Mekane Tibebat

Mekane Tibebat መካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ የአብነት ት/ቤትና አቡነ ፊሊጶስ ?

07/31/2022

መካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ የአብነት ት/ቤትና አቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ሊባኖስ የገዳም ምርቃት

የመካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ አዳሪ የአብነት ት/ቤት እና የአቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ገዳም ምሥረታ በዓል።
04/11/2022

የመካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ አዳሪ የአብነት ት/ቤት እና የአቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ገዳም ምሥረታ በዓል።

የመካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ አዳሪ የአብነት ትቤት እና የአቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ገዳም ምሥረታ በታላቅ ድምቀት ተከበረ፤ ክብርና ምስጋና ለአምላክ ይሁን እና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ...
04/11/2022

የመካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ አዳሪ የአብነት ትቤት እና የአቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ገዳም ምሥረታ በታላቅ ድምቀት ተከበረ፤ ክብርና ምስጋና ለአምላክ ይሁን እና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በተለይ ሕጻናትን ታሳቢ ተደርጎ ለመጀመሪያ ጊዜ በውጪው ዓለም የተመሠረተ ታላቅ ገዳም ነው፤ ራዕዩ ሰፊ እና ትልቅ ተስፋ ሰጪ ብሎም ነገ ቅድስት ቤተክርስቲያን ተተኪ ትውልድ አላት ወላዲቱ ቅድስት ቤተክርስቲያን አልነጠፈችም የሚያስብል ሥራ ነው እንበርታ እናግዝ የራሳችንን ድርሻ እንወጣ እንላለን።

መካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ የአብነት ት/ቤት እና አቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ገዳም የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እንዲሁም በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው  የሚገኙ ካህና...
04/11/2022

መካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ የአብነት ት/ቤት እና አቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ገዳም የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እንዲሁም በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚገኙ ካህናት ምዕምናን ምዕመናት በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል፤ የሀገረ ስብከቱም ሊቀ ጳጳስ የቦታውን ስም እና ራዕይ ተመልክተው አባቶችን እና ምዕመናኑን እንዲበረቱ፣ እንዲጠነክሩ አባታዊ ምክር እና ቡራኬ በመስጥት የበዓሉ ፍፃሜ ሆኗል፤
የአቡነ ፊሊጶስ ቡራኬ ረደኤት እንዳይለየን ብሎም የተጀመረውን ሥራ ከዳር ለማድረስ የሁላችንም ተሣትፎ እንዳይለየን በታላቁ አባት አቡነ ፊሊጶስ ገዳም ስም በአክብሮት ለመጠቆም እንወዳለን።

የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የድንግል ማርያም የአሥራት ልጆች ኦርቶዶክሳዊያን በመጪው ቅዳሜ ማለትም ሚያዚያ 1 ቀን 2014 (April 9, 2022) የመካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ የአብ...
04/06/2022

የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የድንግል ማርያም የአሥራት ልጆች ኦርቶዶክሳዊያን በመጪው ቅዳሜ ማለትም ሚያዚያ 1 ቀን 2014 (April 9, 2022) የመካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ የአብነት ት/ቤትና አቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ገዳም ምረቃ ወይንም የመሠረት ድንጋይ የሚቀመጥበት ስለሆነ በእለቱ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እንዲሁም ተጋባዥ ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ አባቶች ስለሚገኙ በቦታው ተገኝተው የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል፤
ለመምጣት ከተለያዩ የዋሺንግተን ዲሲና፣ ሜሪላን እንዲሁም ቨርጂኒያ ግዛቶች ቫኖች ስላዘጋጀን የሚከተለውን የጉግል ፎርም በመሙላት በቦታው እንዲገኙልን ስንልን በትህትና እንገልጻለን።
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSedhidjB8iaNHzSMRt07EF7U1ifs9Sgqqw7hex6PbZCQxTSqQ/viewform

03/28/2022

በመጪው ሚያዚያ ፩ ቀን ፳፻፲፬ ዓም ማለትም (April 9, 2022) at 11:00 am. የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በሚገኙበት የመሠረት ድንጋይ ይቀመጣል፤ በዚህ ታሪካዊ ቀን ላይ በመገኘት የቡራኬው ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል፤
የነገዋን የቤተክርሲትያን ተረካቢ ሕፃናት የሚታነፁበት ገዳም

የመካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ አዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት ዋና ዓላምዋ፤ ተተኪውን ትውልድ በዚህ ሃገር ማፍራት ነው
03/15/2022

የመካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ አዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት ዋና ዓላምዋ፤ ተተኪውን ትውልድ በዚህ ሃገር ማፍራት ነው

መካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ የአዳሪ አብነት ት/ቤትና አቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ገዳም በኪንግ ጆርጅ ካውንቲ ቨርጂኒያ እንደ አምላክ ፈቃድ ተመሥርቷል፤ እንኳን ለመላው ኦርቶዶክዋው....

መካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ አዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት እና የአቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ገዳም: በመጪው ሚያዚያ ፩ ቀን ፳፻፲፬ ዓም ማለትም  April 9, 2022 at 11:00 AM....
03/11/2022

መካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ አዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት እና የአቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ገዳም: በመጪው ሚያዚያ ፩ ቀን ፳፻፲፬ ዓም ማለትም April 9, 2022 at 11:00 AM. የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሚገኙበት የመሠረት ድንጋይ ይቀመጣል፤ በዚህ ታሪካዊ ቀን ላይ በመገኘት የቡራኬው ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ አስቀድመን መልዕክታችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን፤
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን።
መካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ አዳሪ የ አብነት ትምህርት ቤት

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ። ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በ...
03/07/2022

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ።
ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።
በሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ፣ ጥር 14 ቀን 1972 ዓ.ም. ከተሾሙት 15 ብፁዓን አባቶች አንዱ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፤ እስከ ዕርጅና ዘመናቸው ከቆዩበት ደብረ ብርሃን ቀደም ብሎ፣ በአርሲ እና በመቐለ አህጉረ ስብከት ተመድበው ጉልሕ ሐዋርያዊ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡
የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን።

Address

16076 Kings Mill Road
King George, VA
22485

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mekane Tibebat posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Mekane Tibebat:

Share