Hope 4 Peace

Hope 4 Peace ተስፋ ለሰላም | Hope for Peace

ህዝቢ ኣብ ልዕሊ ህዝቢ ክዘምት ዝግበር ዘሎ ዳግማይ ሽርሒ ክፈሽል ይግባእ!ካብ ተስፋ ንሰላም ዝተዋህበ መግለጺዕለት 23 መጋቢት 2016 ዓ.ምቀዳማይ ሚኒስተር ኣብይ ኣሕመድ ናብ ስልጣን ካብ ...
04/05/2024

ህዝቢ ኣብ ልዕሊ ህዝቢ ክዘምት ዝግበር ዘሎ ዳግማይ ሽርሒ ክፈሽል ይግባእ!
ካብ ተስፋ ንሰላም ዝተዋህበ መግለጺ

ዕለት 23 መጋቢት 2016 ዓ.ም

ቀዳማይ ሚኒስተር ኣብይ ኣሕመድ ናብ ስልጣን ካብ ዝመፅእ ንዳሓር ኣብ ኢትዮጵያ ብኣሽሓት ዝቁፀሩ ጎንፅታት ተፈጢሮም እዮም። ኣብ ሰሜናዊ ክፋል ሃገርናን ኣብ ክልል ኦሮሚያን ከቢድ ህልቂት ዘስዐቡ ኲናት ተኻይዶምን ይካየዱን ኣለዉ። ኣብቲ ቅድሚ ሓደ ዓመት ብስምምዕ ሰላም ፕሪቶርያ ደው ዝበለ ክልላት ኣምሓራን ዓፋርን ሓዊሱ ብቐንዱ ኣብ ትግራይ ብዝተኻየደ ኲናት ኣብ ታሪኽ ሃገርና ተራእዩ ብዘይፈልጥ መልክዑ ልዕሊ 1 ሚልዮን ዜጋታት ከም ዝሞቱን ልዕሊ 4 ሚልዮን ዝኾኑ ድማ ካብ መንበሪኦም ከም ዝተመዛበሉን ይግመት።

እዞም ውግኣት ብቐንዱ ኣብ መንጎ መንግስትን ተቓወምቲ ፖለቲካዊ ሓይልታትን ዝካየዱ እካ እንተኾኑ ካብ ዝሓለፈ ታሪኽና ብዝተፈለየ መንገዲ ግን እቶም ጎንፅታት ኣብ መንጎ ህዝቢ ንህዝቢ ዝኾኑሉ ኣጋጣሚታት ተራእዩ እዩ። ብፍላይ ኣብ ትግራይ ኣብ ዝተኻየደ ኲናት ንዘበናት ብሰላማዊ ጉርብትናን ሕውነትን ተኣሳሲሮም ይነብሩ ዝነበሩ ህዝብታት ኣምሓራን ትግራይን ሰለባ እቲ ጎንፂ ኾይኖም። ቐንዲ ምኽንያት ምስረታ ዉዳበ ተስፋ ንሰላም እዚ ኩነታት እዚ ዝፈጠሮ ዓብይ ስግኣት እዩ።

ተስፋ ንሰላም እዞም ነዊሕ ግዘ ዘቑፀረ ናይ ሓባር ታሪኽ፣ ባህሊ፣ ስነ-ልቦናን መንነትን ዝካፈሉ ህዝብታት ኣብ መንጎኦም ዝኾነ ይኹን ዓይነት ጎንፅን ፍልልይን እንተሃለወ እኳ ዳግማይ ናብ ውግእ ክኣትውን ደም ክፋሰሱን ኣይግባእን ዝብል ፅኑዕ እምነት ብምሓዝ ኣብ መንጎ ክልቲኦም ህዝብታት ዘሎ ሰላማዊ ርክብ ንምጥንኻር ዓሊሙ ዝተመስረተ እዩ።

ምፍራም ስምምዕ ሰላም ፕሪቶሪያ ምስ ብዙሕ ጉድለታቱ እንተኾነ እውን ውግእ ደው ካብ ምባል ሓሊፉ ንምስኻዕ ዕላማ ውዳበና እውን ፅቡቅ ዕድል ክፈጥር ከም ዝኽእል ብምሕሳብ ደጊፍናዮ ኢና፡፡ኣብ ክልላት ኣምሓራን ኦሮምያን ተመሳሳሊ ስምምዕ ሰላም ተፈሪሙ አብ ዉሽጠን ዝካየድ ዘሎ ኩናት ደው ክብል እዩ ዝብል ትፅቢት እውን ነይሩና። ይኹን እምበር ተጀሚሩ ዘሎ ሰላም ክጠናኸርን ክሰፍሕን እዩ ኢልና ተስፋ ኣብ ዝገበርናሉ ኣብዚ ሐዚ ግዘ ህዝቢ ትግራይን ኣምሓራን ናብ ዝላዓለ ህልቂት ዘእቱ ደበና ኲናት የንፀላሉ ክምዘሎ ንዕዘብ ኣለና ፡፡

