Gasha Amhara / ጋሻ አማራ

Gasha Amhara / ጋሻ አማራ Advocate, educate/inform the wider international community about the plight of Amharas in Ethiopia.

ስለአማራ ህዝብ የህልውና ትግልና አንድነት ተብሎ በታላቁ እስክንድር ነጋ እየተከፈለ ያለ ያልተነገረ ታላቅ መስዋእትነት ‼️በወዳጅና በጠላት 7/24 ሰዓት ስሙ እየተብጠለጠለ በዝምታ ድባብ የማ...
05/18/2024

ስለአማራ ህዝብ የህልውና ትግልና አንድነት ተብሎ በታላቁ እስክንድር ነጋ እየተከፈለ ያለ ያልተነገረ ታላቅ መስዋእትነት ‼️

በወዳጅና በጠላት 7/24 ሰዓት ስሙ እየተብጠለጠለ በዝምታ ድባብ የማስተናገዱ ምስጢር ምንድነው??

*** ወንድወሰን ተክሉ***

💥💥💥 እየተሰደቡ ዝም ለማለት፤ እየተብጠለጠሉ ዝም ለማለት ታላቁ እስክንድርን መሆን ሳይጠይቅ አይቀርም

ሁላችንም ብንሆን ስማችን ሲነሳ Re-act እናደርጋለን፡ ብዙዎች ስማቸው አንዴ ተነስቶ መቶ ግዜ ስማቸውን ለማጥራት መልሰው መላልሰው ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ አንዳንዲች ደግሞ በዝምታ ልጔም እራሳቸውን ለጉመውና ሸብበው ግን ስማቸው በክፉ ሲነሳ ብቅ ብለው ከመቅጽፈት ምላሽ ሲሰጡ ይሰማል፡፡ በወዳጅም ሆነ በጠላት ስሙ almost 7/24hr እየተጠራ ቅንጣት ምላሽ ሳይሰጥ በዝ፤ታው ድባብ በስራው ላይ ብቻ አትኩሮ የሚሰራ ሰው ቢኖር ያለአንዳች ማጋነን ታላቁ እስክንድር ነጋ ብቻ እና ብቻ ነው፡፡

የታላቁን ስም ሁሉም ያነሳዋል፡፡ ከትናንሾቹ እስከ ትላልቆቹ ስሙን ያነሱታል፡፡ ትናንሾቹ ስል በእድሜ ያልበሰሉ እንቦቆቅላ ታዳጊዎቻችንን ማለቴ ሳይሆን የህይወታቸውን አብዛኛውን እድሜ ቅርጥፍ አድርገው የበሉ ከሀምሳና ከስድሳ በላይ ሆነው ግን በአሳስብ አድጎ ህጻን የሆኑትን ማለቴ ነው፡፡

ታላቁ እስክንድር ነጋ በወርሃ ሀምሌ አጋማሽ በ2022 ላይ ከአሜሪካን በመጣ ማግስት ደብዛውን አጥፍቶ ለትጥቅ ትግሉ ወደ ጫካ ከገባበት ግዜ ጀምሮ ስሙ ከጠላት ጎራ በኩል ብቻ ሳይሆን የትግል አጋርህ ነን ከሚሉት የቅርብ ሰዎችም ጭምር ስሙ ነጋ ጠባ Almost 7/24hrs በሚያስብል ደረጃ እየተነሳ ሲተች፤ሲብጠለጠልና ብሎም ሲደገፍ እነሆ ወደ ሁለተኛ አመቱ በተቃረበበት ሁኔታ ታላቁ ሰው ቅንጣት ታክል ምላሽ ሳይሰጥና አካሄዱን፤ አቌሙን ሳይቀይር የተነሳበትን ዓላማን ከግብ ለማድረስ ድምጹን አጥፍቶ ታግሎ በማታገል ላይ ያለ ልዪ ሰው ነው፡፡

የታላቁ እስክንድር ነጋ ስም ከትግል አጋሮቹ አርበኛ ዘመነ ካሴ፤አስረስ ማረ ዳምጤ፤አበበ ፈንታውን ጨምሮ በበርካታ አጋሮቹ በበጎና በትችት ነቀፌታ ስሙ እየተጠራ ሲገለጽ የሰማና ያወቀ ቢሆንም ታላቁ ሰው ግን ብቅ ብሎ በአንዳቸውም ላይ ምላሽ ያልሰጠ ሰው በመሆን ይታወቃል፡፡

ይህ አይነቱ ስብእና ከብዙዎቻችን ዘንድ ፈጽሞ የሌለ ግን ለአንድ ህዝብ የህልውና ትግል አደረጃጀት እጅግ ወሳኝ በሆነ ሁኔታ የሚያስፈልግና የሚጠቅም ልዩ ተሰጥኦ መሆኑን መገንዘብና መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ታላቁ ሰው የአማራን ህዝብ የህልውናን ትግል በትጥቅ ለመክፈት አምኖበት ወደ ጫካ ከገባበት ወርሃ ሀምሌ 2022 ጀምሮ እስከዛሬዋ እለት ድረስ የአንዱንም ታጋይ ወንድሙን ስም ጠርቶ ምላሽ ባለመስጠት ዝምታው ሪኮርድ የሰበረ ሰው መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን? ስሙ ነጋ ጠባ እየተጠራ ለድፍን ሁለት ዓመት ያህል በዝምታ ስራው ላይ ማተኮር የቻለ ከታላቁ ሰው በስተቀር ማን አለ?? ያጋነንኩ ከሆነ ስም ጥቀሱልኝ፤ ለመቀበል ልቤና ዓይኔ ክፍት ነውና እቀበላለሁ፡፡

በሪኮርድ ደረጃ በዚህ ሁለት ዓመት ሊሞላው እየተቃረበ በመጣው የታላቁ ሰው ወደ ጫካ መግባት ሂደት ውስጥ ታላቁ ሰው አንድ ግዜ ብቻ የማንንም ስም ሳይጠቅስ ለመጀመሪያ ግዜ የደም ነጋዴዎች በማለት በህልውና ትግሉ ላይ ታላቅ ተግዳሮት የፈጸሙትን ሀይሎች የገለጸበትን አገላለጽ ከመስማታችን በስተቀር ታላቁ ሰው ስለጠላት እንጂ ስለአጋር ወንድሙ ቅንጣት ያህል የክፋት ቃል የማይወጣው ሰው መሆኑን በተግባር ያረጋገጠልን ልዩ ሰው ነው ፡፡

በተለይ በተለይ እራሱን ዓለም አቀፍ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪ IFCC ብሎ በሚጠራው ቡድን በሶስት ሚዲያዎች (አሻራ ሚዲያ፤ ማገር ሚዲያና የ IFCC channel ) በኩል በተክሌ ይሻው፤ አቻምየለህ ታምሩ፤ሀብታሙ ተገኝ፤ጋሻው ካሴና መሰል ቡድን ከወርሀ ታህሳስ 2023 እስከ ጥር 2024 ድረስ ሰባት ተከታታይ ፕሮግራም በማዘጋጀት ታላቁ ሰው ያልዋለበትን እንደዋለ አድርገው በማስተጋባት ያለስሙ ስም ሲሰጡት የሰጠው ምላሽ በዝምታ ስራውን መስራትን ብቻ ነበር የመረጠው፡፡ ይህ ፍጹማዊ ዝምታው ግን ከአክብሮት ይልቅ ለሀሰበ ድኩማን እንጭጮችና ሰርጎ ገብ የአማራ ህዝብ ጠላቶች የልብ ልብ ሰጠና እንደ ዋን ወያኔ (ዋን አማራ) ከአማራው በላይ አማራ ነኝ ለማለት የቃጣቸው እንጭጭ ሰርጎ ገቦች (ግርማ ካሳ፤ ዘመድኩን ነቀለ) አይነት አይናቸውን በጨው ያጠቡ ደናቁርቶች ታላቁን ሰው ስሙን እያነሱ ነጋ ጠባ እንዲያብጠለጥሉት እድል የሰጠ ሆነ፡፡

ከሁሉም በላይ መቼም ሆነ መች ፈጽሞ የማንረሳው ጥቃት የተሰነዘረው በኤሊያስ ክፍሌ አዛዥነት መረጃ ቲቪ ስር በተሰበሰቡ ኮልኮሌ None AMHARA አወቅን ባይ ጥልቅ ብዬ ሰርጎ ገቦች (ዘመድኩን ነቀለ፤ ግርማ ካሳ) በኩል የተከፈተበትን ተከታታይ የስም ማጠልሻ ዘመቻን ነው፡፡ እስቲ ይታያችሁ የበረከት ስምኦን ታዛዥ የመለስ ዜናዊ አድናቂና አምላኬ የሆነው ዘመድኩን ነቀለ የሚባል እብድ ከህወሃት ኢህአዴግ እስከ ኦህዴድ ብልጽግና የተፈራረቁትን ገዢዎችን («መለስ ዜናዊ፤ ኃይለማሪያም ደሳለኝና አቢይ አህመድን) በመታገል ጽናቱ ልዪ ሪኮርድ ካለው ታላቁ ሰው ይበልጥ ለአማራ ህዝብ አዋቂና ተቆርቌሪ መስሎ ታላቁን እስክንድር ነጋን ከትግሉ ውጣና ገዳም ግባ ብሎ መዳፈርን መፈጸም የመሰል ሰቅጣጭ ድድብና ይፈጸማል ብለን ፈጽሞ ባንገምትም - ዘመድኩን ነቀለ ግርማ ካሳ ኤሊያስ ክፍሌ በታላቅ ድፍረትና ድንቁርና ጸረ እስክንድር ዘመቻ ሲከፍቱ ያየንበትን ክስተት መቼም የማንረሳው ጥቃት መሆኑን የምንገልጸው ሀቅ ነው፡፡

💥💥💥 እዚህጋ ለእውነተኛውና Conscious ለሆነው ነገደ አማራ ተወላጅ የምጠይቀው ጥያቄ ለመሆኑ ዘመድኩን ነቀለ የሚባል ዘላን እብድ ብድግ ብሎ ታላቁን ሰው ከትግል ውጣና ገዳም ግባ ብሎ ሲለፋደድ፦

📌 1ኛ - እንዴት አንድ በጀርመን ያለ None AMHARA በሀገር ውስጥ ህይወቱን ለመስዋእትነት ሰጥቶ የሚታገልን ታጋይ ከትግሉ ወጥተህ ከፈለግክ ገዳም ካልሆነም ወደ ዲሲ ተጔዝ ልትል የቻልከው ብላችሁ ያላፋጠጣችሁት ???

