የአማራ ነፃነት ንቅናቄ -Amhara Liberation Movement

የአማራ ነፃነት ንቅናቄ -Amhara Liberation Movement We advocate for Ethnic Amharas in Ethiopia who are being killed by the central government.

We advocate for Ethnic Amharas to end their oppression, subjugation, genocide, displacements, starvation and blame arising from false narratives.

08/23/2025
03/09/2024

በህይወት የመኖር መብትህን እና ነፃነትህን የደፈረ መንግሥት በአስቸኳይ ተወግዶ አሁኑኑ ከህዘብ-በህዝብ-ለህዘብ በሆነ አስተዳደር መተካት አለበት።
ዶ/ር ሀይማኖት አሰፋ ናደው, የአማራ ነፃነት ንቅናቄ መስራች እና መሪ, ግንቦት 1, 2014
ፍፁም የአስተዳደር ስርዓት እና በእውነት የተመሰረተ ፍትሐዊ መንግሥት በዚህ ምድር ኖሮ አያውቅም፤ የለምም። ከሰው ልጅ ስግብግብነት የተነሳ ወደፊትም ይኖራል ተብሎ አይገመትም። ነገር ግን አማራጭ መሞከር የህይወት ሀቅ ነውና አማራጭ እናቀርባለን፤ እንሞክራለንም።
ነፃነት እና ራስን በራስ ማስተዳደር ተፈጥሮአዊ መብቶች ናቸው። ሌሎች የሚሰጡህ ወይም ሊነፍጉህ የሚችሉት አይደለም። የፍፁም ነፃነት መገለጫው የእያንዳንዱ ግለሰብ መብት ሙሉ በሙሉ መከበር ነው። ይህ ማለት ደግሞ እያንዳንዱ ሰው በህይወት የመኖር ፣ በነፃነት የፈለገውን ሀሳብ ማራመድ ፣ በፈቀደው መልኩ መደራጀት ፣ ያለማንም ፈቃድ መፃፍ ፣ መናገር ፣ መንቀፍ መቻል ፣ ንብረት ማፍራት እና ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሃብት ንብረቱን ለፈለገው ጉዳይ የማዋል ፣ የመሬቱ ፍፁም ባለቤት የመሆን ፣ ይበጁኛል የሚላቸውን ተወካዮቹን ከወገኑ መርጦ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ፣ የመረጣቸውን ተወካዮችም በፈለገው ጊዜ የሚቀይርበት ፣ የፈቀደውን የራስ መከላከያ የሚታጠቅበትና ራሱ ሲፈቅድ እና ይጠቅመኛል ብሎ ሲያምን ብቻ ሀገር በተባለ አወቃቀር የሚሳተፍበት ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት ፈላጭ ቆራጭ ማዕከላዊ መንግሥት ባልነበረባቸው ረጅም ዘመናት ራሱን በራሱ በሰላም ያስተዳድር እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስተምሩናል።
የራስ በራስ አስተዳደር (Self-governance) ማለት ህዝቡ በየአካባቢው በመሰለዉ ሁኔታ ፣ በዘር፣ በቋንቋ ፣ በእምነት ፣ በሀይማኖት ፣ በጎጥ ፣ በመንደር እና በመሳሰሉት ተደራጅቶ : ራሱን በራሱ ለማስተዳደር አብረውት የሚሰሩ እና አብረውት የሚኖሩ ከራሱ ተወካዮች መርጦ : ሰርቶ ያገኘውን ሀብት-ንብረት የራሱን ኑሮ ማሻሻያ እያዋለ በሂደት ይህንን የራስን በራስ አስተዳደር በየደረጃው እያሳደገ ፣ ጠቃሚነቱን እየመረመረ : ከሚመስሉት ጋር በፍትህ በእኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ህብረትና አንድነት እያሳደገ ፤ ወደ ወረዳ ፣ ዞን (አውራጃ) ፣ ሀገረ ግዛት አሳድጎ ፤ ከፈቀደው ማህበረሰብ ጋር ተከባብሮ የሚኖርበት ሰርዓት ነው ::
በጥንቷ ግሪክ ፈላስፋው ፕላቶ ራስን የመግዛት ጽንሰ-ሐሳብ የራስ ጌታ የመሆን ችሎታ አድርጎ አስቀምጦታል። ግለሰቦች ወይም ቡድኖች የራሳቸውን ደስታና ፍላጎት እስካላስተዳድሩ ድረስ ነፃነትን ሊያገኙ እንደማይችሉ ይልቁንም በባርነት ውስጥ እንደሚገኙ ይገልጻል። በዚህ መሠረት ይህ መርህ መሠረታዊ የሞራል ነፃነት ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ የፖለቲካ ነፃነት ሁኔታ እና የማንኛውም የፖለቲካ መዋቅር ነፃነት እና ራስን በራስ የማስተዳደር ሁኔታም ጭምር ነው።
የራስ በራስ አስተዳደር እያንዳንዱ ማህበረሰብ በአደረጃጀቱ መጠንም ሰላማዊ ፣ ፀጥተኛ ፣ ጤናማ እና
ደስተኛ ህይወት ፤ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች (የትምህርት፣ የጤና ፣ የፀጥታ ፣ የመንገድ ፣ እና ሌሎችም ) እራሱ ጥሮ-ግሮ ባፈራው ሀብት ገንብቶ የሚጠቀምበት ፍፁም የራስ በራስ ለራስ የሆነ አስተዳደራዊ ስርዐት ነው።
እንግዲህ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድር ማህበረሰብ በአቅራቢያው ካሉ ሌሎች ማህበረሰቦች ጋር በዋናነት የራሱን ጥቅምና መብት ታሳቢ አድርጎ በንግድ ፣ በፀጥታ እና ለሰላም አሰፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ለይ በፍጹም ፈቃደኛነት ፣ በመከባበር ፣ ሰጥቶ በመቀበል ፤ በፍትህ እና በሙሉ እኩልነት ላይ ተመስርቶ ትብብርና እና ግንኙነት የሚፈጥርበት ስርአት ነው።
ጆን ሎክ የራስ በራስ አስተዳደር ፅንሰ ሀሳብን በማጠናከር እውነተኛ ነፃነት (Genuine Freedom) የግንዛቤ ፣ ራስን መምራት እና ራስን ማስተዳደር ነው ይላል ። እናም የሰው ልጅ ራስን በራስ ለማስተዳደር ያለው አቅም የነፃነት ሁሉ ምንጭ ነው። ከዚህ አንፃር ነፃነት ይዞታ ሳይሆን ተግባር ነው። ሎክ ምክንያታዊነት ለእውነተኛ ኤጀንሲ እና ራስን በራስ ማስተዳደር ቁልፍ እንደሆነ እና የፖለቲካ አስተዳደር የሚቻለው በራስ በመመራት እንደሆነ ይጠቁማል። የጆን ሎክ የራስ በራስ አስተዳደር የፖለቲካ ፍልስፍና በከፊል በአሜሪካ መስራች አባቶች ተወስዷል። ራስን በራስ የማስተዳደር የፖለቲካ ፍልስፍና በፍፁም ነፃነት እና ራስን በመግዛት ላይ የተመሰረተ ነው ። ራስን በራስ የማስተዳደር የፖለቲካ ፍልስፍና በዘመናችን ወቅታዊ ምሁራን ጊልስ ዴሌውዝ፣ ሚሼል ፎውካልት፣ ጁዲት በትለር፣ ዊልያም ኢ. ኮኖሊ እና ሌሎችም ተዳሷል።
በብሔር-ብሔረሰቦች አውድ ራስን በራስ ማስተዳደር ብሔራዊ ሉዓላዊነት (National Sovereignty) ይባላል ። ይህም በዓለም አቀፍ ሕግ ውስጥ ጠቃሚ ጽንሰ-ሐሳብ ነው። ከአስተዳደራዊ ክፍፍል አንፃር ራሱን የሚያስተዳድር ክልል ራሱን የቻለ ክልል ይባላል። ራስን በራስ ማስተዳደር ደግሞ አንድ ሕዝብ ወይም የስነ ሕዝብ አወቃቀር ከቅኝ ግዛት፣ ፍፁም መንግሥት፣ ፍፁም ንጉሣዊ አገዛዝ ወይም የትኛውም መንግሥት እነርሱን በበቂ ሁኔታ እንደማይወክላቸው የሚገነዘቡበት የፖለቲካ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው። ስለዚህም ራስን በራስ ማስተዳደር የብዙ ዲሞክራሲ፣ ሪፐብሊካኖች እና ብሔርተኛ መንግስታት መሰረታዊ መርሆ ነው። የሞሃንዳስ ጋንዲ "ስዋራጅ" የሚለው ቃል የዚህ ራስን በራስ የማስተዳደር ርዕዮተ ዓለም ክፍል ነው። ሄንሪ ዴቪድ ቶሬው ከሥነ ምግባር ውጭ በሆኑ መንግስታት ምትክ ራስን በራስ የማስተዳደር ዋና ደጋፊ ነበር።
አሁን በኢትዮጵያ በስራ ላይ ያለው ህገ መንግሥት በሀገሪቱ ውስጥ የጨቋኝ ተጨቋኝ ግንኙነት አለ ብለው በሚያምኑ ወገኖች የተቀረፀና ፤ ጠንካራ ማእከላዊ መንግሥት በማቋቋም ፣ በቋንቋ እና ዘር ላይ ተመርኩዞ ለህዝቡ እኛ እናውቅልሃለን በሚሉ አላዋቂዎች በግድ የተጫነ የመግዣ መሳሪያ ነው።
በሁሉም ተቀባይነት ያለውን ፍትሃዊ ፣ ነፃ ፣ ሰላማዊ እና የበለፀገ ማህበረሰብ ለመገንባት ደግሞ በጥቂት እናውቅልሃለን በሚሉ የተቀረጸው ፣ ያለ-ገደብ የህዝባችንን መብትና ጥቅም በሚጎዳ መልኩ እጅግ በርካታ ሃላፊነቶችን ጠቅሎ በማዕከላዊ መንግሥት ስር ያስገባው ፣ ለህዝቦች እልፍ አእላፍ ሞት፣ መደፈር ፣ መፈናቀል ፤ ለማህበራዊ ትስስር መበጣጠስ ምክንያት የሆነው ፣ ለህዝብ በችጋር መገረፍ፣ ለሀገር መበታተን እና ተዘርዝሮ ለማያልቅ መከራ የዳረገን ህገ መንግሥት በአጣዳፊ ተቀዶ ተጥሎ በአዲስ ሀገረ ህግ መቀየር አለበት። አዲሱ ሀገረ ህግም እጅግ ውስን ሀላፊነት እና ስልጣን ያለው ፣ በሁሉም ህዝብ ሙሉ ፈቃደኛነት (ይሁንታ) እንዲሁም ፍፁም እና ሙሉ ውክልና ተረቆ መፅደቅ አለበት።

