Digital weyane movement

Digital weyane movement ወያነ

He**in
06/08/2020

He**in

05/22/2020

ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ማእከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ከ17 ዓመታት በላይ ፤ ካለምንም እረፍት በሞት በስደትና በመከራ ሳትምበረከክ የታገልከው ጀግና ታጋይ ህዝባችን።

ለመሪ ድርጅታችሁ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ከጨቅላ ዕድሜዋ ጀምራችሁ ኮትኩታችሁ ያሳደጋችሁ ወላጆች፤ ወንድምና እህቶች በሙሉ፣

የአብራካቹ ልጅ የሆነው ህወሓት ከአጋር ኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ታጋዮች ጋራ የጣምራ ክንዱን በማስተባበር ግፈኛውን የደርግ ሰራዊት ዶግ አመድ አድርጎ፤ መንበረ መንግስት የሆነችው አዲስ አበባን በትግሉ ነፃ በማውጣት፤ ከ16 ዓመት በላይ የፈጀው እጅግ መራራ የትጥቅ ትግል በድል አጠናቋል።

ልጆቻችሁ ሞት እና መከራ ወደነገሰበት የትግል ሜዳ በሚሰማሩበት ጊዜ፤ ልክ ወደ ሰርግ እንደሚሄዱ ቆጥራችሁ፤ አልብሳችሁ መርቃችሁና ጥይት በግንባርህ እንጂ በጀርባህ እንዳይመታህ በማለት ውድ ልጆቻችሁን መክራችሁ የሸኛችሁ የጀግንነት ምንጭ የሆናችሁ ወላጆች!

በታሪካችን ጅረት ላይ ምንግዜም ልዩ የክብር ቦታ ይዛችሁ የምተኖሩት፤ ትዳር ከትግልና ድል ቦኋላ ይሁንልን ብላችሁ ቁምጣ ሱሪ አጥልቃችሁ የታገላችሁ እናቶችና እህቶች!
የጀግንነታችሁ አሻራና ዳና ያልለቀቀው ጀግና ሰራዊታችን ከአጋር እህት ድርጅቶች ጋራ በመሆን፤ ዘራችሁን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ሌት ተቀን ሲጨፈጭፋችሁ ከነበረው አረመኔ ስርዓት በመስዋእትነት ገላግሎችኋል ። ኩራትና ወደር የሌለው ደስታ ይሰማችሁ። በደስታ እልል በሉ።
ጀግንነትህ ወዳጅና ጠላት የመሰከረለት፤ የህዝብ ልጅና ፤ የህዝቦች መብት መጠበቅያ ግምብ የሆንከው ጀግና ሰራዊታችን! የሰው ልጅ ይቋቋመዋል ተብሎ ከሚገመት በላይ መከራን ተቋቁመህ ከትግል አጋሮችህ ጋራ ክንድህን አጣምረህ ድል የተጎናፀፍከው አምበሳው ሰራዊታችን! የፀና እምነትና መርህ ባለቤትና የኩራታችን ምንጭ የሆንከው ጀግናው ሰራዊታችን። ድል ተጎናፅፈናል። አረሜኒያዊው የደርግ ሰርዓት ደምስሰናልና፤ አሁን ከመላው ህዝብ ጋራ ሁነህ ተደሰት። ጮክ ብለህ እልልታህን አሰማ፤ ያለምንም ጥርጥር የሚገባህ ድል ስለጨበጥክ በደስታ ቦርቅ! ዝለል!
የትግራይ ህዝብ ገና በጥዋቱ ትግል ሲጀምር፤ ለሌሎች አልምበረከክም፤ በአገሬ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥሬ አልኖርም፤ በተፈጥሮ ሃብት የታደለ መሬት እያለኝ በስደትና መከራ እየተቆራመድኩ አልኖርም፤ የሚል የማይናወጥ ፍላጎትና ዓላማ አንግቦ ነበር ለትግል የተንቀሳቀሰው።

መብቱን እና ጥቅሞቹን ለመጠበቀ እንጂ፤ የሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ መብትና ጥቅም ለመጋፋት ከቶ አልነበረም። ግፍ እና ጭቆናን ለማስወገድ እንጂ የነበረው ጭቆናና ግፍ በሌላ ጭቆናና ግፍ ለመተካት አልነበረም። ሁሉም ህዝቦች በነፃ ፍላጎትና በጋራ ተግባብተው ተፋቅረው በእኩልነት የሚኖሩባት አዲስ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመፍጠር እንጂ፤ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንዳልነበረች ሆና እንድትበታተን ለማድረግ አይደለም። ዛሬ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን የትግል አጋሮቹ ጋራ ተቃቅፎ ድል በጨበጠበት ወቅት የሚሰርዘው ወይም የሚተካው አዲስ ዓላማ የለውም።

ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች በነፃ ፍላጎታችነና በጋራ ተቃቅፈን በሰላም በእኩልነት አብረን የምንኖርባት በጥረታችንና በላባችን ሃገራችንን አልምተን ከችግርና መከራ ከድህነት አረንቋ የምንላቀቅበት ሁኔታ ለመፍጠር፤ የትግራይ ህዝብ ቀደም ብሎም እንደታገለው ሁሉ ፤ ለወደፊቱም ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በፍፁም አያጠራጥርም።

የትግራይ ህዝብም ይሁን ሌሎች ታጋይ ኢትዮጵያውያን ፤ መሳርያ አንግበው የታገሉት የጦርነት ሱስ ኑሮዋቸው ሳይሆን፤ ቀደም ብለው ለተዘረዘሩት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚጠቅሙ መሰረታዊ ዓላማዎች በተግባር ለማዋል ሌላ የአማራጭ በር ሁሉ ስለተዘጋባቸው ነበር።
የሰላምና የዲሞክራሲ፤ የወንድማማችነትና የእድገት መንገድ ፤ በጨቋኝ ግፈኞች የመሳርያና የሰራዊት አጥር ስለታጠረ፤ ይህ አጥር ለማፍረስ ሌላ አማራጭ ስለታጣ ነበር። አሁን ኢህአዴግና ሌሎች በአገሪቱ ውስጥ የነበሩ የነፃነት ታጋዮች ባስመዘገቡት አንፀባራቂ ድል፤ የጨቋኞችና የግፈኞች ፍላጎት ተንኮታኩቷል። አጥሩ ተሰብሯል።

ከእንግዲህ ወዲያ ተባብረንና ተቃቅፈን ወደ ዘላቂ ሰላምና አስተማማኝ ዴሞክራሲ፤ ወደ ዘላቂ እድገትና ብልፅግና የምንገሰግስበት ሁኔታ ተመቻችቷል። ይህ ወርቃማ ዕድል ሊያመልጠን አይገባውም። ይህ ወርቃማ እድል ሊባክንና ሊሰናከል ከቶውንም አይገባውም። ይህንን ዕድል በሚገባ ልንጠቀምበት፤ ልንጠብቀው፤ ልንንከባከበውና ልናሰፋው ይገባል።

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር፤ የሽግገር ፕሮግራሙን መሰረት በማድረግ የሁሉም ጭቁን ህዝቦች ጥማት ለማርካት ባለፈው ጊዜ ያለእረፍት እንደታገለ ሁሉ፤ ለወደፊትም በከፍተኛ ህዝባዊ እምነትና ቆራጥነት ያለምንም እረፍት እንደሚታገል የሚያጠራጥር አይሆንም።

ባለፈው ትግል አዎንታዊ ድርሻ ያልነበራቸው ኋይሎች፤ የጭቁን ህዝቦች የሰላም የዲሞክራሲና ዕድገት ጉዞ መቀልበስ የሚችል ኋይል እንደሌለ ተገንዝበው፤ ካለፈው ስህተታቸው ተምረው በዚህ በተቀደደው አዲስ የታሪክ ምእራፍ በንቃትና በገምቢ ድርሻ እንዲሳተፉ የኢህአዴግ ምኞት ነው። ካሁን ወድያ ተመልሶ ወደ ባርነትና አድልዎ የሚገባለቸው ህዝብ እንደሌለ ሊገነዘቡ ይገባል።

ካሁን በኋላ የሚጨቆንላቸው፤ የሚጨፈጨፍላቸው የሚዋረድላቸው ህዝብ እንደሌለ ሊረዱት ይገባል። ካሁን በኋላ በሰላም በዲሞክራሲና በእድገት ጎዳና ላይ አጥር ሊያበጁ እንደማይፈቅድላቸው ሊያስተውሉ ይገባል። ጊዜው ያለፈበት የግፍ ፤ ጭቆናና ብዝበዛ ስርአታቸውን በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ለመመለስ የሚጥሩ ከሆኑ ግን፤ ግፈኛውን የደርግ ሰራዊት የደመሰሰ የኢትዮጵያ ሰራዊት ፤ መብቱና ድሎቹ እንደገና አሳልፎ የሚሰጣቸው እንዳልሆነ ሊያጤኑት ይይገባል።

የኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች የሰላምና ዴሞክራሲ ጥሪ ረግጠው የማይረካው ፍላጎታቸውን ለማስፈፀም የሚከጅሉ ከሆነ የነብር ጭራ እየጨበጡ እንደሆነ ልናስገነዝባቸው እንወዳለን። በስንት መከራና መስዋእትነት የተገኘው ድል ዋስትና ለመስጠት መላው የኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች ተደራጅተውና ታጥቀው ዘብ ቆመው እንዳለ ልናስገነዝባቸው እንወዳለን።
ለዚህ ድል እንድንበቃ፤ ብዙ የማይተካ ውድ የወጣቶች ህይወት ከፍለናል። እሳት ለሚተፋ የጠላት መትረየሶች በአፈሙዝ ይዘው የሚቀሙ እልፍ ጀግና ወጣት ታሪክ ሰሪዎች ከፍለናል። በርከታ ሮጠው ያልጠገቡ ፤ ባለራእይና ሩቅ አላሚ ወጣቶች፤ ጉልበታቸው ተሰባብሮ ዓይኖቻቸው ጠፍቷል።

የበርካታ ህፃናት፤ ሽማግሌዎችና ሰላማዊ ዜጎች ህይወት ጠፍቷል። የብርሃን ጮራ ፍንጣቂ ለማየት የበቃነው በነዚህ ውድ ወገኖቻችን መስዋእትነት ነው። በነዛ ህይወታቸው አልፎ ዝናቸው ዘልአለማዊ በሆነው፤ ጉልበታቸው ተሰብሮ ጀግንነታቸው ግን እስከወዲያኛው የማይደመሰሰው ሰማእታቶቻችን ነው ድል የተጎናፀፍነው። መላው ህዝባችን ዛሬም ሆነ እስከወዲያኛው ፤ ዘልአለማዊ ክብር ለትግሉ ሰማእታት በል።

እናንተ ጀግና ያፈራች ማህፀንና የትግሉ ባለቤት የሆናቹ እናቶች በአጠቃላይ፤ እናንተ “እናትህ አንተን ወልዳ ትምከን” ያስባላችሁና ምርጥ ጀግኖች ወልዳችሁ ያሳደጋችሁ እናቶች! ከመቃብር በላይ የሚጠራ ስምና ክብር ያላቸው ልጆች ወልዳችሁ በማሳደጋችሁ፤ ወደር የለሽ ኩራት ይሰማችሁ።

ዓይኖቻችሁ የሃዘን ሳይሆን የደስታ እምባ ያንቡ። እኔ የውድ ሰማእት እናት ፤ የዘልአለማዊ ፍሬ ባለቤት ነኝ ብላችሁ ፎክሩ! ዕለል በሉ። ከተባረከ ማህፀናቹ ያፈራቹሃቸው ልጆቻችሁ፤ ለአንድ ቤተሰብ ሳይሆን ለመላው ዓለም የሚተርፍ ፍሬ አፍርተውላቹሃል።

ተንከባክባችሁ ያሳደጋቹሃቸው እጅግ የምትወድዋቸው ልጆቻችሁ ወደ ጀግንነት አውድማ አሰማርታችሁ ስታበቁ፤ ከድል በኋላ ተመልሳችሁ በኩራት አቅፋችሁ ለመሳም ዕድሉን ያላገኛችሁ ወላጆች። ልጆቻችሁ ልክ ከፊት ለፊታችሁ እንደቆሙ በመቁጠር አበጀሀ የኔ ልጅ ብላችሁ በአይነ ህሊና ጨብጧቸው።

ምንም እንኳ ልጆቻችሁ ለሁሉም ወደማይቀርለት መቃብር ቢገቡም፤ ምንም እንኳ አካላቸው ቢጎድል፤ ከመቃብር በላይ ዘልአለማዊ የሆነ ገናና ስምና ዝና ያተረፉ ናቸው። እነዚህ ጀግኖች ከአብራካችሁ የተገኙ በመሆናቸው፤ እኔ የጀግና አባት፤ እኔ የአንበሳ አባት በማለት ፎክሩ። የሃዘን ጥላ ፈፅማ አጠገባችሁ አታስጠጉ። ምንግዜም ፈገግታ፤ ኩራትና ደስታ ልበሱ። የእነኝህን ጀግኖች ታሪክ፤ ኢህአዴግና አሁን ያለው ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤ መጪው ትውልድም በፍፁም አይረሳውም። ስለዚህ ከመላው ህዝባችሁ ጋር ሆናችሁ ተፈስሁ፤ ተደሰቱ። ኩራት ይሰማችሁ!

