Wollega Amharan Association

Wollega Amharan Association OUR STORY SHALL BE TOLD!

ሰበር ዜናበአጣዬ ከተማ ከባድ ተኩስ እንደሚሰማ ነዋሪዎች ተናገሩ!በሰሜን ሸዋ ዞን የኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መቀመጫ በሆነችው አጣዬ ከተማ ከባድ የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ ህይወታቸውን ለማትረ...
01/24/2023

ሰበር ዜና

በአጣዬ ከተማ ከባድ ተኩስ እንደሚሰማ ነዋሪዎች ተናገሩ!

በሰሜን ሸዋ ዞን የኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መቀመጫ በሆነችው አጣዬ ከተማ ከባድ የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ ህይወታቸውን ለማትረፍ እየሸሹ የሚገኙ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ እንዳሉት፣ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ መግባታቸውን ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ አክለውም፣ የፌዴራል እና የክልል የጸጥታ አካላት በከተማዋ ቢኖሩም ቁጥራቸው አነስተኛ በመሆኑ ታጣቂዎቹን ወደ ከተማዋ ከመግባት መከላከል አልቻሉም ብለዋል።

በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከስምንት ጊዜ በላይ የኦነግ ሸኔ ጥቃት ሰለባ የሆነችው የአጣዬ ከተማ፤ ዳግም ለጥቃት ተዳርጋለች።

ከሰሞኑ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጸጥታ ኃይሎች እና በንፁሃን ላይ ተኩስ ከፍተው መጠነ ሰፊ ጉዳት እያደረሱ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ አጣዬ ከተማ የገቡ ሲሆን፤ ከባድ ተኩስ እንደሚሰማም ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የከተማው ነዋሪ አረጋግጠዋል።

የፌዴራሉ መንግሥት የከፋ ጉዳተ ሳይደርስ ተጨማሪ ኃይል ወደ ከተማዋ እንዲያሰማራም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል ሲል የአማራ ድምፅ ዘግቧል።

ሰበር ዜና!በሰሜን ሸዋ ዞን ጀውሃን ጨምሮ ወሰን ቁርቁር እንዲሁም ጀጀባ እና ሰንበቴ ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተኩስ መክፈታቸው ተገለፀ!በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ...
01/23/2023

ሰበር ዜና!

በሰሜን ሸዋ ዞን ጀውሃን ጨምሮ ወሰን ቁርቁር እንዲሁም ጀጀባ እና ሰንበቴ ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተኩስ መክፈታቸው ተገለፀ!

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ስር በሚገኘው ጀውሃ ቀበሌን ጨምሮ ወሰን ቁርቁር፣ ጀጀባ እና ሰንበቴ ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ዛሬ ጥር 15/2015 ዓ/ም ከረፋዱ ጀምሮ ተኩስ መክፈታቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ነግረውኛል ሲል የአማራ ድምፅ ዘግቧል።

በአማራ ክልል የኦሮሞ ልዩ ዞን ስር መሽገው የሚገኙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ጥር 13/2015 ዓ/ም አመሻሹን በኤፍራታና ግድም ወረዳ ጀውሃ ቀበሌ በሚገኘው የአማራ ልዩ ኃይል ካምፕ ላይ ጥቃት ከፍተው የነበረ ሲሆን፣ በዚህም ከ30 በላይ ልዩ ኃይሎች መገደላቸው ታውቋል።

ታጣቂዎቹ በድጋሚ ዛሬ ጥር 15/2015 ዓ/ም ከረፋዱ ሦስት ሰዓት ገደማ ጀምሮ በኤፍራታና ግድም ወረዳ ስር በምትገኘው ጀውሃ ቀበሌን ጭምሮ ወሰን ቁርቁር፣ ጀጀባ እና ሰንበቴ ላይ በቡድን መሳሪያ ጭምር የታገዘ ተኩስ መክፈታቸውን ነው የአከባቢው ነዋሪዎች ያረጋገጡት።

በአከባቢው የሚገኙት የክልሉ ልዩ ኃይሎች በታጣቂዎቹ የተከፈተውን ጥቃት ለመከላከል ሙከራ እያደረጉ ነው የተባለ ሲሆን ነገር ግን ተኩሱ አድማሱን እያሰፋ መሆኑ ተመላክቷል።

