Ermiyas Girma

Ermiyas Girma "እኔ ታናሽና የተናቅሁ ነኝ ትእዛዛትህን ግን አልረሳሁም"
መዝ:- 118 - 141
(4)

የሐሙስ ሰይፈ ሥላሴ  (መቅድሙና የዘወትሩ ከበታች ተካቷል)አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በእውነት አምናለሁ። ፩. ልዩ በሆነ ስጦታ ስለተሰጠኝ ጸጋና ቍጥር የሌለውን...
09/02/2026

የሐሙስ ሰይፈ ሥላሴ (መቅድሙና የዘወትሩ ከበታች ተካቷል)

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በእውነት አምናለሁ።

፩. ልዩ በሆነ ስጦታ ስለተሰጠኝ ጸጋና ቍጥር የሌለውን ቸርነቱንና በረከቱን በኔ ላይ ላበዛ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀርባለሁ።
፪. አቤቱ እምነቴ በአንተ ላይ ነው አቤቱ ጠብቀኝ እንጂ አትጣለኝ አንተን ተስፋ የሚያደርጉትን ሁሉ አትጥላቸውምና።
፫. አቤቱ ደካማነቴንና ውርደቴን ተመልክተህ በደሌንና ኃጢአቴን ይቅር በል።
፬. አቤቱ ፈቃድህን እፈጽም ዘንድ በቀናች ጐዳና ምራኝ ፍላጐቴንም አሟላልኝ።
፭. አቤቱ ከጠላቶቼና በኔም ላይ ተንኮል ከሚያስቡ ሁሉ አድነኝ። ሰይጣንና ሠራዊቱንም ሁሉ ከኔ አርቅ።
፮. አቤቱ ፍጹም ንስሐን ስጠኝ ኃጢአቴንም አስተሥርይልኝ ዳግም በምትመጣበትም ጊዜ ይቅር በለኝ በጐ ነገር ካልሠሩ በስተቀር የሠራዊት ብዛት ወይም ገንዘብና ልጅ አንደማይጠቅሙ አውቃለሁና።
፯. አቤቱ በችግሬ ጊዜ ፈጥነህ አድነኝ የአብርሃምና የልጆቹንም በረከት በኔ ላይ አሳድር።
፰. አቤቱ በመዓልትና በሌሊት በጠዋትና በማታ ከዕለት እኪት ሰውረኝ ከአመፀኛና ከተንኮለኛም ሰው አድነኝ።
፱. አቤቱ ልቡናዬን ከክፉ ሐሳብ ንጹሕ አድርግልኝና በቅድስት ጥምቀትህ ከተጠመቁ ወዳጆችህ ጻድቃን ጋራ አንድ አድርገኝ።
፲. አቤቱ በእኔ ላይ ባመጣኸው ነገር ማለት ረሀብ ወይም ጥጋብ ሕይወት ወይም ደዌ ደስታ ወይም ሐዘን በመሳሰሉትም ሁሉ አንተን ፈጽሜ አመሰግናለሁ።
፲፩. አቤቱ ፈጣሪየ እግዚአብሔር ሆይ ፊትህን ከእኔ አትመልስ ቸርነትህንም ከላዬ ላይ አታርቅ፤ አቤቱ አምላኬ ሆይ ከገሃነም እሳት አድነኝ።
፲፪. አቤቱ ፈቃድህ በቅዱሳኖችህ ላይ እንደሆነ ሁሉ እናትና አባቴንም ይቅር ትላቸው ዘንድ ፈቃድህ ይሁን ሁሉ ይቻልሃልና።
፲፫. ለጌትነትህ ፍጹም ምስጋና ይገባል ለዘላለሙ አሜን።
፲፬. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በፍጹም አካሉ ሦስት ሲሆን በባሕርዩ ግን አንድ አምላክ ነው።
፲፭. ሦስት የብርሃን አዕማድ በመጠን ወይም በባሕርይ ግን አንድ ነው።
፲፮. ሦስት የመባርቅት ብልጭታ ሦስት ነጐድጓድ ነገር ግን በአንድ ድምፀ ግርማ የተጠቃለለ።
፲፯. ሦስት የእሳት ባሕርይ ነገር ግን አንድ ብርሃን።
፲፰. አብ እሳት ነው ወልድ እሳት ነው መንፈስ ቅዱስ እሳት ነው የሙቀት ባሕርያቸው ግን አንድ ነው።
፲፱. አብ ነድ ነው ወልድ ነድ ነው መንፈስ ቅዱስ ነድ ነው የብርሃን ነፀብራቃቸው ግን አንድ ነው።
፳. አብ ፍሕም ነው ወልድ ፍሕም ነው መንፈስ ቅዱስ ፍሕም ነው፤ የግለት ባሕርያቸው ግን አንድ ነው።
፳፩. አብ ነበልባል ነው ወልድ ነበልባል ነው መንፈስ ቅዱስም ነበልባል ነው ብርሃናቸው ግን አንድ ነው ለዘላለሙ ፈጽሞ የማይደርቅና የማይጐድል የቸርነታቸው ባሕርና የይቅርታቸው ምንጭ አንድ ነው።
፳፪. የገዥነታቸው ሥልጣን አንድ የሆነ ሦስት ልዑላን ገዥዎች ናቸው።
፳፫. የትእዛዛቸው ባሕርይ አንድ የሆነ ሦስት ጌቶች ናቸው።
፳፬. ሦስት ገጽ አንድ አመለካከት (ባሕርይ) ናቸው።
፳፭. ሦስት አካል አንድ አምሳል ናቸው።
፳፮. ሦስት ነገሥታት አንድ አገዛዝ ናቸው።
፳፯. ለመንግሥታቸው የጊዜ ገደብ ወይም ፈረቃ የለውም ሥልጣናቸውና የጌትነታቸው ክብር አንድ ነው እንጂ።
፳፰. እነሆ በዚህ አብ በሚከበርበት ገንዘብ ወልድ ይከበራል መንፈስ ቅዱስም ይከበራል።
፳፱. ወልድ በሚከበርበት ገንዘብ አብ ይከበራል መንፈስ ቅዱስም ይከበራል።
፴. እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ በሚከበርበት ገንዘብ አብ ይከበራል ወልድም ይከበራል።
፴፩. በቅዱስ መጽሐፍ ወልድን የሚያከብሩት ሁሉ እንደዚሁ አብን ያከብሩታል ወልድን የማያከብረው ግን የላከው አብን አላከበረውም ተብሎ ተጽፎአልና።
፴፪. ሃይማኖት ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ ትታሰባለች በወልድ ትዘጋጃለች በመንፈስ ቅዱስ ትፈጸማለች።
፴፫. በቅድስት ሥላሴ እምነት መሠረት ትጸናለች።
፴፬. የቅድስት ሥላሴ እምነት የሃይማኖት መጨረሻ ናት።
፴፭. እሊህን የሥላሴን ሦስትነት የሚክድ የሥላሴ መዓት በላዩ ላይ ይወርድበታል።
፴፮. በሥላሴ የሚያምን ግን ጽኑዕ የሥላሴን ተስፋ ያገኛል።
፴፯. የሥላሴ እምነት መግቢያ በር ወልድ ዋሕድ ብሎ ማመን ነው።
፴፰. በቅዱስ ወንጌል በወልድ ያመነ የዘለዓለም ሕይወት አለው ተብሎ እንደተጻፈ።
፴፱. ወልድን የካደ አብን ወይም መንፈስ ቅዱስን ካደ ማለት ነው።
፵. ለዓለሙ ሁሉ ሕይወት ይሆን ዘንድ አንድነቱ ከሱ ሳይለይ አካላዊ ቃሉን በላከ በአብ አምናለሁ።
፵፩. ከአባቱ አንድነት (አጠገብ) ሳይለይ ዓለሙን ሁሉ ለማዳን በተላከ በወልድ አምናለሁ።
፵፪. ዓለምን በመላ ይቀድሳት ዘንድ ከአብ በወጣ ከወልድ በተገኘ (ከወልድ ዘንድ ባለ) በመንፈስ ቅዱስም አምናለሁ።
፵፫. እነሆ እሱም ጰራቅሊጦስ የንጽሕናና የቅድስና መንፈስ ነው።
፵፬. ጰራቅሊጦስ የስጦታ ምንጭ ነው፤ ጰራቅሊጦስ ተቀድቶ የሚጠጣ የዕውቀት መጠጥ ነው፤ ጰራቅሊጦስ ዕድፍን የሚያነፃ ውሃን የሚቀድስ ነው።
፵፭. ጰራቅሊጦስ የሃይማኖትን አልጫነት የሚያጣፍጥ የልቡና ጨው ነው፤ ጰራቅሊጦስ በጭለማ ላሉ የሚያበራ የይቅርታ ብርሃን ነው።
፵፮. ጰራቅሊጦስ በምሥጢረ ቍርባን ላይ የሚረብ ጸዓዳ መለኮታዊ ርግብ ነው፤ ጰራቅሊጦስ የይሁዳ ኮረብቶች በጽዮን አዳራሽ የሚጠጡት የእሳት ጐርፍ ወይም ፈሳሽ ነው፤ ጰራቅሊጦስ ድንጋዮችን የሚፈረካክስ የእሳት መዶሻ ነው።
፵፯. ጰራቅሊጦስ አሸናፊ ነው ለሰማዕታት መመኪያ የተሰበሩትን የሚጠግን ነው።
፵፰. ጰራቅሊጦስ ፍጹም የከበረ የአብና የወልድ የባሕርይ ሕይወት ነው።
፵፱. ጰራቅሊጦስ መጉደል ወይም መጨመር ሳይኖርበት በህልውናው አምላክ ነው።
፶. ጰራቅሊጦስ እንደ አብና እንደ ወልድ በሰማየ ሰማያት በምድርም ሁሉ ላይ መንግሥቱ የመላ ነው።
፶፩. ጰራቅሊጦስ የማይዳሰስ የእሳት ነበልባል ነው።
፶፪. ጰራቅሊጦስ የነፍስና የሥጋ ጽንዕ ነው።
፶፫. ጰራቅሊጦስ የወርቅ ሐር ግምጃ የቅዱሳን የጌጣቸው ልብስ ነው።
፶፬. ጰራቅሊጦስ የጻድቃን የባለሟልነታቸው የራስ ወርቅ ነው።
፶፭. ጰራቅሊጦስ የምስራችን በመያዝ ከኢየሩሳሌም ወደ ፋርስ የተላከ ንስረ ትንቢት ነው።
፶፮. ጰራቅሊጦስ በጽዮን አደባባይ በቶማስ ላይ በቅዱስ ነቢይ ፊት የበራ ነው።
፶፯. ጰራቅሊጦስ ሐዲስ ወንጌልን ያስተምር ዘንድ ጳውሎስን የጠቀሰ የሕይወት መብረቅ ነው።
፶፰. ጰራቅሊጦስ ሐዋርያትን የወይን ጠጅ ሳይጠጡ ያሰከረ ነው።
፶፱. ጰራቅሊጦስ ሐዋርያትን በሀገሩ ሁሉ ያናገረ ነው።
፷. ጰራቅሊጦስ ቅድስት ለምትሆን ሦስትነቱ እንሰግድ ዘንድ ያስተምረናል ይመክረናል።
፷፩. ቅድመ ዓለም ለነበረ ፍጹም አንድነቱ ለሱ ስግደት ይገባል ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
፷፪. በነቢያት አንደበት የወልድን መምጣት መነገርና በአቸናፊው በእግዚአብሔር ቀኝ ባለ የጌትነቱ ዙፋን ሳይለይ ወደዚህ ዓለም መላኩን አምናለሁ።
፷፫. ያለ ዘርዐ ብእሲ በቅድስት ድንግል ማርያም ማሕፀን ማደሩን አምናለሁ።
፷፬. ከላይ ሳይጐድል ማሕተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ በማይመረመር ድንቅ ምስጢር ወለደችው።
፷፭. ያለመጨመር ወይም ያለመጉደል ሥጋ ከመለኮት ጋር ፍጹም እንደ ተዋሐደ አምናለሁ።
፷፮. ከተሠወሩ የተሠወረ እሱ በሥጋ መገለጹን አምናለሁ።
፷፯. እሱ የቅዱሳን መገኛ ምንጭ ሲሆን እንደ ኃጥኣን ጥምቀቱን በውሀ አደረገ።
፷፰. ይህን ሃይማኖት በፍፁም ልቡናየ አምኜ በዮርዳኖስ ባሕር በተገለጠው ሦስትነቱ አመልካለሁ ቅዱስ ወንጌል እንደተናገረ እንዲህ ሲል።
፷፱. ጌታ ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ ከባሕሩ ወጣ ሰማይም ተከፈተ።
፸. በዚህን ጊዜ በነጭ ርግብ አምሣል መንፈስ ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ።
፸፩. እነሆ አብ ስለ ልጁ እንዲህ ሲል መሰከረ ይህ የምወልደው የምወደው ልጄ ነው ስለሆነም እሱ የሚነግራችሁን ስሙት አለ።
፸፪. እንግዲህ የዚህ የሥላሴ የማይከፈል የማይለይ መለኮት እነሆ ተገለጸ ሥላሴን አንድ ገጽ ነው የሚሉ የርጉም ሰባልዮስ ልጆች ይፈሩ ይዋረዱ።
፸፫. ወልድ በደብረ ታቦር ተራራ ላይ መልኩ እንደተለወጠና ፊቱም እንደ መብረቅ ብርሃን በበራ ጊዜ ዳግመኛ ይህ ሦስትነት ታወቀ ተረዳ።
፸፬. እነሆ በሁለቱ መልክተኞች ነቢያትና በሦስቱ ሰባክያን ሐዋርያቶች ፊት ልብስ አጣቢ እንደዚህ አድርጐ ሊያነፃው በማይቻል ሁኔታ ልብሱ እንደመብረቅ ብልጭታ አንጸባርቋልና።
፸፭. በዚያም ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በነጭ ርግብ አምሳል ወረደ ፤ አብም የእውነት ምስክር በመሆን ሰዎች እስኪሰሙ ድረስ እሱ ወልድ አባት ሆይ ልጅህን አክብረው ባለው ጊዜ እንደ ቀድሞው ልጁን አከበረው።
፸፮. ከዚህም በኋላ ቅድመ ዓለም ከኔ ዘንድ ባለህ ክብር ዛሬም ክብርህን እመሰክራለሁ የሚል ቃል ከደመና መጣ።
፸፯. በዚያም የነበሩ ወይም የቆሙ ሰዎች ሰምተው ነጐድጓድ ነው ተባባሉ።
፸፰. መልአክ ነው የተነጋገረው ያሉም አሉ።
፸፱. የሥላሴ አንድ አምላክ መሆን በዚህ ግብር ታወቀ ተረዳ።
፹. የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሥርዓት በዚህ የሥላሴ አርአያ ተመሠረተ።
፹፩. ሥላሴ የክርስቲያን ጥንታዊ የሃይማኖታቸው ማረጋገጫ የብርሃን ማኅተም ነው።
፹፪. ሥላሴ ከዘመናትና ከአዝማናት በፊት አሉ።
፹፫. ሥላሴ አዳምን በመፍጠራቸው ሦስትነታቸው ታወቀ።
፹፬. ሥላሴ የሰናኦርን ሰዎች ቋንቋ በመለያየታቸው ሦስትነታቸው ታወቀ።
፹፭. የሥላሴ ሦስትነትና አንድነት በአብርሃም ቤት ታወቀ።
፹፮. የሥላሴ ሦስትነታቸው በዮርዳኖስ ታወቀ።
፹፯. የሥላሴ ሦስትነት በታቦር ተራራ ላይ ታወቀ።
፹፰. በዚህች በቅድስት ሥላሴ እምነት ልዩ ሦስት የሚሆን እሱ የቸርነት በሩን ይከፍትልኝ ዘንድ ኃጥእ የምሆን እኔ እማፀናለሁ ነፍስና ሥጋዬን አደራ አስጠብቃለሁ።
፹፱. ሥላሴ የሐዲስ ሥርዓት ዘመን ከመመሥረቱ በፊት በብሉይ ዘመነ ሕግ የታወቀ ነው።
፺. ስለዚህም ከነቢያት ወገን የፈጠረህና ያጸናህም እሱ አብ ነው ሲሉ የተናገሩ አሉ።
፺፩. ስለ ወልድም ሕፃን ተወለደልን ወልድም ለኩነተ ሥጋ ተሰጠልን በማለት የተናገሩ አሉ።
፺፪. ዳግመኛ ስለመንፈስ ቅዱስም ቅዱስ መንፈስህ በጽድቅ ጐዳና ይምራኝ ሲሉ የተናገሩ አሉ።
፺፫. እነሆ ይህ የሥላሴ ስም ቅድመ ዓለም እንደ ነበረና እስከ ዘለዓለምም የሚኖር መሆኑ ታወቀ ተረዳ።
፺፬. የአብ ስም ከፀሐይ ፍጥረት በፊት የነበረ ነው።
፺፭. የወልድ ስም ከፀሐይ መገኘት በፊት የነበረ ነው።
፺፮. የመንፈስ ቅዱስም ስም ከፀሐይ ተፈጥሮ በፊት የነበረ ነው።
፺፯. ከፍጥረተ ፀሐይ በፊት ስሙ የነበረ ነው ተብሎ በነቢያት ተነግሯልና።
፺፰. ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም ለታመኑ የሕይወት መታወቂያ ማኅተም ነው ለዝንጉዎች ግን የጥፋታቸው ቁልፍ ነው።
፺፱. ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የሕሙማን መፈወሻ የክፉዎች አጋንንት ማባረሪያ ነው።
፻. ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የአስማተኞችን ወይም የጠንቋዮችን ጥበብ የሚያጠፋና የሟርተኞችን መርዝ የሚያበርስ (የሚያከሽፍ) ነው።
፻፩. ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የበሽተኞች መድኃኒት የሙታን ትንሣኤያቸው ነው።
፻፪. ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም አሸናፊ የሆኑ የሰማዕታት የገድላቸው ሞገስ የብሩካን ጻድቃን የጸሎታቸው የመልካም መዓዛ ሽታ ነው።
፻፫. ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የረከሱትን የሚቀድሳቸው የተዳደፉትን የሚያነጻቸው ነው።
፻፬. ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም እንደ መጐናጸፊያ እጐናጸፈዋለሁ ከዕንቁ እንደ ተሠራ እንደ እራስ ወርቅም እቀዳጀዋለሁ።
፻፭. በዚህ ግሩም በሆነ የሥላሴ ስም እታመናለሁ በመጐንበስም እሰግድለታለሁ።
፻፮. ለዚህ ግሩም አስፈሪና አስደንጋጭ ለሆነ የሥላሴ ስም በፊቱ ተንበርክኬ በደስታ እሰግዳለሁ።
፻፯. ቅዱሳን ካሉበት ያገባኝ ዘንድ በዚህ ግሩም በሚሆን በሥላሴ ስም እማፀናለሁ ነፍስና ሥጋዬንም አማፅናለሁ ይህችውም ለዘላለሙ የጽዮን ብርሃን የሚያበራባት ሰማያዊት አዳራሽ ነች።
፻፰. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው በወዳጃቸው . . . ላይ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

