Tegbar Organization

Tegbar Organization Bridging the Gap to Quality Healthcare! Tegbar Organization provides essential funding for urgent medical care in Ethiopia. Tegbaraid.org

As a registered 501(c)3 non-profit organization, we rely on your generous support to make an impact.

                   #ጤና      #ጉንፋን
08/19/2026

#ጤና #ጉንፋን

🫁 ጉንፋን ወደ ሳንባ ምች ሊቀየር እንደሚችል ያውቃሉን?🤧 ወይስ ሳንባ ምች መጀመሪያ ላይ ጉንፋን መስሎ ይሆን?❗ ሁለቱም እውነት ሊሆን ይችላል!💡 እንዴት?🦠 አንዳንድ ጊዜ የበሽታ መከላከያ ...
08/18/2026

🫁 ጉንፋን ወደ ሳንባ ምች ሊቀየር እንደሚችል ያውቃሉን?

🤧 ወይስ ሳንባ ምች መጀመሪያ ላይ ጉንፋን መስሎ ይሆን?

❗ ሁለቱም እውነት ሊሆን ይችላል!

💡 እንዴት?

🦠 አንዳንድ ጊዜ የበሽታ መከላከያ አቅማችን ሲዳከም ፤ ተራ ጉንፋን የመሰለን በሽታ የሳንባ ምች ሆኖ ያሰቃየናል!

🤔 ታድያ ምን ያድርጉ? እንዴት ይከላከሉ?
🔎 ታዲያ ሳንባ ምችን ከጉንፋን እንዴት እንለየዋለን?
🚨 የትኞቹ ምልክቶች አስቸኳይ ሕክምና ይፈልጋሉ?
🛡️ ሳንባ ምችንስ እንዴት እንከላከል?

📖 ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ። ምልክቶቹን ይወቁ፤ በጊዜ እርምጃ ይውሰዱ።

https://www.tegbaraid.org/post/pneumonia
#ጤና #ጉንፋን

የሳንባ ምች (Pneumonia) እንደ ጉንፋን በሚመስሉ ምልክቶች ሊጀምር ይችላል። ነገር ግን ኢንፌክሽኑ ወደ ሳንባ ሲደርስ ሳል፣ ትኩሳት፣ የደረት ህመም እና የመተንፈስ ችግር እንዲባባስ ሊያደር.....

🩺 ዓመታዊ የጤና ምርመራ ማለት ብዙ ላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ ማለት ነውን? 🤔🔬 ብዙዎቻችን “ዓመታዊ የጤና ምርመራ” ስንል የኩላሊት፣ የጉበት፣ የልብ፣ የቪታሚን ዲ፣ የታይሮይድ እና ሌሎችንም...
08/15/2026

🩺 ዓመታዊ የጤና ምርመራ ማለት ብዙ ላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ ማለት ነውን? 🤔

🔬 ብዙዎቻችን “ዓመታዊ የጤና ምርመራ” ስንል የኩላሊት፣ የጉበት፣ የልብ፣ የቪታሚን ዲ፣ የታይሮይድ እና ሌሎችንም ምርመራዎች በጅምላ እናደርጋለን።

❓ ይህ በህክምናው ይመከራልን?
⚠️ ብዙ ምርመራ ብዙ ጤና አይደለም!!

📋 አንዳንድ ምርመራዎች በየጊዜው መደረጋቸው አስፈላጊ ሲሆን፤ ሌሎች ግን ምልክት፣ የበሽታ ታሪክ፣ የቤተሰብ ታሪክ ወይም ሌላ የአደጋ ምክንያት ሲኖር ብቻ ሊመከሩ ይችላሉ።

❓ ታድያ የትኞቹን ምርመራ መቼ ያድርጉ?
🧪 በየዓመቱ ማድረግ የማያስፈልግዎ የላብራቶሪ ምርመራዎች ምንድናቸው?

