EthioPost ኢትዮ-ፖስት

EthioPost ኢትዮ-ፖስት EthioPost is all about Ethiopian culture, education, sport, technology, news, music, movie, & jokes.

ሰበር ዜና Breaking News!ስዩም መስፍንን እና አባይ ፀሐዬን ጨምሮ የጁንታው ቀንደኛ አመራሮች ተደመሰሱ**************************የመከላከያ ሰራዊት ሀይል ስምሪት መምሪያ...
01/13/2021

ሰበር ዜና Breaking News!

ስዩም መስፍንን እና አባይ ፀሐዬን ጨምሮ የጁንታው ቀንደኛ አመራሮች ተደመሰሱ
**************************

የመከላከያ ሰራዊት ሀይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋደል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ዛሬም እንደ ትናንቱ አስደናቂ ጀግንነታቸውን በአንፀባራቂ ድል ታጅበው በድል መወጣት መቀጠላቸውን ለኢዜአ ገልፀዋል።

አሁንም የተቀሩትን የጁንታ አመራሮች የገቡበት ገብተው የማደን ተግባራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋልም ብለዋል።

የጁንታው ቡድን ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ በስልጣን ላይ እያለ ኢትዮዽያዊ፣ ከስልጣን ሲወርድና የማይመች ሁኔታ ሲፈጠር ደግሞ አገርን የመበታተንና የማተራመስ ስትራቴጂ ነድፎ የማያሸንፈውንና የማይወጣውን ውጊያ በአባት አርበኝነት ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ እንደቆየ ጠቁመዋል።

ከዚህ ተግባሩ ሊቆጠብም ሆነ ከትላንት ሊማር ያልቻለው የጁንታው ቡድን በሰራዊታችን ላይ ውጊያ ከፍቶ በለኮሰው እሳት በመለብለብ ላይ እንደሚገኝም አረጋግጠዋል።

የጁንታው ቡድን አመራሮች ባለፈው ጥቅምት መጨረሻ በመቀሌ በተካሄደው ዘመቻና ድምሰሳ ወቅት በ48 ሰዓት እጅ እንዲሰጡ ቢለመኑም፣ በማናለብኝነትና ትዕቢተኝነት እምቢ በማለት ወደ ጫካ መግባታቸውን ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አስታውሰዋል።

በድጋሚም የአገር መከላከያ ሰራዊት የሀገር ሽማግሌ ጭምር በመላክ እጅ እንዲሰጡ፣ ትጥቅ እንዲፈቱና ጉዳዩቸው በህግ እንዲታይ ቢያስጠይቅም አሻፈረኝ ብለውና የያዙትን የጥበቃ ሀይል በመተማመን እንዲሁም “ተመልሰን እንነሳለን” በሚል የድሮ ብሂል ተሳስተው ያለ እድሜያቸው በዱር በገደሉ ተሸሽገዋል ብለዋል፤ ዋሻዎችን በመጠቀምም ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን እይታ ውጪ ለመሆን ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ሲሉም ገልፀዋል።

ሆኖም ደከመኝ ሰለቸኝ የማይለው ጀግናዊ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ሀይሎች በዛሬው እለት በጋራ ባደረጉት ጠንካራ ፍተሻ በተከዜ ወንዝ ዳርቻ ቀደም ሲል ሰራዊቱን በማስመታት ኢትዮጵያን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ፣ ሲያቅዱና ሲመሩ የነበሩ ቀንደኛ የጁንታው አመራሮች ከጥበቃ ሀይላቸው ጋር በነበረው ተኩስ ልውውጥ በውጊያ ላይ ከነጥበቃዎቻቸውና የጥበቃ ወታደራዊ አራሮቻቸው ጋር መደምሰሳቸውን ለኢዜአ ገልፀዋል።

እነዚሁ በነበረው ውጊያ ከጥበቃዎቻቸው ጋር አብረው የተደመሰሱ የጁንታው አመራሮች፣

1. አቶ ስዩም መስፍን፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ እንዲሁም ውጊያውን የመሩና ሰራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ያዘዙ፣ በመጨረሻም በሰራዊቱ ላይ ውጊያ እንዲከፈት ትዕዛዝ የሰጡ፣

2. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ፣ የጁንታው ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

3. አቶ አባይ ፀሃዬ፣ የጁንታው ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

4. ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ ከመከላከያ የከዳ ከነጥበቃዎቻቸው ተደምስሰዋል

በሌላ በኩል በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊና የክልል አመራሮች
1. ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን፣ ከመከላከያ የከዳ
2. ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
3. ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
4. ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረ
5. አቶ መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ፣ የክልሉ ውሃ ስራዎች ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበረ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋደል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው፣ ባስተላለፉት መልዕክት፣ አሁንም በየዋሻው የተደበቁ የጁንታው ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