ተአምር፦

፩. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው በወዳጃቸው ላይ ይደርና ሥሉስ ቅዱስ ያደረጉት ተአምራት ይህ ነው።
፪. የሃይማኖትን ሕግ የደነገጉ እሊህ ሦስት መቶ ዓሥራ ስምንት ሊቃነ ጳጳሳት ስለሃይማኖት ጉዳይ ከከሐዲው አርዮስ ጋር ክርክር በጀመሩ ጊዜ።
፫. እነሆ ሥላሴ በአንድነት ክቡራን በሚሆኑ ሊቃውንቶች ስብሰባ መካከል ተገኙ፤ ተቀመጡ።
፬. ከዚህ በኋላ ከሐዲው አርዮስ ለሦስት መቶ ዓሥራ ስምንት ሊቃውንት ወልድ እኮን ቅድመ ዓለም ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አልነበረም አላቸው።
፭. ሦስት መቶ ዓሥራ ስምንቱ ሊቃውንትም ሕግ ተላላፊውና ከሐዲው አርዮስ ሆይ ስለዚህ ነገር የምንሰጥህን መልስ በፀጥታ አዳምጥ አሉት።
፮. ወልድስ ያለምንም ጉድለት እና ልዩነት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፯. አብ በህልውናው አምላክ ሲሆን በደላችንን ይቅር ይለን ዘንድ አንድ ልጁን ላከልን።
፰. ወልድም በህልውናው አምላክ ሲሆን ስለኛ እንደ የዋህ በግ ተሰዋልን።
፱. ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙንም ሰጠን ሥጋው የእውነት መብል ደሙም የሕይወት መጠጥ ነው በእውነት።
፲. አርዮስም እሊህን ሊቃውንት ወንድሞቼ ሆይ ትሰሙኝ እንደሆነ ልንገራችሁ አላቸው።
፲፩. ወልድን ከኛ የነሣው ሥጋ ሩቅ ብእሲ አደረገው ከአብ ቀኝና ከመንፈስ ቅዱስ አንድነት ለይቶታልና።
፲፪. ይህም ከቅድስት ድንግል ማርያም የለበሰው ሥጋ ሐሞት አጠጥቶ ለሞት አደረሰው እንጂ ለሕይወት አልሆነውም።
፲፫. ከሞተም በኋላ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ግንኙነት አላደረገም ከነእርሱ ጋር የመለኮት አንድነት የለውምና አላቸው።
፲፬. ሦስት መቶ ዓሥራ ስምንት ሊቃውንትም አንት ከሐዲ ከልብህ አድምጥ መጽሐፍ የተናገረውን እናመጣልሃለን ወይም እናስረዳሃለን።
፲፭. የሰውን ልጅ ሥጋውን ካል በላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ የዘለዓለም ሕይወት የላችሁም።
፲፮. ዳግመኛም ሥጋዬን የእውነት መብል ደሜም የሕይወት መጠጥ ነው ብሏልና አሉት።
፲፯. አርዮስም ሦስት መቶ ዓሥራ ስምንቱን ሊቃውንት ሥጋውንና ደሙን መቼ ነው የሰጣችሁት ከመሰቀሉ በፊት ነው ወይስ ከስቅለቱ በኋላ ሥጋውንና ደሙን ሊሰጣችሁ የመጣ ከሆነስ በሱ ዙፋን ላይ ማን ተቀመጠ አላቸው።
፲፰. ሦስት መቶ ዓሥራ ስምንቱ ሊቃውንትም አርዮስ ሆይ ኤጲፋንዮስ በመጽሐፉ ሐሙስ ማታ ለዓርብ አጥቢያ ጌታ በወዳጁ በአልዓዛር ቤት ገብቶ ተቀምጦ በእራት ላይ ሳለ ለወንድሞቹ ለሐዋርያት ኅብስቱን በሥጋው ወይኑን በደሙ ለውጦ ሰጣቸው ብሎ የተናገረውን አልሰማህምን አሉት።
፲፱. ቄርሎስም [ኋላ ዘመን ላይ] ይህ ኅብስት የበላ ይህንም ጽዋ የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው ብሎ ተናገረ።
፳. ነባቤ መለኮት ጎርጎርዮስም [ኋላ ዘመን ላይ] መለኮትን ማርያም በማኅፀኗ ተሸከመችው እሱም ሥጋ ለበሰ። በማኅፀኗ ተወሰነ ብሏል አሉት።
፳፩. ይህም ሥጋ መለኮትን በመዋሐድ አባታችን አዳምን ያዳነ ነው።
፳፪. ዳግመኛም ሳዊሮስ [ኋላ ዘመን ላይ] ይህ ሥጋ ከሞተ በኋላ ከሙታን ተለይቶ በመነሣት በኪሩቤል ላይ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ ከእሱም አልተለየም ብሎ ተናገረ።
፳፫. በዚህን ጊዜ ጐስቋላው አርዮስ በመዘበት ወንድሞቼ ሆይ በቀናች ሃይማኖታችሁ አምኛለሁ አላቸው።
፳፬. ከዚህ በኋላ ሠለስቱ ምዕት ከአንተ እንተባበር ዘንድ ቅዱስ ቁርባን እንሥራ ብለው እንደ አቤል መሥዋዕት የሠመረ መሥዋዕት አዘጋጁ።
፳፭. ይህ አርዮስም ከእነሱ ጋር ቅዳሴ ገባ።
፳፮. በቅዳሴውም ሥነ ሥርዓት ላይ ከነሱ መካከል አንደኛው ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ (ቅዱስ እለእስክንድሮስ ዘቁስጥንጥንያ) አንዱ አብ ቅዱስ አንዱ ወልድ ቅዱስ አንዱ መንፈስ ቅዱስም ቅዱስ ነው በማለት በታላቅ ቃል አሰምቶ አመሰገነ።
፳፯. ሌሎቹም መንፈስ ቅዱስን ላክልን ሲሉ ተሰጥዎውን መለሱ።
፳፰. በዚህ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ ወርዶ በመሠዊያው በቁርባኑ ላይ ተቀመጠ።
፳፱. መንፈስ ቅዱስም የአርዮስን ሕሊና በመረመረ ጊዜ የአርዮስ የሆድ ዕቃው ታወከ።
፴. ፈጥኖም ከቤተ መቅደስ ወጣና ወደ መፀዳጃ ክፍል (ቦታ) ሄደ።
፴፩. እየተቻኮለ ሲሄድ መንፈስ ቅዱስን በሕፃን አምሣል ቆሞ አገኘ ውና እንዲህ ሲል ጠየ ቀው።
፴፪. ሕፃኑ ልጅ ሆይ አንድ ሰው በአፉ አምኖ በልቡ ቢክድ ምን ይሆናል አለው።
፴፫. ሕፃኑም መጽሐፍ አፍም ልብም በአንድነት ይመኑ ያለውን አልሰማህምን አለው።
፴፬. እንዲህም ሲባባሉ የአርዮስ አንጀቱ ወጣ።
፴፭. በዚህም ጊዜ ከሆዱ የወጣውን አንጀቱን ለመብላት ውሾች ይጣሉበት ጀመር።
፴፮. ከዚህ በኋላ ሠለስቱ ምዕት የሆነውን ሁሉ ሰምተው ወደሱ መጡ።
፴፯. በመጡም ጊዜ በመጸዳጃው ቦታ ወድቆ ሞቶ አገኙት።
፴፰. እሊያ ውሽችም ሆድ ዕቃውን ለመብላት በሚያገለባብጡበት ጊዜ ከልቡ ውስጥ ወልድ ፍጡር የሚል ቃል ተገኘ።
፴፱. እኒህ ሥላሴ ያለመለየት በከበረ አንድነት ይህን ታላቅ ተአምር አደረጉ።
፵. የኒቅያም ሰዎች ይህን ተአምር አይተው አደነቁ እሰከ ዛሬም ድረስ ይህችን የቀናች የኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖት እያስተማሩ ናቸው።
፵፩. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው ከወዳጃቸው . . . ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