06/16/2022

ምን እናድርግ? ምን ይደረግ?

የዐማራ ፖለቲካ የትርፍ ጊዜ ሥራ አይደለም

ከኢያሱ ኤፍሬም ፡ ለንደን የካቲት 9 2014፡ 2022 ፌብሩወሪ 16, ረቡዕ

ምን እናድርግ? ምን ይደረግ? ይህ ጥያቄ ዘወትር በለንደን ያለ ወዳጄ የሚጠይቀኝ ጥያቂ ነው፡፡ በተቻለኝ መጠን እና ባለኝ ውስን እውቀት ለብዙ ጊዜ ልመልስለት ሞክሪያለሁ፡፡ በእኔ እና በወዳጄ መካከል የነበረው ያለውን እና የሚቀጥለውን ጥያቄ እና መልስ ለብዕር ወዳጆቼም ትምህርት ይሆናል ብዬ በማስቤ በእዚህች አጭር ፅሁፍ ላካፍላችሁ ወደድኩኝ፡፡ ይቀጥላል ያልኩበት ወዳጄም መጠየቁን እኔም መመለሴን እንደ ሚቀጥል አውቃለሁ እና፡፡
በኢትዮጵያ በተለይም በዐማራ ፖለቲካ ውስጥ መደነባበር እና ግራ መጋባት ፡ አለመሰባሰብ እና አለመደማመጥ ፡ አለመተባበር እና አለመተጋገዝ እንዲሁም መጠላልፍ እና መነቋቆር መገለጫችኝ ከሆነ ከርሞል፡፡ ይህንንም የፖለቲካ እፀፅ በመጥቀም ጥላቶቻችን ወይ አደናግራቸው ወይ አሳምናቸው የሚል ሽውራራ መርሆ አንግተው አፈናቅለውን እና ገለውን 100 ሚሊዮን ብር ሊሰጡን ቤታችን ድርስ ያለ ሕፍረት ተከስተዋል፡፡
አሁን ዐማራ ያለበትን የፖለቲካ እውነታ እንዲለወጥ የማይሻ አንዳችም ዐማራ የለም ፡፡ ሁሉም በየፊናው የራሱን ድርሻ ለመወጣት ተፍ ተፍ ደፋ ቀና ይላል፡፡ ሁሉም በየጓዳው ያጉተመትማል፡፡ ግማሹ በግል ግማሹ በማህበር ተደራጅቶ የራሱን አስተዋፃኦ ለትግሎ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡ በቅርቡ ግልፅ ደብዳቤ ለዐማራ መስትዳደር አመራሮች (ለብአዴን) ተብሎ ከወደ አሜሪካ የተፃፋው ደብዳቤ አስራ ሰባት የዐማራ ድርጅቶች ይሁንታቸውን ችረውታል፡፡ ፋኖን በገንዘብም ለመርዳትም ሆነ አይዞህ ለማለት በጋሻ ዙሪያ፡ ብዙ ግለስቦች እና ቡድኖች ተሰባስበዋል፡፡ አለን በተባለው የዐማራ ስብስብ በትንሹ አስራ ሶሶት ድርጅቶ ከየአገሩ እድምትኞች ናቸው፡፡ በማህበራዊ ዜና አውታሩም ዘርፍ ( ሚዲያ ) የዐማራን ብሶት እና በደል እንዲሁም የትግል አቅታጫ የሚጎስሙ የዜና አውታሮች ቁጥራቸው ብዙ ነው ፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን አንዳችም ነገር ጥብ የሚል አይመስልም፡፡ ለዚህም ነው ወዳጄ ዘወትር እየደወለ ኢያሱ ምን እናድርግ? ምን ይደረግ? ብሎ የሚጠይቀኝ ፣፡፤ የኔም የዘወትር መልሴ በጥቅሉ እንደራጅ፣ እንንቃ፣ እንታጠቅ፣ እንታገል የሚልነው፡፡ ይህ መልሴ አሁንም ለወዳጄ አላራካውም ፡፤ ደግሞ መጥቶም ምን እናድርግ? ምን የደርግ? ብሎ ይጠይቃል ፡፡ አሁንም መልሴ እንዲህ እንደ ጀረት ውሃ ይፈሳል፡፡ ሰሜ ካለ
በኔ እምነት፣ እይታ እና ንባብ መሰረት ፖለቲካ በትርፍ ጊዜ የሚሰራ ስራ አይደልም፡፡ እስካሁን የተሳካላቸውም ሆነ ያለተሳካለቸው የፖለቲካ ንቅናቄዎች የተከናወኑት ጨርቀን ማቄን ሳይሉ፡ የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ ሳይሉ፡ ችግር፣ መከራ እና ሞትን ሳይፈሩ ሙሉ እውቀታቸው፡ ሐብታቸውን ፡ ጉልበታቸውን ፡ጊዚያቸውን እና ብሎም ሕይወታቸውን ለትግሎ መሰዋት ባደረጉ ሰዎች የተከናወነ ነው፡፡ ይህን በብዙ ምሳሌ ማስራዳት ይቻላል፡፡ ከትልቁ ምሳሌ እንነሳ፡ ፡ ለምሳሌ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ዘመን የሰው ልጆችን ለማዳን ያደረገው የማዳን ስራ በትርፍ ጊዜው የተከናወነ ሳይሆን ሙሉ ጊዜውን ሰጥቶ ቄራኔዎ ላይ ተቀብሎ ነው፡፡ እንዲሁም ነብዩ መሐመድ የእስልምናን ሐይማኖትን መስርቶ ሲያስተምር ከአምላክ የተሰጠውን ሐላፊነት የተወጣው በትርፍ ጊዜ ሳይሆን ሙሉ ጊዘውን ሰጥቶ ነው፡፡ እንዲያውም ቆረሾች ባሳደዱት ጊዜ ቤተሰቡን ወደ ኢትዮጵያ እንደላከ ሁላችንም እናውቃለን ፡፡ ይህ ማለት የነብዩ መሐመድ የራሱን ነፍስ ብቻ ሳይሆን የቤተስቡን እና የተክታዩቹም ነፍስ አሲዞ ነው እምነቱን ያስፋፋው ፡፡
ወደ ምድራዊው የፖለቲካ ትግል ስንገባ ፡ ማንዴላ እና ባልደረቦቹ ለነፃነት ትግላቸው ለ27 አመታት በሮቢን እስር ቤት መማቀቃቸውን እና በተመሳሳይ ሁኔታው የትግል አጋሮቻቸው በስደት መገላታቸው መሰዋታቸው የሚታወቅ ነው፡፡ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግርስ የደቡብ አፍሪካን የዘረኛ አገዛዝ ገርሠው የጣሉት ጨርቄን ማቄን ፡ ሳይሉ ህይወታቸውን አሲዘው ስለታገሉ ነው፡፡ ሁሉም የኮንግረሱ ታጋዮች ሙሉ ጊዚያቸውን ሰጠው ነው የታገሉት፡፡
በሌላም በኩል ዛሬ በዐማራውም ላይ ይሁን በኢትዮጵያ ላይ አጠቃላይ ውድመት ያደረሱን ትህነጎች ከአንዴም ሁሌቴ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ ሳይሉ፡፡ ለእኩይ አላማቸውም ቢሆንም አላማችን ብለው ላመኑበት ነገር፡ ከአንዴም ሁለቴ ትግራይ በረሃ ገብተው አፈር ሆነው አፋር ልስው እስካሁንም እየተፋለሙ ይገኛሉ ፡፡ ምን ያህል ይበድሉን ምን ያህል እኩይ አላማ ይኑራቸው ከፃድቃንን እና ባልደርቦቹን ውሳኔ አለመማር ንፉግነት ብቻ ሳይሆን አስተዋይነትም አይሆንም፡፡ ከፉ ሰው እቃ ብቻ አይደለም የሚያስገዛው ፡ መጥፊያ መንገዱንም ያስተምራል፡፡
ዛሬ በዐማራ የሕልውና ትግል ውስጥ እሳተፋለሁ የሚል ዐማራ ሁሉ እኔንም ጨምሮ ከሞቀ ቤቱ ሙቅ ከበሪድ እያማረጠ በተለያየ አጋጣሚ ያካበተውን ትምህርታዊ እውቀት በመጠቀም በዐማራ ሕዝብ ላይ ብሎም በአገሩ ላይ የሚደርሰውን ወድመት እና በደል ከመተንተን የዘለቀ ስራ እየሰራ አይደለም፡፡ እንዲህ አይነቱ አካሄድ በፖለቲካው ጥበብ ውስጥ የዱካ አብዮተኞች ወይም Armchair Revolutionary ተብለው ይታወቃሉ፡፡ ይህን ተመለክቶ አንድ የተፃፋ ቁም ነገር ላካፍላችሁ፡፡ በ1937 ኤ ዘ አ የነበረው የሩሲያ ፈላስፋ ኒኮላይ አሌካሳድሮቪች፡ ፕሊካሃኖቭ ስለተባለው የመጀመሪያ የሩሲያ ማርክሲስት አብዮተኛ ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር: "After years of living in Western Europe, Plekhanov became entirely a Western and of a very rationalist sort, fairly cultured, although his culture was not of the highest kind; more of an armchair revolutionary than a practical one. He could be a leader of a Marxist school of thought, but he could not be a leader of a revolution; that was made clear at the time of the revolution" ይህን መረጃ ዊኪፒዲያ ጎራ ብለው ይመልከቱ፡፡
ዛሬ በዐማራ ፖለቲካ ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ ፕሊክሃኖቮች አሉ፡፡ የዐማራውን አብዮት እጃቸውን ጠቅልለው ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ፡ ማር ሰርቃ ገደል መዝለል እንዳቃታት የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ ሳይሉ ግንባር ገብተው በግንባር ከመምራት ይልቅ ሚስታቸውን እና ልጆቻቸውን አቅፈው ከሞቀ ቤታቸው ሙቅ ከበሪድ እያማረጡ፡ በየወሩ የሚገባላቸውን ደሞዝ እየቆጠሩ ዱካቸው ላይ ተቀምጠው ግፋ በለው የሚሉ ቤት ይቁጠራቸው፡፡ ለዚህም ትልቁ ማሳያ ከወደ አሜሪካ እና አውሮፓ ወቅቱን እየጠበቁ የሚሰጠው የመግለጫ ጋጋታ ነው፡፡ እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ነፃነት በእርዱኝ ( Gofundme): በሹክሹክታ ወሬ ( Twitter): በበይነ መረብ ወግ ( Zoom)፡ በይነ መረብ እምቢልታ (YouTube): በከታበ ገፅታ ( Face Book) እና በሌሎችም ማህበራዊ የወሬ አውታሮች በሚደረግ ጫጫታ አይደለም ፡፡ እውነት እላችኋለሁ በዱካ ፖለቲካ ነፃነት አይደልም የነፃነት ቁራጭ አናገኝም፡
መቋጫ ፡ ወዳጄ በየጊዜው ምንን ይደረግ? ምን እናድርግ? ብሎ ለሚጠይቀኝ ጥያቄ መልሴ አማራን እና ኢትዮጵያን የውሽጥ እና የውጭ ጠላቶች ከደገሱላት ጥፋት ለማዳን ከተፈለገ የትርፍ ጊዜ ፖለቲካ አቁመን ሙሉ ጊዚያችንን፡ እውቀታችን፡ ገንዘባችን እና ሕይወታችንን ሰጥተን የምንታገልበት የምናታግልበት ስብእና እና መድረክ ሊኖረን ይገባል የሚል ነው፡ በአጭሩ የዱካ አርበኝኘት፡ የዱካ ፋኖነት፡ የዱካ አብዮታዊነት ፡ የዱካ ፖለቲካ በማሶገድ ፡ እንደ መልካም ገበሬ ሞፈር እና ከቀንበር አቀናጅተን በሬዎቻንን ጠምደን የትግሉን እርሻ ማራስ፣ ዘሩን መዝራት ፡ አዝመራውን ማጨድ እና መውቃት ወደ ጎተራ ማስገባት አለብን፡፡ የማህበራዊ ዜና አውታሮች የትግሎ አባሪዎች እንጂ ዋንኛ የትግል መድረኮች ሊሆኑ አይችሉም፡፡

The so-called international community is Hypocritical! When are you going to care? If you can not profit, do not human l...
05/26/2022

The so-called international community is Hypocritical!
When are you going to care? If you can not profit, do not human lives matter to you?
Ethnic Amhara’s plight continues unabated.
# The Oromo’s intensified massacres, displacements & imprisonments of ethnic Amharas in Ethiopia.
# Amharas are fighting for survival, we have a moral duty to assist!