“ትርጉም ለሌለው ጁንታ ጠባቂ በመሆን ውድ ህይወታቸውን አትገብሩ፣ ከቻላችሁ ይዛችኋቸው፣ ካልቻላችሁ በሰላም ለሰራዊቱ እጅ እንድትሰጡ ጥሪ አቀርባለሁ” ብለዋል።

በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ጁንታው ተመልሶ ይመጣል በሚል ያላቸው ግምት የተሳሳተና የጁንታው ቡድን ዘመን ያከተመ መሆኑን አውቀው፣ ከሀገራቸውና ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ ሽግግር መንግስት ጎን በመሆን ትግራይን እንዲያደራጁ፣ እንዲያለሙና መላው ህዝብም የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

እስክንድር ነጋን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ላይ ምስክር ለማሰማት መጋቢት 29 እና 30 ቀን 2013 ቀጠሮ ተሰጠ ******************የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ሕገ መንግሥታዊ ...
12/25/2020

እስክንድር ነጋን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ላይ ምስክር ለማሰማት መጋቢት 29 እና 30 ቀን 2013 ቀጠሮ ተሰጠ
******************

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ሕገ መንግሥታዊ እና የፀረ ሽብር ጉዳዮች ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ የሚገኙ አራት ተከሳሾች ዛሬ የተከሰሱበትን ወንጀል ክደው በመከራከራቸው የዐቃቤ ሕግን ምስክር ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቷል።

በዛሬው የችሎት ውሎው ተከሳሾቹ የእምነት ክህደት ቃል እንዲሰጡ ተደርጓል።

ተከሳሾቹም ወንጀሉን አልፈጸምንም ብለዋል።

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ተከሳሾቹ ወንጀሉን ክደው ስለተከራከሩ ምስክር ማሰማት ይፈቀድልኝ በማለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ችሎቱም መጋቢት 29 እና 30 ቀን 2013 ዓ.ምን ጨምሮ በሚያዚያ ወር ውስጥ በድምሩ ዐሥር ቀናት ያህል ምስክር እንዲያሰማ ፈቅዷል።

የትህነጉ ጌታቸው ረዳ ወንድም: ሞላ ረዳየጌታቸው ረዳ ታናሽ ወንድም ሲሆን የሚኖረው በአሜሪካን ሀገር ሚኖሶታ ግዛት ነው። በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ December 22, 2020 ማክሰኞ በጌታቸው...
12/23/2020

የትህነጉ ጌታቸው ረዳ ወንድም: ሞላ ረዳ

የጌታቸው ረዳ ታናሽ ወንድም ሲሆን የሚኖረው በአሜሪካን ሀገር ሚኖሶታ ግዛት ነው።

በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ December 22, 2020 ማክሰኞ በጌታቸው ረዳ የትዊተር አካውንት ላይ "አለን አልሞትንም" የምትል አጭር ጽሁፍ ጣል አድርጎ ህዝቡን ሲያንጫጫ ውሏል!!

የ computer Science ባለሞያዎች ከየት ትዊት እንደተደገ location check አድርገው ከአሜሪካ Minnesota ግዛት መሆኑን አረጋግጥወል::

ታህሳስ  4 ቀን 2013የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ ፣ ዛሬ በመቀሌ ከመከላከያ ከፍተኛ አዛዦችና ከየግንባሩ አዛዦች ጋር መክረዋል ።በምክክር መድረኩ ላይ ፣ የ...
12/13/2020

ታህሳስ 4 ቀን 2013

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ ፣ ዛሬ በመቀሌ ከመከላከያ ከፍተኛ አዛዦችና ከየግንባሩ አዛዦች ጋር መክረዋል ።

በምክክር መድረኩ ላይ ፣ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ፣ ም/ኢታማዦር ሹም አበባው ታደሰን ጨምሮ ሁሉም የግንባር አዛዦች ተሳትፈዋል ።

ጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ፣ በስራችሁ ኮርቻለሁ ። ልምዳችሁን ለመጪው ትውልድ በማውረስ ታሪክ የማይረሳው ጀግንነታችሁ ሲታወስ ይኖራል ብለዋል ።

ብዙአየሁ ተሾመ

ቤቲ ተከሰሰች
12/06/2020

ቤቲ ተከሰሰች

12/05/2020

ያንተ ዘር ከሌላው ዘር የተሻለ ሆኖ ከተሰማህ ቆፍረህ ዝራው።

Breaking newsሰበር መረጃየትህነጉ ደብረፂየን ተደብቆ ከስግደኞች ጋር ወደ ደቡብ ሱዳን በመግባት ከጠላት ግብፅ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር እየተገናኘ መሆኑ መረጃ ደርሶናል
11/30/2020

