ODAA International Humanitarian Aid

ODAA International Humanitarian Aid ODAA Humanitarian Aid is an organization dedicated to identifying & assisting human rights abuse victims.

We strive to alleviate the suffering of victims by providing basic necessities, psychological support & rehabilitation.

በፊንፊኔ ዙርያ   የዋቄፈና እምነት ተከታዮች ገልማ የኦሮሞን ወግና ባህል ሲንከባከብ ሲጠብቅና ሲያጠናክር ለአስራ አራት አመት የቆየ ነው። ለብዙ ግዜያት በኪራይ ሲቸገር ቆይቶ በቅርቡ በመዋጮ...
07/21/2022

በፊንፊኔ ዙርያ የዋቄፈና እምነት ተከታዮች ገልማ የኦሮሞን ወግና ባህል ሲንከባከብ ሲጠብቅና ሲያጠናክር ለአስራ አራት አመት የቆየ ነው። ለብዙ ግዜያት በኪራይ ሲቸገር ቆይቶ በቅርቡ በመዋጮ #430 ካሬ ገዝተው ሲያበቁ ቤት ለመስራት አቅም አጥሯቸዋል። ሌሎች ቤተ እምነቶች መሬት በወረራ መልክ ጭምር እየያዙ ሀይማኖታቸውን ሲያስፋፉ ሀገር በቀሉ #ዋቄፈታ በአባት ሀገር ኦሮምያ ቤተ አምልኮውን መገንብያ ቦታ አጥቶ መንገላታቱ ያስገርማል። የዋቄፈና እምነት ከፖለቲካው በበለጠ ለኦሮሞ አንድነት ገንቢ ሚና ይጫወታል።

Oda international Humanitarian Aid የድርሻችንን እንወጣ በማለት ከHaaromsa ጋር በመተባበር ባለ12ፌሮ×13 ገዝቶ አስረክቧል።

★ የእምነቱ ተከታይ የሆናችሁ እንዲሁም የኦሮሞ ባህል፣ቋንቋና ማንነት ማበብ ላይ ግድ የሚላችሁ ሁሉ የዋቄፈና እምነት ተከታዮች ገልማ ማሰርያ የሚውል በገንዘብ በአይነት ድጋፍ በማድረግ የኦሮሙማ ግዴታችሁን እንድትወጡ እንላለን።

CBE- 1000471816853

Oromia Bank- 1147487800001

05/23/2022

በርሲሳ ተፈራ ተኤራ

- በርሲሳ ተፈራ ተኤራ ለ76ኛ ጊዜ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን አስተምረው በባልቻ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ አስመርቀዋል። እዛው ጠባብ ብርሃን የሌለው ቤት ውስጥ እየኖሩ ብርሃን መስጠታቸውን ቀጥለዋል።

ረጅም እድሜ ለአባታችን 😍

https://t.me/HawiiEr

★ Konsartii Deeggarsa Kabbadaa GarramaCaamsaa 14 bara 2014 Sa'a 7:30 @ Galma Everastitti.★ የምትችሉ ሰዎች የድጋፍ ኮንሰርቱ ላይ ተገኝታች...
05/16/2022

★ Konsartii Deeggarsa Kabbadaa Garrama

Caamsaa 14 bara 2014 Sa'a 7:30 @ Galma Everastitti.

★ የምትችሉ ሰዎች የድጋፍ ኮንሰርቱ ላይ ተገኝታችሁ የበኩላችሁን አድርጉ ያልቻላችሁ ጓደኛ ወዳጅ ዘመድ ጋብዙ 🙏

***********************************

ከሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት የኦሮሞ ህዝብ የደረሰበት ሀዘን ከፍተኛ እንደነበር የሚታወቅ ነው። ሰኔ 23 ሀዘናቸውን ለመግለፅ በወጡ ሰዎች ላይ ጀሞ ሚካኤል አከባቢ በተወረወረ ቦንብ ሰባት ሰው ሞቶው በርካቶችም ቆስለው እንደነበር ይታወቃል። ሀዘናቸውን ሊገልፁ ወጥተው ቦንብ ተወርውሮባቸው ከቆሰሉት መሀል የሚባል ወጣት በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶ ሁለት እግሮቹን አጥቷል። ከበደ ገረማ የሁለት ልጆች አባትና በኪራይ ቤት የሚኖር ከባድ ችግር ውስጥ ያለ ወጣት ሲሆን፣ አሁን ላይ አንድ እጁ የማይሰራ ተከታታይ ህክምና የሚያስፈልገው መሆኑን በአካል ተገኝተን አረጋግጠናል።

