Ethiopian Community Center in Maryland

Ethiopian Community Center in Maryland Make it possible for like-minded individuals to meet and contribute to the community. Identify professionals and make it possible for them to contribute

04/10/2025

Please watch parents !!

04/03/2025
Another magnificent senior day celebration unfolds on this radiant day! Meet next week, every Thursday 12-2 pm at the Et...
03/20/2025

Another magnificent senior day celebration unfolds on this radiant day!

Meet next week, every Thursday 12-2 pm at the Ethiopian Community Center in Maryland !

ሮድ ቱ ሂሊንግበታዳጊ ልጆቻችን የስነ-ልቡና ደህንነትበወላጆችና በልጆች መካከል ስላለው ጤናማና ውጤታማ ግንኙነትእንደ ሰደድ እሳት ልጆቻችንን እየፈጀብን ስላለው ከሱስና ተያያዥ ጉዳዮች የሚጠበ...
03/17/2025

ሮድ ቱ ሂሊንግ

በታዳጊ ልጆቻችን የስነ-ልቡና ደህንነት

በወላጆችና በልጆች መካከል ስላለው ጤናማና ውጤታማ ግንኙነት

እንደ ሰደድ እሳት ልጆቻችንን እየፈጀብን ስላለው ከሱስና ተያያዥ ጉዳዮች የሚጠበቁበትን ጥበብና ብልሀት የሚማሩበት

ብዙዎች በየቤታችን በብዙ መከራ ውስጥ ስለምናልፍባቸው ጉዳዮቻችን በስመጥር ባለሞያዎች እጅግ ጠቃሚ ትምህርት የሚገኝበት

ችግሩ ላይ ብቻ ሳይሆን መፍትሄውን የምንረዳበት ሮድ ቱ ሂል ሜሪላንድ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲና ሌሎች አጋር አካላት ጋር ይዞላችሁ መጥቶል

ቅዳሜ ማርች 22 ከ12 - 7 ሰዓት

ታኮማ በሚገኘው ሞንትጎሞሪ ኮሌጅ

የአንጀት ካንሰር በቀላሉ መከላከል የሚቻል ነገር ግን በአሜሪካ ሶስተኛው ገዳይ ካንሰር በሽታ ነው:: ቅድመ ምርመራ ማድረግ በቀላሉ በሽታውን ለመከላከል ወሳኝ ነው:: ሜሪላንድ የሚገኘው የኢት...
01/31/2025

የአንጀት ካንሰር በቀላሉ መከላከል የሚቻል ነገር ግን በአሜሪካ ሶስተኛው ገዳይ ካንሰር በሽታ ነው:: ቅድመ ምርመራ ማድረግ በቀላሉ በሽታውን ለመከላከል ወሳኝ ነው:: ሜሪላንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ከጆን ሆፕኪንስ ጋር በመተባበር ጥቂት ሰዎች የሚሳተፉበት ጥናት ላይ በትብብር ይሰራል

ዕድሜው ከ45 ዓመት በላይ

የአንጀት ካንሰር ቅድመ ምርመራ አድርጎ የማያውቅ

እንግሊዝኛ ማንበብና መረዳት የሚችል

ቦልቲሞር ወይም ፒጂ ነዋሪ ከሆኑ በዚህ ጥናት መሳተፍ ይችላሉ:: ጥናቱ

የ1 ሰዓት የግሩፕ ውይይት ለዚህ 30$ ጊፍት ካርድ ያገኛሉ

1:30 ትምህርት መካፈል ... ለዚህ የ40$ ጊፍት ካርድ ያገኛሉ

የ30 ደቂቃ የስልክ ውይይት ... ለዚህ የ10$ ጊፍት ካርድ ያገኛሉ ...

ለመሳተፍ አሁኑኑ በውስጥ መስመር ይጻፉልን::

Another successful senior day at the Ethiopian Community Center!
01/31/2025

Another successful senior day at the Ethiopian Community Center!