***************

የሰይፈ ሥላሴ መቅድም

፩. ስቡሕ ወውዱስ እኩት ወቅዱስ እየተባለ በፍጹም ምስጋና የሚመሰገን፤ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመን የሥላሴን ጥንተ ህልውና የሚናገር መጽሐፍ ለመጻፍ (ለመጸለይ) እንጀምራለን ።
፪. ነገር ግን እግዚአብሔር በሰጠን የችሎታ መጠን ለመናገር እንሞክራለን እንጂ ጽፈንስ ለመጨረስ፤ ችሎታ አይኖረንም።
፫. የምስጋናቸውንስ ነገር ሰማይና ምድር ወረቀት ወይም ብራና ቢሆኑ ከፍጥረተ ዓለም እስከ ኅልቀተ ዓለም ያለው ርደተ ዝናም ቀለም ቢሆን ይልቁንም ዓለም በጠቅላላው ለዚህ ተግባር ቢውል ተጽፎ የሚያልቅ አይደለም ለዘለዓለሙ በእውነት።
፬. ሰማይና ምድር ከመፈጠራቸው አስቀድሞ ሥላሴ በብቸኝነት ክብራቸው በአካል ሦስት በመለኮትና በፈቃድ በባሕርይ በትእዛዝ ግን አንዳችም ልዩነት ሣይኖርባቸው የነበሩ ናቸው ።
፭. አብ ያለወልድና ያለመንፈስ ቅዱስ ለአንዲት ሰዓት ስንኳ ብቻውን የነበረበት ጊዜ የለም።
፮. ወልድም ያለ አብና ያለ መንፈስ ቅዱስ ለአንዲት ደቂቃ ስንኳ ብቻውን የነበረበት ጊዜ የለም።
፯. መንፈስ ቅዱስም ያለ አብና ያለ ወልድ ለአንዲት ሰኮንድ ስንኳ ብቻውን የነበረበት ጊዜ የለም።
፰. ለአብ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ ልዩ ፈቃድና እዘዝ የለውም።
፱. ለወልድም ከአብና ከመንፈሰ ቅዱስ የተለየ ልዩ ሥልጣንና ክሂል የለውም።
፲. ለመንፈስ ቅዱስም ከአብና ከወልድ የተለየ ምንም ዓይነት ሥልጣን የለውም።
፲፩. በማደህየትና በማበልፀግ በማዋረድና በማክበር ፍጹም ልዩነት የለባቸውም።
፲፪. በአንድነት በሦስትነት ይሰገዳሉ ይመለካሉ፤ ሁሉንም በየነገዱ በመፍጠር ትክክል ናቸው እንጂ ጉድለት ወይም ሕፀፅ ያሣዩበት ጊዜ የለም።
፲፫. እንደዚሁም ለአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአንድ ቃል ሰውን በአርአያችንና በምሳሌያችን እንፍጠር አሉ።
፲፬. እነሆ በመጀመሪያዪቱ ቀን በዕለተ እሑድ ስምንት ፍጥረታትን ማለት ሰማይንና ምድርን ጨለማንና ብርሃንን ነፋስንና እሳትን ውሀን መላእክትን ፈጥረው መላእክትን ግን በመቶ ነገድ ከፈሏቸው የመላእክትም ሁሉ አለቃቸው ሳጥናኤል (ዲያብሎስ) ነበረ።
፲፭. ከዚህ በኋላ መላእክትን በሙሉ ጨለማ ጋረዳቸው ሸፈናቸው።
፲፮. በዚህን ጊዜ መላእክት እርስ በራሳቸው ማን ፈጠረን ጌታችን ማነው በማንስ እናመልካለን ተባባሉ።
፲፯. ትምክህተኛው ወይም ሰይጣኑ መልአክም ይህን ቃል ሰምቶ ግራ ቀኝ ቢመለከት ከሌሎቹ የእርሱ ማዕርግ በልጦ ስለአገኘው እነሆ አምላካችሁና ፈጣሪያችሁ ገዥአችሁም እኔ ነኝ ሲል በድፍረት ተናገረ።
፲፰. ከዚህ በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከመከካላቸው ተነሥቶ ቆመና እናንት ማኅበረ መላእክት ሆይ፥ አምላካችንን እስክናውቅ ወይም እስክናገኘው ድረስ በእምነታችን ጸንተን መቆየት አለብን እንጂ በዚህ በሐሰተኛና በተንኮለኛ መልአክ አነጋገር ተወናብዳችሁ እንዳታምኑ ሲል በታላቅ ቃል አሰምቶ ተናገረ።
፲፱. በዚህም ጊዜ ኪሩቤልና ሱራፌል ዙፋኑን እንደ ተሸከሙ የሥላሴ ብርሃነ መለኮት ተገለጠ አንፀባረቀ በዓለሙ ሁሉ ላይም ብርሃን ይሁን አለ።
፳. ከዚህም በኋላ የዲያብሎስ የገዥነት ሥልጣኑ ተሽሮ እጅ እግሩን በእሳት ሠንሠለት ታሠረ።
፳፩. የተጐናጸፈውን ብርሃን ገፈው የጨለማ ጨርቅ አለበሱት የእሳት ነጐድጓድ አወረዱበት በልቡናው ፍርሃትን አሳደሩበት በዚህም ዘለዓለማዊው የሥላሴ መንግሥት በመላእክት ሁሉ ዘንድ ታወቀ ተረዳ።
፳፪. መላእክትንም ከነሱ ይለዩት ዘንድ አዘዝዋቸውና እነሱም ከመካከላቸው አውግዘው ለዩት።
፳፫. ሥሉስ ቅዱስም አንተ ርጉም ከኛ ራቅ መኖሪያህም በመንጸፈ ደይን ይሁን በማለት አስወገዱት።
፳፬. ይህ ርጉም መልአክም ጌቶቼ ከቶ ምሕረት የላችሁምን አላቸው።
፳፭. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም በእርግጥ አንተን ለመሰለ ሁሉ ምሕረት የለንም አሉት።
፳፮. በዚህ ጊዜ ይህ ርጉም መልአክ ጌቶቼ ሆይ፥ ከነዚህ ሁሉ የተፈጥሮ ጓደኞቼ ነገደ መላእክት ተለይቼ ስሄድ አላሳዝናችሁምን ሲል በማሳዘን ጮኾ ተናገረ።
፳፯. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም በማይቻልህ የአምላክነትን ባሕርይ ለመፈታተንና የማታልፈውን መንግሥታችንን ለመገልበጥ ያደረግኸው ሙከራና ድፍረት አያሳፍርህምን ይልቁንም በቃልህ አምነውበት አንተን የተከተሉ ሁሉ አብረውህ ከአንተ ጋር ይሂዱ አሉት።
፳፰. ቀጥሎም በልዩ አስተሳሰብህ አምላካዊ መንግሥትን ስትሻ ተገኝተሃልና መኖሪያህ ዕመቀ ዕመቃት ይሁን ቅዱስ ስማችን በተጠራበት ቦታ ሁሉ አትድረስ አሉት።
፳፱. ወገኖችህ መላእክት በጠላትነት ይነሱብህ በአለት ድንጋይ (ዕብነ ሩካም) በእሳት መንዶ እራስ እራስክን ይቀጥቅጡህ አሉት።
፴. ዳግመኛም ምግብህ የእሳት አሎሎ (ኮረት) መጠጥህ የእሳት ፍላት ይሁን መዘዋወሪያህ (መመላለሻህ) መንጸፈ ደይን ይሁን መቀመጫህ የእሳት መንኰራኵር ይሁን መኖሪያህም በጨለማ ውስጥ ይሁን ሲሉ ረገሙት።
፴፩. ይህንንም ካሉት በኋላ የቤቱ ዙሪያ በእሳት የታጠረ በውስጡም እሳት የሚነድበት ሆኖ ወደ ተዘጋጀለት ቤት በዚያ ይኖር ዘንድ ገባ ዕመቀ ዕመቃት መንጸፈ ደይን ወረደ።
፴፪. እሱ ግን በልቡ እግዚአብሔር እንደኔ ያለ ፍጡር አያገኝም ስለሆነም መልሶ እንደ ቀድሞው አገልጋዩ ያደርገኛል። ከቀድሞ የተፈጥሮ ጓደኞቼ ከሆኑ መላእክትም ሁሉ ጋራ ሥራዬን እቀጥላለሁ። ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እተካከላለሁ። ለአብ ምስጋና አቀርባለሁ ከእሱም ጋር ነግሼ እኖራለሁ። ስለዚህም እርሱ አብ ያከብረኛል ወልድም ከአእላፍ መላእክቶቹ ጋር መጥቶ ይቀበለኛል። ከእሱም ጋር እኖራለሁ። የአብን የዙፋን መጋረጃ ገልጬ እገባና በቀኙ ያስቀምጠኛል። ከዚያም በሱ ላይ እሠለጥናለሁ። ከወልድ ራስ ላይ ዘውድን እነጥቃለሁ። ከመንፈስ ቅዱስም ላይ የብርሃን አክሊል ወስጄ እቀዳጅና ለዚያች ከማዕርጌ ላይ ያዋረደችኝና እጅግ አስፈሪ ለሆነችው ዙፋን ባለቤት እሆናለሁ።
፴፫. ከዚያም የቀድሞ ሥልጣኔን በእጄ ከአደረግሁ በኋላ ከኔ አፈንግጠው መመሪያየን ሳይቀበሉ የቀሩትንና በእኔ ሥልጣን ላይ የተቀመጡትን ጠላቶቼን ሁሉ በቁጥጥሬ ሥር አውላቸዋለሁ በማለት ታበየ።
፴፬. ይህንንም በልቡ ሐሳብ በሚልበት ጊዜ ይህ ዲያብሎስ ትሉ ወደ ማያንቀላፋበት ጢሱ እሳቱ ወደ ማይጠፋበት በሲኦል የረግረግ ጨለማ በድንገት ተወርውሮ ሰጠመ (ሠረገ)።
፴፭. እንደዚሁም ሁሉ ጠላቶቼ በሲኦል መካከል ባለ ጨለማ ውስጥ ይጣሉ እኔ አገልጋያችሁ . . . በእናንተ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ተማፅኛለሁና እስከ ዘላለሙ አሜን።