05/13/2022

የግድያው አዋጅ እና ያለሰለጠነው አሰልጣኝ፡ መደመር አሳይቶ የሚቀንስ

ከኢያሱ ኤፍሬም ገ/ሐና፡ ከለንደን ሚያዚያ 19 2014 ፡ 2022 ኤፕሪል 27, ረቡዕ፡ አንብቡት ፡ አካፍሉት ተቹት
መግቢያ
እንደ ማናቸውም የኑሮ የተፈጥሮ ሕግ ቋንቋም የራሱ ሕግ አለው ፡፡ ይህ ሕግ ለረጅም ዘመን ሲወርድ ሲወራርርድ የመጣ በመሆኑ ሁሉም የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ያላንዳች ብዥታ የቋንቋን ሕግ ተከትሎ ቋንቋን ይጠቀሙበታል፡ የቋንቋን ሕግ አክብረን ቋንቋን ባንጠቀም ኖሮ እርስ በርሳችን ሳንግባባ አንዱ ፍቅር ሲል አንዱ ፀብ የተባለ ከመስለው መፋቀራችን ይቀር እና ልንገዳዳል እንችል ነበር፡፡ ስለ ቋንቋ ነገር ካነሳሁ አይቀር ስለ ባቢሎን ግንብ እና ፍፃሜው ከቅዱስ መፅሐፍ ላይ የተፃፋን መጥቅስ ለመግለፅ ያስብኩትን ሐሳብ ያጠናክራል እንዲህም ይላል፡ “እግዚአብሔርም አለ፡ - እነሆ፣ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፣ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም። ኑ፣ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው ። እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ። ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ ዘፍ 11: 1 9”
በጥቅሉ አብዮት የሚለው ቃል እና ተግባር ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ በተለይ ደግሞ ወያኔ ወደ ስልጣን ከመጣች ጀምሮ የቃላቶች ተፈጥሯዊ ባሕሪ እና ተግባራቸው ለየቅል ሆነዋል ፡፡ ከዚህ ውስጥ አንድ ቃል ጎልቶ ይወጣል ፡፡ እሱም ስልጠና የሚለው ቃል እና ተግባሩ ነው፡፡ ከስልጠና ከምናውቀው ባሕሪ ተለይቶ እና ለየት ያለ ካባ ለብሶ ወደ ተግባር ከገባ እረጅም ዘመን ተቆጥሯል፡፡ ማንም ሰው ስልጠና ሲባል የቃሉ ትርጉም የሚያሳየው ያላወቀውን ወይም አዲስ ነገር ለማወቅ የሚሰጥ አጭር ትምህርታዊ ሂዳት ማለት ነው፡፡ ሰለጠነ ማለት፡ አወቀ፡ ነቃ ፡ተረዳ ፡ተማራ የሚለውን ቃል ሲስጠን፡ አሰለጠነ የሚለው ቃል አሳወቀ፡ አነቃ፡ አስተማረ ፡ አሰረዳ የሚሉትን ተጉዳኝ ፍችዎች ይሰጠናል፡፡ በፈረንጆች አንደበት ስልጠና የሚለውን ቃል እንደሚከተለው ይፈታል፡፡ “Training is teaching, or developing in oneself or others, any skills and knowledge or fitness that relate to specific useful competencies. Training has specific goals of improving one's capability, capacity, productivity and performance.”
ነገር ግን በዘመነ ወያኔ እና አሁን ባለው በዘመነ አረመኔ ( አብይ) ስልጠና ማለት ስልጣን አዳጋ ላይ በወደቀበት ሰአት አደጋ ሊያመጡ ይችላሉ የተባሉትን ግለስቦች፡ ቡድኖች እና ሃሳቦችን በግልፅ እና በስውር መምቻ መሳሪያ ማለት ነው፡፡ በሌላም በኩል ስልጠና ማለት በፓርቲም ሆነ በፖለቲካ መስመር ውስጥ ወዳጅ እና ጠላትን ለይቶ ማሳያ እና መመንጠሪያ ዘዴ መድረክ ማለት ነው፡፡ አሁን ደግሞ ትንሽ ከፍ ብሎ እና ተሻሽሎ ሕብዝ እና አገር ማሽበሪያ ማስጠንቀቂያ እና ማስፋራሪያ ሆኖ ተሻሽሏል፡፡ ይህን ያልኩበትን ምክንያት ደረጃ በደረጃ አስረዳለሁ እና ተከተሉኝ ፡፡ እኔም ላሰልጥናችሁ ለምን ይቅርብኝ
አብይ ( ያልሰለጠነው አሰልጣኝ) ሁለት ስልጠና ለከፍተኛ የወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራሮች በገሐድ ስጥቷል፡፡ በርግጥ አብይ የሰጠው ስልጥና ለየት የሚያደረገው ለአገር ለምድሩ በሕዝብ መገናኛ እወቁልኝ ማለቱ ነው፡፡ ብዙዎቻችን እንደተረዳነው እና እንደገባን አብይ ጀነራሎቹንም ሆነ የፓርቲ አባሎቹን ስብስቦ ስልጠና ሳይሆን የሰጠው በስልጣኑ ላይ ያለውን አደጋ ስጋት እና ጭንቀት የገለፀበት ከመሆኑም በለይ ይህን ስጋት እና ጭንቀት እንዴት እና በምን መንገድ ለማሶገድ እንደተዘጋጀ ይፋ ያደረገበት መድረክ ነው፡፡ ለዚህም ትለቁ ማሳያው በቅርቡ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሚያዚያ 14፣ 2014 ዓ.ም የወጣው የነፃ እርምጃ ( ግድያ) መግለጫ ነው፡፡
በእዚህ አጭር ፅሁፍ የሶስቱን ክስተቶች ማለትም፡ ለጀነራሎቹን ፣ የፓርቲ አባሎች ( ካድሬዎች ) የተሰጠውን ስልጠና እና ከብ.ደ.ም/ቤ የተሰጠውን የእግላለን መግለጫ በጋራ እንመለከታለን ፡፡ እንዚህ ሶስቱ ክስተቶች የተነጣጠሉ ሳይሆኑ አንድ አካል ናቸው አላማቸውም አንድ እና አንድ መሆኑን እንፈትሻለን የተቆለፈውንም ቁልፍ ከፍተን ለማየት እንሞክራለን፡፡ የኢትዮጵያ ጠላቶች አንድም ሶስትም ናቸው ፡፡