ቅድሚ ሐዚ እውን እንተኾነ እቲ ኣዕናዊ ኲናት ዝተጀመረ ድሕሪ ናይ ቃላት ጦርነት እዩ፣ ኣብዚ ቀረባ ግዜ ዝወፁ ዘለዉ ሃይለ ቃል ዝተመልኦም መግለፅታት እውን ካሊእ ከቢድ ህልቂት ኣብ ቅድሜና ከም ዝተሃቀነ ዘመላኽት ስግኣት ፈጢሩልና ኣሎ፡፡ ከም እምነት ውዳበና ይትረፍ ካልኣይ ዙር ኲናት ምውላዕ እቲ ናይ ዝሓለፈ ኲናት እውን ትርጉም ኣልባን መሰረታዊ ጥፍኣት ዘስዓበን ታሪኻዊ ስሕተት እዩ፡፡ ኲናት እቲ ገዛኢ ሓይሊ ስልጣኑ ንምንዋሕ ዝጥቀመሉ ኣማራፂ እምበር ናይ ህዝብታት ረብሓን ድሌትን ዘየማልእ ብምኻኑ እዚ ምዕራፍ እዚ ክዕፆ ይግባእ፡፡ ስለዝኾነ ህዝብና፦

ቀዳማይ፦ ኣብ ሰሜናዊ ክፋል እታ ሃገር ዝርከቡ ህዝብታት ነንሕድሕዶም እናዋግኡ ብምድኻም ዕድመ ስልጣን ምንዋሕ ቀንዲ ዕላማ እዚ ስርዓት ምዃኑ፤

ካልኣይ፦ ኣብ ቀረባ ግዘ ዝተፈጠረ ልውውጥ ሃይለ-ቃል ድሌታት እቲ ስርዓት ንምዕዋት ኮነ ኢልካ ዝተፈጠረ ውዲት ምዃኑ፤

ሳልሳይ፦ ካብ ሕሉፍ ጌጋታት ብዘይምምሃር ኣብ መፃወድያ ውዲት እቲ ስርዓት ብምውዳቅ ንዳግማይ ኲናት ምልዕዓል ካሊእ ታሪኻዊ ስሕተት ከም ዝኸውን፤

ራብዓይ፦ ድሕሪ ሐዚ ካልእ ንክልቲኡ ህዝብታት ዘሳትፍ ኲናት ዝገደደ ህልቂት ከስዕብ ጥራይ ዘይኮነስ ንመላእ ሃገርን ህላወ ህዝብን ኣብ ሓደጋ ዘእቱ ምዃኑ፤

ሓምሻይ፦ ኣብ መንጎ ክልቲኡ ህዝብታት ዘሎ ዘይምርድዳእ ብሰለማዊ፣ ሕጋውን ዴሞክራስያውን መንገዲ ካብ ምፍታሕ ወፃኢ ብኲናት ዘላቒ መፍትሒ ክመፅእ ከምዘይኽእል ብምግንዛብ ነቲ በቲ ስርዓት ተወጢኑ ዘሎ ኲናት ናይ ምልዕዓል ውዲት ብብቕዓት ከፍሽሎ ይግባእ።

ንክልቲኡ ህዝብታት ንውክል ኢና እትብሉ ፖለቲካዊ ሓይልታት፣ ጋዜጠኛታት፣ ነጠፍቲ ማሕበራዊ ሚዲያን ካልኦት ፅዕንቶ ፈጠርቲ ኣካላትን ንህዝባዊ ረብሓን ደሕንነትን ተገደስቲ እንተኾይንኩም፡ ኣብ ክንዲ ግዳይ ሽርሒ እቲ ስርዓት ብምዃን ኲናት ምልዕዓል ኣብ መንጎ ክልቲኡ ህዝብታት ዝነበረ ሰለማዊ ዝምድና ናብ ንቡሩ ንምምላስ በርቲዕኹም ክትሰርሑ ይግባእ ኢልና ንኣምን፣ ብጥብቂ እውን ነዘኻኽር። ብዝኾነ ይኹን ዕላማ ሓደ ህዝቢ ኣንፃር ካሊእ ህዝቢ ንክዘምት ምልዕዓል ፀረ-ህዝብነተ እምበር ሓልዮት ክኸውን ኣይኽእልን። ድሌት ህዝቢ ዘላቒ ዝኾነ ሰላም፣ ዴሞክራስን ልምዓትን እምበር ጎንፅን ኲናትን ኣይኮነን።