ሰይፈ ሥላሴ ዘዘወትር

፩. አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምናለሁ እማጸናለሁ።
፪. የዓለም ገዥ ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፥ በወዳጃችሁ በአብርሃም ቤት እንደገባችሁ ከናንተ ዘንድ የሚሰጠውን የሰማዕትነት አክሊል እቀዳጅ ዘንድ ተድላ ደስታ ካለበት ገነት አግቡኝ።
፫. ኃጢአቴን በይቅርታ ቃል ደምስሳችሁ ነፍሴን ከሚቃወሟት አጋንንት አድኗት።
፬. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ በእውነት ስማችሁን እጠራ ዘንድ ከወደቅሁበት አንሡኝ በቸርነታችሁም ከሩቅ ጥቀሱኝ ከቀትር ጋኔን ከድንገተኛ መጋኛ ትጠብቁኝ ዘንድ እማፀናለሁ።
፭. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ የምስጋና ፍሬ እንዳፈራና ከአንደበቴም የጸሎት እሸት አበረክትላችሁ ዘንድ በልቡናዬ እርሻ ላይ መልካሙን ፍሬ ትዘሩ ዘንድ እማፀናለሁ።
፮. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ ኃያሉ ስማችሁ የሚጋፉኝን ይጋፋቸው ዘንድ የሚቃወሙኝንም እንዲቃወማቸውና ፈርኦንን በነቢዩ በሙሴ ምክንያት እንዳሰጠመው ያሰጥማቸው ዘንድ በእናንተ እማፀናለሁ።
፯. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ በአርያም ባለው ጽርሐ መንግሥታችሁ እማፀናለሁ ስለ ዕዝራና ሄኖክም ሲባል ገነትን ስለጐበኛችሁ እኔን ባሪያችሁን በቸርነታችሁ ጐብኙኝ።
፰. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ በስማችሁ ብዙ ተአምራትን ያደረገና ኮከበ ክብር የተባለ የሰማዕታት አለቃ በሚሆን በኃያሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ለመፍረድ በልዳ ሀገር የተሰበሰቡትን ፸ (ሰብዓ) ነገሥታትን ደምስሳችሁ እንዳጠፋችኋቸው የኔንም ጠላቶች ትደመስሱልኝ ዘንድ እማፀናለሁ።
፱. ጠላቶቾ የሆኑ ሁሉ በመለኮታዊ ሰይፍ ይ*ጨ*ፍ*ጨ*ፉ ነበልባላዊ በሚሆን ቃላችሁና ሥልጣናችሁ ይንደዱ ይቃጠሉ በሲኦል የጨለማ አዘቅት ውስጥ ይዝቀጡ ወይም ይስጠሙ ሐዘን ከላያቸው አይራቅ ትካዜም ከልባቸው አይጥፋ።
፲. ጠላቶቼ እኔ ከምድረ ገጽ ላይ እንድጠፋ በፈለጉ ጊዜ እነሱን ራሳቸውን እንደ ቃየልና ይሁዳ በዱርና በበረሃ በታትኗቸውና ሲቅበዘበዙ ይኑሩ።
፲፩. አዳምና ሔዋን ከገነት በመውጣታቸው እንዳለቀሱ ጠላቶቼንም የጨርቅ መቀነቻ አስታጥቋቸውና ሲያለቅሱ ይኑሩ።
፲፪. በኔም ላይ ጥፋትን እንዳያመጡብኝ ጥልቅ በሆነ በእሳት ባሕር አስጥሟቸው።
፲፫. አሁንም እነሆ ጠላቶቼ በእሾህና አሜካላ በተታታ ወጥመድ ውስጥ ይግቡ።
፲፬. ልዩ ሦስት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ ለእኔ ለባሪያችሁ ፍጹም ይቅርታን ታደርጉልኝ ዘንድ እማልዳለሁ።
፲፭. ጠላቶቼ ግን በፊታቸው ከፍርሃት በስተቀር በፍጹም ደስታን አያግኙ።
፲፮. ወንጀለኞች እንደሚታሠሩ እጅ እግራቸውን በእሳት ሠንሠለት እሠሯቸው እንጂ።
፲፯. ዳግመኛም ቀድሞ አዳም ከነ ልጆቹ በሲኦል ጨለማ እንደተከበበ እነሱንም የመከራ ጨለማ ይክበባቸው።
፲፰. ጠላቶቼን በውሾች ማደሪያ አሳድሯቸው የምታስፈራዋን ያችን የእሳት ባሕር አታሻግሯቸው።
፲፱. በእሳት ቀስት (ፍላፃ) ንደፏቸው ልዩ ልዩ ደዌና መቅሠፍት ይታዘዝባቸው የምሕረት ዝናም (ጠል) አይውረድላቸው የሕይወት ቃል አትመልሱላቸው።
፳. ልዩ ሦስት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ ጽንዕት በሆነች መለኮታዊት እጃችሁ ትባርኩኝና መላእክትም ሁሉ በክንፋቸው በእኔ ላይ ይረቡ ዘንድ እማፀናለሁ።
፳፩. ነፍሴ ወይም ሰውነቴ በእናንተ ዘንድ የተጠማች እንዳትሆን ከዐራቱ አፍላጋት በሚፈስ ውሀ አርኳት (አጠጧት)።
፳፪. ነፍሴ ወይም ሰውነቴ በፊታችሁ የተራበች ሆና እንዳትገኝ የሕይወት ኅብስት መግቧት።
፳፫. የነፍስና የሥጋ ገዥ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ የምስጋና ፍሬ አቀርብላችሁ ዘንድ ጾምና ጸሎት ወዳድ እንድታደርጉኝ እማጸናለሁ።
፳፬. ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር መኖሪያዬን በገነት አድርጉልኝ ከዕለት እኪት ከዘመን መንሱት ሠውሩኝ።
፳፭. እኔ በደለኛ የምሆን አገልጋያችሁ . . . ከድንገተኛ ሞት እድን ዘንድ ልዩ ሦስት በሚሆን ስማችሁ እማፀናለሁ ነፍሴንና ሥጋዬንም አደራ አስጠብቃለሁ። በዚያም ጊዜ ምሕረት ይደረግልኝ አሜን።
፳፮. ዳግመኛም በሁሉ ላይ ሥልጣን ባለው በእግዚአብሔር አብ ስም ዕውቀትን በሚገልጽ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እና ያዘኑትን በሚያረጋጋ እውነተኛ አዳኝ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ ስም እማፀናለሁ።
፳፯. በአካል ሦስት ሲሆን በመለኮት ግን አንድ አምላክ በሚሆን እማፀናለሁ።
፳፰. በየጊዜውና በየሰዓቱ እንግዳ ለሚሆንና ለማይጠገበው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ፍቅር እማፀናለሁ።
፳፱. በማይጠፋ በማያረጅና በማያልፍ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አነዋወር እማፀናለሁ።
፴. ተነግሮ በማያልቅ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ የጌትነት ምስጋና እማፀናለሁ።
፴፩. ዓለሙን ሁሉ ለይኩን ብሎ በአንዲት ቃል በፈጠረ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ጥበብ እማፀናለሁ።
፴፪. በግልጽና በሥውር ያለውን ዓለም በሙሉ በአጸና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ኃይል እማፀናለሁ።
፴፫. ለመግደልና ለማዳን በሚችል በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ፍርድ እማፀናለሁ።
፴፬. ከምድረ ገጽ ጸብን ክርክርን በሚሽር በሚያጠፋና በሚደመስስ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ቃል እማፀናለሁ።
፴፭. በሚያደኸይና በሚያበለጽግ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ መንግሥት ወይም ሥልጣን እማፀናለሁ።
፴፮. እጅግ በሚያስፈራና ነፍስና ሥጋን በሚያስደነግጥ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ግርማ እማፀናለሁ።
፴፯. ከአፉ በሚወጣ የእሳት ሰይፍ የጠላትን ወጥመድ (አሽክላ) የሚቆራርጥ በመለኮት በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እማፀናለሁ።
፴፰. አሌፍ፣ ቤት፣ ጋሜል፣ ዳሌጥ፣ ሄ፣ ዋው፣ ዛይ፣ ሔት፣ ጤት፣ ዮድ፣ ካፍ፣ ላሜድ፣ ሜም፣ ኖን፣ ሳምኬት፣ ዔ፣ ፌ፣ ጻዴ፣ ቆፍ፣ ሬስ፣ ሳን፣ ታው በሚባል (ሉ) በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያመንኩ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ ልመናዬ ወዳንተ ትቀርብ ዘንድ እማፀናለሁ።
፴፱. የመምጣቱ ዜና በነቢያት አንደበት በተነገረና ከቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም በተወለደ ጌታ እማፀናለሁ።
፵. ዳግመኛም በማየ ዮርዳኖስ በተጠመቀውና የጌትነቱ ክብር በደብረ ታቦር በተገለጸው አምላክ እማፀናለሁ።
፵፩. ሀገሩ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተብላ በምትጠራውና ማደሪያውን በአርያም መሠወሪያውንም የእሳት መጋረጃ ባደረገ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እማፀናለሁ።
፵፪. በለበሰው ሥጋ በተሰቀለበት በመካነ ስቅለቱ በቀራንዮ በመካነ መቃብሩ በጎልጎታ ከሙታን ተለይቶ በሦስተኛው ቀን በመነሣቱ በዐርባኛው ቀን ወደ ሰማይ በማረጉና ይህን ዓለም ለማሳለፍ ዳግመኛ በመምጣቱ እማፀናለሁ።
፵፫. ለአዳምና ለልጆቹ ለዘሩም ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ ከሰማይ በወረደ በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ እማፀናለሁ።
፵፬. በዚህ ሁሉ በተጠሩትና ባልተጠሩት አምላካዊና የመማፀኛ ስሞች እናንት ርኵሳን አጋንንት እኵያንና መሠርያን ሰብዓዊ ፍጥረቶች ሁሉ በየጊዜውና በየሰዓቱ የእግዚአብሔር አገልጋዩ ከምሆን ከኔ ዘንድ እንዳትቀርቡ የተወገዛችሁ ሁኑ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን።
፵፭. የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር አብ ይክበር ይመስገን አሜን።
፵፮. ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ የባሕርይ አንድ ልጁ የሚሆን እግዚአብሔር ወልድም ይክበር ይመስገን አሜን።
፵፯. የአብና የወልድ የባሕርይ ሕይወታቸው የሚሆን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ይክበር ይመስገን አሜን።
፵፰. አብ የባሕርይ አምላክ ነው የጌትነቱም ዙፋን ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፵፱. ወልድ የባሕርይ አምላክ ነው የጌትነቱም ዙፋን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፶. መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ አምላክ ነው የጌትነቱ ዙፋንም ከአብ ከወልድ ጋር ትክክል ነው።
፶፩. እንግዲህ በአንድ የጌትነት ዙፋን ላይ የአካል ሦስትነትና የመለኮት አንድነት እንዳለ እናምናለን።
፶፪. ለማይጠቀለል ለሥላሴ አንድነት ምስጋና ይገባል።
፶፫. ለማይከፋፈል ለሥላሴ ሦስትነት ምስጋና ይገባል።
፶፬. የዝርውነት ባሕርይ ለሌለው ለሥላሴ ሐሳብ ምስጋና ይገባል።
፶፭. ለማይመረመር ለሥላሴ አነዋወር ምስጋና ይገባል።
፶፮. ሰማይና ምድር ለማይወስኑት ለአካለ ሥላሴ ምስጋና ይገባል።
፶፯. ተመራምሮ ለማይደረስበት ለሥላሴ ቅድምና ምስጋና ይገባል።
፶፰. ኅልፈት ውላጤ ለሌለበት ለሥላሴ መንግሥት ምስጋና ይገባል።
፶፱. ልዩ ተጨማሪ ስም ለማያስፈልገው (ለማይስማማው) ለሥላሴ ምስጋና ይገባል።
፷. ከፍጹም ሦስትነት ወደ ዐራተኛነት ከፍ ለማይል ፍጹም የስም ሦስትነት ምስጋና ይገባል።
፷፩. ከፍጹም የገጽ ሦስትነት ወደ ሁለተኝነት ገጽ ዝቅ ለማይል የገጽ ሦስትነት ምስጋና ይገባል።
፷፪. ለማይወሰን ለሥላሴ ቸርነት ምስጋና ይገባል።
፷፫. ልዩ ሦስት ለሚሆኑ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል።
፷፬. በልዩ የነደ እሳት ነፀብራቅ ለተከበበችና ሁሉ በሁሉ ሙሉ ለሆነች ሥላሴነት ምስጋና ይገባል። ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