በችግር ውስጥ ያለውን ወንድማችንን ማገዝ የምትችሉ ሁሉ ከጎኑ እንድትቆሙ በአክብሮት እንጠይቃለን።

ልጁን በቀጥታ ማግኘት ለምትፈልጉ👉 0995000651

ለወንድማችን ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ👇
Awash Bank - 01320694697600
Oromia Bank - 1341236900002
COOP - 1030900069685
CBE - 1000456608993

HaaHaaromsa FinfinneenHaaromsa Finfinnee

05/09/2022

ከሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት የኦሮሞ ህዝብ የደረሰበት ሀዘን ከፍተኛ እንደነበር የሚታወቅ ነው። ሰኔ 23 ሀዘናቸውን ለመግለፅ በወጡ ሰዎች ላይ ጀሞ ሚካኤል አከባቢ በተወረወረ ቦንብ ሰባት ሰው ሞቶው በርካቶችም ቆስለው እንደነበር ይታወቃል። ሀዘናቸውን ሊገልፁ ወጥተው ቦንብ ተወርውሮባቸው ከቆሰሉት መሀል የሚባል ወጣት በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶ ሁለት እግሮቹን አጥቷል። ከበደ ገረማ የሁለት ልጆች አባትና በኪራይ ቤት የሚኖር ከባድ ችግር ውስጥ ያለ ወጣት ሲሆን፣ አሁን ላይ አንድ እጁ የማይሰራ ተከታታይ ህክምና የሚያስፈልገው መሆኑን በአካል ተገኝተን አረጋግጠናል። ማህበራችን ከ ODAA International Humanitarian Aid ጋር በመተባበር የ10,000 ብር ድጋፍ አድርጓል።

በችግር ውስጥ ያለውን ወንድማችንን ማገዝ የምትችሉ ሁሉ ከጎኑ እንድትቆሙ በአክብሮት እንጠይቃለን።

ልጁን በቀጥታ ማግኘት ለምትፈልጉ👉 0995000651

ለወንድማችን ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ👇
Awash Bank - 01320694697600
Oromia Bank - 1341236900002
COOP - 1030900069685
CBE - 1000456608993

Haaromsa Finfinnee

ትግል ዘርፈ ብዙ ነው።በተግባር ዋጋ የሚከፍል እንዳለ ሁሉ ፣በገንዘብ የሚረዳ፣በሀሳብ የሚያግዝ፣የተሰዉ ጀግና ልጆቹን መዘከርና ቤተሰቦቻቸውን መርዳትም አንዱ የትግል መገለጫ ነው።በዛሬው እለት...
05/09/2022

ትግል ዘርፈ ብዙ ነው።በተግባር ዋጋ የሚከፍል እንዳለ ሁሉ ፣በገንዘብ የሚረዳ፣በሀሳብ የሚያግዝ፣የተሰዉ ጀግና ልጆቹን መዘከርና ቤተሰቦቻቸውን መርዳትም አንዱ የትግል መገለጫ ነው።

በዛሬው እለት ለሞገስ ቤተሰቦች ከ ODAA International Humanitarian Aid በተገኘ ድጋፍ Haaromsa Finfinnee እና በአዶዬ ማህበር ጋር በመተባበር 6500ብር ድጋፍ አድርገናል!
-----------------------------------------------------------
ሞገስ ደምሴ ማኮ ይባላል በ1975 ፊንፊኔ ስር ቡራዩ የተወለደ ሲሆን አባቱ በልጅነቱ በመሞታቸው ቤተሰቡን ለማገዝ ደፋ ቀና በማለት ወደ ንግድ አለም ተሰማራ። በትምህርቱ ጠንካራና ጎበዝ በመሆኑ እንዲሁም #በሰቦናነቱ የተወደደና የተከበረ ነበር።