የአማራ ድምፅ ሚድያ አነጋግሬያቸዋለው ያላቸው የጀውሃ ቀበሌ ነዋሪዎች፡ "አከባቢውን ለቀን እንዳንወጣ መንገድ ተዘግቷል" ያሉ ሲሆን የክልሉ መንግስት ተጨማሪ የፀጥታ ኃይል አሰማርቶ እንዲታደጋቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በኦሮሚያ ልዩ ዞን የጅሌ ሙጥጋ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በበኩሉ "ሰንበቴ ከተማ ጭንቅ ውስጥ ገብታለች" ሲል በማህበራዊ ትስስር ገፁ ያሰፈረ ሲሆን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎቹ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ካሰባሰብኩት መረጃ ለማረጋገጥ ችያለሁ ሲል የአማራ ድምፅ በዘገባው አካቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ!ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 74(2) መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ የሚከ...
01/20/2023

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 74(2) መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ የሚከተሉትን ሹመቶች እንዲያጸድቅ ጠይቀዋል፦

1. ዶ/ር አለሙ ስሜ - የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር

2. ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ - የማዕድን ሚኒስትር

3. ዶ/ር ግርማ አመንቴ - የግብርና ሚኒስትር

በተጨማሪም ከጥር 10፣ 2015 ጀምሮ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰተዋል፦

1. አቶ ማሞ ምሕረቱ - የብሔራዊ ባንክ ገዢ

2. ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር

3. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት - የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር

4. አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ - የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር

5. አቶ መለሰ አለሙ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ የዘርፍ አስተባባሪ ተደርገው ተሹመዋል።

ሰበር ዜና!በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሀንስ ከተማ ውጥረት መንገሱ ተሰማ!በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሀንስ ከተማ የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች የከተራ በዓልን በማክበር ላይ የነ...
01/18/2023

ሰበር ዜና!

በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሀንስ ከተማ ውጥረት መንገሱ ተሰማ!

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሀንስ ከተማ የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች የከተራ በዓልን በማክበር ላይ የነበሩ የፋኖ አባላትን ትጥቅ ለማስፈታት ባደረጉት ሙከራ በከተማዋ ውጥረት ነግሶ ማምሸቱን በስፍራው የሚገኙ የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ገለፁ።

ትጥቅ ለማስፈታት የተላኩት የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ዛሬ ጥር 10/2015 ዓ/ም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ገደማ በመተማ ዮሀንስ ከተማ ልዩ ስሙ ኩራዝ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ፅላት ወደ ባህረ ጥምቀቱ ሸኝተው ሲመለሱ የነበሩ የፋኖ አባላትን ትጥቅ ለማስፈታት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን በዚህም በከተማዋ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን ነው የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ያየረጋገጡት።

የፋኖ አባላቱ ትጥቃችንን አናወርድም በሚል ከመንግስት ታጣቂዎቹ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብተው ያመሹ ሲሆን የሀገር ሽማግሌዎች የተፈጠረው ችግር በውይይት እንዲፈታ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙም ተመላክቷል።

ትጥቅ ለማስፈታት የተላኩት የመንግስት ፀጥታ ኃይሎቹ፡ የፋኖ አባላቱን የጥምቀት በዓልን ለማክበር ወደ ባህረ ጥምቀቱ እንዳይሄዱ የከለከሉ ሲሆን ከዚህ አልፎ ትጥቃችሁን አውርዱ በሚል አምባጓሮ መፍጠራቸውን ነው የአይን እማኞቹ ለአማራ ድምፅ የገለፁት።

የተፈጠረውን ችግር በማስመልከት ለአማራ ድምፅ እጭር ማብራሪያ የሰጡት የፋኖ አባላቱ፡ "እንደማንኛውም የእምነቱ ተከታይ በዓሉን የማክበር መብት አለን" ያሉ ሲሆን "የወልቃይት እና የራያ ጉዳይ እልባት ሳያገኙ ትጥቅ መፍታት የማይታሰብ ነገር ነው" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአማራ ድምፅ እንደዘገበው!