09/02/2026
👉"አሁንም የሰማይ ቅዱሳን ሆይ . . . እናንተን ይማጠናሉ" መጽ. ሄኖ. 2፥30👉"መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ" ማቴ. 18፥10👉"ሁለቱም መላእክት ...
09/01/2026

👉"አሁንም የሰማይ ቅዱሳን ሆይ . . . እናንተን ይማጠናሉ" መጽ. ሄኖ. 2፥30

👉"መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ" ማቴ. 18፥10

👉"ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፤ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ አላቸውም፦ ጌቶቼ ሆይ፥ ወደ ባሪያችሁ ቤት አቅኑ፥ ከዚያም እደሩ፥ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ። እነርሱም፦ በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም አሉት። እጅግም ዘበዘባቸው፤ ወደ እርሱም አቀኑ፥ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ እነርሱም በሉ።" ዘፍ. 19፥1-3

👉"ያንጊዜም ሚካኤልና ገብርኤል፥ ሱርያልና ዑራኤል በሰማይ ሆነው ጎበኙ። በምድርም ላይ የሚፈስስውን ብዙ ደምና በምድር ላይ የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አዩ።" መጽ. ሄኖ. 2፥27-28

👉"አሁንም የሰማይ ቅዱሳን ሆይ፥ የሰዎች ነፍሳት ፍርድን ወደ እግዚአብሔር አግቡልን እያሉ እናንተን ይማጠናሉ።" መጽ. ሄኖ. 2፥30

👉"ወደ ኖኅም ሱርያልን (አርሰየላልዩርን/እሥራልዩን) ላከው" መጽ. ሄኖ. 3፥1

👉"[መልአኩንም] አብዝቼም ለመንኩት/ዘበዘብኩት" ሔርማ ኖላዊ 3ኛ መጽሐፍ፣ 5ኛ ምሳሌ፣ 4ኛ ምዕራፍ (90-140ዓ.እ)

👉"That in heaven their angels do always behold the face of my Father which is in heaven." Matt. 18:10

👉"And there came two angels to S***m at even; and Lot sat in the gate of S***m: and Lot seeing them rose up to meet them; and he bowed himself with his face toward the ground; And he said, Behold now, my lords, turn in, I pray you, into your servant's house, and tarry all night, and wash your feet, and ye shall rise up early, and go on your ways. And they said, Nay; but we will abide in the street all night. And he pressed upon them greatly; and they turned in unto him, and entered into his house; and he made them a feast, and did bake unleavened bread, and they did eat." Gen. 19:1-3

👉"And it came to pass in those days, that Michael and Gabriel, Suriel and Uriel, looked down from heaven. And they beheld the great shedding of blood upon the earth, and all the violence that was wrought upon the earth." Enoch 2:27-28

👉"Even now, O ye saints of heaven, the souls of men cry unto you, beseeching you to bear their cause before God." Enoch 2:30

👉"And He sent Suriel to Noah" Enoch 3:1

👉"I prayed him much" The Shepherd of Hermas, Third Book, Fifth Similitude, Chapter 4)

👉"የምድር ዳርቻዎችም በእጁ ውስጥ ናቸው፥ የተራሮች ከፍታዎች የእርሱ ናቸው።" መዝ. 94(95)፥4 👉"In his hand are the deep places of the earth: the stren...
09/01/2026

👉"የምድር ዳርቻዎችም በእጁ ውስጥ ናቸው፥ የተራሮች ከፍታዎች የእርሱ ናቸው።" መዝ. 94(95)፥4

👉"In his hand are the deep places of the earth: the strength of the hills is His also." Ps. 95:4

👉"በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።" 2ኛ ጴጥ. 3፥18 👉"But grow in grace, a...
09/01/2026

👉"በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።" 2ኛ ጴጥ. 3፥18

👉"But grow in grace, and in the knowledge of our Lord and Saviour Jesus Christ. To Him be glory both now and for ever. Amen." 2Pet. 3:18

የረቡዕ ሰይፈ ሥላሴ (መቅድሙና የዘወትሩ ከበታች ተካቷል)አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በእውነት አምናለሁ። ፩. የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክር...
09/01/2026

የረቡዕ ሰይፈ ሥላሴ (መቅድሙና የዘወትሩ ከበታች ተካቷል)

