አማራ ታሪኩን በልጆቹ ይፅፋል _Ethiopia

አማራ ታሪኩን በልጆቹ ይፅፋል _Ethiopia ይህ ፔጅ የተቋቋመበት አላማ በየቦታው በግፍ እየተሰቃየ ላለው የአማራ ህዝብ እንዲሁም ድምፅ ሚሆናቸው ላጡ ኢትዮጵያዊያን ድምፅ ለመሆን ነው።

14/03/2026
ዘወትራዊ የሆነው የሀይል ግንባታ ስራችን በድርጅታችን አፋብን ውስጥም ከእስከዛሬው በላቀ ሁናቴ እየተከናወነ ነው።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።አረመኔው አገዛዝ በ...
13/03/2026

ዘወትራዊ የሆነው የሀይል ግንባታ ስራችን በድርጅታችን አፋብን ውስጥም ከእስከዛሬው በላቀ ሁናቴ እየተከናወነ ነው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አረመኔው አገዛዝ በቅዠት ዓለሙ ዋሻ ፈልፍለው ገብተዋል፣ ገዳም ተሸሽገዋል፣ የቀሩን ትቂቶች ናቼው፣ ሰማዩም ምድሩም የኔ ነው እያለ ሀሳዊ ወሬውን በሚነዛበት በዚ ሰዓት ሀገር ሲሰራ ሀሳብ፣ሀገሬ በፋሽት ስትወረር ህይወት በተገበረበት፣ሰጋዊነትን ከመንፈሳዊነት አስተባብረው በያዙ ባለብዙ ፀጋወች ምድር ዲማ፣ለምጨና ሶማ አካባቢ ምኒልክ ዕዝ፣አሳምነው ዕዝ እና ቴወድርስ ዕዝ 64ኛ ክፍለ ጦር በጋራ ለ6 ወራት ያሰለጠኗቼውን 2000(ሁለት ሺህ)ኮማንዶ ዛሬ መጋቢት 4/07/2018 ዓ.ም አስመርቋል።

ለ6ወራት ያሰለጠነው የኮማንዶ ኃይል ብቸኛ ጠላቱ አረመኒያዊ አገዛዙ ብቻ መሆኑን ጠንቅቆ የሚረዳ ለሁሉም የሰው ልጆች ፀር ከሆነው ስርዓት ውጭ ለማንም ስጋት የማይሆን ዛሬ በየ ደጃችን የገባውን አራዊት ሰራዊት ነጻ ማውጣትን ብቻ ግቡ ያደረገ ሳይሆን ከሚገባቼው ሌሎች ወገኖቻችን ጋር በምንመሰርተው ሀገረ መንግስት ልክ የተሰራ በአካል የበቃ በአዕምሮ የዳበረ ነው።

ለዛሬ ምርቃት የበቁት ልጆች ከሁሉም በላይ በድሮን፣ጀት፣መድፍ እና መሰል የጠላት መራወጥ ውስጥ ያለፉ ሁኔታ የፈተናቼው፣ ብአዴን ለዘመናት ያጠረውን የጎጃም፣ጎንደር፣ሸዋና ወሎየነት አጥር በመስበር ወንዝ የማይከፍለውን፣ተራራ የማይጋርደውን አድማሳዊ የሆነውን አማራ በትክክል የሚወክሉ ከሶስቱ ክፍለ ሀገር ብቻ ሳይሆን ጅማና ወለጋ፣መተከልና ሐዋሳ ድረስ በመምጣት የሰለጠኑ መሆናቼው ልዩ ያደርጋቼዋል።

የሀይል ግንባታ ስራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!!! መረጃው የአርበኛ እሸቱ ጌትነት ነው

የአማራ ሕዝብ አንድነት – የህልውና፣ የፖለቲካ እና የታሪክ ጉዳይበዘመናት ሁሉ የታየው የፖለቲካ እውነት አንድ ነው፤ የተባበረ ሕዝብ ያሸንፋል፤ የተከፋፈለ ሕዝብ ግን ይወድቃል። ይህ እውነት ...
10/03/2026

የአማራ ሕዝብ አንድነት – የህልውና፣ የፖለቲካ እና የታሪክ ጉዳይ

በዘመናት ሁሉ የታየው የፖለቲካ እውነት አንድ ነው፤ የተባበረ ሕዝብ ያሸንፋል፤ የተከፋፈለ ሕዝብ ግን ይወድቃል። ይህ እውነት በታሪክ፣ በጦርነት፣ በፖለቲካ እና በህዝብ እንቅስቃሴ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ ታይቷል።
ዛሬ የአማራ ሕዝብ በታሪኩ ውስጥ ከባድ የፖለቲካ እና የደህንነት ፈተና አጋጥሞታል። በብዙ አካባቢዎች በዘር መሰረት ጥቃት፣ መፈናቀል፣ ንብረት ጥፋት እና የሕይወት ኪሳራ ተከስቷል። ነገር ግን ይህን ችግር የሚያበዛው ውጭ ጠላት ብቻ አይደለም፤ የውስጥ መከፋፈል እንጂ
እኛ በፖለቲካ፣ በድርጅት፣ በአካባቢ ወይም በሃሳብ እየተከፋፈልን እንገኛለን። ግን ጠላቶቻችን ሲገድሉን ወይም ሲያጠቁን እነዚህን ልዩነቶችን አያዩም። ለእነርሱ እኛ ሁሉ አማራ ነን። ስለዚህ እኛ እርስ በርሳችን መከፋፈል የለብንም፤ ዋና ጉዳያችን ላይ ማተኮር አለብን።

