ዲሲ ግብረ ኃይል DC Task Forces

ዲሲ ግብረ ኃይል DC Task Forces Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ዲሲ ግብረ ኃይል DC Task Forces, Community Center, Washington D.C., DC.

08/15/2023
የ "ጉማ አዋርድ" አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ ትናንት ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል ከተካሄደው የሽልማት ስነ ስርአት በኋላ ለእስር ተዳርጓል። በስፍራው ከነበሩ ሰዎች በደረሰኝ መረጃ መሰረት ዮናስን ...
06/10/2023

የ "ጉማ አዋርድ" አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ ትናንት ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል ከተካሄደው የሽልማት ስነ ስርአት በኋላ ለእስር ተዳርጓል።

በስፍራው ከነበሩ ሰዎች በደረሰኝ መረጃ መሰረት ዮናስን ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ከምሽቱ 5 ሰአት ገደማ ከነባለቤቱ አስረው ወስደዋቸዋል። ባለቤቱ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ብትፈታም ዮናስ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኝ ታውቋል።

በትናንትናው ፕሮግራም ላይ "ልጅ ማኛ" በሚል የምትታወቀው ቲክቶከር ባደረገችው ሜካፕ ምክንያት "ልጅቷን አምጡ" በሚል አዘጋጆቹ ተጠይቀው እንደነበር እና እስሩም ከእሱ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል በስፍራው የነበሩ ግለሰቦች እና ሌሎች ምንጮች አረጋግጠውልኛል።

የኔ ጥያቄ:

- ሜካፕ ተቀብቶም ይሁን ፒካፕ ተኮናትሮ ሀሳብን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መግለፅ በቃ ተከልክሏል?

- የፕሮግራሙ አዘጋጅ የተለያየ ልብስ ለብሶ እና ሜካፕ ተቀብቶ ለሚመጣው የሀገር ህዝብ ሁሉ ሀላፊነት አለበት?
Elias Meseret

በወቅታዊ ጉዳይ ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ-------------------------------------መብቱን በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ በወጣ ህዝብ ሙስ...
05/26/2023

በወቅታዊ ጉዳይ ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ
-------------------------------------

መብቱን በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ በወጣ ህዝብ ሙስሊም ላይ የተወሰደው እርምጃ ፍፅም ተቀባይነት የሌለው ፣ ኢ-ፍትሃዊና ኢ-ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ያወግዛል።

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ሲቲ የመስጅድ ፈረሳ እንዲቆምና የፈረሱትም በአስቸኳይ መተኪያ እንዲሰጣቸው እንዲሁም በጉዳዩ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ለሚመለከተው አካል ለማሳወቅ የተሞከረ ሲሆን የመስጅድ ፈረሳው ባለመቆሙ ህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን በዛሬው እለት በአደባባይ ድምፁን በሰላማዊ መንገድ አሰምቷል።

ይህንንም ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ተከትሎ በታላቁ አንዋር መስጅድ የፀጥታ አካል በወሰዱት ኢ-ህገ መንግስታዊ እና ኢ ሰብአዊ እርምጃ የሰው ሂይወት አልፋል፣ብዙሃን ቆስለዋል።

በመሆኑም ይህንን አስከፊ ጥቃት የፈፀሙ እና ያስፈፀሙ የፅጥታ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀን እንጠይቃለን ።

በቀጣይም የሚመለከተው አካል በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተከናወነ ያለውን ድርጊት እንዲያስቆምነና ወደ ውይይት በመምጣት ስር ነቀል የእርምትና እርምጃ ተጠናክሮ እንዲተገበር አጥብቀን እንጠይቃለን።

የሀይማኖት ጉዳይ እና የእምነት ተቋማት ጉዳይ ሁሌም ቢሆን በስክነት መታየት ሲገባው ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በእምነት በተቋማቱ ጉዳይ ሲከተሉት የነበረውን አካያሄድ እንደ ተሞክሮ ከመውሰድ ይልቅ በዚህ አከያሄድ የተሰራው አስነዋሪ ተግባር የሀገራችንን ብሎም የከተማችንን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ እየጣለ ይገኛል።