ፓቶክራሲ (Pathocracy)
በሰለጠኑት አገሮች መሪዎች በተቻለ መጠን ከሕዝባቸው ጋራ ለመገናኘት የተለያየ መድረክ ይፈጥራሉ ፡ ለምሳሌ በእንግሊዝ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር በፓርላማ እየቀረበ ወቅታዊ የሆኑን የፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያውዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን በጥያቄና መልስ ለፓርላማው ያስርዳል ሕዝቡም ይስማል፡፡ The Prime Minister answers questions from MPs in the Commons every sitting Wednesday. The session normally starts with a routine question from an MP about the Prime Minister's engagements. በተጨማሪ ጠ/ሚ በሂደበት ቦታ ሁሉ ዱካውን የሚከተሉት ጋዜጥኞች ወቅቱን የጠበቀ ጥያቄ ይጠይቁታል እሱም ይመልሳል ፡፡
በአንድ ወቅት በላቲን አሜሪካ በምትጋኘው ቬኒዚውላ ፕሬዘዳተ የነበርው ሁጎ ቻቬስ Hugo Chávez ( ነፍሱን ይማረው) ሰላም ፕሬዘዳንት (Aló Presidente) የተሰኘ የቴሊቪዥን እና የሬዲዎ መርሃግብር ነበረው ፡፡ በአዚህም መርሃ ግብር ቻቬስ ከሕዝብ ጋራ በመገናኘት ሃሳቡን ይሽጣል ( ያው የእሱ የፖለቲካ ጉድለት እንደ ተጠበቀ ሆኖ፡ አሜሪካም አትወደውም ነበር) ፡፡ Although Chávez typically appeared on television several times a week, Aló Presidente was his opportunity to reach most families on their day off
በተቃራኒው ለኢትዮጵያ ፓርላማ ባይተዋር የሆነው አብይ በፓርላማ ቀርቦ ጥያቄ እና መልስ የመስጠት ባሕል የለውም ፡፡ የጥያቄ እና መረሃ ግብር ተካሄደ ከተባለ ቀድሞ የተዘጋጀ ጥያቄ እንኳን ተጠይቆ ፓርላሜንቱን ስድቦ እና አዋርዶ ነው የሚወጣው፡፡ ለማስታውስ ያህል የአማራ ተማሪዎች መታገታቸውን ተከትሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠውን መልስ ማስታውሱ በቂ ነው፡፡ ለአብይ ፓርላማው የአፍ መፀዳጃው ነው፡፡
በተጨማሪ ለውስጥም ሆነ ለውጭ ጋዜጠኞች ዝግ የሆነው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ( እሱን ጨምሮ) ወቅታዊ ጥያቄዎች የማይጠየቅ የማይመልስ እውነተኛን ጥያቄ የሚፈራ እና ጋዜጠኛን በሩቁ የሚሽሽ ሰው ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱ አደባባይ ወጥቶ ለድንገተኛ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የማይደፍር ፣ ልበ ድንጉጥ፣ አቅመ ቢስ፣ በራሱ አለመተማመን ስብእና የተላበሰ ግለስብ ነው፡፡ ይህም የሆነበት ዋኝና ምክኛት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የስነ ልቦና ስለባ ነው የሚል መላ ምት አለኝ፡ ምክንያቱም የስነ ልቦና ጉድለቶችን የሚያሳዩ ብዙ ምልክቶች አሉ ታይተውበታል፡ በእዚህ ላይ የስነ ልቦና ባለሞያዎች ሞያዊ ምክራችሁን ብታካፍሉን መልካም ነው እላለሁ ፡፡
ይህን በተመለከተ ሳልጠቅሰው የማላልፈው ሰው የፖላንዱ ( ፖሊሽ) ሰነልቦና አዋቄው Andrew Lobaczewski ነው፡፡ አንድሩ ላባዚስኪ በሂትለር እና በእስታሊን ስቃይ ከደረሰበት በኋላ በፖለቲካ እና በተቃወሰ ስነ ልቦና መካከል ያለውን ግንኙነት ለመረዳት ከፈተኛ ምርመርን አከናውኗል ፡፡ ይህንንም ተመርኩዞ Political Ponerology: A Science on the Nature of Evil Adjusted for Political Purposes: የሚል መፅሐፍ ፅፏል፡ He wanted to understand why psychopaths and narcissists are so strongly attracted to power as well as the processes by which they take over governments and countries. አንድሩ ደረገው ጥናት ላይ ተመርኩዞ እንዲህ አይነቶቹን ፖለቲከኞች ፓቶክራሲ (Pathocracy) ብሎ ስይሟቸዋል ወደ አማርኛው ስንተርጉመው የእብዶች አስተዳደር የሚል ትርጉም ይሰጠናል፡፡ እንግዲህ የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል የሚለውን ብሄላ ለአንድ አፍታ አናስበው፡፡ የሚገርመው በቀርብ ቀን አብይ ካድሬዎችን ሰብስቦ በሰጠው ስልጠና ላይ ስለተለያየ አስተዳዳር (ከራሲ) ገለፃ ሲሰጥ ነበር፡ ግን እሱን የሚመለከተውን ፓቶክራሲ መኖሩንም አልሰማም፡፡ ለማናቸውም Pathocracy a government that is made up of people with personality disorders, such as psychopaths and narcissists፡ ሳይኮፓቶች እና ናርሲስቶች የሚገለፁባቸው ብዙ ባህሪያቶች አሏቸው ከብዙ በጥቂቱ ፡ ሲበዛ ቀጣፊዎች (Pathological Liars) ናቸው፣ ሲበዛ አታላይ (Manipulative) ናቸው ፡ አስምሳዮች (Superficial Charm) ያለቸው ናቸው፡፡
እንግዲህ አብይ እጅግ ውስብስብ በሆነ የስነ ልቦና ቀውስ ውስጥ ያለ እና የስልጣን ጥማቱን ለማርካት አገሪቱን በምስቅልቅል ሁኔታ እየመራ ያለ ሰው ነው፡፡ ያም ስለሆነ እንደ ማናቸውም አምባ ገነን እና የስነ ልቦና ቀውስ አንዳለበት መሪዎች አብይ ስልጣኑ አደጋ ላይ የወደቀ መስሎ ከተሰማው ስልጣኑን ከአደጋ ለመጠበቅ ያልተጠበቁ እና አስደንጋጭ እርምጃዎች ይወስዳል፡፡ እንግዲህ አብይ አንዴ ከጦር ጀነራሎች ቀጥሎ ከብልፅግና መአከላዊ አባሎች ( ከፍተኛ አድሬዎች) ጋራ እና በመጨረሻም ከደህነነት አመራሮች ጋራ ተማከሮ ያወጣውን አዋጅ መመርመር ያለብን ከላይ ከተቀመጠው ተጨባጭ ሁኔታ ጋራ በማገናዘብ ነው፡፡ አምባቢያን በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ንባብ እንድታደርጉ እጋብዛለሁ ፡፡
የጀነራሎቹ ስልጠና ሚስጢር