📌 2ኛ - በምን ስሌትና ሎጂክ ነው አንድ ምትክ የለሽ ብርቅዬ ህይወቱ እንደሚሰዋ እያወቀ ግን ከነገደ አማራ ህልውና አይበልጥም ብሎ ታግሎ በማታገል ሂደት ውስጥ ሊከሰት የሚችልን የህይወት መስዋእትነትን ለመቀበል ወስኖ ጫካ የገባን ብርቅዬን የአማራን ልጅ አንድ ጀርመን የተጎለተ እብድ ኦሮሞ (ዘመድኩን ነቀለ ) እና አሜሪካን የተጎለተ ማንነት የለሹ ባዶ እራስ (ግርማ ካሳ) ጫካ ውስጥ ሆኖ ከሚታገለው አማራ ወገንህ (ታላቁ እስክንድር) በልጦብህ ዘመዴ ያለው እውነት ነው፡ እስክንድር ወጥቶ መልስ ይስጥበት እያልክ ልታስተጋባ የቻልከው ???

ወንድ ሆንክ ሴት፤ ወጣት ሆንክ አዛውንት፤ ምሁር ሆንክ መሀይም ለአንተ/ቺ ነገዳዊ ህልውና እና ነጻነት ብሎ ታግሎ ለማታገል ጫካ የገባን ታላቁን እስክንድር ይልቅ ይህ ወፍ ዘራሽ የሆነው ዘመድኩን፤ግርማና ኤሊያስ ክፍሌ በልጠውብህ ያወናበዱህ ሁሉ Shame on You ልንልህ እንወዳለን፡፡ አንተ አማራ ነኝ እያልክ ከመሪህ ታላቁ ሰው ይልቅ ሊመራህ የማይችለውንና ሊመራህ የማይገባውን ኦሮሞውን ዘመዴን እና ግርማ ተብዬውን የቅናት ሴራን ወሬ ተከትለህ የምትወዛገብ ካለህ Shame on You አንተ ተወልጃለሁ ብትልም ያልተፈጠርክ መናፍስት መሆንህን ልንገልጽልህ እንወዳለን፡፡ በሀገር ውስጥ ሆኖ ዋጋ እየከፈለ ያለውን እውነተኛን አማራ፤ ጀርመንና አሜሪካን ከተጎለተ ኢሮሞ ተወላጅ (ዘመድኩንና ግርማ) አሳንሰህ ለኦሮሞዎቹ ጩህት ልብና ጆሮህን በመስጠት ዘመዴ ለአማራ አስቦ ነው፤ ግርማ ለአማራ አስቦ ነው የምትል ሰው ነኝ ባይ አማራ ካለህ ቁርጥህን እወቅ አንተ/ቺ ሰው መሳይ መናፍስት የእንግዴ ልጅ ናችሁ፡፡

በዚህ ሰአት የነገደ አማራ ተወላጅ ሆኖ የኦሮሞው ዘመድኩን በቀለ ግርማ ካሳ ኤሊያስ ክፍሌና መረጃ ቲቪ ደጋፊና ተከታይ የሆነ ሰው ካለ እውነት እውነት እላለሁ አማራ መባሉ ይቅርና Councsiou የሆነ የሰው ልጅ ነው የማይባል - ወዳጅና ጠላቱን የማያውቅ ( ልክ እንደ በግ፤ፍየል፤ዶሮና ላም) ከጠላቱ ጋር የሚኖርና ጠላቱን የሚያገለግል እንሥሳ መሆኑን ይወቅ፡፡

አንድ Councsiou ነኝ የሚል አማራ ነኝ ባይ በምንም ዓይነት ተአምርና ሎጂክ ለነገደ አማራ ህዝብ ሁለንተናዊ ነጻነትና ሁለንተናዊ ህልውና ብሎ ጫካ ውስጥ እየታገለ ያለን እውነተኛን አማራ (ታላቁ እስክንድር ነጋን) በአንድ ለአማራው ከአማራው በላይ አውቅልሀለሁ ባይ ብልጣብልጥ ኦሮሞ ጩህትና ልፈፋ ተደነባብሮ ዘመዴ ያለው እውነት ይሆን ብሎ ፈጽሞ አይወዛገብም፡፡ ለእኔ ለአማራው የሚቀርበው ማን ነው ??

ለእኔ ብሎ ጫካ ውስጥ እየታገለ ያለው እውነተኛው አማራ (ታላቁ እስክንድር ) ነው ወይንስ አማራ ሳይሆን ከአማራ በላይ አማራ ነኝ በማለት ጀርመንና አሜሪካን ቁጭ ብሎ በአማራ ስም የሚነግደውን ዘመዴ፤ኤሊያስ፤ግርማ እና በዲያስፖራ የብ ዓዴን ክንፍ የሚባለው ቡድን ነው ?

ወርቅን ያየ ሁሉ ወርቅነቱን አያውቅም፡፡ ወርቅን ከብረት ወይም ከነሀስ ለይቶ የሚያውቀው ወርቅን ያወቀ ብቻ ነው፡፡

እኛ ወርቆቻችንን እና ብርቆቻችን ወርቅነት ለማወቅ መጀመሪያ እኛ ወርቅን ከብረት ለይተን የምናውቅ መሆን ይገባናል፡፡ ወርቅና ቆርቆሮ እኩል ለሚመስለው ደንቆሮ በታላቁ እስክንድር እና በሀሳበ ድኩማኖቹ ኦሮሞዎች (ዘመድኩንና መሰሎቹ) መካከል ልዩነት መኖሩን ማወቅ ባለመቻል ከእስክንድር ይልቅ ኦሮሞው ዘመድኩን ለአማራው አስቦ ነው በሚል ድንቁርናዊ አመክኒዮ አማራ ሆኖ ለዘመዴ ዘላናዊ ጩህት ልብና ጆሮውን የሚሰጥ ሆኖ እናገኛለን፡፡

ለመሆኑ ታላቁ ሰው ለምንድነው ይህንን ያህል መስዋእትነት ለአማራው እየከፈለ እራሱን በዝምታ የሸበበውን?? አማራ ነኝ የሚለውስ ለምንድነው ይህንን የታላቁን ሰው ታላቅ መስዋእትነትን ማወቅና መረዳት ያልቻለው??

ለመሆኑ የአማራን ህዝብ አንድነት ለመጠበቅ ታላቁ ሰው የፈጸማቸው ወሳኝ ተግባራት ምንድናቸው ?? ለምሳሌ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት ምስረታን በተመለከተ የታላቁ ሰው አቌም ድርሻና ሚና ምን ነበር??

ቆማጣን ቆማጣ ነህ ካላሉት ልፈትፍት ይላል፡፡
የታላቁ ሰው ዝምታ ለወፍ ዘራሾቹ የልብ ልብ በመስጠት እንደፈለጉ እንዲጨማለቁ አድርጔል፡፡ እናም ጋሻ ሚዲያ በተለየ ሁኔታ ለአማራ ህዝብ አንድነት ተብሎ በታላቁ ሰው የተፈጸመንና እየተፈጸመም ያለን ታላቅ ስራን የማቅረቡን ጉዳይ ክፍል አንድን እነሆ ዛሬ ማቅረቡን እየገለጸ በቀጣይ የዛሬውን ጥያቄ መልስን ጨምሮ እስከዛሬ ያልተገለጹ ተጋድሎዎችን በተከታታይ የምናቀርብ መሆኑን በመግለጽ የዛሬውን መጣጥፍ ስንደመድም - በጫካ እየታገለ ካለው እውነተኛው አማራ ይልቅ በጀርመንና አሜሪካ ያለው ኦሮሞ ለአማራው ያውቃል፤ ይቆረቆራል የሚል ካል እሱ/ሧ በቁም ያሉ የበከቱ ምውታን መሆናቸውን እንዲያውቁ በመግለጽ ነውና በቀጣይ እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት፤ አበቃሁ ፡፡

++++++++++++++***+++

👉 Join Us

💥 Gasha Media Discussion Forum

📌https://chat.whatsapp.com/CWRh7ScRFcs3mAhpSMwQFN

📌 https://t.me/GMMediad

የአሜሪካው ጆ ባይደን አስተዳደር አዲስ አበባ ባለው አምባሰደሩ በኩል ለአራት የኢትዮጲያ ኃይሎች ያስተላለፈው ጥሪ እና እድምታው ሲፈተሽ -‼️‼️*** ወንድወሰን ተክሉ***💥 በአዲስ አበባ የ...
05/16/2024

የአሜሪካው ጆ ባይደን አስተዳደር አዲስ አበባ ባለው አምባሰደሩ በኩል ለአራት የኢትዮጲያ ኃይሎች ያስተላለፈው ጥሪ እና እድምታው ሲፈተሽ -‼️‼️

*** ወንድወሰን ተክሉ***

💥 በአዲስ አበባ የተላለፈው የአምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ መልእክትና ጥሪ ‼️

የአሜሪካው ጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጲያ ጉዳይ ላይ የስቴት ዲፓርትመንቱን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእከተኛን አምባሳደር ማይክ ሀመርን ወደ አዲስ አበባ በመላክና ብሎም አዲስ አበባ ባለው አምባሳደሩ ኤርቪን ማሲንጋ በኩል መግለጫ በሉት ጥሪን በማስተላለፍ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ውስጣዊ የነጻነት ጦርነት ለማስቆም ያሰበ መሆኑን አመላክቷል፡፡

የአምባሳደር ማይክ ሀመር የአዲስ አበባን ጉዞ ወደ ጎን በማድረግ አምባሳደር ኤርቬን ማሲንጋ ባስተላለፈው ጥሪና መልእክት ላይ ስናተኩር ጥሪው በኢትዮጲያ ውስጥ ላሉት ወሳኝ አራት ኃይሎች የተላለፈ መልእክትና ጥሪ ሆኖ እናገኛለን፡፡

የአምባሳደሩን መግለጫ ጥሪ እና መልእክት እያልን የምንገልጽበት ምክንያት ለአራቱ ኃይሎች የተላለፈው የመግለጫ ይዘት በሁለት ተከፍሎ ለአንደኛው ጎራ - ማለትም ለአቢይ መራሹ የብልጽግና ገዢ ሀይል በመላው ኢትዮጲያ ተኩስ አቁም አዋጅ በአስቸኳይ እንዲያውጅ ጥሪ ሲያስተላልፍ ለተቀሩት ሶስት ኃይሎች ደግሞ - ለአማራ ፋኖ፤ ለትግራዩ ህወሃት እና ለኦሮሞው ኦነግ OLA ያስተላለፈው ጥሪ ሳይሆን መልእክት በመሆኑ የአምባሳደሩን መግለጫ ለአራት የኢትዮጲያ ሀይሎች የተላለፈ ጥሪና መልእክት እያልን ለመግለጽ የቻልነው፡፡