ስለዝኾነ ድማ ስምምዕ ሰላም ፕሪቶሪያ ዘለውዎ ጉድለታት ብምምላእ ዘላቒ ፍታሕ ብዘምፅእ መንገዲ ክጠናኸር ይግባእ እምበር እቲ ስምምዕ ኣፍሪስካ ናብ ካሊእ ኣዕናዊ ኲናት ምእታው ግቡእ ኣይከውንን። ልዕሊ ማንም ወናኒ እዛ ሃገር ዝኾነ ህዝቢ “ካብ ሕዚ ኲናት ይኣክል!” ብምባል ናይዚ ስርዓት ሽርሕን ውዲትን ንከፍሽል ተስፋ ንስላም ፃዊዒታ ተቕርብ፡፡

ተስፋ ንሰላም፣ ሰሜን አሜሪካ
ሰላም ንህልውናና!

Web page: https://h4peace.org/ti/
Twitter page: https://Twitter.com/Hope4Peace2023

ንሰላምን ሕብረትን ድልድላት ንስራሕ ርኸቡና ብታሪኽ ዘይተራእየ ዘሕዝን ምዕራፍ ዓሚቝ ብሄራዊ ምፍልላይ ኣብ መንጎ እቶም ንዘመናት ሕውነት ዝነበሮም ማሕበረሰባት ልዑል ዘይምትእምማን ...

The Regime's Plot to Start Another Inter-Community War Must Be Thwarted! A Statement from Hope for Peace April 1, 2024Si...
04/03/2024

The Regime's Plot to Start Another Inter-Community War Must Be Thwarted!
A Statement from Hope for Peace

April 1, 2024

Since Prime Minister Abiy Ahmed came to power in 2018, thousands of clashes have occurred throughout Ethiopia. In the northern part of our country and further south in the Oromia region, many deadly wars have been fought; some are still ongoing. In the wars that took place in northern Ethiopia, primarily in Tigray, but also in the Amhara and Afar regions, and which stopped a year ago following the Pretoria Peace Agreement, more than 1 million people are believed to have perished, and more than 4 million people have been displaced from their homes.

Although these wars were waged mainly between the government and rival political forces, unlike in our history, they quickly morphed into people-to-people conflicts. In the Tigray war, in particular, the Amhara and Tigray peoples, who for centuries have lived together in peace and harmony as neighbors and children of one country, took opposite sides and fought a bloody war. Hope for Peace was created due to the existential threat to the two communities this fact brought.

Hope for Peace was established with the firm belief that these two communities who share a long history, culture, beliefs, and identity should not fight and shed blood again regardless of any contradictions and differences that may come between them. Our group also aims to strengthen the peaceful co-existence and relationship between these two peoples.

Despite its shortcomings, we supported the Pretoria Peace Agreement thinking that it would not only stop the war, but also create a conducive environment to achieve our objectives. We also thought that similar peace agreements would be signed in the Amhara and Oromia regions to stop the ongoing wars there in these communities. However, at a time when we hoped that peace would be strengthened and expanded, we are observing a dangerous situation developing in which the peoples of Tigray and Amhara could potentially enter yet another war leading to further death and destruction.

Just as the destructive wars of the recent past started with the exchange of words, we fear that the recent inflammatory statements circulating around may be precursors to future hostilities. It is our group’s firm belief that, just as the wars of the past were tragic and historic mistakes, another round of war will also end up the same, this time much worse. Wars cannot achieve the interests and needs of our people other than to temporarily sustain the regime's power. For this reason, we believe, the war option must remain a closed option.

Thus, recognizing that:
1. One of the main objectives of the current regime is to prolong its life by having the people of northern Ethiopia fight against one another and weaken themselves in the process,
2. The recent exchange of hostile words was deliberately created to achieve this regime's dangerous objective,
3. Not learning from past mistakes and falling into the regime's conspiracy traps and starting another round of war would be yet another historic mistake,
4. A new war between the two peoples will not only result in another deadly outcome, but also endanger the very existence of the entire country and its people, and
5. Any disputes between the two peoples can only be resolved through peaceful, legal, and democratic means – and not through wars – we call on the people to resolutely thwart the regime's plot to start war all over again.