በማናቸም መስፈርት እና በአብላጫው ጊዜ ለወታደራዊ አመራሮች የሚሰጥ ስልጠና ይዘቱ ወታደራዊ መሆን አለበት ፡፡ በባህሪው ወታደራዊ ስልጠናም ሆነ ስብሰባ ሚስጢራዊ ነው፡፡ እንኳን በአደባባይ ለሕዝብ ሊቀርብ ቀርቶ በተለያየ የእርከን ደረጃ ያሉ ወታደሮች የማይመለከታቸውን የስብሰባም ሆነ የስልጠና ይዘት አይገለፅላቸውም፡፡በወታደራዊ አለም ውስጥ ማውቅ ያልብህን ብቻ ታውቃልህ የሚለው መመሪያ በጥብቅ ይተገበራል (on a need-to-know basis) : ይህን ስል ግን ወታደሩ በአግር ጉዳይ አይስበሰብም አይመያይም ማለት አይደልም፡፡
በሲቪል አስተዳደር የምትመራው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ የሆነው አብይ አህመድ በውጊያ ወቅጥ የሚለበሰውን ወታደራዊ ልብስ ወይም Army Combat Uniform ተላብሶ ከፍተኛ የጦር አመራሮችን በስልጠና ስም ሰብስቦ ሲያወያይ በቀርቡ አይተናል ስምተናል፡ ይባስ ብሎ ስብሰባው በአሱ አጠራር ስልጠና ዓለም እንዲያውቀው በብዙሃን መገናኛ አስራጭቶልናታ፡፡ ይህን በኔ እይታ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የፖለቲካ ፍርሃት ( Heights level political paranoia) ብዬዋልሁ፡፡ ነገር ግን ይህ ፖለቲካ ፍርሃት የወለደው በስልጠና አላማ እና ግቡ በስልጠና ስም የተሰበስቡትን የጦር መኮኖች ለማስልጠን ሳይሆን አብይ ይመለከተዋል ላለው ማህበረስብ የሚፈልገውን መልእክት ለማስተላለፍ የተጠቀመብት መድረክ ነው፡፡
አብይ ጀነራሎች ስብስቦ ብዙ ሐሳቦችን አንስቷል ፡፡ ኢኮኖሚ ፡ ወታደራዊ፡ ዲፕሎማሲ እና ፖለቲካ፡፡ ሲጀመር ሁሉም የሞያ ዘርፍ አለው ግብርና ጉዳይ የምታወራው በስራው ላይ ለተሰማሩትን ወይም ሁሉም የአገሪቱ ወታደራዊም ሆነ ሲቪል አመራሮች እንዲሁም የሚመለከታቸው የሲቪክ አመራሮች ባሉበት ነው ፡፡ ይህ የሚደረገው የስብሰባው አላማ በእውነተኛ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚወያይ እና ቀጣዩን የመንግስት ትልም ወይም እራይ ለሕዝብ ለመሽጥ ስታስብ ነው፡፡ ነገር ግን የአብይ በስልጠና ስም የሰበስባቸውን ጀነራሎች ሊነግራቸው የፈላገው የመጨረሻው የስልጣን ማስጠብቂያ መሳሪያች እንሱ መሆናቸው እና ስልጣኑንም ለመቀናቀን ያስቡትን ሰዋች ውይም ቡድኖች ለማስተንቀቅ ነው፡፡ ይህን ለማየት ከተናገረው አንዲት ነገር እንመለከት ፡፡
አብይ የሚከተለውን ይላል
“መከላከያ እና ፖለቲካ ያላቸው ወይም የነበራቸው መጋባት ነው፡ ካድሬ የራሱን ስራ ሳይሰራ ልማት ሳያመጣ በኮራብሽን ሕዝብ እያሳቀቀ እና እየገደለ መከላከያ ጋ ተለጥፎ እንዲጨማለቅ መፍቀድ የለባችሁም፡ እያደረገ ያለው እንድሱ ነው ፡፡ ይስረቃል የራሱን ያከማቻል መጠቀሚያ ያደረጋል፡ እዚህ ኦሮሞ አማራ ምናምን እያለ አጭበርባሪ፡ እናተ ክብራችሁን መጠበቅ አለባችሁ፡ ወታደር መሆን አልባቹሁ ፡ ባያድላችሁ ነው እንጂ የትኛውም ካድሬ የእናትን እሩብ አያክልም ብዙ ጊዜ ነግሪያችኋለሁ፡ አያከልም፡ በጭንቅ ጊዜ እኮ እናተ ናችሁ ሕዝቡን ያወያያችሁት፡ እናተ ናችሁ፣ የተዋጋችሁት እናተ ናችሁ፣ በቦቴ ውሃ ያጠጣችሁ እናተ ናችሁ ካድሬ አይደልም፡፡ ግን they want to manipulate: ጥሎ እየሸሸ በውጊያ ጊዜ በሰላሙ ጊዜ ይገመግማል ፡ ይሄ አንዱ በሽታ ነው፡ ሶስተኛው ሪፎርሙ ብቻውን አለመመራቱ ነው፡ ውጊያ አለ፣ ችግር አለ፣ መካራ አለ ብቻውን አልተመራም የሀብት ውስንነት አለ፣ በጣም ከፍተኛ ሀብት የሚጠይቀው ነው ጥቅማጥቅም ችግር አለ፡ ወታደሩ በቂ አይደለም አሁን እኮ ነው ቤት ይሰጣቸው መሬት ይስጣቸው ማንም በህግ ያወጣነው እድሜ ይራዘም ያልነው እንጂ ፡ ወታደሩ ሲኖር ጀነራል ነው ሲወጣ ደሃ ነው፡፡”
ይህ ከላይ የተጠቀሰው የአብይ ንግግር ወይም ስልጣና መልእክት ነው ፡፡ በስልጠና ስም ሊተላለፍ የተፈለገው ቁልፍ መልእክት የእሱን ስልጣን ጥያቄ ውስጥ በከተቱት እና በጀነራሎቹ (በወታደሮቹ) መካከል ቅራኔ እና አለመተማመን ለመፍጠር የታቀደ ነው፡፡ ከእዚህ መልእክት የምንረዳው አብይ መፈንቅለ መንግስት ይደረግብኛል ብሎ ስግቷል ፡፡ አንድ ነገር ማወቅ ያለብን አብይ እራሱ ካድሬ እና የካድሬዎች አለቃም ነው፡፡ አብይ ስለ የትኛው ካድሬ እንደሚያወራ ባይታውቅም ትምህርታዊ ግምት መውስድ ይቻላል (የተገፉትን የብአዴን አመራሮችን ማለቱ ነው)፡፡ አብይ በእዚህ ንግግሩ የብልፅግና አመራር ( ካድሬ) ሕዝብን የሚያሳቅቅ ፡ ሕዝብን የሚገድል መሆኑን በግልፅ አስቅምቶታል፡፡ ካድሬው ( የብልፅግናው አመራር) ማለት ነው ይሰርቃል ሀብት ያከማቻል ፡፡ ይህ ለሕዝብ ግልፅ የሆነ እና የአደባባይ ሚስጢር ነው፡፡ እነ አገኘሁ ተሻገር በሚሊዮን እንደ ሰረቁ እናውቃልን፡፡ ጌታ ለፍርድ በቀረበበት ወቅት የተሰበሰበው ሕዝብ ባርባራስን ልቀቀልን እየሱስን ስቀልልን እንዳሉት ዛሬ አብይም ሌቦችን ነፍሰ ጋዳዮችን (ተመንስገን ጥሩነህ እና ሽመለስ አብዲሳ) ከጎኖ አስቀምጦ ሰው ተበደለ አገር ተጎዳ ያሉትን ለማሳደድ እና ለመስቀል ተንስቷል፡፡ ወታደሮቹንም እንደ ሮም ወታደሮች ለቄሳር ታማኝ እንዲሆኑ ተምበርክኮ ለምኗል ወደፊትም ለውለታቸው እንድሚከፍላቸው ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ ጥያቄው መሆን ያለበት
ወታደሩ በጥቅም ተታሎ፣ ተገዝቶ እና ተዘናግቶ አገር እየፈረሰች የአገር ጥቅም እየተሸጠ ፡ ሕዝብ እየተበደለ ( እየታረደ ፣ እየተፈናቀለ እና እየተራበ) የአንድ ግለሰብ ስልጣን ያስጠብቃል የሚል እምነት የለኝም ፡ ወታደሩ ከሕዝብ አብራክ የወጣ የደሃ ልጅ ነው የወታደሩ ታማኘንት ለሕዝብ እንጂ አብይ በኮድ እንደነገረን የእሱን ስልጣን ማስጠብቂያ መሳሪያ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም፡፡ወታደሩም ይህን ይቀበላል፡፡
የማይለውጠው ለውጥ (Paradigm shift)
የፈረንጅ አፍ በተለይ እንግሊዘኛ ድሪቶ የሆነ ቋንቋ ነው፡፡ የእንግሊዝ ቻናልን ( ባህር) ተሻግሮ ወደ ኢንግላንድ የገባው የአንግሎ ፈርሲያን ቋንቋ እዛው ቢቀር ኖሮ የአንድ መንደር ቋንቋ ሆኖ ይቀር ነበር፡፡ ነገር ግን ወደ እንግሊዝ በተሰደዱም ሆነ ከንግሊዝ በተለያየ ምክንያት ወደ ተለያየ የዓለም ዳርቻ በተጓዙ እንግሊዞች ምክንያት በተለይ በንግድ እና በጦርነት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ዳብሮ እና አድጎ ዛሬ የዓለም መግባቢያ ሆኗል፡፡