ሆኖም የአምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን አስር ደቂቃ የፈጀውን መግለጫን ይዘት በአጭር ቃል ጭምቅ አድርጎ ለማቅረብ - አምባሳደሩ በኢትዮጲያ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት ይሰፍን ዘንድ እየተካሄዱ ያሉ የህልውና ትጥቅ ትግሎችና (የአማራ ፋኖ) በኦሮሚያ ውስጥ በ OLA እየተካሄደ ያለው የስልጣን ጦርነት ቆሞ ወደ ሰላማዊ ኑሮ ለመመለስ በገዢው የብልጽግና ቡድን በኩል በመላው ኢትዮጲያ የሚጸና የተኩስ አቌም አዋጅ እንዲታወጅ እና በታጋዮች በኩል ደግሞ የሚታሉለትን ዓላማን በሰላማዊ የድርድርና የንግግር መንገድ ለመመለስ ነፍጣቸውን እንዲያዘቀዝቁ የሚጠይቅ ጥሪና መልእክት ነው ብሎ መግለጽ ይቻላል፡፡

በአጭሩ አሜሪካን ለአቢይ መራሹ የፋሺስት ቡድን ተኩስ አቁም አውጅ ስትል ለታጋይ ሀይሎች ደግሞ ተኩስ አቁሙን ተቀብላችሁ በብሄራዊ ምክክርና ንግግር ጉባኤ በኩል ሁላችሁም ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ በመምጣት ተደራደሩ የሚል ነው፡፡

አሜሪካን ይህንን መግለጫ ያወጣቺው በኢትዮጲያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ ለአሜሪካን ጥቅም የኢትዮጲያ መረጋጋትና ሰላም እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚ ከመሆኑ የተነሳ የቀረበ የመፍትሄ አቅጣጫ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
የመፍትሄው ሀሳብ ከእኛ ከአማራ ህዝብ የህልውና ትግል አንጻር በተለይም ከምንታገለው ፋሺስታዊው ስርዓት ባህርይ፤ፖሊሲና ዓላማ አንጻር ያልቀረበ የመፍትሄ አቅጣጫ መሆኑን በመረዳት እንመልከተው፡፡

💥💥💥 የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል እና በአሜሪካን አምባሳደር የቀረበው የተደራደሩ የመፍትሄ ሀሳብ

የአማራ ህዝብ ''እያደረገ ያለው ትግል የቱንም ያህል ፍትሃዊነት ያለው ትግል ቢሆንም ከትጥቅ ትግል መለስ በድርድርና በንግግር ጥያቄዎቹን ማስመለስ ይችላል በማለት አምባሰዳር ኤርቪን ማሲንጋ ተናግራል፡፡አምባሳደሩ በተመሳሳይ ሁኔታ ለኦነጉ OLA ሲናገር ታንዛኒያ ሄዳችሁ ያደረጋችሁት የሰላም ድርድር ለጊዜው ውጤት ባያመጣም ምንም ተስፋ ሳትቆርጡ ጥያቄያችሁን በሰላማዊ መንገድ በድርድር ለመመለስ መጣራችሁን ቀጥሉ በማለት የተናገረ ሲሆን የትግራዩን ህወሃት ደግሞ በጉልበትና በሀይል መሬትን ከመውረር በመታቀብ ተፈናቃዮችን መልሶ የማስፈርን ስራና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ከመተግበር አንጻር ሀላፊነታችሁን ተወጡ ሲል ነው የተናገረው፡፡

የአማባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ የመፍትሄ አቅጣጫ እና የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ሲነጻጸሩ Compatibility ያጣጠራቸው ሆነው እናያለን፡፡

ሲጀመር አምባሳደሩም ሆነ የሚወክለው የአሜሪካን መንግስት የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ከኦሮሞው ኦነግ OLA እና ከትግራዩ ህወሃት ሁኔታ ጋር በማዳበል በአንድ ቅርጫት ውስጥ ከትተው እኩል በአንድነት ችግራችሁን በድርድር ፍቱ የሚል የመፍትሄ አቅጣጫ ማቅረብ ፈጽሞ አይገባቸውም፡፡ የኦሮሞው ኦነግOLA የሚዋጋበት ምክንያት እና የአማራ ፋኖ የሚታገልበት ምክንያት የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት ያለው ነው፡፡ አንደኛው (ኦነግ) ለስልጣን የሚዋጋ ሲሆን የአማራ ፋኖ ግን የህልውና ትግል ነው እየታገለ ያለው፡፡

The absence of peace,justice,equality and dialogue is Civil War የአማራ ህዝብ የህልውና ጦርነት የሰላማዊ ትግል (ድርድር፤ንግግር፤ፍትህ) በሮች መዘጋት የተፈጠረ የህልውና ትግል ነው፡፡ ይህ የህልውና ትግል ማለት የነገደ አማራ ህዝብ በነገዳዊ ማንነቱ ላይ የተመሰረተ ዘር ተኮር ጭፍጨፋና ዘር ተኮር ምንጠራ የወለደው የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ትግል ማለት ሲሆን በዚሁ በተዘጋ ተመሳሳይ በር (ድርድር፤ንግግር) በኩል እየተካሄደ ያለውን የህልውናን ትግል አቁሙና መልስ ወደ ድርድር ግቡ በማለት ለትግል ያበቃንን ዋና ችግር መፍታት አይቻልም፡፡

የአማራ ህዝብ የህልውና ጦርነት የፈነዳው የሰላማዊ ትግል መድረክ (ንግግር፤ድርድር) ሙሉ በሙሉ መዘጋት የተነሳ የፈነዳ ትግል ሆኖ ሳለ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ የአማራ ፋኖ የሚያደርገውን ትግል አቁሞ ለንግግርና ለድርድር ይቀመጥ ብሎ ሀሳብ ማቅረቡ የህልውናውን ትግል አፈጣጠርና ባህርይን ካለማወቅና ወይም ለማወቅም ካለመፈለግ እማይሰራ የመፍትሄ ሀሳብ ነው ያቀረበው ብለን ለመግለጽ የቻልነው፡፡ የሰላማዊ ትግል መድረክ መዘጋት፤ የሰላማዊ ንግግርና ድርድር መድረክና በር ተጠርቅሞ መዘጋት የአማራን ህዝብ የህልውናን ትግል የፈጠረ ሆኖ ሳለ የአሜሪካው አምባሳደር አዲስ የመፍትሄ አቅጣጫና አዲስ የማደራደሪያ ቀመር ከማቅረብ ይልቅ በፋሺስታዊው የአቢይ መራሹ ሀይል በተዘጋው ድርድርና ንግግር ችግራችሁን ፍቱ ብሎ መግለጽ ለይስሙላ ያህል አሜሪካን ዝም ብላለች ላለመባል የተነገረ አባባል ካልሆነ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የእርሰበርስ ጦርነት ያስቆማል ተብሎ በማሰብ የተነገረ አይደለም ማለት ይቻለናል፡፡

💥💥💥 የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል የሚመራውና የሚወሰነው በአሜሪካም ሆነ በጠላታችን ፋሺስታዊው የኦህዴድ/ብዓዴን ብልጽግና ሳይሆን በአማራ ፋኖ እና በአማራ ፋኖ ብቻ በመሆኑ ፋኖ ሁለንተናዊ ትኩረቱን ለስርነቀል ድል ላይ ያተኮረ ትግሉ ላይ ብቻ መሆን አለበት

አሜሪካን አዲስ አበባ ባለው አምባሳድራ በኩል በኢትዮጲያ ውስጥ ላሉት አራቱ ሀያላን ሀይሎች - የአማራ ፋኖ፤ የትግራዩ ህወሃት፤ የኦሮሞው ኦነግና የአቢይ መራሹ ኦህዴድ/ብዓዴን ብልጽግና ቡድን - ያስተላለፈቺው ጥሪና መልእክት በኢትዮጲያና በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያለውን የአሜሪካንን ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር ኢትዮጲያ ውስጥ ፍትህ ኖረ አክኖረ፤ እኩልነት ኖረ አልኖረ፤ ዴሞክራሲ ኖረ አልኖረ ግን የእርሰበርስ ጦርነት የሌለባት እና ሰላምና መረጋጋት ያለባት ኢትዮጲያ ታስፈልገናለች በሚል ስሌትና ግምገማ ለስርዓቱ የተኩስ አቁም አዋጅ እንዲያውጅና ለታጋይ ሀይሎች ደግሞ ወደ ድርድር እንድትቀርቡ ማለቷን መረዳት ችለናል፡፡

ሆኖም ይህ የአሜሪካ ፍላጎትና ዓላማ ይሁን እንጂ ወሳኞቹ እኛው እራሳችን ፤ በተለይም የክንደ ነበልባሉ ፋኖ ትግል ወሳኝ መሆኑን ሁሉም ፋኖ ብቻ ሳይሆን መላው አማራ ማወቅ ያለበት ሀቅ ነው፡፡ ከሁለትና ሶስት ዓመት በፊት ስሙ እማይጠራውን የአማራን ጉዳይ ዛሬ ከዋይት ሀውስ እስከ ተመድ፤ ጄኔቫ፤ለንደን፤ብራሰልስና መስል መናገሻዎች ውስጥ ስሙ እንዲነሳና ብሎም ተደራደሩ የሚለውንም ሀሳብ እንኳን እንዲሰነዝሩ ያስቻለው የክንደ ነበልባሉ ፋኖ አስደናቂ ትግልና ተጋድሎ ነው እንጂ የአሜሪካንም ሆኖ የሌሎች ሀገራት ሰብዓዊነት ፈጽሞ አይደለም፡፡ ህልውናችን በክንዳችን የሚለው ዘመንና ትውልድ ተሻጋሪ መፈክርን አንግቦ የተነሳው የአማራ ህዝብ ትግል እድል እጣፈንታው የሚወሰነው በራሱ በአማራ ፋኖ ቆራጥ ትግል እና ትግል ብቻ በመሆኑ የአሜሪካን ጥሪም ሆነ መልእክት በትግሉ ላይ የሚያስከትለው እድምታ በእኛ በአማራ ህዝብ በጎ ፈቃደኝነት ላይ ብቻ የተመሰረተ ሆኖ ነው የምናየው፡፡ እኛ የሚሰጠንን ሁሉ የምንቀበል ከሆነ እኛ በምንፈልገውና በምንታገልለት መንገድ ሳይሆን ሌሎች በሚፈልጉበት ሁኔታ ትግሉ ላይ የተጽእኖ እድምታ ይኖረዋል፡እኛ ያልተቀበልነው ከሆነ ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ ቅንጣት ተጽእኖ ሳይኖረውና በትግላችን ጎዳና ላይ ለውጥ ሳይመጣ ትግሉ እስከድል ይቀጥላል፡፡