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በእውነት አምናለሁ።

፩. የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ይክበር ይመስገን በግልጽና በሥውር ስለሰጠኝ ጸጋ በየሰዓቱ ሁሉ አመሰግነዋለሁ።
፪. አቤቱ በዚች በተባረከች ዕለት ጸሎቴን ትሰማኝና ልመናዬንም ትቀበል ዘንድ በገናንነትህና በአስፈሪነትህ በኃያልነትህና በመለኮትነትህ እለምንሃለሁ አቤቱ ኃጢአቴን ያስተሥርይልኝ ዘንድ የተወደደው ልጅህን ቅዱስ ሥጋውንና ክብር ደሙን ለመቀበል የበቃሁ አድርገኝ።
፫. ፍርሃት በሌለበት ረድኤትህ ጠብቀኝ አቤቱ ሰውነቴን በተንኮል ከሚፈልጓት ተንኮለኞች ሁሉ አድነኝ ትዕቢትን ትምክህትን ቂምና ምቀኝነት ቁጣና በደልን የመሳሰሉትንም ክፋቶች ሁሉ ከእኔ አርቅልኝ።
፬. አቤቱ በጌትነትህ ይቅር ባይነትህና ቸርነት ሥውሩንና ግልጹን ታላቁንና ታናሹን ኃጢአቴን በደሌንም ሁሉ ይቅር በል።
፭. አቤቱ በቅዱስ ወንጌልህ ትእዛዝ መሠረት በጐዳናህ እንድሄድ አድርገኝ አቤቱ የሰይጣንን የልቡን ክፋትና መቃጥኑንም (ወጥመዱን) ከእኔ አርቅልኝ እኔ ባሪያህ ፍጹም ደሀና ምስኪን የተናቅሁና ደካማም ነኝና።
፮. አቤቱ መልካሙን በአደረግኽልኝ ፈንታ የክፋትን መልስ መለስኩልህ የቸርነትህን ጸጋ ሰጠኸኝ እኔ ግን ደግሜ በደልኩ ከክፋቴ እስክመለስ ጠበቅኸኝ በእውነትም ጐዳና መራኸኝ እኔ ግን ከኃጢአቴ አልተመለስኩም።
፯. አሁንም አቤቱ እንደ ቸርነትህ ይቅር እንድትለኝና በክንፈ ረድኤትህም ትሠውረኝ ዘንድ ቅዱስ ፈቃድህን እማልዳለሁ ወይም እጠይቃለሁ።
፰. አቤቱ ጎዳናዬን በሰላምና በደኅንነት አቅና በቸርነትህና በይቅርታህ ከክፉ ነገር ተወግጄ መልካሙን ነገር እንድከተል አድርገኝ።
፱. ለአንተ ክብር ምስጋና ስግደት ይገባል ለዘለዓለሙ አሜን።
፲. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአነዋወር አንድ በገጽ ሦስት ናቸው፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት በመለኮት አንድ ናቸው።
፲፩. አብ በአካሉ ፍጹም ነው ወልድም በአካሉ ፍጹም ነው መንፈስ ቅዱስም በአካሉ ፍጹም ነው እሊህ ሦስቱ አካላት በመለኮት አንድ ናቸው።
፲፪. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ኃያልና የሚያስፈራ ዓይኑ እንደ እሳት የሚነድ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፲፫. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር የራስ ፀጉሩ እንደበረድ የነፃ እንደ ሰርዲኖስና ኢያሰጲድ ዕንቍ የከበረ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፲፬. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር የመቅደሱ አጥር በእሳት የታጠረ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፲፭. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር በጠላት ፊት የማይበገር እሱ ጽኑዕ አዳራሽ (ግንብ) ነው።
፲፮. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አግዚአብሔር ጠፈርን ያለምሰሶ መሬትን ያለመሠረት ፈጥሮ ያለድጋፍ በቃል ብቻ ያጸና እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፲፯. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ሁሉን በየወገኑ የሚገዛ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፲፰. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር መንግሥቱ የማያልፍ ግዛቱም ለትውልደ ትውልድ (ለዘለዓለም) የሚኖር እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፲፱. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር የሦስትነቱ ሥርዓት የማይለወጥና ለሦስትነቱ ምስጋና የሚገባው እርሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፳. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር በመባርቅት የሚላኩት ነጐድጓድ የሚያመሰግኑት እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፳፩. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ሦስት ሲሆን አንድ አንድ ሲሆን ሦስት የሚሆን እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
፳፪. ዓለምን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፫. ቁጣውን በቸርነቱ ባሕር የሚያሰጥማት እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፬. የመቅሠፍቱን እሳት በይቅርታው ውሃ የሚያጠፋ እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፭. የማይቀየም የዋህ ንስሐን የሚወድ እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፮. ኃጢአትን በቸርነቱ ጥላ የሚሸፍን እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፯. አበሳን በቸርነቱ ጉድጓድ የሚደፍን እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፰. በደልን በትዕግሥቱ መጋረጃ የሚጋርድ እሱ እግዚአብሔር ምስጉን ነው።
፳፱. ለእርሱ ለብቻው ምስጋና ይገባል። ለመንግሥቱም እዘዝ ይገባል። ለሦስትነቱ ክብር ይገባል ለከኃሊነቱ ኃይል ይገባል። ለመለኮቱ ሥልጣን ይገባል ለዘላለሙ።
፴. መለኮት በገጽ ሦስት ሲሆን በአንዲት ክሂሎት ሰማይና ምድርን ባሕርንም በውስጧም የሚገኙትን ሁሉ የፈጠረ እሱ ነው።
፴፩. መለኮት በአካል ሦስት ሲሆን መለኮቱ አንድ ነው ስለሆነም በአንድነት ኅብረት ብርሃንን ከጨለማ የለየ እሱ ነው።
፴፪. መለኮት በሥሉስ አካሉ ሰውን በአርአያችንና በምሳሌያችን እንፍጠር ብሎ አዳምን የፈጠረ እሱ ነው።
፴፫. ዳግመኛም ሥላሴ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ አሉ።
፴፬. የሥላሴ ምክር በጥቅመ ሰናኦር ቋንቋዎችን ለያየ እርሱ ቅሉ አንድነታቸውና ሦስትነታቸውን ሲያጠይቅ ኑ እንውረድና የከለዳውያንን ነገር እንበትንባቸው ብሏልና።
፴፭. ሥላሴ ወይም ሦስትነት ከመለኮቱ የአንድነት አነዋወር ሳይነዋወጽ በሦስት ሰዎች አምሣል በቤተ አብርሃም ተስተናገደ።
፴፮. ይስሐቅን ለመዋጀት በበግ አምሳል ለተመሰለ መለኮት ምስጋና ይገባል።
፴፯. ከኤሳው ይልቅ የያዕቆብን ሥነ ባሕርይ የመረጠ እንዲሁም በመሰላል ላይ ሆኖ ለተገለጸለት መለኮት መስጋና ይገባል።
፴፰. ሰዋስውም የተባለችው ከመለኮታዊ ፀሐይ ጋር የመለኮት አዳራሽ በማኅፀኗ የተወሰነ የቅድስት ማርያም አምሳል ነው።
፴፱. ለእርስዋ በሰማይና በምድር በባሕርና በቀላያት ሁሉ አገልግሎትና ምስጋና ይገባል ለዘለዓለሙ አሜን።
፵. ዳግመኛም ጎህ እስኪቀድ ድረስ ለዚህ ለተመረጠ ሰው (ያዕቆብ) በጐበዝ ሰው አምሳል ለተገለጸ መለኮት ምስጋና ይገባል።
፵፩. በዚህ ጊዜ ስለ ምሥጢረ ትስብእቱ ሲታገለው ሰው አምላክ አምላክ ሰው ለመሆኑ ምስጢር በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እድል ገጠመህ ሲል አመለከተው።
፵፪. ይህንንም ቃል መሠረት በማድረግ ሁሉን ፈጸመ በወንጌል እንደ ተነገረው የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ተብሏልና።
፵፫. በይሁዳ ዕፃ የአንበሳ ልጅ ተብሎ ለተሰየመ መለኮት ምስጋና ይገባል።
፵፬. ከተሸጠ ዮሴፍ ጋር ላልተለየ መለኮት ምስጋና ይገባል።
፵፭. በታላቅ ኃይልና በጽኑ ክንድ ዓሥራ ሁለቱን ነገደ እስራኤል ከባርነት ነፃ ላወጣ መለኮት ምስጋና ይገባል።
፵፮. እርሱ ቅሉ አብ አሕዛብ በኃይሌ (በማዳኔ) ይተማመናሉ እውነትም በእርሱ ጸንታ ትኖራለች ብሎ እንደ ተናገረ መዝራዕት የተባለም የአብ አንድ ልጁ የሚሆን ወልድ ነው።
፵፯. ዕንጨቱን ባለማቃጠል በዕንጨቱ ላይ በሚታይ ነደ እሳት አምሳል ለሙሴ ለተገለጸለት የእግዚአብሔር መልክተኛ ምስጋና ይገባል።
፵፰. ዕፀ ጳጦስም የተባለችው ድንግል ማርያም ስትሆን መልአክ የተባለውም የእግዚአብሔር ልጅ ነው።
፵፱. የአብ ቃል እርሱ መለኮታዊ አካሉ ፍጹም እሳት የሆነ የአምላክነት ባሕርይ ያለው በሐር ግምጃ ላይ ተዋሕዶ የሚያበራ ንጹሕና ጽሩይ ብርሃን ነው።
፶. ወልድ ልጅ በመባል ከባሕርይ አባቱ እግዚአብሔር አብና ከባሕርይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አያንስም።
፶፩. እርሱ አብ በፍጹም አካሉ እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል አባት ነውና መለኮታዊ አካሉ እሳተ ነበልባል ነው።
፶፪. አብ አባት በመሆኑ ከባሕርይ ልጁ ከእግዚአብሔር ወልድና ከባሕርይ ሕይወቱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አይበልጥም።
፶፫. እርሱ መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር ነው፤ መለኮታዊ አካሉ ፍጹም እሳት ነው ከአብ ከወልድ ጋር በአገዛዝ አንድ በሥልጣን ትክክል ነው።
፶፬. እሊህ ገዥዎች በገጽ ሦስት በፈቃድ አንድ ናቸው በመለኮትና በማንኛውም ሥነ ባሕርይ ሁሉ ፍጹም ልዩነት የለባቸውም።
፶፭. አንደኛው ከሁለተኛው ሁለተኛው ከሦስተኛው ሳይለይ በመለኮት አንድ ናቸው እንጂ እነሱ አንድ አምላክ ናቸውና።
፶፮. የአብ ህልውና ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፶፯. የወልድም ህልውና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፶፰. የመንፈስ ቅዱስም ህልውና ከአብ ከወልድ ጋር አንድ ነው።
፶፱. የአብ መንግሥት ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፷. የወልድ መንግሥት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፷፩. የመንፈስ ቅዱስም መንግሥት ከአብና ከወልድ ጋር ትክክል ነው።
፷፪. የአብ መለኮት ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፷፫. የወልድ መለኮት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፷፬. የመንፈስ ቅዱስም መለኮት ከአብ ከወልድ ጋር አንድ ነው።
፷፭. የአብ ሥልጣን ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን ጋር አይለይም።
፷፮. የወልድ ሥልጣን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን ልዩነት የለበትም።
፷፯. የመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን ከአብ ከወልድ ሥልጣን ፈጽሞ አይለይም።
፷፰. የአብ ባሕርይ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፷፱. የወልድ ባሕርይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው።
፸. የመንፈስ ቅዱስ ባሕርይ ከአብ ከወልድ ጋር አንድ ነው።
፸፩. በዚህ በሥላሴ አንድነት ሥሉስ ቅዱስ ስለ ሦስትነታቸው ብለው በየጊዜውና በየሰዓቱ ለዘወትር ፈጽመው ይቅር ይሉኝ ዘንድ እማፀናለሁ ነፍሴንና ሥጋዬንም አደራ አስጠብቃለሁ።
፸፪. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው በወዳጃቸው . . . ላይ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

ተአምር፦

፩. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው በወዳጃቸው . . . ላይ ለዘላለሙ ይደርና ሥሉስ ቅዱስ ያደረጉት ተአምራት ይህ ነው።
፪. እግዚአብሔርን የሚፈራ አንድ ጸድቅ ሰው በፍልስጤም አገር ነበረ።
፫. እሱም ቅዱሳት መጻሕፍትን የመጻፍ ችሎታ ነበረው በጽሕፈት ዐዋቂነቱም ከሌሎች ጸሐፊዎች ሁሉ በጣም ብልጫ ያለው ነበረ።
፬. ከዕለታት ባንደኛው ቀን በበጐ ሥራው የተደነቀ አንድ አገረ ገዥ መጥቶ አንተ ደገኛ የሆንክ ወንድሜ ሆይ ክቡር የሚሆን ሰይፈ ሥላሴ የሚባል መጽሐፍ ትጽፍልኝ ዘንድ ወዳንተ መጥቻለሁ በማለት ጸሐፊውን ጠየቀውና እሺ በጐ አሰኘው።
፭. መጽሐፉንም በሚጽፍለት ጊዜ በአፃፃፉ ሥላሴን ደስ ለማሰኘት የሥሉስ ቅዱስን ስም እጅግ በሚያበራ የወርቅ ቀለም ይጽፍለት ነበር።
፮. ሥራውንም በዚህ ዓይነት ቀጥሎ ሳለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
፯. እነሆ መላእክት ክንፋቸውን በመዘርጋት የዚህን የጸሐፊ ነፍስ ለመቀበል ወደሱ መጡ።
፰. መላእክትም ከሥሉስ ቅዱስ ዙፋን ፊት ባቀረቡት ጊዜ የሰማይና የምድር ገዥዎች ሥላሴ እንዲህ አሉት።
፱. አንተ ጸሐፊ በሕይወትህ ሳለህ ስማችንን አስጊጠህ እንደ ጻፍክ ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት ና ግባ አሉት።
፲. ሥላሴም ይህን ካሉት በኋላ መላእክት ተሸክመው ወስደው ከእግረ መንበር አደረሱትና ረቂቅና ለመስማት እጅግ አስደናቂ የሆነ የሥላሴን ምስጢር አስተማሩት።
፲፩. ዳግመኛም እኒሁ መላእክት አንተ ጸሐፊ ሆይ በወርቅ ዓምድ ላይ የተጻፈውን ስምህን ታይ ዘንድ ና እንውሰድህ አሉት።
፲፪. ጸሐፊውም ስሙን በተመለከተ ጊዜ ፈጽሞ ተደሰተ ቀጥሎም ገዥዎቼ ሥላሴ ሆይ ምን ሥራ ሠራሁላችሁና ነው የማይመጣጠነኝና ተገቢዬም ያይደለ ዋጋ የሰጣችሁኝ በማለት ተናገረ።
፲፫. ዳግመኛም ሥሉስ ቅዱስ አንተ መልካም ጸሐፊ አንተስ መልካሙን ሁሉ አደረግህልን ካንተ በኩል የቀረ ነገር የለም በሕይወትህ ሳለህ ቅዱስ መጽሐፍን በምትጽፍበት ጊዜ ለስማችን ታላቅ ክብር ሰጥተኸዋልና አሉት።
፲፬. ይህንም ካሉት በኋላ የብርሃን መጐናጸፊያ አጐናጽፈው የወርቅ ዘውድ አቀዳጁትና ዕዝራና ሄኖክ ኤልያስም በሕይወታቸው ካሉበት በተድላ ገነት አስቀመጡት።
፲፭. የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ እንግዲህ ሥላሴ በሰማይ በሕይወት አዳራሽ ያስገቡን ዘንድ ስማቸውን እናክብር ከፍ ከፍም እናድርግ።
፲፮. ዳግመኛም አሸናፊ ለሚሆን ስማቸው እንገዛ የእሳት ሰይፋቸውን መዘው ባሉ መላእክት እጅ ይጠብቁንና ከድንገተኛ ሞት ይሠውሩን ዘንድ።
፲፯. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው ከወዳጃቸው ከ . . . ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

