Risala International

Risala International Risala International is a non-profit organization based in Minnesota that works on solving religious, political and social justice of Oromo/Ethiopian Muslims.
(209)

10/04/2026

Loola dhuma hin qabnee

09/30/2026

7ቱ ክሶችና የፍረጃ ፖለቲካ ተቃርኖ ትናንትና ዛሬ
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

በአሕመዲን ጀበል
✅✅✅✅✅

ይህን ጽሁፍ አንብቦ መጨረስ የማይችል አርፎ ቢቀመጥ ይሻለዋል!
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧

በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ መብትና እኩልነትን የጠየቀ አካል የሚገጥመው የመጀመሪያው ፈተና የሐሳብ ሙግት ሳይሆን የጥላቻና የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው። ትናንት እኔም ሆንኩ ሌሎች በማኅበራዊ ሚዲያም ሆነ በመሬት ላይ የሙስሊሞችን የመብትና የእኩልነት ጥያቄ ስናነሳ ፣ ጥያቄውን አስጥለው ድምፃችንን ለማፈን የቋመጡ አካላት ያልመዘዙብን ታርጋ አልነበረም።

በተለይም የኔን የፌስቡክ ገጽ ኮመንት ያነበበ ማንኛውም ሰው በኔ ላይ ከተዘመቱት መርዘኛ ፍረጃዎች መካከል «ባንዳ»፣ «የግብጽ ተላላኪ»፣ «ዘረኛ»፣ «ጨፍጫፊ/ገዳይ፣አይኤስ»፣ «ፀረ-ኢትዮጵያ»፥ «ኦነግ» እና «ወሃቢያ» የሚሉት ግንባር ቀደሞቹ እንደነበሩ ያስታውሳል።

የእነዚህን ፍረጃዎች ትክክለኛ መገለጫ ይዞ ዛሬ ላይ ቆም ብሎ ለታዘበ ግን ታሪክ እንዴት አስገራሚ ዳኛ እንደሆነች ይመሰክራል። ትናንት እኛ ላይ ሲለጥፏቸው የነበሩትን ሰባቱንም ፍረጃዎች፣ ዛሬ እነዚያው አካላት ራሳቸው በተግባር ተላብሰውት ስናይ ነገሩ አስገራሚ ተቃርኖ ሆኖ እናገኘዋለን።እስኪ አንድ በአንድ እንያቸው።ሳይሰለቹ እስከመጨረሻው እንዲያነቡ እየጋበዝኩ መልዕክቱ ለሌሎች እንዲደርስ ሼር፣ላይክና አስተያየትዎን ከስር እንዲያሰፍሩ እጠይቃለሁ።መልካም ንባብ።

«ባንዳ» እና ባንዳነት
💢💢💢💢💢💢

ባንዳ ማለት ለግል ወይም ለጠባብ ቡድኑ ጥቅም አሊያም ለሥልጣን ሲል ከሀገሩ ጋር ጠብ ካለው ባዕድ ኃይል ጋር አብሮ በማሴር፣ የገዛ ወገኑን ደኅንነትና የሀገሩን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ትናንት የኔ የፌስቡክ ገጽ ኮመንት ላይ ሳይቀር ሰላማዊ የመብት ጥያቄያችንን በባንዳነት ይፈርጁት ነበር። ዓላማቸውም በከሃዲነት ታርጋ የሕዝቡን እኩልነት ጥያቄ ማፈን ነበር።

የታሪክ ምጸቱ የሚጀምረው እዚህ ጋር ነው። ትናንት እኛን «ባንዳ» ሲሉ የነበሩት አካላት፣ ዛሬ ለሥልጣን ሲሉ የሀገርን ህልውና ለአደጋ የሚያጋልጥ መንገድ መርጠው ጭምብላቸው ወደቀ፤ እርቃናቸውንም ወጡ። በታሪክ ከኢትዮጵያ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ካሉ የውጭ ኃይሎች ጋር ለማበር ደጅ ሲጠኑና የሀገራቸው መዳከም ለሚመኛቸው ባዕዳን በር ሲከፍቱ አደባባይ ላይ እየታዩ ነው።