Breaking news
ሰበር መረጃ
የትህነጉ ደብረፂየን ተደብቆ ከስግደኞች ጋር ወደ ደቡብ ሱዳን በመግባት ከጠላት ግብፅ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር እየተገናኘ መሆኑ መረጃ ደርሶናል

የእርዳታ ጥሪአቅም ያለው በገንዘቡ የሌለው ሼር በማድረግ ይርዳ #ማይካድራ እንርዳ  help  የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እንዳረጋገጡት በዐማራነታቸው ብቻ ተመርጠው ከስድስት መቶ በላይ ወገኖቻች...
11/29/2020

የእርዳታ ጥሪ
አቅም ያለው በገንዘቡ የሌለው ሼር በማድረግ ይርዳ
#ማይካድራ እንርዳ help

የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እንዳረጋገጡት በዐማራነታቸው ብቻ ተመርጠው ከስድስት መቶ በላይ ወገኖቻችን ተጨፍጭፈዋል፤ ብዙ ሽህዎች ወገኖቻችን ተሰደዋል። የእነዚህን ወገኖቻችንን ቤተሰቦችና የተሰደዱትን የመርዳት ሃላፊነት ግዴታችንን እንወጣ። ለወገን ደራሹ ወገን ነው።

Amnesty, the UN High Commissioner for Human Rights, and the Ethiopian Human Rights Commission confirm that more than 600 innocent civilians have been massacred in Mai Kadra, Ethiopia; tens of thousands have been forced to flee. They need our help.

https://www.gofundme.com/f/ethiopians-have-been-massacred?fbclid=IwAR13OMsxXSn8tuyPdYFdIIXqqxvlH1TsayClN1JA3WYf4Ot9DvY-m7us8Zk

ማሳሰቢያ !!!!!!!!!!! እርዳታ በሚያደርጉበት ጊዜ ጎ-ፈንድ-ሚ የሚጠይቅዎትን ተጨማሪ ች… Global Alliance for the Rights of Ethiopians needs your support for Let's help war victims in northern Ethiopia

11/29/2020

🎵 ዘመን አመጣሽ የዘር በሽታ
መድሀኒት አለው የማታ ማታ 🎵

ሀገር በወገን እንዴት ይረታ
ፍቅር በነገር እንዴት ይፈታ
ዘር ሳይለያየን ወይ ሐይማኖት
ከጥንት በፍቅር የኖርንባት
እናት ኢትዮጵያ ውድት ውድቷ
በጎጆ አያልቅም ሙሽርነቷ

🎵 ዘመን አመጣሽ የዘር በሽታ
መድሀኒት አለው የማታ ማታ 🎵
#ኢትዮጵያ

11/28/2020

ሰበር ዜና: አሁን በውስጥ በደረሰን መረጃ ትህነግ ከተደበቀችበት በ4 ሮኬት የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራን መታች:: Reports of four rockets hitting Asmara

11/28/2020

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መቀሌ ከተማ መግባቱ ሰምተናል።
የትህነግ አመራሮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የቤት ለቤት አሰሳ እየተካሄደ መሆኑን ሰምተናል‼️

ሰበር መረጃ ዳንኤል ብርሃኔን ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም አገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ 7 ግለሰቦች እና በ27 ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዘዝ መውጣቱን ፌዴራል ፖሊስ አስታ...
11/28/2020

ሰበር መረጃ
ዳንኤል ብርሃኔን ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም አገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ 7 ግለሰቦች እና በ27 ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዘዝ መውጣቱን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ
----------------------------------------------
የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙና በተለያዩ እርከን በሚገኙ 27 ወታደራዊ ሹማምንት በፈፀሙት የዘረፋ ወንጀል ንብረታቸው የሚፈለግ የጁንታው ህወሃት ቡድን አባላት እና ዳንኤል ብርሃኔ፣ ዶክተር እዝቅኤል ገቢሳ፣ ዶክተር አወል አሎ ቃሲም እና ሌሎች አምስት ግለሰቦች በአሃገር ውስጥና ባህር ማዶ ሆነው የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም አገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የመያዣ ትዕዘዝ መውጣቱን ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በመግለጫው መሠረት ቀደም ሲል በፈፀሙት የአገር ክህደት ወንጀል የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው 117 ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች በተጨማሪ ስማቸው ቀጥሎ የተገለፀው 7 በተለያየ እርከን ላይ የሚገኙ ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዛዝ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

Address

Central Expressway
Dallas, TX
75231

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioPost ኢትዮ-ፖስት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to EthioPost ኢትዮ-ፖስት:

Featured

Share