Badr Ethiopia

Badr strives to foster transformative social change by implementing impactful, sustainable, and scalable solutions grounded in Islamic principles, empowering the Ethiopian Muslim community.

08/30/2026

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሰው ልጅ በምድር ላይ የሚያሳልፈው ዕድሜ በዓመታት ብዛት ሳይሆን፣ ለትውልድ ጥሎት በሚያልፈው የማይሽር በጎ አሻራ ይለካል። ላለፉት አርባ ዓመታት የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን መብት፣ ክብርና አንድነት ለማስጠበቅ ግንባር ቀደም ታጋይ፣ መሪ እና የሕዝብ አገልጋይ የነበሩት ክቡር ሐጂ ነጂብ መሐመድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ሐጂ ነጂብ በሕይወት ዘመናቸው ከሠሯቸው አንጸባራቂ ታሪኮች መካከል፣ ከዛሬ 25 ዓመታት በፊት ከጥቂት ጓዶቻቸው ጋር በመሆን 'በድር ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት'ን መመስረታቸው ግንባር ቀደሙ ነው። የተቋሙ ፕሬዝዳንት በመሆን በማገልገልም፣ ከሀገር ውጭ በሚኖረው የዲያስፖራ ማህበረሰብ ዘንድ ጠንካራ የትስስር፣ የመረዳዳት እና የአንድነት መንፈስ እንዲገነባ የላቀ ሚና ተጫውተዋል። "የበድር ታሪክ ከሐጂ ነጂብ ስምና አስተዋጽኦ ፈጽሞ ተነጥሎ አይታይም" ሲል ተቋሙ ባወጣው የሐዘን መግለጫ የኚህን ታላቅ ሰው ውለታ አስታውሷል።

የሐጂ ነጂብ የትግል ምዕራፍ በተቋም ምስረታ ብቻ የተገደበ አልነበረም። የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የመብት ጥያቄ አንግበው አምባገነን ሥርዓቶችን በድፍረት ከመሞገት ወደኋላ ብለው አያውቁም። በሀገር ቤት የነበረውን የመብት ጥያቄ በማስተጋባት ከወንድሞቻቸው ጋር በመሆን ፊት ለፊት የተጋፈጡ ሲሆን፣ በተለይም በ'ድምፃችን ይሰማ' የመብት ትግል ወቅት ለእስር የተዳረጉትንና ቤተሰቦቻቸውን በክፉ ቀናቸው ከጎን በመቆም ያሳዩት የማይናወጥ አጋርነት በማህበረሰቡ ልብ ውስጥ ለዘላለም ተቀርጾ የሚኖር ነው።

የበድር ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት፣ ማህበረሰቡ ይህንን ታላቅ አገልጋይ በሞት በማጣቱ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል። "እኚህ ታላቅ ሰው በአካል ከዚህ ዓለም ቢለዩንም፣ የሠሩት መልካም ሥራ፣ ያስተላለፉት እሴት እና የቆሙለት ዓላማ በትውልድ ልብ ውስጥ ይኖራል" በማለትም ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ እንዲሁም የበድር አባል ለሆነው ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን አባላት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ መጽናናትን ተመኝቷል።

ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሒ ራጂኡን! አላህ (ሱ.ወ) ለሐጂ ነጂብ መሐመድ ምሕረቱን አውርዶ በጀነተል ፊርደውስ እንዲያኖራቸው እንመኛለን።

የሐዘን መግለጫ ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሒ ራጂኡን!! ታላቅ ታጋይ፣ መሪና የማህበረሰብ አገልጋይ በነበሩት በክቡር ሐጂ ነጂብ መሐመድ ህልፈት በድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያዊያን  ሙስሊሞች ድርጅ...
08/30/2026

የሐዘን መግለጫ
ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሒ ራጂኡን!!