▶️ ለመረዳት ሙሉውን ቪድዮ ይመልከቱ።
📌 ይህን መረጃ ለሚያስፈልገው ሰው ያጋሩ።

https://youtu.be/iIir72OKvIU

#የጤናምርመራ #ጤና

ብዙዎቻችን በየጊዜው የጤና ምርመራ ማድረግ እንፈልጋለን። ግን ትልቁ ችግር ምን ምርመራ ማድረግ እንዳለብን ...

🔨 ቴታነስ በዝገት ይመጣል🦠 ቴታነስ በዝገት ይመጣልን?ይህ የተለመደ ግንዛቤ፤ በብዙዎቻችን አእምሮ የተቀረጸ ነው።🤔 ታድያ በዛገ ብረት የተወጋ ሰው ለምን በቴታነስ ይያዛል?💉 መከላከያውስ ምን...
08/13/2026

🔨 ቴታነስ በዝገት ይመጣል🦠 ቴታነስ በዝገት ይመጣልን?

ይህ የተለመደ ግንዛቤ፤ በብዙዎቻችን አእምሮ የተቀረጸ ነው።

🤔 ታድያ በዛገ ብረት የተወጋ ሰው ለምን በቴታነስ ይያዛል?
💉 መከላከያውስ ምንድነው?
⚠️ የቴታነስ ምልክቶቹስ?

ቴታነስ መንጋጋን እንደሚቆልፍ ያውቃሉ? ምራቅን መዋጥ እንኳን ሊያስቸግር እንደሚችልስ?
👉 እንግዲያውስ ግንዛቤዎን ለማስፋት ፤ ይህንን ትምህርታዊ ጽሑፍ ያንብቡ።

https://www.tegbaraid.org/post/tetanus

#የጤናምክር #ጤና

አንድ ሰው በዛገ ብረት ሲወጋ "ቴታነስ ይይዘዋል" የሚለው የተለመደ ግንዛቤ ፍጹም ስህተት መሆኑን ያውቃሉ? ከዝገቱ ጀርባ ያለውን እውነተኛ ጠላት፣ የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ አስደንጋጭ ምልክ....

የኮሌስትሮል ምርመራ አድርገዋልን? ቁጥሮቹ ምን ማለት እንደሆኑ ያውቃሉን? አስፈላጊ የኮሌስትሮል ምርመራ ቁጥሮች እነሆ!             #ጤና  #ኮሌስትሮል #የልብጤና  #የጤናምክር
08/12/2026

የኮሌስትሮል ምርመራ አድርገዋልን? ቁጥሮቹ ምን ማለት እንደሆኑ ያውቃሉን? አስፈላጊ የኮሌስትሮል ምርመራ ቁጥሮች እነሆ!

#ጤና #ኮሌስትሮል #የልብጤና #የጤናምክር

🩸 ኮሌስትሮል ከፍ ሲል ምን ይሰማዎታል?🤕 ራስ ምታት?😴 ድካም?❤️ የደረት ሕመም?😮‍💨 ትንፋሽ ማጠር?ወይስ… ምንም? 🤔እውነቱ ከሚጠብቁት በጣም የተለየ ሊሆን ይችላል።ምላሹ ያስገርምዎታል… ...
08/10/2026

🩸 ኮሌስትሮል ከፍ ሲል ምን ይሰማዎታል?
🤕 ራስ ምታት?
😴 ድካም?
❤️ የደረት ሕመም?
😮‍💨 ትንፋሽ ማጠር?
ወይስ… ምንም? 🤔
እውነቱ ከሚጠብቁት በጣም የተለየ ሊሆን ይችላል።
ምላሹ ያስገርምዎታል… ያንብቡ! 👇
https://www.tegbaraid.org/post/cholesterol
#ጤና #ኮሌስትሮል #የልብጤና #የጤናምክር

ከፍተኛ ኮሌስትሮል ብዙ ጊዜ ምንም ምልክት ሳያሳይ ለዓመታት ሊቆይ ይችላል። ራስዎን ጤነኛ እየተሰማዎትም ቢሆን ኮሌስትሮልዎ ከፍ ሊል ይችላል። ምልክቶችን ከመጠበቅ ይልቅ ምርመራ ማድ.....

