03/03/2020
yes we can!
የሕዳሴ ግድቡ የውሃ ሙሌት በመጪው ክረምት እንደሚጀመር የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ
*******************
በመጪው ክረምት በሕዳሴ ግድቡ የውሃ መሙላት እንደሚጀመር እና የግድቡ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ መሰረት እንደሚቀጥል የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በግድቡ ሁለት ተርባይኖች የሚጀመረው የቅድመ ሀይል ማመንጨት ስራም በተያዘለት እቅድ መሰረት እንደሚጀመርም አስታውቀዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ እና ሂደት እንዲሁም የድርድር ሁኔታ ላይ በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት መግለጫ ተሰጥቷል፡፡
በመግለጫው ላይ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው አሜሪካ የግድቡን ሙሌት በተመለከተ ያወጣችው መግለጫ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
አሜሪካ የተፋሰሱ አገራት በራሳቸው ወደ ስምምነት እንዲደርሱ ግፊት በማድረግ በጎ ሚናዋን ብቻ እንድትወጣ ኢትዮጵያ እንደምትፈልግ እና በሌላ ተፅዕኖ የሚሆን ነገር እንደሌለም ሚንስትሩ አረጋግጠዋል።
በእዮብ ሞገስ