International Ethiopian Athlete's Association

International Ethiopian Athlete's Association Founded in August, 2020 Our organization focused on organizing athletics activities and supporting athletes with special needs.

International Ethiopian Athlete's Association is a not-for-profit organization founded in Aug 2020 by a group of former and current Ethiopian Athletes. We encourage and support teamwork, discipline, and respect for others. We welcome all former and current Ethiopian athletes to join us and support our cause.

Celebrating my 4th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉
05/04/2025

Celebrating my 4th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

01/01/2024
01/01/2024

ከዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር አዲሱን የአውሮፖዊያን አዲስ ዓመት 2024 ምክንያት በማድረግ ለመላው ኢትዮጲያዊያን ለአትሌቶችና ለመላው የስፖርት ቤተሰብ የተላለፈ የመልካም ምኞት መልእክት ።

ከዓለም አቀፍ  የኢትዮጵያ አትሌትች ማህበር ********************************************      በአስደማሚ  ድል እንደጀመራችሁ  ቀሪዎቹንም ውድድሮች   በአኩሪ  ...
08/25/2023

ከዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ አትሌትች ማህበር
********************************************

በአስደማሚ ድል እንደጀመራችሁ ቀሪዎቹንም ውድድሮች በአኩሪ ድሎች እንድትጨርሱ ሲል
የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር የተለመደውን መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

በቡዳፔስት የሚደረገው አስራ ዘጠነኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የተሰለፉት አትሌቶቻችን የተለመደው ብቃታቸው ገና ከመክፈቻው እለት ጀምሮ ዓለምን ህዝብ በእጅጉ አስደምሞአል።

የትውልድ አደራ የተርከባችሁ ጀግኖች በዘመናችሁ የተሻለ ታሪክ ለማስፃፍ የተጉ እግሮቻችሁ ወደ ቡዳፔስት ከገሰገሱበት እለት ጀምሮ የወገናችሁ ጆሮ የድል ዜና ለመስማት እለት ከእለት ነቅቶ ይጠባበቃል።

ማህፀነ ለምለም የሆነችው ኢትዮጵያ ሃገራችን በየወቅቱ ድልን በድል ላይ እየተጎናፀፉ ባንዲራዋን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ የሚያስደርጉ ጀግኖች አጥታ አታውቅም ።
ከትውልድ ትውልድ ሲቀባበል እስከ ዛሬው የአስራ ዘጠነኛው የቡዳፔስት የአለም ሻምፒዮና ላይ የደረሰው የሃገር ፍቅርና የአሸናፊነት ወኔ ነገም እንዲቀጥል የስፖርት አፍቃሪው ህዝብ ለአትሌቶቻችን የሞራል ድጋፍ መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ይተማመናል።

አትሌቶቻችን እስከ አሁን ያስመዘገቡት ድል ሃገርና ወገንን የሚያኮራ ከመሆኑም በለይ ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ሰንጠርዥ በቀዳሚነት ከተሰለፉት ሃገራት ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ረድፍ ላይ እንድትቀመጥ አድርጎአ ሰንብቷል።

አትሌቶቻችን የአውሮፖን ሙቀታማ የአየር ንብረት ተቋቁመው ተውዳዳሪዎቻቸውን በማስጨነቅ ከተቀዳጁአቸው ታላቅ ድሎች ላይ ተጨማሪ ድሎችን በቀሪዎቹም ቀናት በሌሎች የውድድር አይነቶች በማስመዝገብ ድል የለመደውን ወገናቸውን ዳግም እንደሚያኮሩ ዓለም አቀፍ የኢትዮጵይን አትሌቶች ማህበር ጽኑ እምነት አለው።

የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር በአስራ ዘጠነኛው የቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያን ወክሎ ለተሰለፈው የአትሌቲክስ ቡድናችን እና ለመላው የሉኡካን ቡድኑ አባላት ቀሪዎቹ ቀናት የስኬት እና የተሻሉ ድሎችን ተቀዳጅታችሁ በአሸናፊነት ሰገነት ላይ ደጋግማችሁ በመቆም የኢትዮጵያን ባንዲራ በተደጋጋሚ ከፍ የምታደርጉበት የስኬት ወቅት እንዲሆንላችሁ ከልብ ይመኛል።

ድል ለመላው የኢትዮጵያ አትሌቶች ይሁን

ከዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ።

Address

Silver Spring
Silver Spring, MD

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when International Ethiopian Athlete's Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to International Ethiopian Athlete's Association:

Featured

Share