ባንዳነት መገለጫው ለውጭ ጠላቶች የውስጥ መጠቀሚያ መሆን ነው። የኢትዮጵያ ባላንጣ የሆኑ የግብጽ ሚዲያዎችና አክቲቪስቶች የሰሞኑን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን እያጋነኑ ጮቤ ሲረግጡና በስሜት ድጋፋቸውን ሲቸሩ ማየት የባንዳነት መሥመሩ ወዴት እንደሚያመራ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የግብጽ ባላንጣዎች ለሀገራችን ሰላም ወይም ለሕዝብ ነፃነት አስበው ሳይሆን፣ የሀገራችን ማዕከሉ ተዳክሞ ኢትዮጵያ እንድትፈረካከስ ስለሚፈልጉ ብቻ ነው።

መንግሥትን መቃወም ይቻላል፤ የውጭ ባላንጣ መሣሪያ ሆኖ ሀገርን ማዳከም ግን ባንዳነት ነው። «የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው» በሚል ስሌት የሀገርን ህልውና ለባዕዳን አሳልፎ መስጠት ለሕዝብ ነፃነት አያመጣም።

ታዲያ ዛሬ ላይ ባንዳው ማን ነው? «ጦርነት ይብቃ፤ ሀገር በሰላምና በእኩልነት ትጓዝ» የሚለው ሰላማዊው ሙስሊም ወይስ ለሥልጣን ሲል ከሀገር ባላንጣዎች ደጅ የሚጠናው አካል? መልሱን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የዛሬው ነበራዊ እውነትም በግልጽ እየመሰከረው ነው።

«የግብጽ ተላላኪ»
🔴🔴🔴🔴🔴🔴

«የግብጽ ተላላኪ» ማለት ከካይሮ መመሪያና ገንዘብ ተቀብሎ የሀገሩን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ የውክልና አገልጋይ ነው። ትናንት በኔ ላይም ሆነ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን መበት አጀንዳዎችን ስናነሳ «የግብጽ ተላላኪ» የሚለው የፍረጃ ሀረግ
ይመዘዝ የነበረው እኛን በአሉታዊ ገጽታ በመሳል ሰላማዊ የመብትና የእኩልነት ጥያቄዎች ማስጣል፥ ማፈን እና በአዎንታዊነት እንዳይታይ ለማድረግ ነበር።

የታሪክ ምጸቱ የሚጀምረው እዚህ ጋር ነው። ትናንት እኛን «የግብጽ ተላላኪ» እያሉ ያለምክንያት ሲፈርጁ የነበሩት አካላት፣ ዛሬ «እኔ ካልገዛኋት ኢትዮጵያ በአፍጢሟ ትደፋ» እያሉ ከሀገር ህልውና ይልቅ ሥልጣንን አስቀድመው ጭምብላቸው ወለቀ፤ እርቃናቸውንም ወጡ። ይባስ ብለው «መንግሥትን ለመጣል ከማንም ጋር እንሠራለን» እያሉ እስከ መናገር ደረሱ።

የካይሮ ዓላማ ዘመናት ቢቀየሩም ያው ነው፤ «ኢትዮጵያን በውስጥ ቀውስ ጠምዶ ሰላም ማሳጣት»። የግብፅ ፖለቲከኞች የናይልን የበላይነት ለማስጠበቅ ሲሉ የእኛን ውስጣዊ ክፍፍልና አማፂያንን እንዴት መጠቀሚያ ማድረግ እንዳለባቸው በይፋ ሲመክሩበት ያየነው እውነታ ነው።

ሀገርና መንግሥት አንድ አይደሉም። መንግሥትን መቃወም እና ከሀገር ጥቅም በተጻራሪ መቆም ፈጽሞ አይገናኙም። በሀገር ጉዳይ ላይ «የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው» የሚለው ስሌት አይሠራም። መንግሥትን ብንቃወም እንኳ፣ የትጥቅና የገንዘብ ድጋፍ ፍለጋ እንደ ግብጽ ካሉ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ማበር ባንዳነት እንጂ ለሕዝብ ነፃነት አያመጣም። የግብጹ መሪ አስመራ፣ የአስመራው ካይሮ የሚመላለሱት ለየትኛው የልማትና ኢንቨስትመንት አጀንዳ ነው?