ቁም ነገሩ በአሜሪካን ፍላጎት እና አላማ ላይ ሳይሆን ያለው በእኛ አቌም፤ጽናትና ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሰረተ ሆኖ ነው የማንኛውም ውጪያዊ ሀይል ፍላጎትና ጥሪ የሚታየው፡፡

በአጭር አማርኛ ወሳኞቹ እኛው ነን፡፡ እኛው አማራዊያን ብቻ እና ብቻ ወሳኞች ነን፡፡ እኛ የተቀበልነው ሁሉ ይፈጸማል፡፡ እኛ ያልተቀበልነው ሁሉ አይደለም የአሜሪካን ጥቅሟን መሰረት ያደረገ የድርድር ጥሪ ይቅርና እኛ ካልፈለግን የሀይማኖት ህግጋቶች እንኳን ተጽእኖ ማምጣት አይቻላቸውምና በእኛው ህዝብ ላይ ያተኮረን ስራ በመስራቱ ላይ ማተኮር ይኖርብናል፡፡

እኛ ያልፈለግነው፤እኛ ያልወደድነውና እኛ ያልተቀበልነው ማን ሆነ ምን በእኛነታችን የህልውና ትግል ላይ ቅንጣት እድምታ አይኖረውም፡፡ ስለሆነም ቁም ነገሩ አሜሪካን ምን አለች ከሚለው ይበልጥ አማራው ምን አለ ? ክንደ ነበልባሉ ፋኖ ምን አለ የሚለው ነውና የአሜሪካን ጥሪ ከትግላችን የሚያናጥበን አይደለም፤ አይሆንምም፡፡

💥💥💥 የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል እና በአሜሪካን በኩል የቀረበውን የድርድር ጥሪና መልእክት በተመለከተ

የአማራ ህዝብ አንዳችም አይነት ድርድር ውስጥ መሳተፍ የለብኝም ብሎ የደመደመ ህዝብ አይደለም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አማራው አሜሪካንን ልታደራድረን አትችልም የሚልም አቌም የያዘ ህዝብ አይደለም፡፡ ሆኖም የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ፍትሃዊ መፍትሄ በማያመጣ የድርድር ድራማ ላይ ተሳትፎ እንዲከሽፍበት አንድም አማራ አይፈልግም፡፡ አንድም የአማራ ፋኖ ለተሰዋበት የህልውና ትግል መፍትሄን ለማያፈልቅ ድርድር ድራማ ላይ ተሳትፎ የህልውናውን ትግል ሲከሽፍ ለማየት የሚፍለግ የለም፡፡ ፋኖ የሆነ ሁሉ ይህንን ከማየት እራሱን ማጥፋት የሚመርጥ ነው፡፡ ይህ ማለት አማራውና የአማራ ፋኖ ' በድርድርና በሰላማዊ ንግግር ላይ ሙሉ በሙሉ በሩን በመዝጋት አልደራደርም ያለ ሳይሆን የድርድርን መሰረታዊ ደረጃና ሂደትን ባላሟላ የይስሙላ ድርድርን ነው መሳታፍን አልፈልግም ብሎ ያለው፡፡

የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል በሰላማዊ ትግል፤ ንግግርና ድርድር መድረኮች መታገድና የንግግር በሮች መዘጋት የተወለደ ትጥቅ ትግል ነው ስንል ዛሬ በአሜሪካን አምባሳደር በኩል እንደተነገረን በፋሺስቱ ስርዓት መሪ ተዋናይነትና አዘጋጅነት በሚካሄደው የምክክርና ንግግር ጉባኤ ስር ተደራደሩ የሚል ጥያቄ ሊያመጣ አይችልም ማለት ነው፡፡

የህልውናው ጦርነት በሰላም በር መዘጋት ከተወለደ በሌለ የሰላም ድርድር ችግራችሁን ፍቱ ማለት የማይሰራ የይስሙላ ሀሳብ ሆኖ ነው የምናየው፡፡

አሜሪካን ግን ይህንን ችግር እፈታለሁ የሚል ቁርጠኛ አቌምና ፍላጎት ይዛ ከተነሳች አዲስ የመፍትሄ ቀመር ይዛ መቅረብ ይኖርባታል፡፡ ይህም አዲሱ የመፍትሄ ማደራደሪያ ቀመር

📌 1ኛ - በመጀመሪያ ከአማራ ህዝብ ጋር ብቻ በሚደረግ ንግግር የመላውን አማራን ህዝብ የህልውናን ትግል ይዘት፤ መነሻና፤መድረሻና ዓላማውን ማወቅ ይኖርባታል

📌 2ኛ - አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች አጋር ሀገራትና አለም አቀፍ ተቌማት ብቻ በአደራዳሪነት የሚሳተፉበትን የአደራዳሪ ኮሚቴ መመስረትና ድርድሩንም በገለልተኛ ስፍራና ቦታ ማድረግ ማዘጋጀት ይገባታል፡፡

📌 3ኛ - የአማራ ፋኖ እና ብሎም የአማራ ህዝብ በዚህ አይነቱ የማደራደሪያ ዝግጅት መስማማቱን መግለጽ ይኖርበታል፡፡

እነዚህን ሶስት መሰረታዊ ጉዳዮችን አሟልታ አሜሪካን ለማደራደር ብትቀርበን አማራው ከአሜሪካን ጋር ለመነጋገር ይችላል፡፡ ዛሬ ግን በአምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ አዲስ አበባ ላይ የተነገረን በምንታገለው ፋሺስታዊ የአቢይ ቡድን አዛዥ ፈላጭ ቆራጭነት ስር ሂዱና ተደራደሩ የሚል ስለሆነ የመላውን አማራን ህዝብ የህልውናን ትግል ያላወቀና ያላገናዘበ ሆኖ በመገኘቱ አማራው የማይሳተፍበት ጥሪ መሆኑን ነው ለአሜሪካን የምንገልጸው፡፡ አበቃሁ፡፡

++++++++++++++***+++

👉 Join Us

💥 Gasha Media Discussion Forum

📌https://chat.whatsapp.com/CWRh7ScRFcs3mAhpSMwQFN

📌 https://t.me/GMMediad

ሰርጎ ገቦቹ የአማራን ህዝብ የህልውናን  ትግል  ለባለቤቱ አማራ ልጅ በመተው እጃቸውን ከህልውና ትግሉ ሙሉ በሙሉ ነቅለው  ማንሳት አለባቸው -‼️‼️የዘመድኩን በቀለ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም አ...
05/15/2024

ሰርጎ ገቦቹ የአማራን ህዝብ የህልውናን ትግል ለባለቤቱ አማራ ልጅ በመተው እጃቸውን ከህልውና ትግሉ ሙሉ በሙሉ ነቅለው ማንሳት አለባቸው -‼️‼️

የዘመድኩን በቀለ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም አውጃለሁ ብልጠት አይነፋም- ሶስታችሁም ወደዳችሁ ጠላችሁ ከአማራ ህዝብ ጉዳይ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ተነቅሳችሁ ትጣላላችሁ ‼️

*** ወንድወሰን ተክሉ***

💥 ያልወለድኩት ልጅ አባባ ሲለኝ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ ‼️

ከአማራ በላይ አማራ መስሎ ለአንተ ለአማራው ከራስህ ከአማራው በላይ አውቅልሀለሁ ብሎ ማጃጃልና በወዳጅ መስሎ መነገድ የተባነነበት ቀሽም ስልት ነው፡፡ አማራው እኮ በግሬደር እስከመቀበር ባደረሰ ጭፍጨፋ የተጨፈጨፈው አማራነቱን እረስቶ በኢትዮጲያዊነቱ ኢትዮጲያ ያለ ሁሉ ቢመራኝ ችግር የለውም ብሎ በመቀመጡ ነው፡፡ ትናንት ግንቦት ሰባት፤ ኢሳት፤አንዳርጋቸው ጽጌ፤ብርሃኑ ነጋ..,ወዘተ አይነቶቹ ድርጅቶች፤ ሚዲያዎችና ግለሰቦች በአማራ ህዝብ ገንዘብ፤ እውቀት፤ የሰው ሀይልና ሎጂሰቲክስ እየተጠቀሙ ግን የአማራን ህዝብ ጥያቄን ቀብረው በመሸጥ ከጨፈጨፉትና ካስጨፈጨፉት አማራው በእጅጉ ብዙ ተምራልና ዛሬ በዚህ ወሳኝ በሆነ የህልውና ትግል ወቅት ከአማራ በላይ አማራ በመምሰል ለሚደረግ የፖለቲካ ቁማር አንድም አማራ ልብና በሩን የሚከፈት የለም፡፡

የእነዚህ ሶስት ሰርጎ ገብ ግብዞች ግብግብ ከአማራ በላይ አማራ በመምሰል ከአማራው በላይ ለአማራ የምናስብ ነን በማለት አማራውን የሚመራህን የምናውቅልህና የምንመርጥልህ እኛ ነን በማለት አይን ያወጣ ግግምና ምክንያት አይደለም እንዴ በለስላሳው እባብ ኤሊያስ ክፍሌ ዋና አዛዥነትና አስተባባሪነት ዘመቻና ክስ እስከመክፈት የደረሱት ??

እስቲ ምን ትላላችሁ በግድ በአማራ ጉዳይ ገብቼ ካላቦካሁ ብሎ ፍርድ ቤት ድረስ ሄዶ ሰውን እስከመክሰስ ደረጃ መድረስ ምን የሚሉት ነው ???