ነገር ግን ከዘመናት እርቀት እና ተወራራሽ ሂደት ቃላቶች የመጀመሪያውን ትርጉማቸውን ትተው ሌላ ትርጓሜ ይዘው ይከስታሉ:: አንዳንዴም ሊሂቃን የቃሉን የመጀመሪያ ትርጉም ወይም ስሩን በማጥናት ለቃሉ አዲስ ወይም ሰፋ ያለ ትርጉማ ይስጡታል፡፡ ከእዚህም አንዱ ፓራዳይም የተሰኛው የግሪክ ቃል ነው፡፡ ፓራዳይም እራሱን ችሉ ትንታኔ የሚስጥበት ቃል ነው፡ በሌላ ቅፅል ሲጨመርበት ሌላ ትርጉማ ይይዛል ለማሳሌ ፓራዳይም ሽፍት ( ለውጥ)፡፡ ይህ ዳግሞ ደግሞ እራሱን የቻለ ትንተና ያስፈልገዋል፡
ፓራዳይምን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ይህን ቃል የአማራኛ አቻ እንፈልግለት፡፡ ፓራዳይም የሁለት ቃላት ውሕደት ውጤት ነው፡፡ አንዱ ፓራ ሲሆን ሌላው ዳይም ነው ፡፡ Paradigm comes from Greek paradeigma, "pattern, example, sample" (ቅርፅ፡ምሳሌ፡ናሙና) from the verb paradeiknum, "exhibit, represent, expose" (ማሰየት፣ ማቅረብ፡ መግለፅ ) and that from para, "beside, beyond" ወይም Greek para- from para (prep.) "Beside, near; issuing from; against, contrary to," (ከጎን ፡ እርቆ፡ ቀርቦ፡ በተቃራኔው) and deiknumi, "to show, to point out or “to reveal”. (ማሳየት ማመልከት)፡፡ ሌላው ፓራ የሚለው የላቲን መሰረት ያለው ሲሆን እሱም ከአደጋ መጠበቅ ፡መከላከል ማዳን የሚለውን ትርጉም ይስጣል Latin origin meaning "defense, protection against; that which protects from፡ ለምሳሌ ፓራሹት (parachute) የሚለው ቃል የፓራ ( ላቲን) እና ሹት (chute) ( ፈረንሳይኛ) ተደምረው ያመጡት ቃል ሲሆን ጥቅል ትርጉሙ ከመውደቅ መዳን ወይም መጠበቅ ማለት ይሆናል፡፡ "defense against" ( para- ) + chute "a fall" (chute). https://www.etymonline.com/word/para
ከላይ እንዳየነው ፓራዳይም ማለት ቅርፅ፣ ምሳሌን ወይም ናሙናን የሚለውን ትርጉም ይስጣል፡፡ ወደ ቀረበ አማርኛ እንውስደው ከተባለ አንድ ሸማኔ የሰራው ወይም የነደፈው አዲስ ጥበብ እንደ ማለት ነው፡፡ ወደ ሽሮ ሜዳ ሄዳችሁ አዲስ ጥበብ ሽማኔው ወይም ሸማ ሻጩ ቢያሳያችሁ ያሳያችሁ ፓራዳይም ( ስም ሲሆን) ፡፡ የማሳየቱ ሂዳቱ ፓራዳይኩኑማይ ( ግሱ) ይሆናል፡ማለት ነው፡፡ ጥበቡን ስራውን አሳየ፡፡
ቃላቶች ባሉበት አይቀመቱም ፓራዳይም አድጎ አስተሳሳብ ፡ አስራር አመላካከት የሚል ትርጉም የሰጠበት ሁኒታ አለ፡፡ The historian of science Thomas Kuhn gave it its contemporary meaning when he adopted the word to refer to the set of concepts and practices that define a scientific discipline at any particular period of time. እንግዲህ ፓራዳይም የሚለው ቃል ከቁሳዊ ትርጉሙ ተላቆ የፅንሰ ሐሳብ መገለጫ ያደርገው ቶማስ ካሃን የተባለ ሳይቲስት ነው ፡፡ https://en.wikipedia.org/wiki/Paradigm በሌላም በኩል ፓራዳይም አንድ ፅሁፍ ፓራዳይም ዝርዝር ትርጓሜ (definition) የለውም ግን ይታወቃል ይለናል Some believe that one cannot define paradigm, however, it could be recognized. Paradigm encompasses world view, assumptions, beliefs, norms, techniques, symbols, and values that tell the advocates what the problem is and how one could solve problems by taking advantage of the paradigm International Journal of Scientific & Engineering Research, Volume 5, Issue 7, July-2014 ሌላው እና ቀለል ያለው ትርጓሜ በ Dr Will Kenton እንዲህ ይተነተናል Paradigms are important because they define how we perceive reality and how we behave within it. Everyone is subject to the limitations and distortions produced by their socially conditioned nature. ሁለችንም በተፈጥሮም ይሁን በማህበራዊ ውቅር የራሳችን ውስንነት አለን ይህም ስለሆነ ፓራዳይም እውነታን እንዴት ማየት እንዳለብን እና እንዴትስ ከእውነታው ጋራ መራመድ እንዳለብን ይገልፅልናል፡፡ Dr. Paul Jenkins በዩቲዩብ ባቀረበው ትንተና እንዲህ ይለናል The truth is that paradigm is one of the made-up words in psychology that simply means the way you see things፡፡ ለምሳሌ ይላል ዶክ ፖዎል፡ አረንጉዴ መነፅር ብናደርግ የምናየው ነግር ሁሉ አረንጓዴ ይሆናል ፡፡ ወይም ሌላ ቀለም ያለው መነፅር ብናዳርግ የምናየው ነገር ሁሉ እንደ መነፅሩ ቀለም ይወስናል፡፡ ቁም ነገሩ የምናይበት መንፅር ተለወጠ እንጂ የምናየው ነገር አልተለወጠም፡፡
አሁን አብይ አባሎቹን ሰብስቦ ፓራዳይምን የነገራቸው ለውስጥ ጋራ አዛምዶ ነው (Paradigm shift)፡፡ በእሱ አባባል “መደመር አዲስ የፖለቲካ ፓራዳይም ነው” ፡፡ መደመር መአቀፍ ነው ፡ መደመር ቋት ነው ፡ መደመር አቅጣጫ ነው ፡ መደመር ፍልስፋና ነው”::
እንግዲህ ሰው መጠየቅ ያለበት አብይ ፓራዳይም ለውጥ ሲለን ምን ማለቱ ነው ? አብይ ቃሉን እና የቃሉን ፅንሰ ሐሳብ አውቆ እያሳውቀ ነው? ወይስ የአብይ ፓራዳይም ለውጥ የሚለውን ቃል ለክህደት፡ ለሸር ፡ ለተንኮል፡ ለወጥመድ በተለዋጭነት ለመጠቀም አስቦ ነው? ወይስ እኔ ያልኳችሁን መደመር ተቀበሉ እያለ ነው? እዚህ ላይ የአብይ ፓራዳይም Kuhn ፡ Kenton Jenkins ካቀረቡት ትርጓሜ ይለያለል በተለይ በ Hassan Azizi የቀረበው Paradigm as a method in the political science የተሰኘውን ስነድ ብንመለከተው አብይ ከሚያስበው እና ከተናገረው የተለየ ሆኖ እናገኘዋልን፡፡ ስለ ፓራዳይም ለውጥ እንዚህን ሁለት ነጥቦች እንቃኝ ከላይ ከተሰጠው ትርጉማ ጋራ እናዛምደው ፡፡
• A paradigm shift is a major change in how people think and get things done that upends and replaces a prior paradigm.
• A paradigm shift can result after the accumulation of anomalies or evidence that challenges the status quo, or due to some revolutionary innovation or discovery.