ሻዕቢያስ የመንግሥት ተቃዋሚዎች ሁሉ የጡት አባት የሚሆነው ከዚህ ከተሰጠው ተልእኮ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? ይህ የግንኙነት መሥመር ግልጽ ያልሆነለት ካለ በሰሞኑ የግብጽ ሚዲያዎችና አክቲቪስቶች በሰሜን ኢትዮጵያ እየተከናወነ ባለው ጦርነት ላይ የሚዘግቡትን ዘገባ፣ በዘገባዎቹ ስር የሚሰጡትን አስተያየት ይመልከት። ኢትዮጵያ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ተመለሰች በሚል ምን ያህል ጮቤ እንደረገጡ አስተውሉ። ከዘገባ እስከ ትንታኔ፣ ከሚታየው ፍላጎታቸው እስከ ትክክለኛነት ለማን ወግነው እየሠሩ እንደሆነ አስተውሉ።

ታዲያ ዛሬ ላይ ተላላኪው ማን ነው? «ጦርነት ይብቃ፤ ሀገር በሰላምና በእኩልነት ትጓዝ» የሚለው ሰላማዊው ሙስሊም ወይስ ለሥልጣን ሲል ከሀገር ባላንጣ ጋር ግንባር ለመፍጠር የሚደራደረው አካል? መልሱን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የዛሬው እውነትም በግልጽ እየመሰከረው ነው።

«ዘረኛ»
❌❌❌

ዘረኛ ማለት ሰውን በብሔሩ ወይም በትውልዱ ብቻ እያበላለጡ የሌሎችን ክብር፣ ሰብአዊ መብትና ዕድል የሚነፍግ፣ የራሱን ዘር ከሁሉ በላይ የተለየ አድርጎ የሚያቀርብ ነው። ትናንት በፌስቡክ ገጼ ላይ በማኅበረሰባችን የደረሱ በደሎችን ስናጋልጥና እኩልነትን ስንጠይቅ «ዘረኛ!» እያሉ ታርጋ ይለጥፉብን ነበር። ዓላማቸውም የእኩልነት ድምፃችንን በጠባብነት አስፈርጀው ለማድበስበስ ነበር። በእርግጥ በደል፥ አድሎና ጭቆና ካለ ለራስ ዘር መበት መሥራትና መቆም አንዳች ችግር ያለው ነገር ባይሆንም ተለይ «አሕመዲን ዘረኛ ነው፤ ለሙስሊሞች ሳይሆን ለዘሩ ነው የቆመው» የሚለው ፍረጃ በስፋት ከተሰራጩት መካከል ነው።

ትናንት እኛን በዘረኝነት የከሰሱት አካላት፣ ዛሬ ራሳቸው የትምክህትና የጠባብነት አውራ ሆነው ጭምብላቸው ወለቀ፤ እርቃናቸውንም ተጋለጡ። ሌላው ቀርቶ መብላትና መጸዳዳት ጭምር እኛ ነን ያስተማርናችሁ ሲሉ ተደመጡ።

የሌላውን ብሔር ህልውናና መብት እንደ ስጋት በመቁጠር፣ ራሳቸውን ብቸኛ የሀገር መስራችና ባለቤት፣ ሌላውን ደግሞ እንደ ባዕድና ሁለተኛ ዜጋ የሚያዩበትን ጽንፈኛ የዘረኝነት አባዜ በተግባር አደባባይ አውጥተውታል።

ዘረኝነት ማለት የራስን መብት ማስከበር ሳይሆን የሌላውን መብት የመደፍጠጥ ፍላጎትና ተግባር ነው። የራስን ማንነት ማወቅና ለተበደለ ወገን መቆም ተፈጥሯዊ መብት እንጂ ዘረኝነት ሊሆን አይችልም። እውነተኛው ዘረኝነት «ከእኔ ብሔር በላይ ማንም ሊኖር አይገባም፤ ሌላው እኔን መስሎ፥ስለኔ ባለውለታነት እየዘመረ እኔ በፈቀድኩለት መንገድና ልክ ብቻ ይኑር» የሚል እብሪት የወለደው ፍላጎት ነው።

ፍትሕና እኩልነትን መፈለግ ከዘረኝነት ጋር አይገናኝም።ስለመላው ወገንና ሀገር የቆሙትን ሁሉ በዘረኝነት እየፈረጁ በሚዲያ ዘገባዎቻቸውም ሆነ በእንቅስቃሴያቸው ስለራሳቸው ዘር ብቻ የሚያቀነቅኑ አካላት ሌላውን «ዘረኛ!» ብለው ለመፈረጅ እንደመሞከራቸው የሚደንቅ ነገር የለም።ታሪክህን ስትናገር ይናደዳሉ። ባህልህን ስታንጸባርቅ አይናቸው ይቀላል። ሃይማኖትህን አጥብቀህ ስትይዝ፥ ስለሃይማኖት ወገኖች ጭቆና ስትናገር ይበግናሉ። የወገንህን ጉዳይ ችላ ብለህ እነርሱ እንደሚፈልጉት ሆነው ስትገኝ አንተ ለነርሱ «ጥሩ ኢትዮጵያዊ» ነህ!