የሆነው ሆኖ በአማራ ጉዳይ ላይ ሰርገው የገቡት ሶስቱ ሰርጎ ገቦች፦

💥 1ኛ - ኤሊያስ ክፍሌ፦

በአማራ ጉዳይ ካልፈተፈትኩ ሞቼ እገኛለሁ ብሏል፡፡ ከመረጃ ቲቪ ውጪ ከማይ ሞቴን እመርጣለሁ ብሏል፡፡ ምንሊክ ሳተላይት ከምሰማ ገድላችሁ ቅበሩኝ ባይ ሆናል፡፡ በፋኖ ዘንድ እየደወልኩ ትእዛዝ ካልሰጠሁ ደም ይነስረኛል ባይ ሆናል፡፡

ስለሆነም ደም እያነሰሩኝ በማንደፋደፍ ላይ ባሉት ምስጢሬንና ሴራዬን በሚያጋልጡት ላይ እስቲ ክስ ከፍቼ ላስፈራራና 'ላስቁማቸው ብሎ ክስ ከፍቶብናል፡፡ የሰርጎ ገቦቹ አለቃ ኤሊያስ ክፍሌ ሰርጎ ገብነቱን ለመከላከል ክስ መከላከያዬ ነው ብሎ እኔን ጨምሮ ወደ አስር በሚጠጉ ላይ ክስ ከፍቷል፡፡ እስቲ የአሜሪካን ፖሊስና ፍርድ ቤት ያስጥሉት እንደሆነ እናያለን፡፡ በእኛ በኩል ይህንን ሰርጎ ገብ ከአማራ ጉዳይ ላይ እጁን እስክንቆርጥ ድረስ እንተገትገዋለን፡፡

ሰላምና ነጻነቱን የሚፈልግ ሰው ቢሆን ኖሮ ወደ አሜሪካን ፍርድ ቤት ተንደርድሮ ሄዶ እባካችሁ አስቁሙልኝ ተማጽኖ በእኛ ላይ ክስ 'ከመክፈት እጅግ ቀላሉ ነገር እጁን ከአማራ ጉዳይ አንስቶ ያሰማራቸውን ውሾቹን ሰብስቦ የከፈተውን ዘመቻ አቁሞ ጤናማ የሆነ የግል ህይወቱን ቢኖር ማንም ስሙን አያነሳውም፡፡ እሱ ሰላማዊ ሆኖ ስሙን የሚያንሳ ቢኖር እንኳን የምንከላከልለት እንሆን ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ ነበር ነው፡፡ የለስላሳው እባብ ኤሊያስ ክፍሌ ምርጫ ግን በ The so called of Charge በእከሳችሃለሁ፤ በከስሻችኃለሁ ስም እኛን Intimidate በማድረግ ለማስቆም ምርጫው በማድረግ ከሶናል፡፡ እናም በመረጠው በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ላይ ጥልቅ ካላልኩ ደሜ መፍሰሱን አቁሞ እሞታለሁ በማለት እስከፍርድ ቤት ድረስ መጋዝ ምርጫው እኛም በእኩል አጸፌታ ሰርጎ የገባውን እጅ እስክንቆርጥ ድረስ በማጋለጡ ሚስማር ነጋ ጠባ እንጠዘጥዘዋለን፡፡

💥 2ኛ - የተኩስ አቁም አውጃለሁ ያለው ዘመድኩን በቀለ

በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ውስጥ ጥልቅ ብሎ ከአማራም በላይ አማራ ነኝ ብሎ አለቃውን ለማስደሰትና ለተከፈለው መጠነስፊ የብልጽግና ፔንጤዎች ገንዘብ ብሎ ከታህሳስ ወር 2023 ጀምሮ በአማራ ታጋዮች ላይ በውስጥ ለውስጥና በገሀድ አደባባይ ከፍተኛ የሆነ ልቅና ክብረ ነክ የስድብ ዘመቻ የከፈተብን ዘመድኩን ነቀለ በዛሬ መል እክቱ ጊዜያዊ የተኩስ ማቆም እንዳውጅ በወዳጆቼ ተገድጃለሁ ብሎ ገልጿል፡፡

«...ሰሞኑን በጀመርኩት የአየር ላይ ውጊያ እየደረሰ ያለውን ጥፋት እና ውድመት በመመልከት እነዚህ የምታዩአቸው ሰማያዊ ሥልጣን፣ የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ በእጃቸው የተሰጣቸው መንፈሳውያን አባቶቼና ወንድሞቼ በጨዋ ደንብ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበውልኝ እኔም ከእናንተ ከአባቶቼማ ቃል አልወጣም በማለት ጊዜአዊ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ፈርሜአለሁ።

እኔ ዘመዴን ገዝተው የተኩስ አቁም እንድፈርም ያስገደዱኝ አባቶቼ ክቡር ቆሞስ አባ ጽጌ ሥላሴ የባልቲሞር ቅድስት ሥላሴ አስተዳዳሪ፣ ቀሲስ ነዋይ ካሳሁን፣ ቀሲስ ሱራፌል ወንድሙ፣ ቀሲስ ሳሙኤል ግዛው ናቸው።

"…ዐወቅኩሽ ናኩሽ አይሠራም። ወዳጆቼ፣ ጓደኞቼ፣ ወንድሞቼ ቢሆኑም በተሰጣቸው ሰማያዊ ሥልጣን ይበልጡኛል። ሳሚ፣ ሱሬ እያልኩ በአደባባይ ብጠራቸውም ነገር ግን አባቶቼ ናቸው እናም ወደ ግዝት ሳይገቡ ከሰፊ ውይይት በኋላ ያዘዙኝን ጊዜአዊ የተኩስ አቁም ስምምነት አክብሬ ተቀብያለሁ። በስምምነታችን መሠረትም የተኩስ አቁም ትእዛዙን አከብራለሁ። ከቃላችሁማ አልወጣም ....» በማለት አስፍራል፡፡

ዘመድኩንን አሁን ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ ያበቃው ሁለት ወሳኝ ክፍል አለ፡፡ የጽኑ ኦርቶዶክሳዊያን ስለሀይማኖታቸው ብለው የሰጡት ፍቅር፤ ድጋፍ እና በመላው የአማራ ህዝብ በተቸረው ገደብና ድንበር የለሽ የገዘብ፤የሎጀስቲክስ ድጋፍና እውቅና ዘመድኩን እስከመንቀል ደረጃ ያደረሰውን እውቅናን ሊያገኝ የቻለ ሰው ነበር፡፡ የሰውዬው ድንበርና ገደብ የለሽነት ስብእና እያደገና እየገዘፈ መጥቶ ከሀይማኖት ጉዳዮች ውስጥ ወጥቶ ጋዜጠኛ ሳይሆን ጋዜጠኛ፤ፖለቲከኛ ሳይሆን ፖለቲከኛ፤ፋኖ ሳይሆን ከሁሉም የበለጠ ፋኖ፤ አማራ ሳይሆን ከአማራም በላይ አማራ ነኝ ባይ ሆኖ ሁሉንም አውቃለሁ ባይ በመሆን የእብደት ስብእናን መገለጫው በማድረግ የተሳዳቢ፤ዘላፊ፤በፈጠራ ስም አጠልሺ ስራን የሚሰራ ሰው የሆነ ነው፡፡

የዘመድኩን ነቀለን ገሀዳዊ ጨርቁን ያልጣለ እብድነት ለማወቅ አንድ ፍንጭ ብቻ መጠቆም ይበቃል፡፡ በዘንድሮ የሁዳዴ ጾም የመጨረሻ ህማማት ሳምንት የፖሰታቸውንና በቲክቶክና በመረጃ ያሰራጫቸውን መልእክቶችን ይዘት በማየት የሰውዬውን እብደት ማወቅ ይቻላል፡፡ የኦርቶዶክስ መምህር የሚባለው ዘመድኩን ነቀለ በስድስቱ የህማማት ቀናት ውስጥ ያስተጋባው ልቅ ስድብ፤ ተራና መሰረተ ቢስ የፍረጃ ዘለፋን ነበር ሲያስተጋባ የታየው፡፡ አንድ ሰው ካላበደ በስተቀር ሀይማኖተኛ ሆኖ፤ ያውም መምህር በሉኝ የሚል ሰው ሆኖ በምንም ዓይነት ተአምር የጌታን ህማማት ሳምንትን በስድብ ሲያፈርስ አይታይም፡፡ የሆነው ግን ይህ ነው፡፡

በአማራና በኦርቶዶክሳዊያን ሁለንተናዊ ድጋፍ እውቅና አግኝቶ እና በሁሉንም አውቄያለሁ መታበይ እራሱን ሁሉንም አዋቂ አድርጎ ያጎረሰውን እጅ፤ እና ለዚህ እውቅና ያበቃውን አማራን እና ትግሉን እኔ ያልኩት ካልሆነ በሚል ያጎረሱትን እጆች መልሶ እየቀረጣጠፈ የሚበላ ሰርጎ ገብ አውሬ ሆነ፡፡

ዛሬ በወዳጆቼ አስገዳጅነት ለጊዜው የሀብታሙን፤የ360 ሚዲያን እና የታላቁን እስክንድር ስም ላላነሳና በአማራም ጉዳይ እጄን ላላስገባ ጊዜያዊ የተኩስ ማቆም አውጃለሁ ብላል፡፡ በእኛ በኩል መጀመሪያውኑ በማያገባህ የገባህ፤ መገኘት በማይገባህ ስፍራ የተገኘህ ነበርክና ከአማራ ጉዳይ ላይ በጊዜያዊነት ሳይሆን ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ እጄን አውጥቻለሁ እስክትልና እስክናረጋግጥ እጁን ከአማራ ጉዳይ አንስቷል ብለን ቅንጣት የምንቀበለው ጉዳይ አይሆንም፡፡

በእኛ በአማራዊያን በኩል ከዚህ ከሰርጎ ገብ ዘመድኩን ነቀለ ገጽና ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ የመገለልን ስራ በመስራት እርቃኑን የማስቀረትን ስራ በመስራቱ ላይ ማተኮር ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ ዘመድኩን ነቀለ የእብደት ጸረ አማራ ዘመቻውን ከከፈተ ግዜ ጅምሮ በአስርሺህ የሚቆጠሩ አማራዊያን ከቴሌግራም ቻናሉ እየለቀቁ ወጥተዋል፡፡ ይህንም በተጨባጭ አረጋግጠናል፡፡ ከ410ሺህ በላይ የነበረው ቴሌግራሙ ዛሬ ወደ 399ሺ አሽቆልቁላል፡፡ የሚወጣ እንጂ የሚገባ የለም፡፡

ይህ ግን በቁ አይደለም፡፡ አማራ የሆነ በሙሉ ከዘመድኩን ነቀለ ቤት ውልቅ ብሎ መውጣት አለበት፡፡ ገጾቹም Unlike Unfollow Unsubscribe , Report Block በማድረግ መቅጣት ይገባል፡፡