አቶ ሺመልስ አብዲሳ የአማራ ተወላጆችን ያገለለ ውይይት ማድረጋቸው ተገለፀ።የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሺመልስ አብዲሳ ከሰሞኑ ከምስራቅ ወለጋ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል የተባ...
01/18/2023

አቶ ሺመልስ አብዲሳ የአማራ ተወላጆችን ያገለለ ውይይት ማድረጋቸው ተገለፀ።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሺመልስ አብዲሳ ከሰሞኑ ከምስራቅ ወለጋ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል የተባለ ሲሆን ነገር ግን ውይይቱ የአማራ ተወላጆችን ያገለለ መሆኑን በዞኑ ስር በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ተናግረዋል።

ውይይቱ የተደረገው ጥር 08/2015 ዓ/ም የዞኑ ዋና መቀመጫ በሆነችው ነቀምቴ ከተማ ሲሆን በመድረኩ ላይም ርዕሰ መርተዳድሩን ጨምሮ ኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማን እና የተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ተብሏል።

በውይይቱ ላይ የጦር መኮንኖች፣ አባገዳዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሸማግሌዎችን ጨምሮ በዞኑ ስር በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል የተባለ ቢሆንም ነገር ግን የአማራ ተወላጅ የሆኑ የዞኑ ነዋሪዎች በውይይቱ እንዲገኙ አለመደረጋቸውን ነው ያረጋገጡት።

የዞኑ ነዋሪዎች እንደገለፁት፡ጊዳ አያና፣ ጊዳ ኪረሙ፣ ዲጋ፣ ሳሲጋ፣ ሊሙ፣ሲቡ ስሬ፣ ጎቡ ሰዮ፣ ጉቶ ጊዳ፣ ዋዩ ጡቃ እና ሌሎችም በርካታ የአማራ ተወላጆች በሚገኙባቸው የምስራቅ ወለጋ ዞን ወረዳዎች ተወክለው ውይይቱ ላይ የተሳተፉ የአማራ ተወላጆች የሉም ያሉ ሲሆን ነቀምቴ ከተማ እንዳይከቡ እየተከለከሉ መሆናቸውንም አመላክተዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ውይይቱን ያደረጉት የአማራ ተወላጆችን ባገለለ መልኩ ነው የሚሉት የዞኑ ነዋሪዎቹ፡ የአማራ ተወላጆችን ጥያቄ እና ችግር የሚረዳላቸው አካል ማጣታቸውን ተናግረዋል።

የክልሉ አመራሮች በዞኑ ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ ለማምጣት ቁርጠኝነት ያላቸው አይመስልም ሲሉ የገለፁት የአማራ ተወላጅ የሆኑ የዞኑ ነዋሪዎች፡ የሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች ተወካይ ባልተገኙበት ሁሉን አቀፍ ውይይት እንደተካሄደ ለማስመሰል የተሄደበት ርቀት ችግሩን ሸፋፍኖ ለማለፍ የተደረገ ጥረት ነው ብለዋል።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፥ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!!!የከተራ_በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።
01/18/2023

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፥ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!!!

የከተራ_በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

በቄለም ወለጋ ዳሊሰዲ ወረዳ ሰላም ለማስከበር የተሰማሩ የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች እገታና ዝርፊያ እየፈፀሙ ነው ተባለ!በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ዳሊሰዲ ወረዳ ልዩ ስሙ መንደር 14 በተባለ...
01/18/2023

በቄለም ወለጋ ዳሊሰዲ ወረዳ ሰላም ለማስከበር የተሰማሩ የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች እገታና ዝርፊያ እየፈፀሙ ነው ተባለ!

በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ዳሊሰዲ ወረዳ ልዩ ስሙ መንደር 14 በተባለ አከባቢ ሰላም ለማስከበር የተላኩ የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች የአማራ ተወላጅ በሆኑ የአከባቢው ነዋሪዎች ላይ እገታ ዝርፊያ እና ድብደባ እየፈፀሙ መሆናቸውን ተጎጂዎቹ ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

የፀጥታ ኃይሎቹ የአማራ ተወላጅ የሆኑ በአከባቢው የሚኖሩ ነጋዴዎችን እና አርሶ አደሮችን በማገትም ከፍተኛ ገንዘብ እየተቀበሉ መሆኑን ለአማራ ድምፅ የገለፁት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ ከዚህ በተጨማሪ ግድያ እና ድብደባ እየፈፀሙባቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

ለአብነትም ከሰሞኑ የአምራ ተወላጅ የሆነ አንድ ነጋዴ ቤት በደረቅ ለሊት የገቡት የፀጥታ ኃይሎቹ፡ የንብረት ዘረፋ ከፈፀሙ ቦኋላ የቤቱ ባለቤት ላይ በጥይት ተኩሰው ያቆሰሉ ሲሆን ወደ ህክምና እንዳይሄድ መከልከላቸውንም የአከባቢው ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