ታላቅ ታጋይ፣ መሪና የማህበረሰብ አገልጋይ በነበሩት በክቡር ሐጂ ነጂብ መሐመድ ህልፈት በድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ድርጅት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።
የተከበሩ ሐጂ ነጂብ መሐመድ የበድር ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት መስራችና ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉ ሲሆን የዲያሰፖራው ማህበረሰብ ጠንካራ ትስስር እንዲኖረው አበክረው የሠሩ እና በተለይም በኢትዮጵያ ሙሰሊሞች የመብት ትግል ሰው በላውን ስርዐት በመጋፈጥ ሀገር ቤት ድረሰ የዲያሰፖራውን ጥያቄ በመያዝ ከወንድሞች ጋር በመሄድ የሞገቱ ከመሆናቸውም ባሻገር በድምፃችን ይሰማ የመብት ትግል ታሣሪዎችንና ቤተሰቦቻቸውን በክፉ ቀን ከጎናቸው በመቆም ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚዘነጋ አይደለም።
ላለፉት አርባ ዓመታት የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን መብት፣ ክብርና አንድነት ለማስጠበቅ በትጋት የታገሉትን፣ ለሙስሊም ዲያስፖራም የማይረሳ አስተዋፅኦ ያደረጉት ክቡር ሐጂ ነጂብ መሐመድ ወደ አኼራ በመሄዳቸው እኛ የበድር አባል ኮሚኒቲዎች አባሎችና አመራሮች የተሰማንን ከፍተኛ ሐዘን በድጋሚ እንገልፃለን።
ሐጂ ነጂብ መሐመድ በሕይወታቸው ዘመናቸው ለሕዝብ ጥቅም፣ ለፍትሕ፣ ለመብት እና ለአንድነት የቆሙ ታላቅ የማህበረሰብ አገልጋይ ነበሩ። በተለይም ከኢትዮጵያ ውጭ በሚኖሩ ወገኖቻችን መካከል የመተባበር፣ የመረዳዳትና የአንድነት መንፈስ እንዲጠናከር በርካታ ሥራዎችን ሠርተዋል።ከዛሬ ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ከጥቂት ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን የበድር ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅትን በመመስረት፣ ድርጅቱንም በፕሬዝዳንትነት በመምራት የድርጅቱን ዓላማና ራዕይ ለማሳካት የላቀ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።የበድር ኢትዮጵያ አመሰራረት ዕድገትና ታሪክ ከሐጂ ነጂብ መሐመድ ስምና አስተዋፅኦ ተነጥሎ የሚታይ አይደለም። ለድርጅቱ መመስረት፣ መጠናከርና በዓላማው ላይ እንዲጸና ያደረጉት ጥረት በድርጅቱ ታሪክ ውስጥ ሁሌም በክብር ይታወሳል።
እኚህ ታላቅ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም፣ የሠሩት መልካም ሥራ፣ ያስተላለፉት እሴት፣ የቆሙለት ዓላማ እና ያሳረፉት አሻራ በትውልድ ልብ ውስጥ ይኖራል። የሰው ልጅ ሕይወት የሚለካው በዓመታት ብቻ ሳይሆን፣ በሕዝብ መካከል በሠራው ሥራና በተወው መልካም አሻራ ነው። ሐጂ ነጂብ መሐመድም ይህንን በሕይወታቸው ካረጋገጡ ጥቂት ጀግኖቻችን መካከል አንዱ ናቸው።
በድር ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት ይህን ታላቅ የማህበረሰብ አገልጋይ በሞት በማጣቱ እጅግ አዝኗል። ለቤተሰቦቻቸው፣ ለዘመድ አዝማዶቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው፣ ለባልደረቦቻቸውና የበድር ኢትዮጵያ አባል ድርጅት ለሆነው ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን አባላት ሀዘናቸውን እንደምንጋራ እየገለፅን ለመላው የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ጥልቅ የሆነ የሐዘን መግለጫችንን እናቀርባለን።አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ለሐጂ ነጂብ መሐመድ ምሕረቱን ይስጣቸው፤ በጀነተል ፊርደውስ ያኑራቸው፤ መልካም ሥራቸውን ሁሉ ለአኼራ መዳኛ ያድርግላቸው። ለቤተሰቦቻቸውና ለሁላችንም የተረፈውን ሕይወት በትዕግሥትና በጽናት እንድንጓዝ ያግዘን።
ሁላችንም ከአላህ ነን፤ ወደ እርሱም ተመላሾች ነን
የበድር ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት
ነሐሴ 2018

ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሒ ራጂኡን!!
08/30/2026

ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሒ ራጂኡን!!

👏👏👏የተለያዩ ሀሳቦች፣ አመለካከቶችና ተሞክሮዎች በሰላማዊ የምክክር መድረክ መቅረባቸውን እንደ ትልቅ የሀገራዊ መግባባት እሴት እንመለከተዋለን። ምክክር ልዩነቶችን በግጭት ሳይሆን በውይይት፣ ...
08/25/2026

👏👏👏የተለያዩ ሀሳቦች፣ አመለካከቶችና ተሞክሮዎች በሰላማዊ የምክክር መድረክ መቅረባቸውን እንደ ትልቅ የሀገራዊ መግባባት እሴት እንመለከተዋለን። ምክክር ልዩነቶችን በግጭት ሳይሆን በውይይት፣ በመተዛዘንና በመግባባት ለመፍታት የሚያስችል የሰላም መሠረት ነው።
ድርጅታችን በድር ኢትዮጵያ በመርህ ደረጃ የሰላም፣ የፍትሕ፣ የመቻቻል፣ የይቅርታ እና የሰው ልጅ ክብር እሴቶችን የሚያጎለብት ማንኛውንም ሀገራዊ ጥረት ይደግፋል። በዚህ መሠረት የሀገራዊ ምክክሩ ውጤቶች ከሰነድና ከመግለጫ ባለፈ ወደ ተጨባጭ ተግባር እንዲለወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በድር ኢትዮጵያ ለምክክሮ ሂደቱ ሰኬት                      የበኩሉን ይወጣል!!!      ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በራሷ ጉዳይ ምክክር ማድረግ እንደሚያስፈልጋት ብዙ...
07/15/2026