💥 3ኛ - የዘገምተኛው ግርማ ካሳ መገገም

የሶስተኛው ሰው ገገማነት በጣም ያስቃል፡፡ የብሄር ተኮር አደረጃጀትን በመቃወምና በማውገዝ እድሜውን የገፋው ግርማ ካሳ አይኑን በጨው አጥቦ ከአማራ በላይ አማራ፤ ከፋኖም በላይ ፋኖ ለመምሰል የሚያደርገው ተከታታይ መጋጋጥ የሰውዬውን እልም ያለ ገገማነትን ያሳያል፡፡

ትንሽ እንኳን ሀፍረት ያልፈጠረበት ግርማ ከአማራ በላይ አማራ ነኝ በሚል መሀይማዊ ድርቅና እና ጥቅማዊ ግግምና ዛሬ እከሌ እከሌ እራሱን ከፋኖ ሰራዊት መለየት አለበት እያለ ሲለቀልቅ ይታያል፡፡ ይህ ህሊናቢስነት ብቻ ሳይሆን ተራና ግላዊ ጥቅመኝነት መታወርንም የሚያሳይ ነው፡፡

የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል የማንም losers መጨማለቂያ ባጣ ቆየኝ አይደለም፡፡ እነዚህ ሶስቱ ሰርጎ ገቦች በአማራ ትግል ውስጥ ድምጻችንን እናሰማ የሚልና ከሃላው ድብቅ አጀንዳ ያላነገበ ቅዱሳዊ ዓላማና አቌም ቢኖራቸው የራሳቸውን ልጔም በመጠቀም ገደብ ሳያልፉ የድጋፍ ድምጽ መስጠት ይችሉ ነበር፡፡ ድንበር ሳይጥሱ ማለት በአማራ ውስጣዊ አደረጃጀትና አመራርን ጉዳይ ለአማራና አማራዊያን ብቻ በመተው ድምጽ መሆን ማለት ነው፡፡

የአማራ ህዝብ ውስጣዊ አደረጃጀትና ይህንንም አደረጃጀትን ከማደራጀት እስከ ታግሎ በማታገል መምራት ያለበት በአማራ እና በአማራ ልጆች ብቻ እና ብቻ ነው፡፡ይህንን ሀቅና እውነታ ተቀብለው ሶስቱም እጃቸውን ካወጡ እስከመፈጠራቸው በመርሳት ስማቸውን ባለማንሳት አንደመድማለን፡፡

በእኛ በኩል መገኘት በማይገባን ስፍራና Cause የተገኘን አይደለንምና የምናቆመው ነገር አይኖርም፡፡ የመጡብን ይመለሱና ያቁሙ እንጂ በእኛ በኩል የምናቆመውም ሆነ የምንተወው ምንም የለም፡፡አበቃሁ፡፡

********++++++++********++++++*******+++

👉 Join Us

💥 Gasha Media Discussion Forum

📌https://chat.whatsapp.com/CWRh7ScRFcs3mAhpSMwQFN

📌 https://t.me/GMMediad

02/25/2024
የፈሪዎችና በቁማቸው የሞቱትን የፍርሃት መደበቂያን ነፍስ ይማርን ቃል በግፍ እየተጨፈጨፉ ላሉ ወገኖቼ እልቂት በመጠቀም ነፍስ ይማር  እያልኩ ፈጽሞ አላልፍም ‼️‼️ነፍስ ይማር አልልም ‼️ ነ...
02/20/2024

የፈሪዎችና በቁማቸው የሞቱትን የፍርሃት መደበቂያን ነፍስ ይማርን ቃል በግፍ እየተጨፈጨፉ ላሉ ወገኖቼ እልቂት በመጠቀም ነፍስ ይማር እያልኩ ፈጽሞ አላልፍም ‼️‼️

ነፍስ ይማር አልልም ‼️ ነፍስ ይማር አልልም ‼️ ነፍስ ይማር አልልም ‼️‼️‼️

የእያንዳንዱን አማራን ደም ለመበቀል ቃል ኪዳን እገባለሁ
ዳግማዊ ማይካድራ በሰላድንጋይ ፋሲክ ከተማ ‼️

*** ወንድወሰን ተክሉ***

💥 የ 60 አማራዊያን ህይወት በሰባት ዙር ድሮን ድብደባ አካላቸው ሙሉ በሙሉ ነዶ እስኪከስል ተቃጥሎ አልቀዋል -‼️‼️‼️
ድርጊቱ አማራ ነኝ የሚልን በሙሉ ባለበት የዓለም ዳርቻ ሆኖ በሰውነቱ ላይ እንደተለኮስ የእሳት ቃጠሎ ያህል ሊያናድደው በቁጭት እሳት ሊያቃጥለው ይገባል ‼️‼️‼️

ጭፍጨፋው ቅንጣት አያሳዝንም ‼️‼️‼️
በንዴት እሳት ግን ያቃጥላል ያንገበግባል ‼️‼️‼️

በሰላ ድንጋይ ፋሲክ ከተማ ዳግማዊ መራዊ ጭፍጨፋ በፋሺስቱ ኦሮሙማ ተፈጽሟል፡፤ በመቶ የሚቆጠሩ አማራዊያን ተጨፍጭፈው አልቀዋል፡፡ የጭፍጨፋው ይዘት በመራዊ በተፈጸመበት አይነት ተመሳሳይ ሁኔታና ስልት አውሬው በፋሲክ ከተማ ቤት ለቤት እየዞረ ባገኘው ሁሉ ላይ ጥይት በማርከፍከፍ የርሸና ተግባር በመፈጸም ነው የጨፈጨፈው፡፡

የፋሲክ ከተማ መንገዶች በአማራዊያን አስከሬን ተሞልቷል፡፡ ቤት ለቤት እየገባ ከሚረሽነው መቺ ሀይል ለማምለጥ የሚሮጠውን በከተማዋ አውራ መንገድ ላይ ያለው ገዳይ ክፍል እየተቀባበለ በጥይት ደብድቦ ይረሽነዋል፡፡

በዚህ ጭፍጭፍ አብዛኛው ተጨፍጫፊ ሰለባዎች ታዳጊ ህጻናት፤ ሴቶችና በእድሜ የገፉ ሲሆን ሮጠው ማምለጥ ያልቻሉም ወጣቶችም ይገኙበታል፡፡ በእድሜ የገፉት፤ ታዳጊ ህጻናትና ሴቶች የሌሎቹን ያህል ሮጠው ማምለጥ ባለመቻል እና እንዲሁም እኛ ከምኑም የሌለንበት አቅመ ደካሞች ስለሆንን አይፈልጉንም በሚልም ስሜት ወራሪው ወደ ከተማዋ ሲገባ ጠላት ገባ እየተባባሉ የቻሉትን ያህል ሮጠው ለመደበቅ ያልፈለጉም ሊሆኑ ይቻላል፡፡

የጠላትን ማንነት ያለማወቅ በሽታ፡፡፡
የጠላትን አረመኔነት ዛሬ ጦርነት ላይ ባለንበት ሁኔታ ላይ ሆነን እንኳን ለይቶ ያለማወቅ በሽታ ሲፈጀን እና ሲያስፈጀን እያየን ነው፡፡ እጅግ ያበግናል፡፡ እጅግም ያቃጥላል፡፡

በመራዊ በመቶ የሚቆጠሩ አማራዊያን በዚህ አይነት ተመሳሳይ የጭፍጨፋ ስልት ከተጨፈጨፉ አስራ አምስት ቀን ቢሞላቸው ነው፡፡ የመራዊን ጭፍጨፋን ተከትሎ ጋሻ ሚዲያ «የመራዊ ቃል ኪዳን ህግ» በሚል መሪ ቃል ዳግማዊ መራዊን በሸዋ፤ በጎንደር፤በወሎና ብሎም በጎጃም እንዳይፈጸም ለመከላከል በመላው አማራ ተፈጻሚና ገቢራዊ የሚሆን የጦርነት ህግ በአስቸኳይ ይውጣ በማለት አስቀምጣ ነበር፡፡ የመራዊ ቃል ኪዳን ህግ ከአንድ መራዊ ጭፍጨፋ የተቀዳ ጽንሰ ሀሳብ ሳይሆን ጭፍጨፋውን የጦርነቱ ማሸነፊያ ስልትና ስትራቴጂ አድርጎ በማጽደቅ ለሚያሰማራው ገዳይ ሰራዊት ከሚሰጠው ትእዛዝ የተቀዳ ነው፡፡

የስርጭት ሽፋኗ እጅግ ውሱን በሆነቺው ጋሻ ሚዲያ የፋሺስቱን ቁንጮ አቢይ አህመድን 10 ሰው መግደል 100 ሰው ዝም ያሰኛል 100 ሰው መግደል 1000 ሰው ዝም ያስብላል በሚለው ስሌት መሰረት በመላው አማራ ህዝብ እየተካሄደ ያለውን የህልውናን ጦርነት ለማስቆም ፋሺስቱ በመቶሺህ የሚቆጠርን አማራ በአሰቃቂ ሁኔታ በመጨፍጨፍ ሚሊዮኖችን ዝም ማስባል እችላለሁ ብሎ የነደፈውን እቅድ መሰረት በማድረግ ዳግማዊ መራዊ ይፈጸማል - ይህ እንዳይሆን ፋኖ መላው የአማራን ህዝብ የሚገዛበትን የጦርነት መተዳደሪያ ህግ - የመራዊ ቃል ኪዳን ብሎ እንዲያወጣ አደራ አደራ አደራ በሚል ውትወታ ያስተጋባነው ዛሬ በሸዋ ሰላ ድንጋይ ፋሲክ ከተማ የተፈጸመው እንደሚፈጸም እርግጠኛ ሆነን በማወቅ ነው፡፡ ቀጣዩ መራዊ ፋሲክ ትሁን ደብረማርቆስ ጎንደር ትሁን ወልዲያ ስፍራውን ለይተን አልጠራንም እንጂ በመላው የአማራ ህዝብ ላይ ዳግማዊ መራዊ እንደሚፈጸም የስር ዓቱን ፖሊሲና ውሳኔን ጠቅሰን ዘግበናል፡፡

በፋሲክ የተካሄደው ጭፍጨፋ በምድርና በሰማይ ሲሆን በሰማይ ድሮን በተከፈተ ጥቃት ቁጥራቸው ተለይቶ የታወቁ ስድሳ አማራዊያን ከእነሚጔዙበት አይሱዚ ተቀጥቅጠው ተቃጥለው አልቀዋል፡፡