ታዲያ ዛሬ ላይ ዘረኛው ማን ነው? «ሁሉም ሕዝብ በክብርና በእኩልነት ይኑር፤ መድልዎ ይብቃ፥ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ነች በተግባርም ሁሉን ትምሰል» የሚለው ኢትዮጵያዊ ወይንስ እነርሱ ኢትዮጵያን ካልመሩ «ብፈልግ ትፍረስ ለኔ ምኔ ነች?» በሚል በጠባቡ የዘር አጥር የታጠረው አካል?

«ጨፍጫፊ/ገዳይ፣ አይኤስ»
⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕

«ጨፍጫፊ ወይም ገዳይ» ማለት ያለ አንዳች ሕጋዊ ምክንያት የንጹሐንን ሕይወት የሚያጠፋ፣ የጅምላ እልቂት የሚያዝ፣ የሚያቅድ ወይም ሆን ብሎ በደቦ የሚያስፈጽም አረመኔ ነው። ትናንት እኔ በማኅበራዊ ሚዲያ በምጽፋቸው ጽሑፎች ስር እየገቡ እኛን በገዳይነትና በአሸባሪነት ይፈርጁን ነበር።

እኛ የመራነው የ«ድምፃችን ይሰማ» ሰላማዊ ንቅናቄ አንዲትም ንጹሕ ነፍስ ያልጠፋበት፣ አንድም መስታወት ያልተሰበረበት፣ በተቃራኒው እኛው ራሳችን የአካልና የታሳሪነት ዋጋ የከፈልንበት የሞራል የበላይነት የነበረው ትግል ነበር። ትናንት በሰላማዊነቱ የመሰከሩና ድምጽ ሆነው የነበሩ አንዳንድ አካላት ጭምር በቅርብ ጊዜያት ዉስጥ ያለአንዳች ማስረጃ ብቻ እኛን «ገዳይ» እያሉ ገጽታ ለማጠልሸት ጥረው ነበር። ብዙም ሳይቆም በገዛ አረመኔያዊ ተግባሮቻቸውና አረመኔያዊ ድርጊቶችን በሚዲያ ለመከላከልና ድጋፍ ለመስጠት በተጓዙት ርቀት ማን ገዳይና ጨፍጫፊ እንደሆነ እውነቱ ተጋለጠ፤

በሀገራችን ማኅበራዊ ሚዲያ መጥቶ ድርጊቶች በቪዲዮ ጭምር መዘገብ ከጀመሩ ወዲህ እውነታውን ሁሉም መረተት ጀመረ፤ባለፉት ዓመታት በመንጋ በደቦ ፍርድ የሰው ልጅ ያለፍርድ ሲገደል፥ ክቡር የሆነው የሰው ልጅ በእሳት ሲቃጠል፣ የሰው ልጅን «ጠብሰን እንበላለን» እያሉ በጭካኔ ሲፎክሩ፣ ንጹሐንን ከባጃጅ እያወረዱ በደቦ ሲገድሉ፥ በሴት የመራቢያ አካል ላይ ዘግናኝ ድርጊት ሲፈጽሙ፥ በቪዲዮ እየቀረጹ የሰው ልጅ በጥይት እሩምታ ሲገድሉና ክብር ሲያዋርዱ የታዩት ገዳዮች ሙስሊሞች አልነበሩም።

በሀገራችን በኢስላምና በሙስሊ ስም ታጥቆና ሸፍቶ ጫካ የገባ ቡድን የለም። ሌላው ቢቀር በኢትዮጵያ የብሄርና የሃይማኖት እኩልነትን ማየት የናይሻው የጽንፈኞች መሪ የሆነው መምህር ፋንታሁን ዋቄ በሚዲያ ቀርቦ በግልጽ እንደመሰከረው፣ ፋኖ በብሔር ስም የተደራጀ የሃይማኖት ታጣቂ ነው።