በሸገር ከተማ መስጅድን በተመለከተ እየተከናወነ ያለው ድርጊት፣ሀላፊነት የጎደለው፣የህዝበ ሙስሊሙን ክብር ያዋረደ፣ሀገራችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ፣የመንግስት የለውጥ ሪፎርምን ወደ ሀላ የሚመልስ በመሆኑ ጉዳዩ እንደ ሀገር ሊታሰብበት ይገባል።

በዛሬውም እለት በመስጅድ ፈረሳ ሳቢያ በሰላማዊ መንገድ መብቱን ለመጠየቅ በወጣው ህዝበ ሙስሊም ላይ በተወሰደው ኢ-ህገ መንግስታዊ እርምጃ ሒይወታቸው ላለፉ አላህ (ሱ.ወ) ጀነትን እንዲወፍቃቸው፣ለመላው ህዝበ ሙስሊም መፅናናትን እንመኛለን።

የከተማችንም ህዝበ ሙስሊሙ በቀጣይ ጉዳዩን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል አደራ እንላለን።

ግንቦት 18/2015

አርቲስት ሜላት ዳዊት እና አርቲስት ቤዛዊት መስፍን መታሰራቸው ተሰምቷል። መንግሰት እነዚህን አርቲስቶች በአስቸኳይ ይፍታ! ጋዜጠኛና አርቲስት በማፈን ህዝባዊ ትግሎችን ማስቆም አይቻልም።
05/25/2023

አርቲስት ሜላት ዳዊት እና አርቲስት ቤዛዊት መስፍን መታሰራቸው ተሰምቷል። መንግሰት እነዚህን አርቲስቶች በአስቸኳይ ይፍታ! ጋዜጠኛና አርቲስት በማፈን ህዝባዊ ትግሎችን ማስቆም አይቻልም።

ሰበር ዜና ታዋቂው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መምህር ብርሃኑ አድማስ ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓም በፀጥታ ኀይሎች ከቢሯቸው መወሰዳቸውን ምንጫችን አድርሶናል ።
05/22/2023

ሰበር ዜና
ታዋቂው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መምህር ብርሃኑ አድማስ ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓም በፀጥታ ኀይሎች ከቢሯቸው መወሰዳቸውን ምንጫችን አድርሶናል ።

የፋሽሽቱ አገዛዝ አብይ አህመድ የማህበረ ቅዱሳንን ቴሌቪዥን አግዷል።
05/21/2023

የፋሽሽቱ አገዛዝ አብይ አህመድ የማህበረ ቅዱሳንን ቴሌቪዥን አግዷል።

05/20/2023

ሰበር ዜና ታላቁ እስክንድር ነጋ መልዕክት አስተላልፋል!!

ወጣት ቢንያም ታደሰ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሚገኝ ሲሆን እስካሁን የፍርድ ቤት ቀጠሮ አልተሰማም። የሚዘግብ ሚዲያ የለም ጠበቃ መኖሩም እንጃ ቢንያም በማሕበራዊ ሚዲያ ንቁ ተሳታፊ ከመሆ...
05/19/2023

ወጣት ቢንያም ታደሰ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሚገኝ ሲሆን እስካሁን የፍርድ ቤት ቀጠሮ አልተሰማም። የሚዘግብ ሚዲያ የለም ጠበቃ መኖሩም እንጃ ቢንያም በማሕበራዊ ሚዲያ ንቁ ተሳታፊ ከመሆን በዘለለ የባልደራስ አባልና ጠንካራ ተሳታፊ የነበረ ወጣት ነው ዛሬ በእስር ላይ ሆኖ አስታወሽ ድምፅ የሚሆነዉ መጥፋቱ ነገ ለወገናቸው የሚቆረቆሩ ሰዎችን ገፍቶ ማሶጣት አደገኛ አካሄድ ሌላ ጠባሳ መሆኑን መገንዘብ ያሻል። ቢንያም ታደሰ ለሕዝብ ጥያቄ ታስሯል። :- ፅናት ሚዲያ

Address

Washington D.C., DC
20011

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዲሲ ግብረ ኃይል DC Task Forces posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ዲሲ ግብረ ኃይል DC Task Forces:

Featured

Share