Ethiopian Zekre Kedusan Bete Gubae Organization የኢትዮጵያ ዝክረ ቅዱሳን ቤተ ጉባኤ ድርጅት

  • Home
  • United States
  • Pittsburgh, PA
  • Ethiopian Zekre Kedusan Bete Gubae Organization የኢትዮጵያ ዝክረ ቅዱሳን ቤተ ጉባኤ ድርጅት

Ethiopian Zekre Kedusan Bete Gubae Organization የኢትዮጵያ ዝክረ ቅዱሳን ቤተ ጉባኤ ድርጅት The Org strives to preserve & support the ancient traditional Ethiopian Orthodox Tewahedo education.

- The Organization strives to preserve and support the ancient Ethiopian Orthodox Tewahedo traditional church education teaching ((Ye-kolo Timhirt) based on the Ethiopian Orthodox Tewahedo Christiaan dogma and doctrine for current and future generations.
- To support new and existing Ethiopian Orthodox Tewahedo traditional church schools (Ye-kolo Timhirt Betoch) in rural Ethiopia to meet their bas

ic needs (food, clean water, clothing, shelter, school materials) and creating a healthy stable living environment.

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የዕርገት በዓል በሰላም አደረሰን/አደረሳችሁ። ጌታችን መድኃኒዓለም የእመቤታችን ቅድስት  ድንግል ማሪያምን ጣዕሟን ፍቅሯን ያሳድርብን፣ በም...
08/21/2026

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የዕርገት በዓል በሰላም አደረሰን/አደረሳችሁ።
ጌታችን መድኃኒዓለም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያምን ጣዕሟን ፍቅሯን ያሳድርብን፣ በምልጃዋ ይማረን።

እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል አደረሳችሁ/አደረሰን። “ደብረ ታቦር ከዘጠኙ አበይት በዓላት አንዱ ነው። ቡሄ ብለን በዓሉን እናከብራለን። በትውፊት ጅራፍ ገምዶ ማጮኽ  የጌታችን የመድኃኔዓለምን ...
08/18/2026

እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል አደረሳችሁ/አደረሰን። “ደብረ ታቦር ከዘጠኙ አበይት በዓላት አንዱ ነው። ቡሄ ብለን በዓሉን እናከብራለን። በትውፊት ጅራፍ ገምዶ ማጮኽ የጌታችን የመድኃኔዓለምን ግርፋቱን ስቀ‍እለቱን እምናስብበት ነው። እንዲሁም ቡሄ ማለት ብርሃን፤ ደማቅ ማለት ሲሆን ችቦ በየቤታችን ወይም ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰብሰብ ብለን በማብራትም በደብረ ታቦር የአምላካችን ብርሀነ መለኮት መገለጥ ጋር እናስበዋለን። “

ሐምሌ ፳፪/22 1928 ዓ:ም ለእናት ሀገር ኢትዮጵያ የተከፈለ መሥዋዕትነት !ስለ አቡነ ጴጥሮስ መስዋዕትነት በደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ መጽሀፍ“የኢትዮጵያ እና የአኢጣሊያ ጦርነት “ በ19...
07/28/2026