Political forces, journalists, social media activists, and other influential groups and individuals who claim to represent the two peoples, and who really care about their interests and security, should work hard to establish and strengthen peaceful relations between these two communities, instead of becoming victims or agents of the regime's plot to instigate more wars. Inciting one people against another for any reason is anti-people by its very nature and cannot be pro-people. What the people want today is a lasting peace, democracy, and development, not conflicts and wars.

We call for the strengthening and implementation of the Pretoria Peace Agreement in a way that will bring about a permanent solution, rather than violating it and entering another round of deadly wars. Hope for Peace makes this call and plea for peace on this occasion and asks the Ethiopian people to just say "enough of war!" and thwart the regime's conspiracy and debauch.

Hope for Peace, North America
Peace for Our Existence!

Website: https://H4Peace.org
Twitter: https://twitter.com/Hope4Peace2023

Building Bridges for Peace and Unity Contact us Unparalleled Tragedy Profound ethnic divisions gave rise to extreme mistrust between communities that once enjoyed brotherly and sisterly relations for centuries. This tragically escalated into wars and devastation on a scale never seen before. Million...

03/31/2024

የአገዛዙ ህዝብን ከህዝብ የማዋጋት ዳግም ሴራ ሊከሽፍ ይገባል!

ከተስፋ ለሰላም የተሰጠ መግለጫ

ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት በኋላ በኢትዯጵያ ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ ግጭቶች ተከስተዋል። በሰሜኑ የአገራችን ክፍልና በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ህዝብ ጨራሽ ጦርነቶች ተካሂደዋል፣ አሁንም በመካሄድ ላይ ይገኛሉ። ከአንድ አመት በፊት በፕሪቶርያው ስምምነት የቆመው የአማራና የአፋር ክልሎችን ጨምሮ በዋናነት በትግራይ በተካሄደው ጦርነት ብቻ በታሪካችን አይተነው በማናውቅ መጠን ከ1 ሚሊየን በላይ የሆነ ህዝብ እንደሞተና ከ4 ሚሊየን የበለጠ ህዝብ ከመኖሪያ ቀየው እንደተፈናቀለ ይገመታል።

እነዚህ ጦርነቶች የሚካሄዱት በዋናነት በመንግስትና በተቀናቃኝ የፖለቲካ ሀይሎች መካከል ቢሆንም ካለፈ ታሪካችን በተለየ መጠንና ሁኔታ ግጭቶቹ የህዝብ-ለህዝብ ግጭት የመሆን አዝማሚያ ሲይዙ ታይቷል። በተለይም በትግራይ በተካሄደው ጦርነት ለዘመናት በሰላማዊ ጉርብትናና በአንድ አገር ልጅነት አብረውና ተዛምደው የኖሩት የአማራና የትግራይ ህዝቦች ጐራ ለይተው የፍልሚያው አካል ሲሆኑ ታይተዋል። ለስብስባችን ተስፋ ለሰላም መመስረት ዋና ምክኒያት የሆነውም ይህ እውነታ የፈጠረው ከፍተኛ ስጋት ነው።

ተስፋ ለሰላም የተቋቋመው እነዚህ የረዥም ጊዜ የጋራ ታሪክ፣ ባህል፣ ስነ-ልቦናና ማንነት ተጋሪ የሆኑ ህዝቦች የትኛውም ዓይነት ቅራኔና ልዩነት በመካከላቸው ቢኖር ዳግም ጐራ ለይተው እርስ-በርስ መዋጋትና ደም መፋሰስ የለባቸውም የሚል ፅኑ እምነት በመያዝና የሁለቱን ህዝቦች ሰላማዊ ግንኙነት ለማጠናከር ነው።

የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት መፈረም ከነጉድለቶቹም ቢሆን ጦርነቱን ከማስቆምም ባሻገር ለስብስባችን ዓላማ መሳካት በጐ ዕድል ሊፈጥር እንደሚችል በማሰብ ደግፈነዋል። በአማራና በኦሮሚያ ክልሎችም ተመሳሳይ የሰላም ስምምነቶች ሊፈረሙና ጦርነቶቹ ሊቆሙ ይችሉ ይሆናል የሚል ግምት ነበረን። ይሁንና የሰላሙ ጅማሮ የበለጠ እየተጠናከረና እየሰፋ ይሄዳል ብለን ተስፋ ባደረግንበት በአሁኑ ወቅት የትግራይንና የአማራን ህዝቦች ለዳግመኛ እልቂት የሚዳርግ ጦርነት እንደገና ሊያገረሽ የሚችልበት አደገኛ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን እየታዘብን ነው።