ሞገስ በ90ዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ ያደረገና ትልቁን ሚና የሚወስድ ነው።በተጨማሪም የኦሮሞን ባህል ማንነትና እምነት ከመመለስ አኳያ የመኖርያ ግቢውን #ለዋቄፈና እምነት ግልጋሎት እንዲውል የለገሰ ሲሆን በዚህም ምክንያት በተለያየ ግዜ የእስር፣የማስፈራርያና የግድያ ሙከራዎች ተደርገውበታል።

ሙሉ የኦሮሞ ህዝብን ባስቆጣው የሀጫሉ ግድያን ተከትሎ በእስር ቤት ውስጥ በደረሰበት ድብደባ ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ማገገም ሳይችል በመቅረቱ ባለፈው ሳምንት ሀምሌ 11 2013 ALH ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ይህ ለራሱ ያልኖረ ደግና ታጋይ/አታጋይ ሰው በፎቶ ላይ እንደምትመለከቱት አራት ትናንሽ ልጆችና ደካማ እናቱን ጥሎ ነው የሞተው።

ስለዚህ በህይወት በነበረ ሰዓት ብዙዎችን ሲረዳና ሲያታግል ለነበረ ጀግና ምላሻችን ምንድን ነው? ተጨማሪ መረጃ የምትፈልጉ ሰዎች ከስር ባለው ስልክ በመደወል የሞገስን ባለቤት ማግኘት ትችላላችሁ!

ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ!
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ👉 1000169380582
0929310411 👉 ሽቶ ሙደሲር አባጅሩ(ባለቤቱ)

07/20/2021
06/10/2021

Obboo Tafarraa Ta'eraa jedhamu. Barnoota Afaan Oromoo waggaa 28f Finfinnee keessattii barsiisaniiru. Waggaa kana keessattiis barattoota kuma 20 ol eebbisisaniiru. Nama gameessa akkanaa ummatasaaf waan Danu gumaachee haar'a jireenya rakkisaa keessattii argamu. Reebiichii yaalin ajjechaa waraanamu, mana dukkana dhiphoo , hiyyummaa belaa fi gidiira rakkina heddu walin wal'aansoo walqabaa har'allee lubbun jiru. Mana dhiphoo ibsaa hin qabne kana keessatti waggaa 28ffaaf jiraataa jiru. Nama kana 'hawwaasnii bal'aan dagate Jira yaadatamu qabu' jechun Waldaan Haaromsa Finfinnee gara mana isaaniittii imalun turti isaan walin godheera. Gahaa ta'u baatus gargaarsa ODA International Humanitarian Aid irraa argatenis deeggarsa qarshii kuma 10 godheraaf.

Turti gaarii!
____

- ተፈራ ታኤራ ጪምሳ ይባላሉ ለ28 አመታት አፋን ኦሮሞን በበጎ ፈቃደኝነት ሲያስተምሩ ቆይተዋል አሁንም እያስተማሩ ይገኛሉ። በነዚህ ግዜያቶችም ከ20ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስተምረው አስመርቀዋል። በከተማችን ፍንፍኔ ብዙዎች የሚያውቋቸው ናቸው ሆኖም ምንም አይነት ድጋፍ የማያገኙ በአሳዛኝ የህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ እያለፉ ያሉ ሰው ናቸው።የሚኖሩበት ቤት እንኳን መብራት የሌለው ተዕለት ጉርሳቸውም የሚቸገሩ አዛውንት አባት ናቸው ይህንን በመገንዘብም ማብራት እንዲያስገቡ፣እንዲሁም ለማለት ወጭያቸውና ለአንዳንድ ነገር እንዲያግዛቸው ከOdaa International Aid በተገኘ ድጋፍ የ 10,000 ብር ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

Warra gargaaruu feetaniif/
መርዳት ለምትፈልጉ
Baankii Daladala Itiyoophiyaa/
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
Lakkii.Herreegaa/ የባንክ ቁጥር
1000304102555