ሐምሌ ፳፪/22 1928 ዓ:ም ለእናት ሀገር ኢትዮጵያ የተከፈለ መሥዋዕትነት !
ስለ አቡነ ጴጥሮስ መስዋዕትነት በደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ መጽሀፍ
“የኢትዮጵያ እና የአኢጣሊያ ጦርነት “ በ1980 የታተመ ከገጽ 155-156 ስለ አቡነ እንዲህ ብሎ መጽሀፉ ላይ አስፍሮታል።
“ፓጃሊ የተባለ የጣሊያን ጋዜጠኛ ባሳተመው መጽሀፋ ላይ
".....አቡኑ ሲገደሉ በዚያው ነበርኩ፤ ጴጥሮስ ረጅምና ብሩህ ገጽታ ያላቸው ናቸው፤ ጥቁር ካባ ለብሰዋል…
“…..የሆቴል ቤቱ ጌታ ግሪካዊው ማንድራኮስ የአቡኑን ንግግር ለጋዜጠኛች ያስተረጉሙ ነበር ፤ አቡኑ በሚገባ የመከላከያ ሀሳባቸውን ሰጡ።
“…ሐምሌ 30 ቀን (እ.ኤ.አ.) በጳጳሱ ላይ የተቋቋመው ችሎት ሕዝብ በተሰበሰበበት በአደባባይ እንዲገደሉ ፈረደ። ይህ ሲሰማ በከተማው ሕዝብ ዘንድ ሽብር ፈጠረ። ጉዳዩም በጋዜጣ እንዳይወጣ ፋሺስቶች ታላቅ ቁጥጥር አደረጉ…”
"...የሞት ፍርዱ በተፈረደባቸው ጊዜ በጸጥታ አዳመጡ። በቀኝ እጃቸው በሰማያዊ ጨርቅ የተሸፈነ መስቀል ይዘው ነበር።ጣልያኖቹ የመግደያ ቦታ አዘጋጅተው አቡነ ጴጥሮስ ተወሰዱ። ፊታቸውንም ወደ ተሰበሰበው ሕዝብ አድርገው ቆሙ።
ጴጥሮስ ሰዓታቸውን አውጥተው አዩ። ወዲያውም አጠገባቸው የነበረውን ኢጣሊያዊ ለመቀመጥ እንዲፈቅድላቸው ጠየቁት። ቀና ብለው ወደ ተቀመጡት ጋዜጠኞችና መኳንንት አዩ፤ የመቀመጥ ጥያቄያቸውንም ትተው ቀጥ ብለው ቆሙ።
ከፊታቸው ለቆሙት ገዳዮቻቸው ተመቻቹ።
አቡኑ ረጋ ብለው ተራመዱ። ካራቢኒዬሮቹም ከመግደያው ቦታ እስኪደርሱ ጠበቁ። ወደ ቦታው ሲደርሱ አንድ አስተርጓሚ ተጠግቶ፣
"ዓይንዎን እንዲሸፈን ይፈልጋሉን?" አላቸው።
እሳቸውም መልሰው፣”የእናንተ ጉዳይ ነው፤ እንደ ፈለጋችሁ አድርጉ፤ ለእኔ ማንኛውም ልዩነት የለውም።" ብለው መለሱ።
ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ ፊታቸውን ወደ ግድግዳው እንዲያዞሩ ተደረገ። እሳቸውን በመግደል ክብር የሚፈልጉት ስምንት ካራቢኒዬሮች ከጴጥሮስ 20 እርምጃ ያህል ርቀው ቆሙ። በአስተኳሹ ትዕዛዝ ተኮሱ። ጴጥሮስ በጥይት ተመትተው ወደ መሬት ወደቁ። ወዲያው አንድ ኢጣሊያዊ ካፒቴን ሐኪም ሬሳቸውን መረመረና፣ «ይህ ቄስ አልሞተም» ብሎ ተናገረ። የካራቢኒዬሮቹ መኮንን ተጠግቶ ሦስት ጥይት ተኩሶ ራሳቸውን ደበደበና ጨረሳቸው።ሬሳቸውም ከከተማ ውጪ ተወስዶ በምስጢር ተቀበረ…..ብሎ ጽፏል።

ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ እንደጻፈው፦
"...ከሚገደሉበት ስፍራ ሲደርሱ አራቱን ማዕዘን በመስቀላቸው ባረኩ። በሕዝቡም ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፦
'ፋሽስቶች የአገራችንን አርበኞች ሽፍታ ቢሏቸው እውነት አይምሰላችሁ። ሽፍታ ማለት ያለ አገሩ መጥቶ የሰውን አገር የሚወር ነው። ይህ በመካከላችሁ የቆሙት አረመኔዎች የኢጣሊያ ፋሽስቶች ናቸው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእነሱ እንዳይገዛ ውጉዝ ነው። የኢትዮጵያም መሬት እንዳትቀበላቸው የተገዘተች ትሁን። ...' ብለው ተናገሩ።

ጠላት ድል ተደርጎ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የብፁዕነታቸውን አኩሪ ታሪክ ትውልድ ሲዘክርላቸው እንዲኖር መታሰቢያ ይሆናቸው ዘንድ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴ አሳሳቢነት ሐምሌ 16 ቀን 1938 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ ሐውልት ቆሞላቸዋል።

ከሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት ከሚለው የተውኔት ግጥም በጥቂቱ የተቀነጨበ
“አዬ፣ ምነው እመ ብርሃን? ኢትዮጵያን ጨከንሽባት?
ምነው ቀኝሽን ረሳሻት?
እስከመቼ ድረስ እንዲህ፣ መቀነትሽን ታጠብቂባት?
ልቦናሽን ታዞሪባት?
ፈተናዋን፣ ሰቀቀኗን፣ ጣሯን ይበቃል ሳትያት?
አላንቺእኮ ማንም የላት….
አውሮጳ እንዲሁ ትናጋዋን፣ በፋሽስታዊ ነቀርሳ
ታርሳ፣ ተምሳ፣ በስብሳ
ሂትለራዊ እባጭ ጫንቃዋን፣ እንደኮረብታ ተጭኗት
ቀና ብላ እውነት እንዳታይ፣ አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት
ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት
ሥልጡን፣ ብኩን፣ መፃጉዕ ናት፤ ….
እና ፈርቼ እንዳልባክን፣ ሲርቀኝ የኃይልሽ ውጋገን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ፣ በርታ በይኝ እመ ብርሃን
ቃል ኪዳኔን እንዳልረሳት፣ እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን፡፡