የአብይን ስልጠና ብሎ ባቀረበው ትንተና አንድ ሐሳብ ነጥሮ ማውጣት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንታቱም አንዱን ጥሎ አንዱን አጠልጥሎ ስለሚናገር ነው ፡፡ ለምሳሌ ስለ እውቀት ማጋራትን በተመለከተ ኦፕን ሶስርስን (open source) አስመልከቶ የሰጠው አስተያየት ከፓራዳይም ለውጥ ጋራ የተያያዘ ነገር የለውም የኦፕን ሶርስ ምክንያቱ የተለያዩ ቢሆንም ከቴክኖሎጂው ባሕሪ የተነሳ ነው፡፡ በእዛው መጠን ኦፕን ሶርስ ያለሆኑ ብዙ ሶፍት ዌሮች አሉ ከእዚህ ውስጥ ትለቁ Microsoft office, Microsoft Windows ነው፡፡ ስለሆነም አብይ ስለ ኦፕትን ሶስር የሰጡት ትንተና ከእውቀት የነፃ የሚያደርገው፡፡ በእርግጥ እንናገር ከተባለ አብይ እና ብልፅግናን አንቆ የያዛቸው Paradigm paralysis ወይም አለመለወጥ ነው ማለትም the refusal or inability to think or see outside or beyond the current framework or way of thinking or seeing or perceiving things፡ አብይ ሕገ መንግስቱን አንቆ ይዞ ፡ የብሔር ፖለቲካ ከመጋረጃ ጀርባ እያከናወነ፡ ኦሮሞን ለጦርነት እያዘጋጀ ፓራዳይም ለውጥ ሊል አይችልም
በአብይ ስልጠና ብሎ ባዘጋጀው መድርክ ሊናገር የፈለገው መደመር ብዬ ያወጣሁንት ኢፍልስፋና (Pseudo philosophy) ተቀበሉኝ ነው፡፡መደመር ማለት አንድ መሆን ማለት ነው፤ ነገር ግን አብይ አንድነት የሚለውን ቃል የመናገር ድፍረቱ የለውም፡፡ አንድነት ካወራ ፡ የቴድሮስን እራይ አንሳ ማለት ነው ፡ አንድነትን ካወራ የሚኒሊክን እራይ አነሳ ማለት ነው፡ አንድነት ካለ የኃይለ ሥላሴን እራይ አነሳ ማለት ነው ፡ አንድነትን ካወራ የመንግስቱን እራይ ተሸከመ ማለት ነው፡፡ አብይ ኢትዮጵያን ይፈግጋታል የሚፈልጋት ግን ለኢትዮጵያን እድገት፡ ስልጣኔ እና ሰላም ሳይሆን ለእሱ የስልጣን ፍላጎት ነው ፡፡ አንድነት ግን የእሱን ፍልጎት አያሳከም ምክንያቱን የእሱ ፍልጎት ማስተብቂታ በልዩነት እና በተቀራኖ ላይ የተመሰረተ እና የተገነባ ስለሆነ ነው፡፡ እንግዲህ የአብይ በመደመር (አንድነት) እና በመቀነስ ( ቅራኔ እና ግጭት ) ስልጣኑን ለማስጠበቅ የሚያደርገው መሳሳብ ነው አብይን እዚህም እዛም የሚያስቀባጥረው ፡፡ በጣም የተመቸኝ ስለ ሙሁራኖች የሰጠው ማብራሪያ ነው፡ ወያኔ አለ አብይ ሊሂቃን መሳዮች (Pseudo intellectual) ፈጠረች ያለው ነው፡፡ አቶ በረክት እንዳሉት የአብይ ወታደራዊም ሆነ የአካዳሚክ ( ዶከትሬት) መአረጎችን የፈጠርችው ወያኔ ባስቀመጠጭው ጎዶሎ መስፈርት መሰርት ነው ፡፡ እሱ ከስምተኛ ከፍል ወደ ዶክትሬት የዘለለበትን እና ከተራ ወታደርነት ወደ ኮኔሬል መአረግ የደረስበትን ሂደት ቢያሳየን መልከም ነው፡፡ አካሄዱ ግን ኢመደበኛ እንደሆነ ሁላችንም እሱም የምናውቀው ጉዳይ ነው አብይ እራሱ Pseudo intellectual እገለጫ ነው
አብይ እንዳለው እናንተ መደመርን ካልተቀበላችሁት ኬኒያ ትቀበለዋልች ሲል የእሱ መደመር ድምበር ተሻጋሪ መሆኑን ነግሮናል፡፡ በእሱ እሳቤ መደመር ድንበር ተሻጋሪ እንደሚሆን አስልቷል ሃቁ ግን የሰበሰባቸው የመአከላዊ ኮሚቴዎች እሱ የፈለገውን የመደመርን ፅንሰ ሃሳብ ተረድተው ተግባራዊ ሊያደርጉ ይቅር እና ስለ ፓራዳይም የተናገረው እሱም አልገባውም እንሱም አልተረዱትም፡፡ መደመር ኩታ ገጠም ማራስ ነው፡ ይልህ እና በአዞ እና በወፍ መካከል ያለውን Symbiotic ግንኙነት መደመር ነው ይልሃል፡፡ የንቦች ተፈጥሯዊ እንቅስቃሴ መደመር ነው ይልሃል ፡፡ በጥቅሉ የእዚህ ሁሉ ድብቅ መልእክት (Subliminal messages) እኔ የምላችሁን ስሙ ከኔ ጋር ሁኑ፡ ለኔ ታማኝ ሁኑ፡ ያ ካለሆነ ውጤቱ የከፋ ነው የሚለው፡ ያን ያስረዳበት ቦታ ፡ ብልፅግና ስትለው ሽኔ ልሁን ካለ ( ፋኖ ማለቱ ነው)፡ ጠዋት ጠዋት የዩንቨርስቲ መምህር ነው ከሰአት ከሰአት አክቲቪት ነው፡፡ ጠዋት ጠዋት ለኮብራ ብልፅግና ሆኖ ከሰአት ከሰአት አክቲቪስት መሆን አይቻልም ( ለዮሃንስ ቧ ያለው ነው)፡ እና የብልፅግና አባልነትን ከጉንዳን ጋራ ያመሳሰለበት ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ንፅፅር የተናገረው ሁሉን ነገር አጠቃሎ ያሳያል፡ ጉንዳን ካለተደመረ ይጠፋል ብሎ ሲናገር፡፡ ጉንዳኑ ትንሽ IQ ያለው፤ ትንሽ አቅም ያለው ፡ ትንሽ ጉልበት ያለው ሲል የብልፅግና አባላትን እንደሆነ ሰልጣኙ የተረዳ አልመሰለኝም፡፡ እንሲህ የመደመር እሳቤዎች እና ማስጠንቀቂያዎች ወደ ሶስተኛው ነጥብ ይወስደናል፡ የደህንነት ( ፌድራል ፖለስ፡ ፌድራዳል ደህነት፡ የመረጃ መረብ ደህንነት ) እና የግድያው አዋጅ፡፡
የደህንነቱ ፀረ ሕዝብ አዋጅ
አብይ ጀነራሎቹን ሰብስቦ እኔን ከጠበቃችሁን ውለታችሁን እከፍላለሁ ብሎ ከነገራቸው በኋላ ቀጥሎ በስልጠና ስም የሰበሰባቸው ከጀነራሎቹ ጋራ ባደረገው ስብሰባ አጭበርባሪ ሌባ ብሎ የሰየመውን ክፍል ወይም የካድሬ ስብስብ ነው፡፡ የካድሬዎቹ ስልጠና ከኔ አመራር እና እሳቤ ውጪ ወደ ውጪ ብሎ ያስረገጠበት እና ያለተደመሩ እንደሚጠፉ አስረግጦ የተናገረበት ነው፡፡ ከመደመር ውጪ ያሉ እና የእሱን ተእዛዛትን ያልተቀብሉትን በተለይ የአማራ ሕዝብ እና የአማራ የፖለቲካ ሃይሎች በጎለበት ለመጭፈልቅ የሚያስችለውን ምክረ ሃሳብ ከአገሩ የፀጥታ (Security) ኃይሎች ጋራ መከሮ እና ዘክሮ የግድያውን እና የጭፍለቃውን አዋጅ በብሔራዊ ደህነንት በኩል አሳውጇል፡፡ ግራዚያኒ ከሞት ተነሳ ማለት አሁን ነው፡፡
የአብይ ፋሽሽታዊ አዋጅ ሶስት ጠላቶች የሚላቸውን ለይቶ አስቀምጧል፡ እንሱም 1ኛ ምንጊዜም የማይተኙት ታሪካዊ ጠላቶቻችን ። 2ኛ ሀገር አልባ ባይተዋሮች፡ 3ኛ ውል አልባ የኢትዮጰያዊያን፡፡ አብይ ታሪካዊ ጠላት ያለውን ኢሳያስን ሲሆን እሱን መዋጋት እንደማይችል ይፋ ሲያደርግ ሁለቱን ጠላቶች ለማጥፋት ግን ቀጠን ያለ አዋጅ አውጆል፡ የአዋጁም ማሳረጊያ እንዲህም ይላል ፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ተሰልፎ የሚገኝ ማንኛውም ሰው፣ አካልና ቡድን ላይ ሕጉ የሚፈቅደውን ተገቢውን ሕግና ጸጥታ የማስከበር ሥራ የምንሠራ መሆኑን እናሳውቃለን። በአማራ ጥቅም እና ሕልውና ላይ ከትህነግ ጋራ በጀርባ የሚደራደረው አብይ ሁለቱ ጠላቶች ያላቸው ማን እንደሆኑ ለመረዳት የአንጎል ስርጀን መሆን አይጠይቅም፡፡ አብይ ከ99% የሚያተኩረው በአማራው ላይ እና በአማራ ላይ ብቻ ነው፡፡ እነዚህም የዳቦ ስም እንደሚከተለው ወጥቶላቸዋል፡፡