የዘር ጥቃት በዓለም ታሪክ

በዓለም ታሪክ ብዙ ሕዝቦች በዘር መሰረት ጥቃት ገጥሟቸዋል። አንዳንዶቹ በአንድነት ቆመው ተቋቁመዋል፤ አንዳንዶቹ ግን በመከፋፈላቸው ታላቅ መከራን ተቀብለዋል።
1. የኩርድ ሕዝብ
የኩርድ ሕዝብ ከ40 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ቢኖረውም አንድ አገር የለውም። እነሱ በቱርክ፣ በኢራቅ፣ በሶርያ እና በኢራን ውስጥ ተከፋፍለው ይኖራሉ። ይህ የፖለቲካ መከፋፈል እና የውስጥ ክፍፍል ግጭት ብዙ ጊዜ ኃይላቸውን አዳክሞታል።
በ1988 በኢራቅ ውስጥ የተካሄደው አንፋል ዘመቻ ብዙ ኩርዶች እንዲገደሉ እና መንደሮቻቸው እንዲወድሙ አደረገ። ይህ ታሪክ አንድ ትምህርት ይሰጣል፤ ሕዝብ በተከፋፈለ ጊዜ ለጥቃት ቀላል ይሆናል።

2. በሩዋንዳ የተከሰተው የዘር ግድያ
በ1994 በሩዋንዳ የተከሰተው የዘር ግድያ በ100 ቀናት ውስጥ ከ800,000 በላይ ሰዎች እንዲገደሉ አደረገ። ይህ የዘር ፖለቲካ እና የማህበረሰብ መከፋፈል ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ አሳይቶን አልፏል።

3. በቦስኒያ የተከሰተው ግጭት
በ1990ዎቹ በቦስኒያ ውስጥ የተከሰተው የዘር እና የሀይማኖት ግጭት ብዙ ሕዝብ እንዲጠፋ አደረገ። እንዲሁም ብዙ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቀሉ።

የአንድነት ኃይል
በተቃራኒው ግን በአንድነት የቆመ ሕዝብ ብዙ ጊዜ ታላላቅ መንግስታትን ግዙፍ ኃይልን አሸንፏል።
የቬትናም ሕዝብ በአንድነት ቆሞ ከታላቅ የጦር ኃይል ጋር ተዋግቶ አሸነፈ።
የአልጄሪያ ሕዝብ በአንድነት ቆሞ ከኮሎኒያል ኃይል ነፃ ሆነ።
ደቡብ አፍሪካ ሕዝብ በአንድነት ተባብሮ የአፓርታይድ ስርዓትን አፈረሰ።
እነዚህ ሁሉ አንድ ነገር ያሳያሉ፤ አንድነት ያለው ሕዝብ የትኛውንም ኃይል ሊያሸንፍ ይችላል።

ለአማራ ሕዝብ የሚያስፈልጉ መፍትሄዎች
1. የውስጥ አንድነት መገንባት
ከፖለቲካ ወይም ከድርጅት ልዩነት በላይ የሕዝብ ደህንነት መሆን አለበት።

2. የጋራ ፖለቲካ እና የጋራ አጀንዳ
የአማራ ሕዝብ ዋና አጀንዳ መሆን ያለበት፦
የሕዝብ ደህንነት
ፍትሕ
ፖለቲካዊ መብት
ኢኮኖሚያዊ ልማት

3. የዲያስፖራ ኃይል
በዓለም ዙሪያ ያሉ አማራዎች በሚዲያ፣ በዲፕሎማሲ እና በኢኮኖሚ ትልቅ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ ይህን ተገንዝበን የሚመለከተን አካላት ሁሉ ይህ እንዲሆን መስራት።

4. የጋራ ተቋማት መገንባት
ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ድርጅቶች በአንድ ዓላማ መስራት አለባቸው።

መደምደሚያ
ዛሬ የአማራ ሕዝብ የገጠመው ፈተና ቀላል አይደለም። ግን ታሪክ ያሳያል፤
አንድነት ያለው ሕዝብ ማንም ኃይል ሊያሸንፈው አይችልም፤ የተከፋፈለ ሕዝብ ግን ለጥቃት ቀላል ይሆናል።
ስለዚህ ዛሬ የአማራ ሕዝብ ትልቁ ተግባር ይህ መሆን አለበት፦
አንድ መሆን፣ ዋና ጉዳዮች ላይ መተኮር እና የሕዝቡን ህልውና መጠበቅ።

ያሬድ ብርሀኑ

09/03/2026

Title: Exclusive Interview | Yared Birhanu on Amhara, Ethiopia’s Politics & the Need for Peaceful DialogueDescription:In this exclusive interview, Free Press...

26/09/2025

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

በ6ኛ ክፍለጦር እና 1ኛ ክፍለጦር  በሚተዳደሩ ነፃቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይቶች እየተደረጉ ነው። ነሀሴ 25/2017ዓ.ም
03/09/2025

በ6ኛ ክፍለጦር እና 1ኛ ክፍለጦር በሚተዳደሩ ነፃቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይቶች እየተደረጉ ነው።
ነሀሴ 25/2017ዓ.ም

26/08/2025

ከግዳጅ ተመልሰናል
አማራ እንቁ ህዝብ ነው ለዚህዝብ ልንሞት ዱርቤቴ ካልን ሁለት አመት አልፎናል። ፋኖ እያላችሁ ድጋፋችሁን አሳዩ

Address

Johannesburg

Telephone

+27781380526

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አማራ ታሪኩን በልጆቹ ይፅፋል _Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to አማራ ታሪኩን በልጆቹ ይፅፋል _Ethiopia:

Share