ስድሳዎቹ አማራዊያን ከክርስትና የሚመለሱ ሴትና ህጻናት የሚበዙበት ሲሆን ድሮኑ እነዚህን ወገኖቻችንን ሙሉ በሙሉ ደምሥሶ ለማጥፋት ሰባት ዙር እየተመላለሰ ጥይትና ቦንብ አያርከፈከፈ እንደፈጃቸው ነው የታወቀው፡፡ የስድሳውም አስከሬን መለየት በማያስችል ሁኔታ ተቃጥሎ ከስሟል፡፡

ይህ በምድርና በሰማይ በተቀናጀ ሁኔታ በተደረገው ጭፍጨፋ እጅግ አሰቃቂና እጅግ በንዴት በቁጭትና በእልህ መላውን አማራ የሚያነድ ጭካኔ ነው የሚያሳዝን ጭፍጨፋ አይደለም፡፡

💥 የአማራው ጠላት ኦሮሙማ በአማራ ላይ የሚፈጽመው አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በሙሉ ያናድዳሉ፤ ያበግናል በንዴትና በእልህ አንጨርጭረው ለበቀል ያስነሳሉ እንጂ ፈጽሞ የሚያሳዝኑ አይባልም ‼️‼️‼️

አማራ የሆንክ በሙሉ ስማ፤ በተለይ አማራ ሆነህ፤ፋኖ ሆነህ፤አንቂ ጋዜጠኛ ሆነህ በጠላታችን የሚፈጸምብንን አረመኔያዊን ጭፍጨፋን እጅግ በሚያሳዝን መልኩ ብዙ ሰው ተጨፈጨፈ እያልክ የምትገልጽና ለተጨፈጨፉት ደግሞ ነፍስ ይማር እያልክ የምትለጥፍ አማራ እባክህ አንድ ግዜ ብቻ ስማኝ፡፡

📌 1ኛ - ጠላታችን የለውም እንጆ ኒውክሌር ቦምብ ቢኖረው በደስታ እየፈነጠዘ የሚጠቀም መሆኑን እወቅ፡፡

📌 2ኛ- አንተን መጥፋት አለብህ ብሎ የተነሳብህን ጠላት እርምጃና ጭፍጨፋን እጅግ በሚያሳዝን ተብሎ አይገለጽም፡፡

👉 እጅግ በጣም የሚያሳዝን ቃል ሁለት እድምታ እወቅ ‼️

📌 1ኛ - የጨፈጨፈን ሊራራልን የሚገባ ሊጨርሰን የማይፈልግ ጸበኛ የሆነ ሰው የፈጸመብን ነው የሚል ትርጉምን Unconsciously በህዝባችን ልብና አ እምሮ ውስጥ ይፈጥራል፡፡ይህ ዓይነቱ ውስጣዊ ስሜት መፈጠር ደግሞ ወገን ጠላትን በጠላትነት ልክ እንዳያየው፤ እንዳይታገለውና እንዳይጠነቀቀው በማድረግ ትልቅ አፍራሽ ሚናን ይጫወታል፡፡

በተጨማሪም እጅግ በጣም በሚያሳዝን መልኩ የሚለው ቃል ጨፍጫፊውን ወዳጅ አድርጎ የሚገነባም ቃል ነው፡፡ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ተፈጸመ የሚባለው ወዳጅ በወዳጁ ላይ ክህደት ሲፈጽም ብቻ ነው፡፡ ወይም ጥቃት ከማይገመትበት ወዳጅ ሀይል ድንገት ሲፈጸም ያሳዝናል ይባላል፡፡ አንተን መጥፋት አለብህ ብሎ ለተነሳ ሀይል የቱንም ያህል አረመኔነት የተሞላበት ሁኔታ ጭፍጨፋን ሲፈጽም ያሳዝናል አይሆንም፤ አይባልም፡፡ ጠላት ሲያጠቃህ አጸፋ ለመመለስ ትናደዳለህ እንጂ ያስዝናል አትልም፡፡

📌 2ኛ- እጅግ ያሳዝናል ቃል ሁለተኛ ትርጉሙ እድምታ ተጨፍጫፊው ለበቀል እንዳይነሳ በማድረግ ያስተኛዋል፡፡ ለበቀል የሚነሳ ሰው ያሳዝናል እያለ የሚያዝነው ሳይሆን እንዴት ተደፈርኩ እንዴት ተደፈርን ብሎ በንዴት እርር ድብን ብሎ የሚጨሰው ሰው ሳይበቀል እረፍት የለውም፡፡ ስለዚህ በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ ያለን የጠላት ጭፍጨፋን እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ሴቶችን ህጻናትን ጨፈጨፈ እያሉ በመዘግብና በማስተጋባት በቁጭት፡በንዴትና በእልህ ተነሳስቶ ለበቀል በራሱ ግዜ ሊነሳ የሚችልን ሰው እንዳይነሳ በማድረግ Unconsciously የማስተኛት ስራን እየሰራችሁ ነውና እባካችሁ የሚፈጸምብንን ጭፍጨፋ አገላለጽና አዘጋገብ ላይ የጥንቃቄ ስራ ይሰራ፡፡

💥💥 እኔ በጠላት እጅ ለተገደለም ሆነ ለተጨፈጨፈ ወገኔ የስላቅ ነፍስ ይማር አልልም
በአንጻሩም በእያንዳንዱ በግፍ የተገደለን አማራን ደም ለመበቀል ቃል ኪዳን እገባለሁ ‼️‼️‼️‼️

የመራዊ ጭፍጨፋ፤ ዛሬ የፋሲክ ጭፍጨፋን እና ወዘተ ጭፍጨፋዎችን ሁሉ በተለኮሰ ሻማ ስር ወይ ከላይ ነፍስ ይማር የምትል ስላቅ ለጥፎ ጭፍጨፋዎችን በዝምታ ማለፍ የዚህ ትውልድ የተለከፈበት ቫይረስ ያህል ሆናል፡፡

እስቲ መጀመሪያ የነፍስ ይማርን ቃል ትርጉም ለይተን እንወቅ፡፡

ነፍስ ይማር መንፈሳዊ ቃል ነው ማለት ይቻላል፡፡ የቃሉ ትርጉም ተፈጻሚ የሚሆነው እዚህ በምድር በህይወት ላለ ሰው ሳይሆን ህይወቱ ላለፈ ሰው እላይ ሰማይ ቤት ፈጣሪ ከገሀነብ ይልቅ በምህረቱ ገነት ያስገባው ዘንድ የሚሰጥ የልመና ቃል ነው፡፡

በሶስቱም ቀደምት ሀይማኖቶች ማለትም ክርስትና ጁደይዝምና እስልምና እምነት አስተምህሮቶች መሰረት ነፍስ ይማር የሚባለው በተፈጥሮ ለሚሞት ብቻ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ አስቀምጧል፡፡ በህመም፤በአደጋ፤በእድሜ ለሚሞት ነፍስ ይማር ይባላል፡፡ በሰው እጅ ለሚሞት፤ እድሜው ለአቅመ ተጠያቂነት (ከ 13-17)ያልደረሰና ብሎም ለሀገሩ፤ ለወገኑ፤ ለቤተሰቡ፤ ለቤት ንብረቱ፤ ለሀይማኖቱ ሲታገል ለሚሞት ነፍስ ይማር አይባልም፡፡ እነዚህ ነፍሳት አውቶማቲክ ገነትን ወራሽ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የዛሬው አይነት የፋሲክና የመራዊ ዓይነት ጭፍጨፋ ሰለባዎች ነፍስ ይማር አይባሉም፡፡ እውነት ለመናገር በእንደዚህ አይነት ሁኔታ የሚሞት ነፍሲያው የጸደቀች እድለኛ ተብሎ ነው በመንፈሳዊ አስተምህሮት ውስጥ በመንፈሳዊ ቅናት የሚታየው፡፡ ብዙዎች በመንፈሳዊ ትምህርት ገፍተውና ምድራዊውን ዓለም ንቀው ወደ ላይ ለመሄድ የሚቸኩሉ ሆን ብለው ወታደር ይሆናሉ፤ አሊያም የተቀደሰ አጥፍቶ መጥፋትም ሲፈጽሙ ይታያሉ፡፡ ስለዚህ በጠላት ለሚጨፈጨፍ ወገናችን እኛ ደማቸውን ለመበቀል ሀላፊነትና ግዴታ ቢኖርብንም ከነፍስ አኳያ ግን ነፍስ ይማር የማይባሉ አውቶማቲክ ጻድቆች ናቸውና ይህንን ትርጉም ካለማወቅ ለሁሉም አይነት አሟሟት ነፍስ ይማር እያሉ በመግለጽ በሟቹ ላይ ተጨማሪ ግድያ ሲፈጽሙ ይታያሉ፡፡

በሰው እጅ ለተገደለ ሰው ነፍስ ይማር ማለት ሁለተኛ ግድያ ነው፡፡ በሰው እጅ የሚገደሉ ነፍሳት በሙሉ ማለት በሚያስችል መልኩ ነፍሲያቸው ወዱያው አታርግም፡፡ መላእክቶችም እነዚህን ነፍሳት ያለመውሰድ ት እዛዝ የተሰጣቸው ስለሆነ አንድ በሰው እጅ ተጨፍጭፎ የተፈደለ ነፍስ በዚሁ ምድር ሆኖ የገዳዩን ለፍርድ መቅረብ ይጠብቃል፡፡ ገዳዩ ለፍርድ ከቀረበ በነጻነት ወደሰማይ ያርጋል፤ ገዳዩ ደግሞ ለፍርድ ካልቀረበ ገዳዩ እስኪሞት ድረስ ያ ነፍስ ምድር ሆኖ ይጠባበቃል፡፡

ይህንን የገለጽኩበት ምክንያት በጠላት እጅ ለተጨፈጨፈና ለተገደለ ሰው ነፍስ ይማር ብሎ መናገር ሁለተኛ ግድያ የሆነበት ምክንያት አንድ ሰው ነፍስ ይማር ብሎ ሲገልጽ ሀዘኑን ገልጾ መገላገሉን ነው የሚያውጀው፡፡ በአንጻሩም እኔ ደሙን ሳልበቀል አልቀመጥም የሚል ሰው ነፍስ ይማር አይልም፡፡ ገዳዩን ማሳደድ ነው የሚጀምረው፤፡ ገዳዩን አሳዶ ሲገድል ደምህን ተበቅያለሁ አሁን ነፍስህም ታርፋለች ብሎ ይገልጻል፡፡በሰው እጅ የተገደለውም ነፍስ ያኔ ታርጋለች፡፡