🥩🍟 እንደ ቀይ ሥጋን እና  ቺፕስ ያሉ ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ ለትልቁ አንጀት ካንሰር የመጋለጥ እድልን እንደሚጨምር ያውቃሉ?አዎ! ይህ በሳይንስ የተረጋገጠ ነው።ከዚህ በተጨማሪ ውፍረት፣ ...
08/08/2026

🥩🍟 እንደ ቀይ ሥጋን እና ቺፕስ ያሉ ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ ለትልቁ አንጀት ካንሰር የመጋለጥ እድልን እንደሚጨምር ያውቃሉ?

አዎ! ይህ በሳይንስ የተረጋገጠ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ውፍረት፣ የስኳር ሕመም፣ ወ.ዘ.ተ... የኮሎሬክታል ካንሰር አደጋን ሊጨምሩ ይችላሉ።

ግን መልካሙ ዜና... ❤️

ካንሰር ከመሆኑ በፊት በምርመራ ማግኘትና ቅድመ-ካንሰር እጢውን ማስወገድ ይቻላል።

🤔 እንዴት?
🔎 የምርመራው ዘዴ ምንድን ነው?
📅 ምርመራውን ከስንት ዓመት ጀምሮ ማድረግ አለብን?

👉 ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሱን በቪዲዮው ይመልከቱ።

ምልክት እስኪመጣ አትጠብቁ። ካንሰር ከመሆኑ በፊት ይከላከሉ።

https://youtu.be/F_KhAAHiZyA

#ጤና #ኢትዮጵያ

የትልቁ አንጀት (ኮሎሬክታል) ካንሰርን ምልክቶች ሳያሳይ በፊት መከላከል እንደሚቻል ያውቃሉ? በዚህ ቪዲዮ ...

👂 ሲያወሩ "ምን?"፣ "ድገመው!" ወይም "በደንብ አልሰማሁህም" የሚሉ ቃላትን በተደጋጋሚ ይጠቀማሉ?📺 ሞባይል ሲመለከቱ ወይም ቲቪ ሲያዩ "ድምጹን ቀንስ!" የሚል ቅሬታ ከቤተሰብዎ ወይም ከጓ...
08/05/2026

👂 ሲያወሩ "ምን?"፣ "ድገመው!" ወይም "በደንብ አልሰማሁህም" የሚሉ ቃላትን በተደጋጋሚ ይጠቀማሉ?

📺 ሞባይል ሲመለከቱ ወይም ቲቪ ሲያዩ "ድምጹን ቀንስ!" የሚል ቅሬታ ከቤተሰብዎ ወይም ከጓደኞችዎ ይደርስዎታል?

ብዙ ሰዎች የመስማት ችግር በድንገት ይጀምራል ብለው ያስባሉ። እውነታው ግን ብዙ ጊዜ በቀስታ ይጀምራል። ሳያስተውሉትም ለዓመታት ሊቆይ ይችላል።

🌍 እንደ ዓለም ጤና ድርጅት (WHO) መረጃ፤ በዓለም ዙሪያ ከ1.5 ቢሊዮን በላይ ሰዎች በተወሰነ ደረጃ የመስማት ችግር አለባቸው።

ይህ ጽሑፍ የመስማት ችግር 10 ቀደምት ምልክቶችን፣ ዋና ዋና መንስኤዎቹን፣ መቼ ወደ ሕክምና መሄድ እንዳለብዎ እና ጆሮዎን እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ በቀላሉ ያስረዳል።

👥 እንደዚህ ዓይነት ችግር ያለበት ሰው ያውቃሉ? እንግዲያውስ ይህን ጽሑፍ ያጋሩት።

https://www.tegbaraid.org/post/hearing-loss

#ጤና #ጆሮ #የጆሮጤና #ኤርፎን #ማዳመጫ

ብዙ ሰዎች የመስማት ችግር በድንገት የሚከሰት ወይም በዕድሜ በገፉ አዋቂዎች ላይ ብቻ የሚገደብ ይመስላቸዋል። ነገር ግን እውነታው ሌላ ነው። የመስማት ችሎታ ማጣት አብዛኛውን ጊዜ የሚጀ...