***************

የሰይፈ ሥላሴ መቅድም

፩. ስቡሕ ወውዱስ እኩት ወቅዱስ እየተባለ በፍጹም ምስጋና የሚመሰገን፤ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመን የሥላሴን ጥንተ ህልውና የሚናገር መጽሐፍ ለመጻፍ (ለመጸለይ) እንጀምራለን ።
፪. ነገር ግን እግዚአብሔር በሰጠን የችሎታ መጠን ለመናገር እንሞክራለን እንጂ ጽፈንስ ለመጨረስ፤ ችሎታ አይኖረንም።
፫. የምስጋናቸውንስ ነገር ሰማይና ምድር ወረቀት ወይም ብራና ቢሆኑ ከፍጥረተ ዓለም እስከ ኅልቀተ ዓለም ያለው ርደተ ዝናም ቀለም ቢሆን ይልቁንም ዓለም በጠቅላላው ለዚህ ተግባር ቢውል ተጽፎ የሚያልቅ አይደለም ለዘለዓለሙ በእውነት።
፬. ሰማይና ምድር ከመፈጠራቸው አስቀድሞ ሥላሴ በብቸኝነት ክብራቸው በአካል ሦስት በመለኮትና በፈቃድ በባሕርይ በትእዛዝ ግን አንዳችም ልዩነት ሣይኖርባቸው የነበሩ ናቸው ።
፭. አብ ያለወልድና ያለመንፈስ ቅዱስ ለአንዲት ሰዓት ስንኳ ብቻውን የነበረበት ጊዜ የለም።
፮. ወልድም ያለ አብና ያለ መንፈስ ቅዱስ ለአንዲት ደቂቃ ስንኳ ብቻውን የነበረበት ጊዜ የለም።
፯. መንፈስ ቅዱስም ያለ አብና ያለ ወልድ ለአንዲት ሰኮንድ ስንኳ ብቻውን የነበረበት ጊዜ የለም።
፰. ለአብ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ ልዩ ፈቃድና እዘዝ የለውም።
፱. ለወልድም ከአብና ከመንፈሰ ቅዱስ የተለየ ልዩ ሥልጣንና ክሂል የለውም።
፲. ለመንፈስ ቅዱስም ከአብና ከወልድ የተለየ ምንም ዓይነት ሥልጣን የለውም።
፲፩. በማደህየትና በማበልፀግ በማዋረድና በማክበር ፍጹም ልዩነት የለባቸውም።
፲፪. በአንድነት በሦስትነት ይሰገዳሉ ይመለካሉ፤ ሁሉንም በየነገዱ በመፍጠር ትክክል ናቸው እንጂ ጉድለት ወይም ሕፀፅ ያሣዩበት ጊዜ የለም።
፲፫. እንደዚሁም ለአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአንድ ቃል ሰውን በአርአያችንና በምሳሌያችን እንፍጠር አሉ።
፲፬. እነሆ በመጀመሪያዪቱ ቀን በዕለተ እሑድ ስምንት ፍጥረታትን ማለት ሰማይንና ምድርን ጨለማንና ብርሃንን ነፋስንና እሳትን ውሀን መላእክትን ፈጥረው መላእክትን ግን በመቶ ነገድ ከፈሏቸው የመላእክትም ሁሉ አለቃቸው ሳጥናኤል (ዲያብሎስ) ነበረ።
፲፭. ከዚህ በኋላ መላእክትን በሙሉ ጨለማ ጋረዳቸው ሸፈናቸው።
፲፮. በዚህን ጊዜ መላእክት እርስ በራሳቸው ማን ፈጠረን ጌታችን ማነው በማንስ እናመልካለን ተባባሉ።
፲፯. ትምክህተኛው ወይም ሰይጣኑ መልአክም ይህን ቃል ሰምቶ ግራ ቀኝ ቢመለከት ከሌሎቹ የእርሱ ማዕርግ በልጦ ስለአገኘው እነሆ አምላካችሁና ፈጣሪያችሁ ገዥአችሁም እኔ ነኝ ሲል በድፍረት ተናገረ።
፲፰. ከዚህ በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከመከካላቸው ተነሥቶ ቆመና እናንት ማኅበረ መላእክት ሆይ፥ አምላካችንን እስክናውቅ ወይም እስክናገኘው ድረስ በእምነታችን ጸንተን መቆየት አለብን እንጂ በዚህ በሐሰተኛና በተንኮለኛ መልአክ አነጋገር ተወናብዳችሁ እንዳታምኑ ሲል በታላቅ ቃል አሰምቶ ተናገረ።
፲፱. በዚህም ጊዜ ኪሩቤልና ሱራፌል ዙፋኑን እንደ ተሸከሙ የሥላሴ ብርሃነ መለኮት ተገለጠ አንፀባረቀ በዓለሙ ሁሉ ላይም ብርሃን ይሁን አለ።
፳. ከዚህም በኋላ የዲያብሎስ የገዥነት ሥልጣኑ ተሽሮ እጅ እግሩን በእሳት ሠንሠለት ታሠረ።
፳፩. የተጐናጸፈውን ብርሃን ገፈው የጨለማ ጨርቅ አለበሱት የእሳት ነጐድጓድ አወረዱበት በልቡናው ፍርሃትን አሳደሩበት በዚህም ዘለዓለማዊው የሥላሴ መንግሥት በመላእክት ሁሉ ዘንድ ታወቀ ተረዳ።
፳፪. መላእክትንም ከነሱ ይለዩት ዘንድ አዘዝዋቸውና እነሱም ከመካከላቸው አውግዘው ለዩት።
፳፫. ሥሉስ ቅዱስም አንተ ርጉም ከኛ ራቅ መኖሪያህም በመንጸፈ ደይን ይሁን በማለት አስወገዱት።
፳፬. ይህ ርጉም መልአክም ጌቶቼ ከቶ ምሕረት የላችሁምን አላቸው።
፳፭. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም በእርግጥ አንተን ለመሰለ ሁሉ ምሕረት የለንም አሉት።
፳፮. በዚህ ጊዜ ይህ ርጉም መልአክ ጌቶቼ ሆይ፥ ከነዚህ ሁሉ የተፈጥሮ ጓደኞቼ ነገደ መላእክት ተለይቼ ስሄድ አላሳዝናችሁምን ሲል በማሳዘን ጮኾ ተናገረ።
፳፯. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም በማይቻልህ የአምላክነትን ባሕርይ ለመፈታተንና የማታልፈውን መንግሥታችንን ለመገልበጥ ያደረግኸው ሙከራና ድፍረት አያሳፍርህምን ይልቁንም በቃልህ አምነውበት አንተን የተከተሉ ሁሉ አብረውህ ከአንተ ጋር ይሂዱ አሉት።
፳፰. ቀጥሎም በልዩ አስተሳሰብህ አምላካዊ መንግሥትን ስትሻ ተገኝተሃልና መኖሪያህ ዕመቀ ዕመቃት ይሁን ቅዱስ ስማችን በተጠራበት ቦታ ሁሉ አትድረስ አሉት።
፳፱. ወገኖችህ መላእክት በጠላትነት ይነሱብህ በአለት ድንጋይ (ዕብነ ሩካም) በእሳት መንዶ እራስ እራስክን ይቀጥቅጡህ አሉት።
፴. ዳግመኛም ምግብህ የእሳት አሎሎ (ኮረት) መጠጥህ የእሳት ፍላት ይሁን መዘዋወሪያህ (መመላለሻህ) መንጸፈ ደይን ይሁን መቀመጫህ የእሳት መንኰራኵር ይሁን መኖሪያህም በጨለማ ውስጥ ይሁን ሲሉ ረገሙት።
፴፩. ይህንንም ካሉት በኋላ የቤቱ ዙሪያ በእሳት የታጠረ በውስጡም እሳት የሚነድበት ሆኖ ወደ ተዘጋጀለት ቤት በዚያ ይኖር ዘንድ ገባ ዕመቀ ዕመቃት መንጸፈ ደይን ወረደ።
፴፪. እሱ ግን በልቡ እግዚአብሔር እንደኔ ያለ ፍጡር አያገኝም ስለሆነም መልሶ እንደ ቀድሞው አገልጋዩ ያደርገኛል። ከቀድሞ የተፈጥሮ ጓደኞቼ ከሆኑ መላእክትም ሁሉ ጋራ ሥራዬን እቀጥላለሁ። ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እተካከላለሁ። ለአብ ምስጋና አቀርባለሁ ከእሱም ጋር ነግሼ እኖራለሁ። ስለዚህም እርሱ አብ ያከብረኛል ወልድም ከአእላፍ መላእክቶቹ ጋር መጥቶ ይቀበለኛል። ከእሱም ጋር እኖራለሁ። የአብን የዙፋን መጋረጃ ገልጬ እገባና በቀኙ ያስቀምጠኛል። ከዚያም በሱ ላይ እሠለጥናለሁ። ከወልድ ራስ ላይ ዘውድን እነጥቃለሁ። ከመንፈስ ቅዱስም ላይ የብርሃን አክሊል ወስጄ እቀዳጅና ለዚያች ከማዕርጌ ላይ ያዋረደችኝና እጅግ አስፈሪ ለሆነችው ዙፋን ባለቤት እሆናለሁ።
፴፫. ከዚያም የቀድሞ ሥልጣኔን በእጄ ከአደረግሁ በኋላ ከኔ አፈንግጠው መመሪያየን ሳይቀበሉ የቀሩትንና በእኔ ሥልጣን ላይ የተቀመጡትን ጠላቶቼን ሁሉ በቁጥጥሬ ሥር አውላቸዋለሁ በማለት ታበየ።
፴፬. ይህንንም በልቡ ሐሳብ በሚልበት ጊዜ ይህ ዲያብሎስ ትሉ ወደ ማያንቀላፋበት ጢሱ እሳቱ ወደ ማይጠፋበት በሲኦል የረግረግ ጨለማ በድንገት ተወርውሮ ሰጠመ (ሠረገ)።
፴፭. እንደዚሁም ሁሉ ጠላቶቼ በሲኦል መካከል ባለ ጨለማ ውስጥ ይጣሉ እኔ አገልጋያችሁ . . . በእናንተ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ተማፅኛለሁና እስከ ዘላለሙ አሜን።