በእኛ ጉዳይ ስንመጣ ደማቸው ያልተመለሱ ሚሊኖን አማሮች ነፍስ ዛሬም ምድር ላይ ፍትህ ጥበቃ ላይ ሆነው ያሉበት ሁኔታ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ ያለን ጭፍጨፋን ነፍስ ይማር ብሎ ማስተጋባት ለበቀል እንዳይነሳ ማድረግ ነው፡፡ይህንን ስናደርግ በተጨፈጨፉት ላይ ነፍሳቸው እዚሁ ምድር እንዲታሰር መፍረድ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም ይህንን ቃል ፈጽሞ አንጠቀም፡፡ማለትም በግፍ ለተጨፈጨፉ ነፍስ ይማር ፈጽሞ አንበል፡፡ በምትኩ ደማቸውን ለመመለስ ቃል ኪዳን እየገባን ለተጨፈጨፉት ፍትህ ፍለጋ እንታገል፡'አበቃሁ፡፡

,🟩🟨🟥🟩🟨🟥🟩🟨🟥

ጋሻ ሚዲያ ‼️‼️‼️‼️

ለበለጠ መረጃና ብሎም ለተሳትፎ የጋሻ ሚዲያን ዓለም አቀፍ የመወያያ ቴሌግራም ቻናልን በመቀላቀል መረጃዎችን በማቀብልና በመቀበል ሂደት ላይ የበኩላችሁን ድርሻ በማበርከት ይሳተፉ 👇👇👇

https://t.me/GMMediad

"ታላቁ እስክንድር በቃሉ የሚፀና ለእውነት ሲል መስዋእትነት ለመክፈል የተዘጋጀ የፅናት ምሳሌ ነው ‼️..እስክንድር የእዲሱ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ስራዊት የበላይ ዘመነ ካሴ እንዲሆን ነበር የፈ...
02/18/2024

"ታላቁ እስክንድር በቃሉ የሚፀና ለእውነት ሲል መስዋእትነት ለመክፈል የተዘጋጀ የፅናት ምሳሌ ነው ‼️
..እስክንድር የእዲሱ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ስራዊት የበላይ ዘመነ ካሴ እንዲሆን ነበር የፈለገው::ዘመነ ካሴ "አልፈልግም እስክንድር መሆን አለበት" በመባባል ላይ ብቻ ነው አለመግባባት የነበረው...». ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

****** ++++++++******

🔥 ታላቁ እስክንድር በቃሉ የሚፀና ለእውነት ሲል መስዋእትነት ለመክፈል የተዘጋጀ የፅናት ምሳሌ ነው:‼️‼️

ከጥቂት ወራት በፊት የፋኖን ትግል በእንድነት ለማቀነባበርና ለማስተባበር በእርበኛ ዘመነ ካሴና በእስክንድር ምሀከል ታላቅ ስምምነት ተደርጎ ነበር:: ይህንንም ታሪካዊ ስምምነት ዋሽንግትን ዲሲ በታላቅ ስብስባ ለይ ለህዝብ እንዲገለፅ ተደርጎ ነበር:: ከዚህች እለት ሁለት ሳምንት በፊት ጀምሮ የዝባዊ ሀይል እና ህዝባዊ ግንባር ተብለው የተስየሙት ድርጅትች ስማቸው እንዲከስምና በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ስራዊት እንዲተካ ስለ ተነገረን ክዚያን ጊዜ ዥምሮ የግንባሩን ስም ከመጠቀም ተቆጥበን ነበር:: ስለሆነም እዲሱ ድርጅት የስራ እስፈፃሚ ኮሚቴ ለማቆቆም አመራሮቻችን ውይይት ላይ ስለሆኑ የህዝባዊ የእማራን ፋኖ ህዝባዊ ስራዊት ስም በይፋ እንዳንጠቀም (የአማራ ህዝባዊ ግንባር ) ስለ ተነገረን የቀድሞውንም የዚህንም ስም ሳንጠቀም ከሁለት ወር በላይ ቆይተናል::

ምንም እንኮን ህዝባዊ ሀይል እንደገና ከስምምነቱ ውጭ በዚህ ስም መጠቀም ቢዥምርም እስክንድር ከዘመነ በቀጥታ እስከምስማ ድረስ በየትኛውም ስም እንዳንጠቀም ነግሮናል:: "ቃል ስለገባሁ ከእሱ ከእራሱ እስካልሰማሁ ድረስ ስምምነቴን ቃሌን አላፈርስም " ብሎ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ቆየን:: ሁለት ወር ተኩል በግብረ ሀይሉም ሆነ በድርጅቱ ደረጃ በይፋ በእንደኛውም ስም አለመጠቀማችን ዋጋ እስከፍሎናል:: ከሁለት ሳምንት በፊት ነው እዲሱን የግብረ ሀይል ስራ እስፈፃሚ ኮሚቴ ማቆቆም የዥመርንነው:: በደጋፊዌቻችንም ሆነ በሌሎች ወገኖች ይህ የድክመት ምልክት ሆኖ የተገመተበት ሁኔታ አለ;; ይህ የጥንካሬ የፅናት ምልክት ነው:: እስክንድር ለሀገሪቱም ሆነ ለፋኖ ሁልጉዜ ያለው አቌም በፅናት ላይ የተመሰረተ ነው:: ክሁለት ወር በላይ በየቦታው ስንዘዋወር "እናንተ ማን ናችሁ? " ስንባል የእዲሱም የቀድሞውንም ስም አለመጠቀማችን በህዝብ መሀከል ብዥታ እስኪፈጠር ድረስ እኛ በስምምነታችን መሰረት ቃላችንን ጠብቀን ተጉዘናል፡፡

ይህ አቌማችን ዛሬም እንደተጠበቀ ከአሁን ዥምሮ ምንም እንኳን በሁለቱ እርበኞች መሀከል ውይይቱ የሚቀጥል ቢሆንም ቃል በተገባው መሰረት በአዲሱ የእማራ ፋኖ ህዝባዊ ስራዊት ስም መጠቀም ጀምረናል:: ዘመነና እስክንድር ውይይታቸውን ሊቀጥሉ እንዲችሉ ሁኔታው አሁንም ፈጽሞ እልተበላሸም::: ያቆሙት የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ስራዊት እሁንም እንዳለ ነው ያለው:: በውይይቱ ወቅት እንደተነገረኝ የአመራር ፋክክር ፈጽሞ አልነበረም:: አንወያይ የነበረው እንደሚመስክር እስክንድር የእዲሱ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ስራዊት የበላይ ዘመነ ካሴ እንዲሆን ነበር እስክንድር የፈለገው::በዘመነ ካሴ በኩል ግን "አልፈልግም እስክንድር መሆን አለበት" በመባባል ላይ ብቻ ነው አለመግባባት የነበረው:: በዚህም ምክንያት ውይይቱ ሊፈርስ ትንሽ ነበር የቀረው ብሎ አወያዩ ነግሮኛል:: ይህ የሚያሳየው በሁለቱ ታጋዮች መሀከል ያለውን መቀራረብ እና መከባበር ነው::

የድርጅቱ ስም እንዳለ ስለ ሆነ አመራሩ ችግር ሆኖ ከታየ ተወያይተው እንደሚፈቱት ያላቸው ቅርበት ያመለክታል;:
በውጭ በኩልም በስምምነታቸው መሰረት አዲሱ ስራ እስፈፃሚ ኮሚቴ በመዋቀር ላይ ነው:: እሁን ባላንበት እጅግ በጣም ጥንቃቄ በሚጠይቅበት የፋኖ የትግል ስልት ዋንኛው "እንድነት ነው" ::ከአቢይና የኦሮሙማ ሰራዊት የበለጠ ዋንኛው ጠላታችን ገና ፍፁም እንድ እለመሆናችን ነው:: በእማራ ምድር ያለው መላው የፋኖ ስራዊት አቆም የጠራበት ወደ ወሳኙ ደረጃ ተላልፈን ትግሉን ከእማራ ምድር እስወጥተን ወደ ፋሺስቱ የፖለቲካ ስርአት ማእከል እዲስ አበባ ለመገስገስ የሚያቆመን እንዳችም ሀይል የለም ‼️

በዚህ ረገድ ታላቁ እስክንድርና እርበኛ ዘመነ እንዲሁም በየ ክፍለሀገሩ ያሉ የእዝ መሪዎችና ልዩነት ባለበት ቦታ ሁሉ ልዬነቶችን ማጥበብ ወይንም ማጥፋት ከሁሉም የበለጠ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው:: እኛም በውጭ ያለን የእነሱ ነፀብራቅ ሆነን ከመቼውም የበለጠ በፋሺስቱ ስርአት እንድነታችንን ለማደፍረስ የተቃጡብንን ልዩ ልዩ ሴራዎችን እያከሸፍን እስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁነታችንን ለሚዋደቀው ለሚስዋው ፉኖ ስራዊት ቃል በመግባት እናረጋግጣለን ‼️‼️

በምክንያት የዘገየውን ስራችንንም በአዲስ መንፈስ ለመቀጠል ተነስተናል:: ብዥታዎች ይጠራሉ:: ሴራዎች ይክሽፋሉ:: እስክንድር: ዘመነ እንዲሁም ሌሎች መሪዎች እንድ ናቸው ‼️‼️

እንድነታቸው እየጎለበተ ይሄዳል ‼️‼️
ጠላትን ደስ እይበለው ‼️‼️ ፋኖዎቻችን ያሽንፋሉ ‼️‼️ በውጭም በውስጥም ያሉ ሴረኞች ይተናሉ:‼️

ድል ለአማራ ፋኖ 🔥🔥🔥
ድል ለአማራ 🔥🔥🔥
ድል ለኢትዮጲያ 🔥🔥🔥

ሻ/ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ
የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት ድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ

,🟩🟨🟥🟩🟨🟥🟩🟨🟥

ጋሻ ሚዲያ ‼️‼️‼️‼️

ለበለጠ መረጃና ብሎም ለተሳትፎ የጋሻ ሚዲያን ዓለም አቀፍ የመወያያ ቴሌግራም ቻናልን በመቀላቀል መረጃዎችን በማቀብልና በመቀበል ሂደት ላይ የበኩላችሁን ድርሻ በማበርከት ይሳተፉ 👇👇👇

https://t.me/GMMediad

Address

Collierville, TN
38017

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gasha Amhara / ጋሻ አማራ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gasha Amhara / ጋሻ አማራ:

Share