የፀጥታ ኃይሎቹ የአከባቢው ነዋሪዎች ላይ እገታ፣ ድብደባ እና ዘረፋ ከፈፀሙ ቦኋላ ለሚድያ እና ለበላይ አካላት እንዳትናገሩ በሚል ዛቻ እና ማስፈራሪያ እያደረሱ መሆኑንም ተጎጂዎቹ ተናግረዋል።

እነዚህ ፀጥታ ለማስከበር በሚል በአከባቢው ተሰማርተው እገታን ጨምሮ ዘረፋ እና ድብደባ የሚፈፅሙ የፀጥታ አካላትን የውሎ አበልን ጨምሮ ደመወዛቸውን እና ቀለባቸውን የአማራ ተወላጅ የሆኑ የአከቢው ነዋሪዎች እንዲሸፍኑ ግዴታ እንደተጣለባቸውም ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም አከባቢውን እንዲጠብቁ በመንግስት የታጠቁ ሚሊሾችን የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የክልሉ ልዩ ኃይሎች በጋራ በመሆን ትጥቅ አስፈትተው ወደ እስር ቤት አስገብተዋቸዋል ያሉት የአከባቢው ነዋሪዎች፡በሚሊሾቹ ምትክ አከባቢውን እንዲጠብቁ የተመደቡት የፀጥታ ኃይሎች ናቸው እገታ፣ የንብረት ዝርፊያ እና ድብደባ እየፈፀሙብን ያሉት ብለዋል።

ይሄንን በማስመልከት የአማራ ድምፅ ሚድያ የዳሊሰዲ ወረዳ አስተዳዳሪ ለሆኑት ለአቶ ዮሀንስ ስልክ በመደወል ምላሽ እንዲሰጡት ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም ነገር ግን አመራሩ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

የአማራ ድምፅ እንደዘገበው

በአዲስ አበባ ከተማ በጉልበት ስራ  የሚተዳደሩ ከ30 በላይ ወጣቶች መታሰራቸው  ተገለፀበአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዛሬ ጥር 06/2015 ዓ/ም ልዩ ስሙ ሃና ማርያም አከባቢ...
01/14/2023

በአዲስ አበባ ከተማ በጉልበት ስራ የሚተዳደሩ ከ30 በላይ ወጣቶች መታሰራቸው ተገለፀ

በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዛሬ ጥር 06/2015 ዓ/ም ልዩ ስሙ ሃና ማርያም አከባቢ በጉልበት ስራ የሚተዳደሩ ከ30 በላይ ወጣቶች መታሰራቸውን የአይን እማኞች ገልፀዋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ስሙ ሃና ማርያም ቀለበት መንገድ አከባቢ ወደ ስራ ለመሰማራት የተሰባሰቡ ከ30 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በፖሊስ ታፍሰው በክፍለ ከተማው ወረዳ 11 ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን ነው የአይን እማኞቹ ያየረጋገጡት።

ከታሰሩት ወጣቶች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት የአማራ ተወላጆች ናቸው የተባለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ የደቡብ ተወላጆች መኖራቸውም ተጠቁሟል።

"በአዲስ አበባ የፋኖ አባላት አሉ በአስቸኳይ በቁጥጥር ስር መዋል አለባቸው" የሚል መመሪያ ከክፍለ ከተማው እንደተሰጠ መስማታቸውን የገለፁት የአይን እማኞቹ ዛሬ የታሰሩት በጉልበት ስራ የተሰማሩ ወጣቶችም በጅምላ ታፍሰው የመታሰራቸው ምክኒያትም ከዚህ ጋር የተያያዘ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ አስተያየታቸውን ሰተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ጥር 11/2015 ዓ/ም ከሚከበረው የጥምቀት በዓል ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ተወላጆች እየታሰሩ መሆኑ ተመላክቷል።

በዚኸው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አከባቢ በቀጣዩ የጥምቀት በአል ያስተባብራሉ በሚል የተጠረጠሩ ሁለት ወጣቶች መታሰራቸውን ነው የአይን እማኞቹ የተናገሩት።

ወጣቶቹ የታሰሩት ጥር 03/2015 ሲሆን እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውም ተገልጿዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በአዲስ አበባ የተለያዪ ክፍለ ከተሞች ከመጭው ጥምቀት በዓል ጋር በተያያዘ ያስተባብራሉ በሚል የተጠረጠሩ በርካታ ወጣቶች እየታሰሩ መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ ሲል የአማራ ድምፅ ዘግቧል።