በድር ኢትዮጵያ ለምክክሮ ሂደቱ ሰኬት
የበኩሉን ይወጣል!!!
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በራሷ ጉዳይ ምክክር ማድረግ እንደሚያስፈልጋት ብዙዎች ያምናሉ።በድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙሰሊሞች ድርጅት በምክክር ሂደቱ ከኢትዮጵያ ሠላም ባሻገር ለዘመናት ሲንከባለሉ የነበሩ የሙስሊሞች ጥያቄዎች ምላሽ ያገኙ ዘንድ የተለያዩ ሰነዶችን በማዘጋጀት ኮሚሽነሮቹ አሜሪካ በመጡበት ወቅትም ሆነ አዲሰ አበባ ለሚገኘው የምክክር ኮሚሽኑ በዝርዝር አቅርቧል።
ኢትዮጵያ ሀገራችን ሣታጣ ያጣች ማደግ እየቻለች የትናንትና ዕዳን ለትውልድ በማሸከም እየገነባን የምናፈርስበትን፣ እየወለድን የምናገዳድልበትን አሰከፊ የመተላለቅ ድርጊት አቁመን ወደ አዲስና የተሻለ የታሪክ ምዕራፍ ለመሸጋገር በድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት ዛሬ በተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ሂደት የበኩሉን አስተዋፅኦለማድረግ በሀገር ቤትም ሆነ በውጪ ያሉ አባሎቹን በማሣተፍ በንቃት በመሣተፍ ላይ ይገኛል።

06/26/2026

👏👏ከበድር ኢትዮጵያ የተሰጠ የእንኳን ደስ አላችሁ መግለጫ
በድር ኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ትግልን አስመልክቶ ለኢትዮጵያው ጠ/ሚ/ር ካቀረባቸው 16 ጥያቄዎች አንዱ የነበረው እና ላለፉት 25 አመታት ህዝበ-ሙስሊሙ ሲቃወመው የነበረው የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 188/1992 ን ሙሉ በሙሉ የሚተካው አዲሱ ረቂቅ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመፅደቁ በድር ኢትዮጵያ የተሰማውን ደስታ ይገልፃል።
በአዲስ መልክ የተዘጋጀው ይህ አዋጅ የፍርድ ቤቶቹን የዳኝነት ሥልጣን፣ አደረጃጀትና አሠራር፣ የዳኞች አሿሿምና በጀት እንዲሁም የፍርድ ቤቶች አስተዳደር ጉባኤን በአዲስ መልክ ማቋቋምን ጨምሮ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችን በዝርዝር አካቷል።
የአዋጁ መፅደቅ ህዝበ ሙስሊሙ ከመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ ሲያነሳ ለነበረው የረጅም ጊዜ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን አዋጁ እንዲፀድቅ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕ/ት የክብር ዶ/ር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ ምሁራን ፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመረሮች፣ ረቂቁን ያዘጋጁ የኮሚቴ አባላት፣ የፓርላማው የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እና አሰተዋፅኦ ላበረከቱ ወገኖች በድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት ከፍተኛ ምስጋናውን ያቀርባል።
በኢትዮጵያ ሙስሊሞች መብት ጉዳይ አስፈላጊውን ከማድረግ ለአፍታም ተዘናግቶ የማያውቀው በድር በድር ኢትዮጵያ በትኩረት ይከታተለው የነበረ ሂደት ዕልባት አግኝቶ በዚህ መልክ በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታችንን ለህዝበ ሙስሊሙ እያስተላለፍን የማሻሻያ አዋጁን ተከትሎ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ለህዝበ ሙስሊሙ ተገቢ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ህዝበ ሙስሊሙ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በድር ኢትዮጵያ ጥሪውን ያስተላልፋል።
በድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት

🌙 እንኳን ለ1448 ዓ.ሂ. አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!            አላህ (ሱ.ወ.) አዲሱን የሂጅራ ዓመት ለመላው የበድር ቤተሰቦችና ሙስሊም ማህበረሰብ የሰላም፣ የምሕረት፣ የበረ...
06/16/2026

🌙 እንኳን ለ1448 ዓ.ሂ. አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!
አላህ (ሱ.ወ.) አዲሱን የሂጅራ ዓመት ለመላው የበድር ቤተሰቦችና ሙስሊም ማህበረሰብ የሰላም፣ የምሕረት፣ የበረካ፣ የጤና፣ የእምነት ጽናትና የመልካም ሥራ ዓመት ያድርግልን።
ይህ አዲስ ዓመት ያለፉትን ስህተቶቻችን በመገምገም፣ ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት በማጠናከር፣ በፍቅር፣ በአንድነትና በመተሳሰብ የምንጓዝበት የበረከት ዓመት ይሁንልን።
መልካም አዲስ ዓመት
! كل عام وأنتم بخير، جعل الله هذا العام عام خير وبر وسلام.

06/05/2026

♦️♦️♦️በአርሲ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን ጥቃትእናወግዛለን !!
ከበድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት የተሰጠ መግለጫ

06/05/2026

Address

5185 MacArthur Boulevard NW
Washington D.C., DC
20016

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Badr Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Badr Ethiopia:

Shortcuts

Featured

Share