የሙስሊሞች ገዳይነት ያለው በጥላቻና በእብሪት በተሞላው አዕምሮ ዉስጥ እንጂ በኢትዮጵያ በሙሉ በታዩና እየታዩ ባሉ የጅምላ ግድያና እልቂት ዉስጥ የለም። ታዲያ ዛሬ ላይ ገዳዩና ጨፍጫፊው ማን ነው? ትናንት ሰላማዊነቱን በተግባር ያስመሰከረው ሙስሊም ወይስ ዛሬ በገዛ ቪዲዮው ጭካኔውን እያሳየ ንጹሐንን የሚጨፈጭፈው ታጣቂ? መልሱን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የዛሬው እውነትም በግልጽ እየመሰከረው ነው።

«ፀረ-ኢትዮጵያ»
💥💥💥💥💥

«ፀረ-ኢትዮጵያ» ማለት የሀገርን የጋራ ህልውና፣ ሰላምና ዘላቂ ኅብረት የሚጻረር፣ ለሀገር ውድቀትና መፈራረስ የሚሠራ ኃይል ነው። ትናንት የኢትዮጵያዊነት ብቸኛ ደረጃ መዳቢዎች እነሱ ብቻ በነበሩበት ወቅት፣ የፌስቡክ ገጼ ላይ ሳይቀር የመብትና የፍትሕ ድምፅ ባሰማን ቁጥር «ፀረ-ኢትዮጵያ» እያሉ ያወግዙን ነበር። ዓላማቸውም የእኩልነት ጥያቄያችንን በሀገር ጠላትነት አስፈርጀው ለማዳፈን ነበር።

ትናንት እኛን «ፀረ-ኢትዮጵያ» እያሉ ያለምክንያት ሲፈርጁ የነበሩት አካላት፣ ዛሬ «እኔ ከሞት ሰርዶ አይብቀል» አይነት አካሄድን በመምረጥ ትናንት ለኢትዮጵያ አንድነት ተቆርቋሪ መስለው ሲሰብኩ የነበሩት፣ ዛሬ «ኢትዮጵያ» የሚል ስም ያለው እንቅስቃሴ ወይም ፓርቲ በሰፈራችን ማለፍ አይችልም እያሉ ሲያግዱና በጠላትነት ሲፈርጁና ሲዝቱ እናያለን።

ሀገር ወዳድነት ማለት የራስን አመለካከት በሌላው ላይ በግድ መጫን አይደለም። ሀገር የሁሉም ዜጎች እኩል መኖሪያ እንጂ የአንድ ቡድን የግል ርስት አይደለችም። «የእኔ ፍላጎት ካልተሳካ ኢትዮጵያ ምኔ ናት?» የሚል አቋም መያዝ የፀረ-ኢትዮጵያዊነት ትክክለኛ መገለጫ ነው።

መንግሥትን መቃወም የዴሞክራሲ አካል ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን «እኔ ካልገዛኋት ሀገሪቱ ትፍረስ» ማለት በቀጥታ የሀገር ጠላት መሆን ነው። የሀገርን አንድነት መሠረት የሚንድ ጽንፈኝነት የትም አያደርስም።

ኢትዮጵያ የጋራ ሀገራችን ናት፤ ኢትዮጵያዊነትም የሁላችንም የጋራ ማንነት ነው። ይሄ ማንነት ደግሞ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እኩል የማይወክልና በአንድ ወገን መልክ ብቻ የተጠረዘ ሊሆን አይችልም፤ አይገባውምም።

ኢትዮጵያ በሁሉም ነገር አካታች እንድትሆን፣ ፍትሕ እንዲሰፍንባትና የሁላችንም ቤት እንድትሆን መጠየቅ የጠለቀ የሀገር ፍቅር እንጂ በምን ተአምር «ፀረ-ኢትዮጵያዊነት» ሊሆን ይችላል? እውነተኛ ፀረ-ኢትዮጵያ ማለት እኮ ሀገሪቱ በጽኑ አንድነት ቆማ በልጆቿ ሁሉ እንድትወደድ የሚያደርገውን አካታችነት መግፋትና ወደ ማያባራ ቀውስና ውድቀት የሚወስዳትን ጠባብ መንገድ መከተል ነው።