ሰይፈ ሥላሴ ዘዘወትር

፩. አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምናለሁ እማጸናለሁ።
፪. የዓለም ገዥ ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፥ በወዳጃችሁ በአብርሃም ቤት እንደገባችሁ ከናንተ ዘንድ የሚሰጠውን የሰማዕትነት አክሊል እቀዳጅ ዘንድ ተድላ ደስታ ካለበት ገነት አግቡኝ።
፫. ኃጢአቴን በይቅርታ ቃል ደምስሳችሁ ነፍሴን ከሚቃወሟት አጋንንት አድኗት።
፬. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ በእውነት ስማችሁን እጠራ ዘንድ ከወደቅሁበት አንሡኝ በቸርነታችሁም ከሩቅ ጥቀሱኝ ከቀትር ጋኔን ከድንገተኛ መጋኛ ትጠብቁኝ ዘንድ እማፀናለሁ።
፭. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ የምስጋና ፍሬ እንዳፈራና ከአንደበቴም የጸሎት እሸት አበረክትላችሁ ዘንድ በልቡናዬ እርሻ ላይ መልካሙን ፍሬ ትዘሩ ዘንድ እማፀናለሁ።
፮. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ ኃያሉ ስማችሁ የሚጋፉኝን ይጋፋቸው ዘንድ የሚቃወሙኝንም እንዲቃወማቸውና ፈርኦንን በነቢዩ በሙሴ ምክንያት እንዳሰጠመው ያሰጥማቸው ዘንድ በእናንተ እማፀናለሁ።
፯. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ በአርያም ባለው ጽርሐ መንግሥታችሁ እማፀናለሁ ስለ ዕዝራና ሄኖክም ሲባል ገነትን ስለጐበኛችሁ እኔን ባሪያችሁን በቸርነታችሁ ጐብኙኝ።
፰. አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ በስማችሁ ብዙ ተአምራትን ያደረገና ኮከበ ክብር የተባለ የሰማዕታት አለቃ በሚሆን በኃያሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ለመፍረድ በልዳ ሀገር የተሰበሰቡትን ፸ (ሰብዓ) ነገሥታትን ደምስሳችሁ እንዳጠፋችኋቸው የኔንም ጠላቶች ትደመስሱልኝ ዘንድ እማፀናለሁ።
፱. ጠላቶቾ የሆኑ ሁሉ በመለኮታዊ ሰይፍ ይ*ጨ*ፍ*ጨ*ፉ ነበልባላዊ በሚሆን ቃላችሁና ሥልጣናችሁ ይንደዱ ይቃጠሉ በሲኦል የጨለማ አዘቅት ውስጥ ይዝቀጡ ወይም ይስጠሙ ሐዘን ከላያቸው አይራቅ ትካዜም ከልባቸው አይጥፋ።
፲. ጠላቶቼ እኔ ከምድረ ገጽ ላይ እንድጠፋ በፈለጉ ጊዜ እነሱን ራሳቸውን እንደ ቃየልና ይሁዳ በዱርና በበረሃ በታትኗቸውና ሲቅበዘበዙ ይኑሩ።
፲፩. አዳምና ሔዋን ከገነት በመውጣታቸው እንዳለቀሱ ጠላቶቼንም የጨርቅ መቀነቻ አስታጥቋቸውና ሲያለቅሱ ይኑሩ።
፲፪. በኔም ላይ ጥፋትን እንዳያመጡብኝ ጥልቅ በሆነ በእሳት ባሕር አስጥሟቸው።
፲፫. አሁንም እነሆ ጠላቶቼ በእሾህና አሜካላ በተታታ ወጥመድ ውስጥ ይግቡ።
፲፬. ልዩ ሦስት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ ለእኔ ለባሪያችሁ ፍጹም ይቅርታን ታደርጉልኝ ዘንድ እማልዳለሁ።
፲፭. ጠላቶቼ ግን በፊታቸው ከፍርሃት በስተቀር በፍጹም ደስታን አያግኙ።
፲፮. ወንጀለኞች እንደሚታሠሩ እጅ እግራቸውን በእሳት ሠንሠለት እሠሯቸው እንጂ።
፲፯. ዳግመኛም ቀድሞ አዳም ከነ ልጆቹ በሲኦል ጨለማ እንደተከበበ እነሱንም የመከራ ጨለማ ይክበባቸው።
፲፰. ጠላቶቼን በውሾች ማደሪያ አሳድሯቸው የምታስፈራዋን ያችን የእሳት ባሕር አታሻግሯቸው።
፲፱. በእሳት ቀስት (ፍላፃ) ንደፏቸው ልዩ ልዩ ደዌና መቅሠፍት ይታዘዝባቸው የምሕረት ዝናም (ጠል) አይውረድላቸው የሕይወት ቃል አትመልሱላቸው።
፳. ልዩ ሦስት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ ጽንዕት በሆነች መለኮታዊት እጃችሁ ትባርኩኝና መላእክትም ሁሉ በክንፋቸው በእኔ ላይ ይረቡ ዘንድ እማፀናለሁ።
፳፩. ነፍሴ ወይም ሰውነቴ በእናንተ ዘንድ የተጠማች እንዳትሆን ከዐራቱ አፍላጋት በሚፈስ ውሀ አርኳት (አጠጧት)።
፳፪. ነፍሴ ወይም ሰውነቴ በፊታችሁ የተራበች ሆና እንዳትገኝ የሕይወት ኅብስት መግቧት።
፳፫. የነፍስና የሥጋ ገዥ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ የምስጋና ፍሬ አቀርብላችሁ ዘንድ ጾምና ጸሎት ወዳድ እንድታደርጉኝ እማጸናለሁ።
፳፬. ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር መኖሪያዬን በገነት አድርጉልኝ ከዕለት እኪት ከዘመን መንሱት ሠውሩኝ።
፳፭. እኔ በደለኛ የምሆን አገልጋያችሁ . . . ከድንገተኛ ሞት እድን ዘንድ ልዩ ሦስት በሚሆን ስማችሁ እማፀናለሁ ነፍሴንና ሥጋዬንም አደራ አስጠብቃለሁ። በዚያም ጊዜ ምሕረት ይደረግልኝ አሜን።
፳፮. ዳግመኛም በሁሉ ላይ ሥልጣን ባለው በእግዚአብሔር አብ ስም ዕውቀትን በሚገልጽ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እና ያዘኑትን በሚያረጋጋ እውነተኛ አዳኝ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ ስም እማፀናለሁ።
፳፯. በአካል ሦስት ሲሆን በመለኮት ግን አንድ አምላክ በሚሆን እማፀናለሁ።
፳፰. በየጊዜውና በየሰዓቱ እንግዳ ለሚሆንና ለማይጠገበው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ፍቅር እማፀናለሁ።
፳፱. በማይጠፋ በማያረጅና በማያልፍ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አነዋወር እማፀናለሁ።
፴. ተነግሮ በማያልቅ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ የጌትነት ምስጋና እማፀናለሁ።
፴፩. ዓለሙን ሁሉ ለይኩን ብሎ በአንዲት ቃል በፈጠረ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ጥበብ እማፀናለሁ።
፴፪. በግልጽና በሥውር ያለውን ዓለም በሙሉ በአጸና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ኃይል እማፀናለሁ።
፴፫. ለመግደልና ለማዳን በሚችል በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ፍርድ እማፀናለሁ።
፴፬. ከምድረ ገጽ ጸብን ክርክርን በሚሽር በሚያጠፋና በሚደመስስ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ቃል እማፀናለሁ።
፴፭. በሚያደኸይና በሚያበለጽግ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ መንግሥት ወይም ሥልጣን እማፀናለሁ።
፴፮. እጅግ በሚያስፈራና ነፍስና ሥጋን በሚያስደነግጥ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ግርማ እማፀናለሁ።
፴፯. ከአፉ በሚወጣ የእሳት ሰይፍ የጠላትን ወጥመድ (አሽክላ) የሚቆራርጥ በመለኮት በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እማፀናለሁ።
፴፰. አሌፍ፣ ቤት፣ ጋሜል፣ ዳሌጥ፣ ሄ፣ ዋው፣ ዛይ፣ ሔት፣ ጤት፣ ዮድ፣ ካፍ፣ ላሜድ፣ ሜም፣ ኖን፣ ሳምኬት፣ ዔ፣ ፌ፣ ጻዴ፣ ቆፍ፣ ሬስ፣ ሳን፣ ታው በሚባል (ሉ) በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያመንኩ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ ልመናዬ ወዳንተ ትቀርብ ዘንድ እማፀናለሁ።
፴፱. የመምጣቱ ዜና በነቢያት አንደበት በተነገረና ከቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም በተወለደ ጌታ እማፀናለሁ።
፵. ዳግመኛም በማየ ዮርዳኖስ በተጠመቀውና የጌትነቱ ክብር በደብረ ታቦር በተገለጸው አምላክ እማፀናለሁ።
፵፩. ሀገሩ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተብላ በምትጠራውና ማደሪያውን በአርያም መሠወሪያውንም የእሳት መጋረጃ ባደረገ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እማፀናለሁ።
፵፪. በለበሰው ሥጋ በተሰቀለበት በመካነ ስቅለቱ በቀራንዮ በመካነ መቃብሩ በጎልጎታ ከሙታን ተለይቶ በሦስተኛው ቀን በመነሣቱ በዐርባኛው ቀን ወደ ሰማይ በማረጉና ይህን ዓለም ለማሳለፍ ዳግመኛ በመምጣቱ እማፀናለሁ።
፵፫. ለአዳምና ለልጆቹ ለዘሩም ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ ከሰማይ በወረደ በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ እማፀናለሁ።
፵፬. በዚህ ሁሉ በተጠሩትና ባልተጠሩት አምላካዊና የመማፀኛ ስሞች እናንት ርኵሳን አጋንንት እኵያንና መሠርያን ሰብዓዊ ፍጥረቶች ሁሉ በየጊዜውና በየሰዓቱ የእግዚአብሔር አገልጋዩ ከምሆን ከኔ ዘንድ እንዳትቀርቡ የተወገዛችሁ ሁኑ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን።
፵፭. የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር አብ ይክበር ይመስገን አሜን።
፵፮. ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ የባሕርይ አንድ ልጁ የሚሆን እግዚአብሔር ወልድም ይክበር ይመስገን አሜን።
፵፯. የአብና የወልድ የባሕርይ ሕይወታቸው የሚሆን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ይክበር ይመስገን አሜን።
፵፰. አብ የባሕርይ አምላክ ነው የጌትነቱም ዙፋን ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፵፱. ወልድ የባሕርይ አምላክ ነው የጌትነቱም ዙፋን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።
፶. መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ አምላክ ነው የጌትነቱ ዙፋንም ከአብ ከወልድ ጋር ትክክል ነው።
፶፩. እንግዲህ በአንድ የጌትነት ዙፋን ላይ የአካል ሦስትነትና የመለኮት አንድነት እንዳለ እናምናለን።
፶፪. ለማይጠቀለል ለሥላሴ አንድነት ምስጋና ይገባል።
፶፫. ለማይከፋፈል ለሥላሴ ሦስትነት ምስጋና ይገባል።
፶፬. የዝርውነት ባሕርይ ለሌለው ለሥላሴ ሐሳብ ምስጋና ይገባል።
፶፭. ለማይመረመር ለሥላሴ አነዋወር ምስጋና ይገባል።
፶፮. ሰማይና ምድር ለማይወስኑት ለአካለ ሥላሴ ምስጋና ይገባል።
፶፯. ተመራምሮ ለማይደረስበት ለሥላሴ ቅድምና ምስጋና ይገባል።
፶፰. ኅልፈት ውላጤ ለሌለበት ለሥላሴ መንግሥት ምስጋና ይገባል።
፶፱. ልዩ ተጨማሪ ስም ለማያስፈልገው (ለማይስማማው) ለሥላሴ ምስጋና ይገባል።
፷. ከፍጹም ሦስትነት ወደ ዐራተኛነት ከፍ ለማይል ፍጹም የስም ሦስትነት ምስጋና ይገባል።
፷፩. ከፍጹም የገጽ ሦስትነት ወደ ሁለተኝነት ገጽ ዝቅ ለማይል የገጽ ሦስትነት ምስጋና ይገባል።
፷፪. ለማይወሰን ለሥላሴ ቸርነት ምስጋና ይገባል።
፷፫. ልዩ ሦስት ለሚሆኑ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል።
፷፬. በልዩ የነደ እሳት ነፀብራቅ ለተከበበችና ሁሉ በሁሉ ሙሉ ለሆነች ሥላሴነት ምስጋና ይገባል። ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

Address

Lancaster, PA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ermiyas Girma posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ermiyas Girma:

Shortcuts

Share