በአዲስ አበባ የአፄ ቴዎድሮስን፣ የአፄ ምኒልክን እና የእቴጌ ጣይቱን  ፎቶ በምታሽከረክሩት ባለሦስት እግር ባጃጅ ላይ ለጥፋችኋል የተባሉ አሽከርካሪዎች እየታሰሩ መሆኑ ተገለፀበአዲስ አበባ ቦ...
01/14/2023

በአዲስ አበባ የአፄ ቴዎድሮስን፣ የአፄ ምኒልክን እና የእቴጌ ጣይቱን ፎቶ በምታሽከረክሩት ባለሦስት እግር ባጃጅ ላይ ለጥፋችኋል የተባሉ አሽከርካሪዎች እየታሰሩ መሆኑ ተገለፀ

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ስሙ ገርጂ አከባቢ የአፄ ቴዎድሮስን እና የአፄ ምኒልክን እንዲሁም የእቴጌ ጣይቱን ፎቶ በምታሽከረክሩት ባለሦስት እግር ባጃጅ ላይ ለጥፋችኋል የተባሉ አሽከርካሪዎች እስከ ንብረቶቻቸው እየታሰሩ መሆኑን ከእስር ያመለጡ አሽከርካሪዎች ገለፁ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ፖሊሶች በወረዳው ገርጂ ኮንዲሚኒየም ወደ ወረገኑ ስምሪት የተሰጣቸው አሽከርካሪዎችን በምታሽከረክሩት ባለ ሦስት እግር ባጃጅ ላይ የአፄ ቴዎድሮስን እና የአፄ ምኒልክን እንዲሁም የእቴጌ ጣይቱን ፎቶ ለጥፋችኋል በሚል ነው የእስር ዘመቻውን የጀመሩት ተብሏል።

ከሳምንት በፊት 15 አሽከርካሪዎች እስከሚያሽከረክሩት ባለ ሦስት እግር ባጃጅ በክፍለ ከተማው ወረዳ 13 ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ ሲሆን ከእስር ለመፈታት እያንዳንዳንቸው ከአምስት ሺ እስከ አስር ሺ ብር እንዲከፍሉ መጠየቃቸውንም ተናግረዋል።

"ከአምስት ሺ እስከ አስር ሺ ብር የተጠየቁትን ገንዘብ የቻሉ ከፍለው እስከ ንብረቶቻቸው ከእስር ተለቀዋል፣ በዘመድ ከእስር እንዲፈቱ የተደረጉም አሉ" የሚሉት አሽከርካሪዎቹ ነገር ግን የተጠየቁትን መክፈል ላልቻሉ ንብረቶቻቸው እንደሚወረስባቸው ማሳሰቢያ ተሰቷቸዋል ብለዋል።

በአከባቢው አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች "የእስር ዘመቻው እንደቀጠለ ነው፡ የነገስታቱን ፎቶ ለጥፋችኋል የተባሉ ሌሎች በርካታ የባጃጅ አሽከርካሪዎችም የእስር ማደኛ ወጥቶባቸው እየተሳደዱ ነው" ያሉ ሲሆን በተለይ የአፄ ቴዎድሮስ እና የአፄ ምኒልክን እንዲሁም የእቴጌ ጣይቱን ፎቶ የለጠፉ ተሽከርካሪዎች ወደ ስምሪት እንዳይገቡ ጥብቅ ክልከላ እንደተጣለባቸው ተናግረዋል።

የባለ ሦስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎቹ፡ የአርቲስቶችን ጨምሮ የተለያዩ ፖለቲከኞችን እና የኳስ ተጫዋቾቾን ፎቶ በተሽከርካሪዎቻቸው ላይ የለጠፉ በርካታ አሽከርካሪዎች በአከባቢው አገልግሎት እየሰጡ ነው ያሉ ሲሆን ከነዚህ መካከል ግን የነገስታቱን ፎቶ የለጠፉ አሽከርካሪዎችን ለብቻ ለይቶ ማሰር እና ማሳደድ እንዲሁም ከስምሪት ማስወጣት አግባብነት የለውም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዳር ድንበር እና ሉአላዊነት እንዳይደፈር ለነፍሳቸው ሳይሰስቱ ትልቅ ዋጋ የከፈሉ የሀገር ባለውለታዎችን በህግ ማስከበር ስም የሚያንኳስሱ አካላት ምን ያህል ስር የሰደደ ጥላቻ እንዳለባቸው ማሳያ ነው ሲሉም አሽከርካሪዎቹ አስተያየታቸውን ሰተዋል የአማራ ድምፅ ዘግቧል።