ሥሜን በሥምሽ ሰይሜ፣
ባገልግሎትሽ ስዋትት
ከዜማ ቤት እቅኔ ቤት፣ ከድጓ ቤት
እመጻሕፍት
ካንቺ ተቆራኝታ ዕድሌ፣ ካንቺ ተቆራኝታ
ነፍሴ
ከቀፈፋ ደጀሰላም፣ ከቤተልሔም
ቅዳሴ
እኰ፣ ቀፎ ዳባ ለብሶ
ቅኔ ዘርፎ ግስ ገሦ
መቅደስ አጥኖ ማኅሌት ቆሞ
በልብስ ተክህኖ አጊጦ፣ በብር አክሊል
ተሸልሞ
እመ ብርሃን ያንች ጽላት፣ ነፍስ ላይ
በእሳት ታትሞ
የመናኒው ያባ ተድላ፣ ረድ ሆኜ፣
አብሮኝ ታድሞ
ሕይወቴ እምነትሽን ጸንሶ
ሥጋ ፈቃዴ ተድሶ
ለሕንፃሽ መዲና ቆሞ፣ ለክብርሽ
ድባብ ምሰሶ
አዎን፣ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ”

ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድኅን ፲፱፻፷፩ ዓ.ም

የሊቀ መላእክት ቅዱስ  ገብርኤል ተራዳኢነት፣ በረከቱ አይለን።
07/25/2026

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት፣ በረከቱ አይለን።

ዕዕለቱ ሐምሌ ፯ ሥሉስ ቅዱስ ለአብርሃም በአንድነትና በሦስትነት ክብሩ የተገለጡለት፣ በቤቱም የተስተናገዱበትl  ነው።የቅድስት ሥላሴ ቸርነት አይለየን።
07/14/2026

ዕዕለቱ ሐምሌ ፯ ሥሉስ ቅዱስ ለአብርሃም በአንድነትና በሦስትነት ክብሩ የተገለጡለት፣ በቤቱም የተስተናገዱበትl ነው።
የቅድስት ሥላሴ ቸርነት አይለየን።

Happy 250th Fourth of July! May God continue to bless the United States of America.
07/03/2026

Happy 250th Fourth of July!
May God continue to bless the United States of America.

የሊቀ መላዕክት ቅዱስ  ሚካኤል ጥበቃው አይለየን፣ረድኤት፣ በረከቱ አይለየን።
06/19/2026

የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ጥበቃው አይለየን፣ረድኤት፣ በረከቱ አይለየን።

06/05/2026

Selam! It is great news for our community in Pennsylvania! This recognition helps create awareness of Ethiopia's important role in world history.
On June 3, 2026, the Pennsylvania House of Representatives voted overwhelmingly to recognize and declare March 2 as Adwa Victory Day in Pennsylvania.
The victory of Battle of Adwa stands as a symbol of freedom, unity, and resistance against colonialism, inspiring people around the world.
God willing, we will celebrate this historic achievement in a big way next year!

Congratulations to everyone who worked to make this happen!

ዕለቱ ግንቦት  ፳፫/23 “በዓለ ጰራቅሊጦስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅደስት ቤተክርስቲያናችን በልዩ ክብርና በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ከምታከብራቸው በዓላት መካከል አንዱ ነው።ከሙታን ተ...
05/30/2026

ዕለቱ ግንቦት ፳፫/23 “በዓለ ጰራቅሊጦስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅደስት ቤተክርስቲያናችን በልዩ ክብርና በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ከምታከብራቸው በዓላት መካከል አንዱ ነው።
ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ ከ፶ኛው፤ ከዐረገ ከ፲ኛው ቀን ጀምሮ እስከሚቀጥለው እሑድ ድረስ ያለው ወቅትም ዘመነ ጰራቅሊጦስ ተብሎ የሚጠራ ነው። በዓለ ጰራቅሊጦስ በየዓመቱ ትንሣኤን ባከበርን በሃምሳኛው ቀን ላይ ይውላል። ጲራቅሊጦስ ማለት ከሦስቱ አካላት አንዱ ለሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስም ነው። በዓለ ጰራቅሊጦስ ‘በዓለ ጰንጠቆስጤም ’ እየተባለም ይጠራል። እንዲሁም ታላቁ ሊቅ ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን በዓል “የቤተክርስቲያን የልደት ቀን” በዓለ ጰራቅሊጦስ ወይም በዓለ ጰንጠቆስጤ ከዘጠኙ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደበትን ቀን የምናስብበት በዓል ነው።”የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና የቅዱሳን ተራዳኢነት አይለየን።

እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በዓለ እርገት አደረሰን/አደረሳችሁ።The Ascension of our Lord!
05/20/2026

እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በዓለ እርገት አደረሰን/አደረሳችሁ።
The Ascension of our Lord!

Address

1712 HAYS Street
Pittsburgh, PA
15218

Telephone

+14123102536

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Zekre Kedusan Bete Gubae Organization የኢትዮጵያ ዝክረ ቅዱሳን ቤተ ጉባኤ ድርጅት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Zekre Kedusan Bete Gubae Organization የኢትዮጵያ ዝክረ ቅዱሳን ቤተ ጉባኤ ድርጅት:

Shortcuts

Share