13) ሰማያዊ አማላጅ
14) የሥላሴ አገልጋይ
15) የፍትህ ሰይፍ የየዘ
16) የነበልባል ሰይፍ ተሸካሚ
17) የክፋት ሰራዊትን አጥፊ
18) የነፍሳት መሪ
19) የቅድስና ምስክር
20) አዋጅ ነጋሪ
21) የመላእክት ሠራዊት ብርሃን
22) የእስራኤል ጠባቂ
23) የመላእክት ጦርነት መሪ
24) ነበልባላዊ
25) የገዳማት ጠባቂ
26) የጥንካሬ ግንብ
27) የመለኮታዊ ኃይል ማኅተም
28) የአምላክ ነጎድጓድ
29) የእግዚአብሔር በቀል ሰይፍ ተሸካሚ
30) የፍርድ አስፈጻሚ
31) የመለኮት ዙፋን ጠባቂ
32) የሰልፉ መሪ
33) የባህራን ወደጅ
34) የጨለማ ውስጥ ብርሃን
35) የጻድቃን ወዳጅ
36) የሰማዕታት ድፍረት
37) የነብያት ረዳት
38) የመሠዊያ ላይ አገልጋይ
39) የጌታ ትእዛዝ ድምፅ
40) የትሁታን ጋሻ
41) የቤተክርስቲያን ጠባቂ
42) በገነት ውስጥ የመጀመሪያው
43) የሰራዊቶች አስታጣቂ
44) የሰማይ የድል መለከት
45) ዘንዶውን ያደቀቀ (ራእይ 12)
46) ንቁ ጠባቂ
47) የመለኮት እሳት ተሸካሚ
48) የገነት ደጃፍ ጠባቂ
49) አዛኝ መልአክ
50) ሩህሩህ መልአክ
51) የተሰደዱትን አዳኝ
52) የተጨቆኑ ረዳት
53) የደካሞች ብርታት
54) መብረቃዊ ልብስ
55) የታዛዥነት አርአያ
56) የመላእክት ዓለም ኮከብ
57) የሕያው አምላክ አገልጋይ
58) የቁጣ አብራጅ
59) ሐዋርያ መልአክ
60) የአጋንንት ፍርሃት
61) የጠዋት ኮከብ
62) የሰራዊተ መላእክት ክብር
63) የሚያቃጥል እሳት
64) የሰማይ ሰራዊት ዓይን
65) የዋህ መልአክ
66) ከዋነኞቹ መልአክ አንዱ
68) ጠላትን የሚያዋርድ
69) መስቀል ተሸካሚ
70) የጽዮን ክብር ጠበቃ
71) በልዑል የተመረጠ
72) የዳግም ምጽአት አርበኛ
73) የቃል ኪዳኑ መልአክ
74) የሰማይ ግዛት አበጋዝ
75) ተወዳጅ መልአክ
76) መንጦላእት ከፋች
77) ባለ መለከት መልአክ
78) የምህረት መልአክ
79) የፍቅር መልአክ
80) የመለኮት መልእክት የሚያስፈጽም
81) እይባን የሚያብስ
82) የእግዚአብሔር ቅጣት መሣሪያ
83) ዐይኑ የሚያበራ
84) ፍርድ ወንበር ፊት አማላጅ
85) የእግዚአብሔር ቅድስና ብርሃን
86) የሕይወት መጽሐፍ ተሸካሚ
87) በለ ራእይ መልአክ
88) በሞት ውስጥ ረዳት
89) ድል አድራጊ
90) የምስኪኖች ወዳጅ
91) ስምህ ድንቅ የሆነ
92) ታማኝ የሕያው ብርሃን
92) የሰማይ ንፅህና ክብር
93) የበረከት ድልድይ
94) የዳንኤል ወዳጅ
95) የመጨረሻውን መለከት አስተዋዋቂ
96) የጻድቃን በረከት አዳይ
97) የክፉዎች ሽብር
98) የኢየሩሳሌም ሰማያዊት ክብር
99) የክርስቶስ ታማኝ አገልጋይ
100) የነፍስ ወዳጅ እና ጠባቂ

ልመናው አማላጅነቱ አይለየን። ይጠብቀን ይጎብኘን ይምራን ይከተለን። አሜን ሳትል አትለፍ!

#አሜን🙏❤🙏
ከመጋቤ ምስጢር ቡሩክ አሳመረ የፌስቡክ ፔጅ የተወሰደ

Address

Washington D.C., DC

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Angetamabo -አንገታም አቦ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Angetamabo -አንገታም አቦ:

Featured

Share