1ኛ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ቡድኖችንና ግለሰቦችን፣ 2ኛ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሠራጨት ሕዝብና ሀገርን ሰላም የሚነሡ አካላትን፣ 3ኛ በሕገ ወጥ መንገድ ታጥቀው የሕዝብን ሰላም የሚነሡና 4ኛ ለታሪካዊ ጠላቶቻችን በተላላኪነት የሚያገለግሉ ቡድኖችን፣ ሊሎችም አሉ

አብይ ባሴረው መሰረት ውጊያውን ሰሞኑን በዋግ ተግኝቶ ባደረግው ንግግር ከፍቶታል፡፡ መለስ የአክሱም ሃውልት ለወላይታው ምኑ ብሎ ነበር አብይ ደግሞ የአክሱም እና ላሊበላ የእናተ የአገዎች (ኩሾች) ነው ሲል ቀጣዩን ጦርነት አሳይቷል፡፡ በሌላ ወቅትም የዛጓኤ ስርአት ማለት የአክሱማት ስራትን ደብድቦ ቀጥቅጦ ያፈረሰ ማለት ነው ሲል አገው እና ትግራይን ለማጋጨት መርዙን ተፍቷል፡፡ በተጨማሪም በጎንደር በፋኖዎች ላይ የሚደረገው የግድያ ሙከራ እና በሃይማኖት ስም በጎንደር የተለኮሰው ግጭት የአብይ አማራን የማጥፋት ስሌት አካል መሆኑ ሊሰመርባት ይገባል፡፡

ያመነ ፣ የተዘጋጀ፣ የፀና፣ የቆረጠ፣ ያሽንፋል ፡፡ አማራ ለማይቀረው ፍልሚያ ተዘጋጅ

የግድያው አዋጅ እና ያለሰለጠነው አሰልጣኝ፡ መደመር አሳይቶ የሚቀንስከኢያሱ ኤፍሬም ገ/ሐና፡ ከለንደን ሚያዚያ 19 2014 ፡ 2022 ኤፕሪል 27, ረቡዕ፡ አንብቡት ፡ አካፍሉት ተቹትመግቢያ...

Address

1600 Pennsylvania Avenue
Washington D.C., DC
20035

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአማራ ነፃነት ንቅናቄ -Amhara Liberation Movement posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የአማራ ነፃነት ንቅናቄ -Amhara Liberation Movement:

Featured

Share