130 ሚልየን ዶላር ስኮላርሺፕ ለሜሪላንድ ተማሪዎችቀጣይ ዓመት ኮሌጅ ለመሄድ የፋይናንሻል ድጋፍና ሌሎችንም ከመንግስት ለመጠየቅ የምዝገባ ቀኑ የሚጠናቀቀው በማርች 1 ስለሆነ ፈጥነው አሁኑኑ ...
01/29/2025

130 ሚልየን ዶላር ስኮላርሺፕ ለሜሪላንድ ተማሪዎች

ቀጣይ ዓመት ኮሌጅ ለመሄድ የፋይናንሻል ድጋፍና ሌሎችንም ከመንግስት ለመጠየቅ የምዝገባ ቀኑ የሚጠናቀቀው በማርች 1 ስለሆነ ፈጥነው አሁኑኑ ያመልክቱ::

Considering college? Maryland has millions of dollars available for you to achieve your higher education goals for 2 year and 4 year colleges or even trade s...

130 million dollars Scholarship for Maryland Students As we look ahead to this Fall, it's crucial to remember that the p...
01/29/2025

130 million dollars Scholarship for Maryland Students

As we look ahead to this Fall, it's crucial to remember that the priority deadline to submit your Free Application for Federal Student Aid (FAFSA) is March 1, 2025. Meeting this deadline means you'll have the BEST chance of securing the MAXIMUM financial aid available to you.

To learn more about the available financial aid and the application process, check out this informative video from our Office of Student Financial Assistance:

For more information watch the video

Considering college? Maryland has millions of dollars available for you to achieve your higher education goals for 2 year and 4 year colleges or even trade s...

01/29/2025

Anteneh Habtesellassie, [1/29/2025 9:25 AM]
🚨አሜሪካ ለሚኖሩ፡ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ ማወቅ ያለብን ነጥቦች🚨
በጋዜጠኛ አበበ ፈለቀ

በዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት ውስጥ ወድቀዋል። የተለያዩ የኢትዮጵያ የንግድ ተቋማት፣ ሬስቶራንቶች፣ ገበያወች ውስጥ የሚሰሩትም በፍርሃት በመዋጣቸው ከቤት አለመውጣትን መርጠዋል።

በዚህ መነሻነት፣ ጉዳዩ ያስጨነቃችሁ አሜሪካ የምትኖሩ የማህበረሰባችን አባላት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ጥንቃቄ ታደርጉ ዘንድ፣ የልዩ ፕሬዝዳንታዊ (Executive Order) ትዕዛዙንና አፈጻጸሙን አገላብጬና የህግ ባለሞያወችን አናግሬ ያገኘሁትን መረጃ ባጭሩ እነሆ።

የዚህ ዘመቻ ዋና ኢላማወች፦
🔴 በአሜሪካ ስርዓት ውስጥ ያልተመዘገቡ (Undocumented)፣ በህጋዊ መንገድ ለመቆየት የሚያበቃ መረጃና ፍቃድ የሌላቸው፣ በየትኛውም የስደተኝነት ወይም የጥገኝነት ማመልከቻ ሂደት ውስጥ የሌሉ፣
🔴 የጥገኝነት ማመልከቻቸው በሁሉም የማመልከት ሂደቶችና ደረጃወች ላይ ውድቅ ተደርጎ በስደተኞች ፍርድ ቤት ሃገር እንዲለቁ (Removal Order) የታዘዙ
🔴 በየትኛውም የጥገኝነት ማመልከቻ ሂደት ውስጥ ያሉ፣ እንዲሁም የስራ፣ የትምህርትም ሆነ የጉብኝት ቪዛ ያላቸው ቢሆኑም በወንጀል የተከሰሱ፣ የተፈረደባቸው፣ የተጠረጠሩ ወይም የወንጀል ታሪክ ያላቸው ከሆነ ለዚህ የአፈሳ ተዕዛዝ የተጋለጡ ናቸው።

ይሄ ዘመቻ የማይመለከታቸው፦
🟢 ህጋዊ ነዋሪወች፤ የመኖርያ ፈቃድ (Green Card) ያላቸው ሰወች ከሃገር የሚያስባርር ወንጀል እስካልፈጸሙ ድረስ
🟢 ቀኑ ያላለፈ ቪዛ ያላቸው፤ የተማሪ፣ የስራ፣ የጉብኝት ቪዛ ያላቸው እና በቪዛው ላይ ያለውን የመቆያ ጊዜና ደንብ/ ግዴታ ያከበሩ
🟢 ጥገኝነት (Asylum) ያመለከቱ ጉዳያቸው በየትኛውም ደረጃም ላይ ቢሆን በሂደት ላይ ያለ፣ የስራ ፈቃድ ያላቸው እና ምንም አይነት የወንጀል ታሪክ የሌላቸው