እውነተኛ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ማለት ሀገሪቱን የአንድ ወገን ብቻ አድርጎ ሌላውን እንደ ባይተዋር ማየትና የዜጎችን ሕጋዊ የመብት ድምፅ በጠላትነት ማፈን ነው። ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ማለት ሀገሪቱ በፍትሕና በእኩልነት ቆማ በልጆቿ ሁሉ እንድትወደድ የሚያደርገውን አካታች መንገድ ገፍቶ፣ ወደ ማያባራ እልቂትና ውድቀት የሚወስዳትን የጥፋት ጎዳና መከተል ነው።

«ኦነግ»
♦♦♦

«ኦነግ» የሚለው ታርጋ ለዓመታት በአንዳንድ አካላት ዘንድ እንደኔ ላሉ የመብት ጠያቂ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆዎችን ለማሸማቀቅና ስም ለማጥፋት የሚመዘዝ የተለመደ ካርድ ሆኖ ቆይቷል። ትናንት በወለጋ፣ በአርሲ ወይም በሌሎች አካባቢዎች ጥቃት በተፈጸመ ቁጥር፣ በማኅበራዊ ሚዲያ በምንጽፋቸው ጽሑፎች፣ ሌላው ቀርቶ ለንጹሐን ወገኖቻችን ሞት ከልብ በመነጨ በጻፍነው የሐዘን መግለጫ ሥር ጭምር እየገቡ «ኦነግ! የእጅህን ታገኛለህ!» እያሉ በተደራጀ መንገድ ይዘምቱብን ነበር። ዓላማቸው ግልጽ ነበር፤ የምናነሳውን የፍትሕና የእኩልነት ድምፅ በፖለቲካ ፍረጃ አጠልሽተው ማፈን።

ትናንት እኛን በጠላትነት ፈርጀው «ኦነግ» ሲሉ የነበሩት ሰዎች፣ ዛሬ ለሥልጣን ፍላጎታቸው ሲሉ ከኦነግ-ሸኔ ጋር ግንባር መፍጠራቸውን በይፋ ሲያውጁ ማየት እጅግ ይገርማል። ትናንት ከእርሱ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ላልነበረኝ ለኔ «የኦነግ ደጋፊ» የሚል ታርጋ የለጠፉብኝ አካላት፣ ዛሬ በተገላቢጦሹ ዞረው ኦነግ-ሸኔን «በክፉ ያነሳ ጠላታችን ነው» እስከማለት ደርሰዋል።

ይህ ነገር በኔ ላይ የተከፈተው ዘመቻ ሁሉ የፈጠራና የስም ማጥፋት ሸፍጥ እንደነበር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ትናንት ንጹሐን ሲገደሉ የኦሮሞ ተወላጅ በመሆኔ ብቻ «አንተ የኦነግ ደጋፊ ነህ፤ የእጅህን ታገኛለህ!» እያሉ የዛቱብኝ ሁሉ፣ ዛሬ ምንም እንዳልተፈጠረ ሆነው ቀርበዋል። «ተሳስተናል» ብለው እውነቱን ሳይናገሩ፣ በኔም ሆነ በሌሎች ላይ ላደረሱት የስም ማጥፋት አንዲት ቃል ይቅርታ ሳይጠይቁ፣ ለደገፋቸውም ሕዝብ ምንም ሳያብራሩ ዛሬ ለሥልጣን ሲሉ ከዚያው አካል ጋር ግንባር መፍጠራቸው የታሪክ ትልቅ ምጸት ነው።

የሥልጣን ጥምና ጉጉት አደገኛ ነገር ነው። መርህ ሲጠፋ ሰውን ክብሩን አስጥሎ የገዛ ቃሉንና ኅሊናውን እንዲክድ ያደርገዋል። ትናንት በኔ ላይ የከፈቱት የማጠልሸት ዘመቻ የፖለቲካ ሴራ እንጂ እውነት እንዳልነበር ዛሬ አደባባይ ወጥቷል። በኔ ላይ ላካሄዱት የሐሰት ውንጀላ ቅንጣት ታህል ጸጸት ሳይሰማቸው፣ ትናንት የረገሙትን ዛሬ ለሥልጣን ሲሉ ማወደስ የሞራል ውድቀትና የፖለቲካ ክስረት እንጂ ለሕዝብ የሚፈይደው ምንም ነገር የለም።