ቀድሞም ቢሆን አውዳሚው ጦርነት የተጀመረው የኃይለ-ቃል ልውውጥን ተከትሎ ነውና የሰሞኑ የመግለጫ ውዝግብም ሌላ የዕልቂት ድግስ ከፊታችን እየታሰበ እንደሆነ የሚያመላክት ስጋት ፈጥሮብናል። በስብስባችን እምነት እንኳንስ ሌላ ዙር ጦርነት መታሰቡና የበፊቱም ጦርነት እርባና-ቢስና ታሪካዊ ስህተት ነበር። የጦርነት አማራጭ የአገዛዙን የስልጣን ፍላጐት ለጊዜው ከማስጠበቅ አልፎ የማንኛውንም ህዝብ ጥቅምና ፍላጐት ሊያሳካ አይችልምና ምዕራፉ የተዘጋ አማራጭ ሊሆን ይገባዋል። ስለሆነም ህዝቡ-

አንደኛ፦ የሰሜኑን ህዝብ እርስ-በርስ እያዋጉ በማዳከም የስልጣን ዕድሜን ለማራዘም መሞከር የዘመኑ አገዛዝ አይነተኛ ዓላማ መሆኑን፤

ሁለተኛ፦ የሰሞኑ የኃይለ-ቃል ልውውጥ የአገዛዙን የሴራ ፍላጐት ለማሳካት ሲባል ሆን ተብሎ የተፈጠረ መሆኑን፤

ሶስተኛ፦ ካለፈው ስህተት ባለመማር በአገዛዙ የሴራ ወጥመድ ላይ ወድቆ ለሌላ ዙር ጦርነት መነሳሳት ሌላ የታሪክ ስህተት እንደሚሆን፤

አራተኛ፦ ከአሁን በኋላ በሁለቱ ህዝቦች ተሳትፎ የሚካሄድ ሌላ ዙር ጦርነት የባሰ የህዝብ ዕልቂት ከማስከተልም ባለፈ አጠቃላይ አገራዊና ህዝባዊ ህልውናን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን፤

አምስተኛ፦ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያሉ አለመግባባቶች ሰላማዊ፣ ህጋዊና ዴሞክራሲያዊ ከሆነ መንገድ ውጭ በጦርነት ዘላቂ መፍትሄ ሊያገኙ እንደማይችሉ በመገንዘብ የአገዛዙን ሌላ ዙር ጦርነት የመጥመቅ ሴራ ህዝቡ በብቃት ሊያከሽፈው ይገባል።

ሁለቱን ህዝቦች እንወክላለን የምትሉ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ጋዜጠኞች፣ ማህበራዊ አንቂዎችና ሌሎች ተሰሚነት ያላችሁ ስብስቦችና ግለሰቦች በእውነትም ለህዝብ ጥቅምና ደህንነት የምታስቡ ከሆነ የአገዛዙ የሴራ ሰለባ ወይንም ቅጥረኛ በመሆን ጦርነት ከመቀስቀስ ይለቅ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ሰላማዊ ግንኙነት እንዲፈጠርና እንዲጠናከር ጠንክራችሁ መስራት ይገባቹሃል ብለን እናምናለን፣ አበክረንም እናስገነዝባለን:: ለማንኛውም ዓላማ ቢሆን ህዝብ ከህዝብ እንዲዋጋ መቀስቀስ የህዝብ ጠላትነት እንጅ ተቆርቋሪነት ሊሆን አይችልም። ህዝቡ ዛሬ ላይ የሚፈልገው ዘላቂ ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት እንጅ ግጭትና ጦርነት አይደለም።

ስለሆነም የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ጉድለቶቹ ተሟልተው ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት በሚያስችል አግባብ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል እንጅ ስምምነቱን ጥሶ ወደ ሌላ አውዳሚ ጦርነት መግባት ተገቢ አይሆንም። ከማንም በላይ የአገሩ ባለቤት የሆነው ህዝብ “ከእንግዲህ ጦርነት በቃኝ!” በማለት የአገዛዙን ሴራና ደባ እንዲያከሽፍ ተስፋ ለሰላም ጥሪውንና ተማፅኖውን በዚህ አጋጣሚ ያቀርባል።

ተስፋ ለሰላም፣ ሰሜን አሜሪካ
ሰላም ለህልውናችን!

መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም.

Address

San Francisco, CA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hope 4 Peace posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Hope 4 Peace:

Share