Ethiopian Community Association in Nashville

Ethiopian Community Association in Nashville Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Community Association in Nashville, Nonprofit Organization, 2201 Murfreesboro Pk D-201, Nashville, TN.

MISSION: Forge a vibrant, empowered Ethiopian community in Nashville by fostering knowledge, responsibility, productivity, and collaboration, while preserving and advancing our rich cultural traditions and diverse heritage.

🎓 ምስጋና ለኢማና (ECAN) የትምህርት ኮሚቴ! 📚የ2026–2027 የትምህርት ዘመንን ስንቀበል፤ የኮምዩኒቲያችንን ወጣቶች ለኮሌጅ ግብአት የሚሆን መረጃ በማቅረብ፣ አቅማቸውን በማጎልበት፣ በ...
08/03/2026

🎓 ምስጋና ለኢማና (ECAN) የትምህርት ኮሚቴ! 📚

የ2026–2027 የትምህርት ዘመንን ስንቀበል፤ የኮምዩኒቲያችንን ወጣቶች ለኮሌጅ ግብአት የሚሆን መረጃ በማቅረብ፣ አቅማቸውን በማጎልበት፣ በማበረታታት እና አቅጣጫ በማሳየት ላሳየው ከፍ ያለ አስተዋፅኦ የኢማናን የትምህርት ኮሚቴ ከፍ ያለ እውቅና በመስጠትና እና ምስጋና በማቅረብ ነው።

በምክር አገልግሎት (mentorship) እና በትምህርታዊ ውይይቶች አማካኝነት፣ ኮሚቴው ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ እና ለኮሌጅ ተማሪዎች ስለ ስኮላርሺፕ ዕድሎች፣ ስለ ፋይናንስ እርዳታ፣ ስለ ኮሌጅ አመራረጥ፣ ስለ ACT/SAT ፈተና ዝግጅት፣ ስለ ሪዙሜ (CV) አጻጻፍ፣ ከክፍል ውጭ ስለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች (extracurricular activities) አስፈላጊነት እና ለትምህርታዊ ስኬት የሚያስፈልጉ ሌሎች በርካታ አስፈላጊ ርዕሶች ላይ ምክር እና መመሪያ ሲሰጥ ቆይቷል።

በተለይም የኢማናን የመጀመሪያውን የስኮላርሺፕ ፕሮግራም ለመጀመር የኮሚቴው ሊቀ-መንበር ዶ/ር ጋሻው በቀለ ላሳዩት አመራር፤ እንዲሁም ሁሉም የኮሚቴው አባላት የስኮላርሺፕ ፈንዱን ለማቋቋም እና የኮምዩኒቲያችን ወጣቶች የወደፊት ህይወት ላይ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ በግላቸው አስተዋጽኦ በማድረጋቸው ትልቅ ምስጋና እናቀርባለን።

ድካማችሁ በማህበረሰባችን ውስጥ ዘላቂ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። የሚቀጥለውን ትውልድ ለማብቃት ስለምታደርጉት ጥረት እናመሰግናለን!

የኮሚቴው ሰብሳቢ- ዶ/ር ጋሻው በቀለ
የኮሚቴ አባላት - ወ/ሮ ማህደረ ደምሴ፣ ረ/ፕሮፌሰር አያናው ሃጎስ፣ ዶ/ር አዲስአለም ተጫኔ፣ ዶ/ር ዳንዔል ኤሬንሶ፣ አቶ ፀሃይ ደመቀ

👏 እባካችሁ ይህንን ድንቅ ኮሚቴ በማመስገን ተቀላቀሉን።

ለሁሉም ተማሪዎች መልካም እና ስኬታማ የ2026–2027 የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

07/31/2026
07/30/2026

በናሽቪል የኢትዮጵያውያን ማህበር (ኢማና) ከAugust ,1 2026 ጀምሮ በየሳምንቱ ቅዳሜ ከ11 AM እስከ 2 PM ድረስ 2201 Murfreesboro Pk, D-201, Nashville, TN 37217 የሚገኘውን ቢሮ ክፍት በማድረግ የኮሚኒቲ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ይገልጻል።

የሚሰጡ አገልግሎቶች፤
• የስራ ዕድል እና ጥቆማ
• የስራ ልምድ/resume ዝግጅት ድጋፍ
• የኢሚግሬሽን ምክር
• የትርጉም ስራ
• የድጋፍ ደብዳቤ
• የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዕድሎች

እርስዎም ወደ ቢሮአችን ብቅ ብለው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑና ለሌሎችም እርዳታ ለሚሹ መረጃውን እንዲያደርሱ በአክብሮት እንጠይቃለን።

ኢማና

📣3 ትልልቅ በዓላት!!!የአዲሱን የኮምዩኒቲ ማዕከል ምርቃት፣ የኢማናን 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል፣ እንዲሁም የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት 2019 በጋራ ለማክበር አብረውን ይሁኑ!ሰኞ፡ ጳጉሜ 2...
07/27/2026

📣3 ትልልቅ በዓላት!!!