ታዲያ ዛሬ ላይ ከኦነግ ጋር ግንባር የፈጠረው ማን ነው? ትናንት በሐሰት ስም ሲለጠፍበት የነበረው ሰላማዊው ሙስሊም ወይስ ዛሬ ለሥልጣን ሲል ከኦነግ-ሸኔ ጋር ጥምረት የፈጠረው አካል? መልሱን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የዛሬው እውነትም በግልጽ እየመሰከረው ነው።

«ወሃቢያ»
🔴🔴🔴🔴

«ወሃቢያ» የሚለው ታርጋ በሀገራችን የሙስሊሙን ማኅበረሰብ የመብትና የእኩልነት ድምፅ ለማፈን የተለመደ የማሸማቀቂያ ካርድ ሆኖ ቆይቷል። ትናንት የኔ የፌስቡክ ገጽ ኮመንት ላይ ሳይቀር እኔንም ሆነ ሌሎችን «ወሃቢያ» እያሉ በጅምላ ይፈርጁን የነበረው ያለምክንያት አይደለም። አንድ ሙስሊም ስለ ዜግነት መብቱ ሲጠይቅ፣ «ሂጃብ አድርጋችሁ መማር አትችሉም፤ አዛን ማሰማት ክልክል ነው» ሲባል «ለምን?» ብሎ ሲከራከር፣ አክሱም ላይ የሙስሊሞች መብት እንዲከበር ሲጠይቅ፣ አሊያም ያቃጠሏቸውን መስጂዶች ጉዳይ አንስቶ ወገኑ ሲበደል ድምፁን ሲያሰማ ወዲያውኑ «ወሃቢያ» የሚል ስም ይለጠፍበታል። ዓላማቸው እጅግ ግልጽ ነበር፤ የምናነሳውን ሕጋዊና ሰላማዊ የመብት ጥያቄ «ከውጭ የመጣ አክራሪነት» አስመስሎ በማቅረብ ሕዝቡን ማሸማቀቅ፣ በሃይማኖታዊ ንትርክ እርስ በርሱ ማባላትና ፍትሐዊ ጥያቄውን በጸጥታ ስጋትነት ፈርጆ ማዳፈን።

እኛ ፍጹም ሰላማዊና ሕገ-መንግሥታዊ የእኩልነት ጥያቄ ስናነሳ «አክራሪ» ያደረጉን እነዚሁ አካላት፣ በብሔር ስም ቢደራጁም ከመንግሥት ጋር በሚያደርጉት የተዘዋዋሪ ድርድር ጭምር ዋነኛ አጀንዳቸው ስለ ብሔሩ ሳይሆን ስለ እምነታቸውና «ቤተክርስቲያን ተገፋች» የሚል ሆኖ ማየታችን እውነተኛ ማንነታቸውን ያጋለጠ ነው። ሌላው ቀርቶ በአርሲም ሆነ በሌላ አካባቢ በታጣቂዎች ንጹሐን ሲገደሉ እንኳ፣ እውነታውን አድበስብሰው «የወሃቢያ ሥራ ነው» እያሉ በሕዝብ መካከል የጥላቻ እሳት ሲያነዱ ማየት የዚሁ አደገኛ ሴራ ማሳያ ነው።

የፍረጃው ዓላማ ዘመናት ቢቀየሩም አልተለወጠም ፤ ሙስሊሙን በገዛ ሀገሩ እንደ ባይተዋር በመሳል ስለ መብቱ እንዳይጠይቅ አንገቱን ማስደፋት። ትናንት በኢትዮጵያ ምድር ለዘመናት በሰላም የኖረውን አማኝ «አክራሪ ናችሁ» እያሉ ሲያጠለሹ የነበሩት ሰዎች፣ ያነሳነው ጥያቄ ሕግ እንደጣሰ የምታሳይ አንዲት ማስረጃ አላቀረቡም። እኛ የጠየቅነው ፍትሕ፣ የመስጂድ ክብርና የዜግነት እኩልነት እንጂ የማንንም እምነት የመንካት አጀንዳ አልነበረንም።