🚨 "ውሻው ትንሽ ነክሶኛል... ምንም አይሆንም!"😔 ይህ ሐረግ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚናገሩት ሲሆን፤ ለአንዳንዶቹ ግን የመጨረሻ ስህተት ይሆናል።😮 አስገራሚው ነገር...☠️ የእ...
08/03/2026

🚨 "ውሻው ትንሽ ነክሶኛል... ምንም አይሆንም!"

😔 ይህ ሐረግ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚናገሩት ሲሆን፤ ለአንዳንዶቹ ግን የመጨረሻ ስህተት ይሆናል።

😮 አስገራሚው ነገር...

☠️ የእብድ ውሻ በሽታ አንዴ ምልክቶች ከታዩ በኋላ፤ ሕክምና ቢጀመርም በአብዛኛው ጊዜ ሕይወትን ማዳን አይቻልም።

✨ ግን...

🩺 ከውሻ ንክሻ በኋላ የሚወሰድ አንድ ቀላል እርምጃ፤ በሽታውን ሙሉ በሙሉ ሊከላከል ይችላል።

❓ ይህ እርምጃ ምንድን ነው?

❓ ብዙ ሰዎች ከውሻ ንክሻ በኋላ የሚፈጽሙት አደገኛ ስህተትስ ምንድን ነው?

📖 ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ። ይህ መረጃ አንድ ቀን ሕይወት ሊያድን ይችላል።

https://www.tegbaraid.org/post/rabies

#ሬቢስ #እብድውሻ #የውሻንክሻ #ጤና

የውሻ ንክሻን በፍጹም "ቀላል ቁስል" ብለው አይለፉ! የሬቢስ (Rabies) ቫይረስ ምልክት ከመታየቱ በፊት ሙሉ በሙሉ መከላከል የሚቻል ቢሆንም፤ ምልክቶቹ ከተከሰቱ በኋላ ግን ለሞት ይዳርጋል። ከ....

08/01/2026

🚨 "ምንም ምልክት የለብዎትም!?" ጤነኛ ነዎት? 🤔

⏳ ለ10 እስከ 15 ዓመታት ያህል ውስጥ ምንም ምልክት ሳያሳይ፤ ወደ ካንሰር ስለሚለወጠው የትልቁ አንጀት ካንሰር ምን ያህል ያውቃሉ?

🦠 አብዛኛው ሰው የኮሎሬክታል ካንሰር በድንገት እንደሚጀምር ያስባል። እውነታው ግን ተገላቢጦሽ ነው። ብዙ ጊዜ እርስዎ ሳያውቁት ያድጋል።

😨 ከዚያስ...
🏥 የካንሰር ምርመራ እና ህክምና ያስፈልጋል!

💚 መልካሙ ዜና ይህ መከላከል ከምንችላቸው የካንሰር አይነቶች ነው።

🎥 የጠለቀ ግንዛቤ እንዲኖርዎ ይህንን ቪድዮ ይመልከቱ!

❤️ ለእርስዎ ብቻ ሳይሆን ለቤተሰብዎና ለወዳጆችዎም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። እስከ መጨረሻው ይመልከቱ! ሕይወት ሊያድን ይችላል። ❤️

https://youtu.be/3VnxwwL52Is

ለ10 እስከ 15 ዓመታት ያህል በሰውነታችን ውስጥ ምንም አይነት ምልክት ሳይታወቅ ሊያድግ የሚችለው የትልቁ...

Address

1401 21st Street Ste R
Sacramento, CA
95811

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tegbar Organization posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share