የአዲሱን የኮምዩኒቲ ማዕከል ምርቃት፣ የኢማናን 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል፣ እንዲሁም የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት 2019 በጋራ ለማክበር አብረውን ይሁኑ!

ሰኞ፡ ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም / SEPTEMBER 7, 2026
ከሰዓት 2:00 PM
5824 PETTUS RD, ANTIOCH, TN 37013

Parent Meeting Event hosted by Utopia Math Academy Friday, July 24, 7 PM Central Time
07/23/2026

Parent Meeting Event hosted by Utopia Math Academy
Friday, July 24, 7 PM Central Time

ውድ በናሽቪልና አካባቢው ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን:-የከተማችን ነዋሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አዱኛ ብርሃኑ ኦላኒ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም ድካም አልፈዋል:: የ...
06/16/2026

ውድ በናሽቪልና አካባቢው ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን:-

የከተማችን ነዋሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አዱኛ ብርሃኑ ኦላኒ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም ድካም አልፈዋል::

የኢትዮጵያዊያን ማህበር በናሽቪል (ECAN) በወንድማችን ያልተጠበቀ ህልፈት ሃዘኑን እየገለፀ ወንድማችንን በክብር ለመሸኘት የሚከተለውን መርሃ ግብር ያሳውቃል:-

Tuesday June 16
4:30PM-7:30pM
ቤተሰቦችን ማፅናናት በ Nashville Ethiopian Evangelical church
2846 Lebanon pk
Nashviille, Tn 37214

Wed June 17, 2026 ስንብት (Visitation)
3:00PM-6:00PM
Ellis Funeral Home
2627 Nollensville Pk
Nashville TN 37211

ፀሎት እና ቀብር :-
ፀሎት (Church Service)
Thursday June 18 1:00PM Nashville Ethiopian Evangelical church
2846 Lebanon pk

ቀብር (Funeral)
Thursday June 18
3:30 PM
Christ Church
15354 Old Hickory Blvd

06/12/2026

ለ2026 የ2ኛ ደረጃ እና ኮሌጅ ተመራቂዎች ያዘጋጀነው የምርቃት ስነ-ስርዓት ነገ ቅዳሜ June 13፤ 2026 ከቀኑ በ 2 PM በኢዜል ሃርዲንግ ትምህርት ቤት (574 Bell Rd, Antioch, TN 37013) ይካሄዳል።

- የኢማና 2026 ስኮላርሺፕ ለአሸናፊዎች ይሸለማል::
- ተመራቂዎች ሰርተፊኬት ይቀበላሉ::
- ወጣቶች ያዘጋጁት ትርዒትም ይቀርባል::

የተመራቂ ቤተሰቦችና የኮምዩኒቲያችን አባላት ለተመራቂዎች በዝግጅቱ በመገኘት ሞራል እንድትሰጡ በአክብሮት እንጠይቃለን።

HAVE YOU HEARED ABOUT ECAN'S SCHOLARSHIP AWARDS FOR 2026 GRADUATES? SCAN THE QR CODE AND COMPLETE THE FORM TO COMPETE FO...
06/08/2026

HAVE YOU HEARED ABOUT ECAN'S SCHOLARSHIP AWARDS FOR 2026 GRADUATES? SCAN THE QR CODE AND COMPLETE THE FORM TO COMPETE FOR ECAN'S SCHOLARSHIPS!

06/06/2026

የኢትዮጵያውያን ማህበር በናሽቪል በዚህ ዓመት የተመረቁ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን አወዳድሮ ለተወሰኑ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ወይም ስኮላርሽፕ መስጠት ይፈልጋል። ተመራቂዎች ከዚህ በታች የተቀመጠውን ቅጽ እስከ ሰኞ ባለው ጊዜ እንዲሞሉ እንድታበረታቱልን ለማሳሰብ እንወዳለን።

Please help find Jonah!
06/06/2026

Please help find Jonah!

Address

2201 Murfreesboro Pk D-201
Nashville, TN
37217

Opening Hours

Monday 10am - 4pm
Tuesday 10am - 4pm
Wednesday 10am - 4pm
Thursday 10am - 4pm
Friday 10am - 4pm

Telephone

+16157829444

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Community Association in Nashville posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Community Association in Nashville:

Share