ሃይማኖተኛ መሆንና ሃይማኖትን ለጥላቻ ፖለቲካ መሣሪያ ማድረግ ፈጽሞ አይገናኙም። የራስን እምነት አጥብቆ መያዝና ስለ ወገን መብት በሰላማዊ መንገድ መሟገት ዜግነታዊ መብት እንጂ አክራሪነት ሊሆን አይችልም። እውነተኛው ጽንፈኝነት የራስን እምነት በጠመንጃ በሌላው ላይ ለመጫን መሞከር ነው።

ዛሬ ላይ መምህር ፋንታሁን ዋቄ በሚዲያ ወጥቶ በግልጽ እንደነገረን፣ በሃይማኖት ዓላማ በብሔር ስም ተደራጅተው፣ ከቤተ እምነታቸው ጭምር መሣሪያ ታጥቀው ማይክ ይዘው ሲናገሩና በየጫካው ሲፎክሩ ስናይ፣ ትናንት እኛን «ወሃቢያ» እያሉ ያጠለሹት ለካስ በውስጣቸው የተሸከሙትን እውነተኛውን አክራሪነት ለመሸፈን እንደነበር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

ታዲያ ዛሬ ላይ አክራሪውና ጽንፈኛው ማን ነው? «እምነቴ ይከበር፤ ሀገሬም የሁሉም እኩል ቤት ትሁን» ብሎ ሰላማዊውን መንገድ የሙጥኝ ያለው ሙስሊም ወይስ ሃይማኖትን የፖለቲካ ዱላ አድርጎ በብሔር ስም የታጠቀው ጽንፈኛ አካል? መልሱን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የዛሬው ነባራዊ እውነትም በግልጽ እየመሰከረው ነው።

ፍረጃዎቹ እንደ መስታወት
🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈

ከላይ ያየናቸው ሁሉ ተደማምረው አንድ ግልጽ እውነት ያሳየናል፤ ትናንት በኔም ሆነ በመብት ጠያቂው ሙስሊም ወገን ላይ የተለጠፉት ሰባቱም መርዘኛ ታርጋዎች፣ የፍትሕና የእኩልነት ድምፃችንን ለማፈን የታለሙ የፈጠራ ሴራዎች እንጂ ቅንጣት ታህል እውነት አልነበራቸውም።

የሥልጣን ጥማት ደግሞ መርህና ኅሊና ሲጎድልበት ሰውን እንዴት እርቃኑን እንደሚያስቀረው ዛሬ በገሃድ እያየነው ነው።

ትናንት ሌላውን ለማጥቆር የተመዘዙት «ባንዳ»፣ «ተላላኪ»፣ «ዘረኛ»፣ «ገዳይ»፣ «ፀረ-ኢትዮጵያ»፣ «ኦነግ» እና «ወሃቢያ» የሚሉት ፍረጃዎች፣ ዛሬ ዞረው የከሳሾቹን እውነተኛ ገጽታ የሚያሳዩ መስተዋቶች ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዛሬ ማን ማን እንደሆነ በደንብ ለይቶ አውቋል። ማን ለሀገር ሰላም፣ ለፍትሕና ለሕዝብ እኩልነት እንደሚቆም፤ ማን ደግሞ ለወንበርና ለጠባብ ቡድን የበላይነት ሲል ከሀገር ባላንጣ ጭምር ተሻርኮ ሀገር እንደሚያፈርስ አደባባይ ላይ የወጣው እውነት እየመሰከረ ነው። ፍረጃና የስም ማጥፋት የጊዜ ጉዳይ እንጂ የትም አያደርስም፤ እውነት ግን ምንም ብትዘገይ የገዛ ቃላቸው እያሳደደ አደባባይ ላይ ፍርዱን መስጠቱ አይቀርም።
ለዛሬ አበቃሁ።ቸር እንሰንብት።

ሰላም ለኢትዮጵያ፣ሰላም ለሀገሬ!

📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶

💥 የአሕመዲን ጀበል የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀሉ! ሊንኩ ከሥር በአስተያየት መስጫው ስር ተጠቅሷል።👇

09/24/2026

Dargaggoo fii Shamarran

09/11/2026
09/10/2026
09/08/2026
SubhanAllah, kaleysuma ture Haji Risala International kan isaan badhaasee. Rabbi Rahmta haagodhuuf
09/05/2026

SubhanAllah, kaleysuma ture Haji Risala International kan isaan badhaasee. Rabbi Rahmta haagodhuuf

Address

Minneapolis, MN

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Risala International posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share