Lakkoofsa Bilbilaa/የስልክ ቁጥር
+251913914189

06/07/2021

ARTIIST BASHANNANAA HAAYILU!
----
Artiist Bashannanaa Haayiluu jedhamaa. Wellisaa fi Barreessaa Muziqaati. Hojiwwan wallee warraaqsaa fi jaalalaa dalagun beekama. Artiist Bashannanaa Haayiluu Qabsawaa gameessaa fi wallee fi hojii artii isaatin lammii isaa tajaajilaa asin gahe dha. Gama qabsootin qabsaawoota gameeyyiirraa fudhun dhalootatti dabarsuf ciichanii umurii isaanii guutuu sabaaf laatan keessatti adda durummaan nama ramadamu dha. Keesumaa Wallee Geelloo fi Kumkummeen Artiin qabsoo warra loboobsan keessaa innii adda dura. Walleewwan isaa FDG finiinsun beekaman keessaa “Oromummaan Dhaloota”, “Nuti Qeerroon Leenca Goota”, “Standup Qeerroo” kanneen jedhaman kan haangafaati fi gurra nama heddun dhagahaamanii hin qufnee haar’as haaraa kan ta’an dhagahaamaa kan jiran dha.

Artiistiin Jabaa akkanaa haar’a haallii innii itti argamu baayyee yaaddeessaa dha. Waan nyaatuu wan uffatu lafuma rafullee nama hin qabne dha. Bashannanaan Oromummaaf nama arsaa kaffalee, samiif lafti Oromummaan beekan. Namanii akkanaa gaafa miidhamu argu, Oromummaatu kufe waan isa kaasu dhabe kan rakkachaa jirutti namatti dhagahaama. Kanaafis Nama kana haala keessa jiru ilaalun rakkosaaf furmaata goochuun, waan yeroon fi sabboonummaan Oromoo nugaafattu dha. Gargaarsa haanga humnaa gochun nama kana gargaarun diirqama Oromummaa haabaanun Dhaamsa keenya.

Bu'uruma kanaan Waldaan Haaromsa Finfinnee gargaarsa maallaqa 'ODA INTERNATIONAL HUMANITARIAN AID' irraa argateen qarshii kuma 10 baasii gochuun Artist Bashannanaa karaarraa kaasun , mana kutaa tokko kireeffachuun meeshalee bu'uraa guutuun jireenya eegalchiise jira. Gamanumaan Uummatnii bal'aan Artistii kana deeggarun diirqama Oromummaa keessan akka bahaattan dhaamsa keenya dabarsinaa!

×××××××××××××××××××

ታጋይና አርቲስት በሸነና ሀይሉ

- አርቲስትና ታጋይ በሸነና በኦሮሞ የትግል አርት ውስጥ ያለፈ ከ35 በላይ ስራዎች ያሉት ሲሆን አሁንም በርካታ ስራዎች በእጁ ይገኛሉ። ይህ አርቲስትና ታጋይ በአሁኑ ሰዓት ቋሚ የሆነ ኑሮ የሌለው ባገኘበት የሚያድር የእለት ጉርሱን ለመሙላት ያቃተው ሆኗል። ይህንን ታጋይና አርቲስት ከOdaa International Aid በተደረገ እገዛ ከሜዳ አንስተን እቤት በመከራየት፣ልብሱን እንዲለውጥ በማድረግ፣የቤት ቁሳቁስ በሟሟላት የሚያስፈልጉትን እቃዎች እንዲያሟላ የገንዘብም ድጋፍ ተደርጎለታል። ይህ እገዛ እራሱን አረጋግቶ ውስጡን የሚያዳምጥበት ሁኔታ ያመቻቻል በእጁም ላይ ያለቁ በርካታ ስራዎች አሉ። በቀጣይ ወደ ሶሻል ሚድያ በማምጣት ሌሎች እገዛ ማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች እንዲያገኙትም ጥረት ይደረጋል ብለን እናምናለን።

Address

Houston, TX
77002

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ODAA International Humanitarian Aid posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share