የአማራ ልዩ ሃይል ከሽሬ እና አካባቢው መውጣቱን መከላከያ አስታወቀ ህወሃት በአጉላ ካምፕ የመጀመሪያ ዙር ከባድ መሳሪያዎችን ማስረከቡን ተከትሎም የአማራ ልዩ ሃይል ከሽሬ ወጥቷል ተብሏል። የ...
01/13/2023

የአማራ ልዩ ሃይል ከሽሬ እና አካባቢው መውጣቱን መከላከያ አስታወቀ

ህወሃት በአጉላ ካምፕ የመጀመሪያ ዙር ከባድ መሳሪያዎችን ማስረከቡን ተከትሎም የአማራ ልዩ ሃይል ከሽሬ ወጥቷል ተብሏል።

የአማራ ልዩ ሃይል ከሽሬ እና አካባቢው እንዲወጣ መደረጉን የመከላከያ ሰራዊት ገልጿል።

በከላከያ ሰራጽ በፌስቡክ ገፁ ባወጣው መግለጫ "በሽሬ እና አካባቢው በግዳጅ ላይ የቆየው የአማራ ልዩ ሀይል ሽኝት ተደርጎለታል" ብሏል።

የአማራ ልዩ ሃይል በሽሬና አካባቢው በግዳጅ ላይ ተሰማርቶ ስለመቆየቱ ከዚህ በፊት በመንግስት ሲነገር አልተደመጠም።

የመከላከያ ሚኒስቴር በመግለጫው የአማራ ልዩ ሃይል ከሽሬ የወጡት በሰላም ስምምነቱ መሰረት መሆኑን ጠቁሟል።

ከሁለት ወራት በፊት የፌዴራል መንግስትና የህወሃት አመራሮች በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በደረሱት የሰላም ስምምነት "የውጭ ሃይሎች" ከትግራይ የሚወጡበት ሁኔታን ለማመቻቸት ተስማምተዋል።

የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ወደ መሬት ለማውረድ የፌደራል መንግስቱ እና የህወሃት ወታደራዊ አመራሮች በኬንያ ናይሮቢ በተፈራረሙት ሰነድም ይሄው ነጥብ ተሰምሮበታል።

በስምምነቱ ህወሃት ከባድ መሳሪያዎችን ማስረከብ ሲጀምር የውጭ ሃይሎችም ከትግራይ እንዲወጡ እንደሚደረግ ተጠቅሷል።

በዚህም መሠረት ህወሃት ከትናንት በስቲያ የመጀመሪያ ዙር ከባድ መሳሪያዎችን አስረክቧል።

ህወሃት ከመቀሌ በ36 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አጉላ ካምፕ ነው የአፍሪካ ህብረት ታዛቢዎች በተገኙበት ከባድ መሳሪያዎችን ያስረከበው።

ይህን ተከትሎም "የኢትዮጵያ መንግስት በሽሬ እና አካባቢው ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ተሠልፎ ሀገራዊ ተልዕኮን ሲፈፅም የነበረው የአማራ ክልል ልዩ ሃይል በስምምነቱ መሠረት ከቀጠናው እንዲወጣ አድርጓል" ብሏል የመከላከያ መግለጫ።

የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ እና የዕዝ አመራሮች በተገኙበት የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ሽኝት እንደተደረገለትም መከላከያ ሰራዊት ገልጿል።

የልዩ ሃይሉ አመራሮች "እስካሁን የከፈልነው ዋጋ ለጋራ ሠላማችን ስንል ነውና በመንግስት ትዕዛዝ መሠረት በተደረሰው የሠላም ስምምነት ሃይላችንን ከሽሬ እና አካባቢው እያሥወጣን ነው" ማለታቸውም ተገልጿል።

“እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ የአገሪቱን እና የዜጎችን ወቅታ ሁኔታ ግምት ዉስጥ ያላስገባ ነዉ።“:-የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋምበአዲስ አበባ ዙሪያ ህገ-ወጥ ናቸዉ የተባሉ ቤ...
01/13/2023

“እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ የአገሪቱን እና የዜጎችን ወቅታ ሁኔታ ግምት ዉስጥ ያላስገባ ነዉ።“:-የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም

በአዲስ አበባ ዙሪያ ህገ-ወጥ ናቸዉ የተባሉ ቤቶች በዘመቻ መልክ እየፈረሱ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሀይሌ በአዲስ አበባ ዙሪያ እና ቡራዩ አካባቢ ቤት እየፈረሰባቸዉ ያሉ በርካታ ዜጎች ወደ ተቋሙ እየመጡ እንደሆነ ለአሐዱ ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

“ተቋማችን ሕገ-ወጥነትን አያበረታታም!“ ያሉት ዶክተር እንዳለ፤ አሁን እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ ወቅታዊ ሁኔታን ታሳቢ ያደረገ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

“ጉዳዩን በሕገ-ወጥነት መነጽር ብቻ መመልከት አግባብ አይደለም” ያሉት ዋና እንባ ጠባቂዉ፤ “የበአል ወቅት እንደመሆኑ በርካታ ተፈናቃዮች በተለያዩ ክልሎች እንደመኖራቸዉ እና ወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ በዘመቻ መልክ ይህን ለመፈጸም አስቻይ አይደለም” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

አክለዉም ”የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ቤት የማፍረስ ዘመቻዉን ከማካሄዳቸዉ በፊት ጊዜዉ አስቻይ ነዉ ወይ የሚለዉን ማየት ነበረባቸዉ“ ብለዋል፡፡

“ሰዎች ሕገ-ወጥ አሊያም ሕግን ባልተከተለ መንገድ ቤት ከገበሬ ላይ የሚገዙበትን ምክንያት የመንግስት አካላት ሊያጤኑት ይገባል” ያሉት ዋና ዳሬክተሩ፤ “የመሬት ፖሊስን በቂ የቤት አቅርቦት እና ተደራሽነት መኖር እና የቤት ሽያጭ ስርዓቶች በሕግ መእቀፍ ዉስጥ ያሉ ናቸዉ ወይ የሚለዉን ከግምት በማስገባት ማስተካከያዎችን መዉሰድ አለባቸዉ” ሲሉ አጽኖት ሰጥተዋል።

የቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ የልጅ ልጅ የልዕልት ሰብለ ደስታ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመበበጎ አድራጎት ሥራቸው የሚታወቁት የቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ የልጅ ልጅ የልዕልት ሰብለ ደስታ ሥርዓተ ቀብር በት...
01/13/2023

የቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ የልጅ ልጅ የልዕልት ሰብለ ደስታ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

በበጎ አድራጎት ሥራቸው የሚታወቁት የቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ የልጅ ልጅ የልዕልት ሰብለ ደስታ ሥርዓተ ቀብር በትናንትናው ዕለት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

በሥርዓተ ቀብሩ ላይም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የንጉሣውያን ቤተሰቦች እና ወዳጆች ተገኝተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ልዕልት ሰብለ ደስታ ለአገር ያበረከቱትን በጎ ተግባራት ገልጸው ያመሰገኑ ሲሆን፤ ለቤተሰቦዎቻቸውም መጽናናትን መመኘታቸውን ከኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

በዕለቱም የልዕልት ሰብለ ደስታ የሕይወት ታሪክ በንባብ የተሰማ ሲሆን፤ ልዕልት ሰብለ ደስታ ከልዕልት ተናኜወርቅ ኃይለ ሥላሴ እና ከራስ ደስታ ዳምጠው ነሐሴ 26 ቀን 1923 በአዲስ አበባ መወለዳቸው ተነግሯል።

በሕይወት ዘመናቸው ለአገርና ለቤተክርስቲያን የሚጠቅሙ በጎ ተግባራትን መፈጸማቸው የተነገረላቸው ልዕልት ሰብለ ደስታ እንደ አያታቸው እቴጌ መነን እና እንደ እናታቸው ልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለ ሥላሴ፣ ሴቶችን በባልትና ትምህርት እና በራስ ዕገዛ ሥራዎች ያሳተፈውን የኢትዮጵያ ሴቶች በጎ አድራጎት ድርጅትን በፕሬዝደንትነት አገልግለዋል።

በእነዚህም ወቅት ለድርጅቱ ገቢ ማስገኛ ዘመናዊነቱ እስከዛሬ የዘለቀውን አዲስ አበባ ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘውን ሕንጻ ማስገንባታቸውም ተገልጿል።

Address

Boston, MA
02110

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wollega Amharan Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Wollega Amharan Association:

Share