ይሄ ጉዳይ የሚመለከታቸው ሰወች ማደረግ ያለባቸው፦
✅ የስደተኛ ጉዳይ አስፈጻሚ ሃይሎች የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካልያዙ በስተቀር የቤታችሁን በር ያለመክፈት መብት አላችሁ
✅ በቁጥጥር ስር ቢውሉም ለማንኛውም ጥያቄ መልስ አለመስጠት እና ጠበቃ የመጠየቅ መብት አላችሁ
✅ ከቦት ቦት ሲንቀሳቀሱ መታወቂያ እና የህጋዊነት መኖርያ ፈቃድ ወይም የማመልከቻ ደረሰኝና ማስረጃወች መያዝ
✅ ለክፉም ለደጉም የአደጋ ጊዜ እቅድ ማውጣት፣ የአስፈላጊ የቤተሰብ ተጠሪወችንና የህግ ባለሞያወችን ስልክ መያዝ
✅ በማመልከቻ ሂደት ላይ ያላችሁ ከጠበቆቻችሁ ጋ መማከር፣ ማመለከቻችሁ ያለበትን ደረጃ በሚገባ ማወቅ፣ የፍርድ ቤት አልያም የቃለመጠይቅ ቀጠሮወችን አለማሳለፍ
✅ የወንጀል ክስ ወይም ታሪክ ካለ የህግ ድጋፍ መፈለግ
✅ ከመጨነቅ ይልቅ ተረጋግቶ ህጋዊ መሰረት ካላቸው እና ከታመኑ ምንጮች ብቻ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃወችን ማግኘት

ይሄ መረጃ ግንዛቤን ለማስፋት የቀረበ እንጂ የህግ ባለሞያን ምክር የሚተካ አለመሆኑን ከወዲሁ መግለጽ እወዳለሁ። መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄወች ሁሉም ሰው እንዳለበት ሁኔታ የሚወሰኑና የሚለያዩ ስለሆኑ ራስን መጠበቅ፣ በእውቀት ላይ የተመሰረተ በቂ መረጃ ላይ መመርኮዝ እና፣ ሁል ጊዜም ቢሆን ህጋዊ ድጋፍን ማግኘት አስፈላጊና ጠቃሚ ነው።

Please join us Thursday night if you are able to and please share it with people you know! The session will be in Amhari...
01/29/2025

Please join us Thursday night if you are able to and please share it with people you know! The session will be in Amharic and very beneficial information.
Here is the link to register:
https://t.me/EthioUS/1/9014

የጆሮና የዓይን እንዲሁም ሙሉ የደም ምርመራን ጨምሮ ሌሎችም የጤና ክትትሎችን እንሹራንስ ቢኖሮትም ባይኖሮትም የፊታችን ቅዳሜ ከጠዋቱ 10 እስከ 2 ሰዓት በፍላየሩ ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ማግ...
01/24/2025

የጆሮና የዓይን እንዲሁም ሙሉ የደም ምርመራን ጨምሮ ሌሎችም የጤና ክትትሎችን እንሹራንስ ቢኖሮትም ባይኖሮትም የፊታችን ቅዳሜ ከጠዋቱ 10 እስከ 2 ሰዓት በፍላየሩ ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ ...

Interested in learning more about Maryland State financial aid, including scholarship and grant programs? Register now f...
01/24/2025

Interested in learning more about Maryland State financial aid, including scholarship and grant programs?

Register now for a virtual scholarship webinar on February 6th, hosted by the Annapolis Alumnae Chapter of Delta Sigma Theta Sorority, Inc.

A representative from MHEC will explain steps to secure funding for career school, community college, or university! To register today, scan the QR code on the flyer or visit this link:
https://bit.ly/4jvj1XU

Address

8701 Georgia Avenue Ste 601
Silver Spring, MD
20910

Opening Hours

Monday 9am - 5pm
Tuesday 9am - 5pm
Wednesday 9am - 5pm
Thursday 9am - 5pm
Friday 9am - 5am

Telephone

(240)8397805

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Community Center in Maryland posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Community Center in Maryland:

Featured

Share