ለዚህ ላገኘናት ድል ዛሬም እንደወትሮው፤ ይልቁንም ከወትሮም በበለጠ ለመጠበቅ ከመላው የአገሪቱ ህዝብ ጎን ዘብ ቁሙላት። መሪ ድርጅታችሁ ኢህአዴግ ምንግዜም ከጎናችሁና ከፊታችሁ ይኖራል። ድል አድርገናል። የጨበጥናት ድል ለመጠበቅ ከመሪ ድርጅታችን ጎን በተጠንቀቅ እንሰለፍ። እንኳን ደስ ያለን! ለበለጠ ድል ደግሞ ምንግዜም ከመሪ ድርጅታችን ኢህአዴግ ጎን እንቁም።

ጀግና ታጋይ ሆይ! የተሰዉ ጓዶችህ ዳና ተከትለህ በቁርጠኝነት ስለታገልክ፤ የህዝብህ ደመኛ ጠላት የነበረውን ስርዓት ደምስሰሃል። የተነሳህለት ትግል ግን ገና አልተቋጨም። በከባድ መስዋእትነት የጨበጥከው ድል ለማስጠበቅ፤ አሁንም ትጥቅህ ጠበቅ አርገህ በተጠንቀቅ ቁም። ህዝቡ ሰላምና መረጋጋቱን እንዲያጣ፤ የህዝብና መንግስት ንብረት ለመዝረፍና ለማውደም የሚንቀሳቀስ ኋይል ተከታትለህ ደምስስ።

ጭቁኑ የኤርትራ ህዝብ ሆይ ! ከ30 መራራ የተጋድሎ ዓመታት በኋላ የራስህን እድል ራስህ የምትወስንበት ሁኔታ ፈጥርሃል። ለዚህ ከልብ በመነጨ እንኳን ደስ አለህ እንላለን። እኛ የኢህአዴግ አባላት ታጋይ ወንድሞችህ፤ ብዙ እየተነገረና ብዙ እየተደረገ ሳለ፤ አእምሮአችን በዚህ ሳይረበሽ ከመብትህ ጎን በጽናት ተሰልፈን ታግለናል። በዚህ ድርጊታችን ደግሞ ኩራት ይሰማናል። ዛሬ በአዲስ የታሪክ ምዕራፍ መግቢያ በደረስንበት ጊዜም ቢሆን፤ ወለም ዘለም ሳንል እንደ ወትሮው፤ ከመብትህ ጎን መሰለፋችንን እንደምንቀጥል እናረጋግጣለን። ዓለምአቀፍ ቁጥጥር ባለበት ሁኔታ የራስህ ዕድል በራስህ እንድትወስንም እንታገላለን። ውሳኔህ ምንም ይሁን ምን ፤ እኛ ለውሳኔህ መከበር አሁንም በጽናት ከጎንህ እንቆማለን።
በአከባቢያችን ሰላምና መረጋጋት መስፈን ለሁላችንም የሚጠቅም ጉዳይ በመሆኑ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (EPLF) ትብብር እንደተለመደው የጠበቀ ይሆን ዘንድ እንደ አንድ ጽኑ ጓደኛህ እንማፀናለን። የተጠየቅነው ዋጋ ከፍለን ከጎንህ እንደቆምን ሁሉ፤ ወደፊትም መብትህና ጥቅምህ የሚፃረር ማንኛውም ነገር ይዘን እንደማንቀርብ ልናረጋግጥልህ እንወዳለን።

የኤርትራ ህዝብም፤ ይጠቅመኛል ብለህ የምትወስነው ውሳኔ ምንም ይሁን ምን ለወደፊት የኢትዮጽያና የኤርትራ ህዝቦች የጋራ ጥቅምና ፍላጎት እንደሚኖራቸው አያጠራጥርም። ስለዚህ ውሳኔህ እንዳለ ሆኖ ለሁለቱም ህዝቦች መልካም ዝምድናና መደጋገፍ በተቻለህ መጠን እንድትተጋ እንጠይቃለን። ልክ በትጥቁ ትግል ጊዜ፤ የተጠየቅነው ዋጋ ከፍለን ከመብት መከበር ጎን እንደቆምን ሁሉ ፤ ለወደፊትም መብትህና ጥቅምህ የሚፃረር ነገር ይዘን እንደማንቀርብ ደግመን እናረጋግጥልሃለን።

ጉንበት 20 /1983 ዓ.ም

Address

England
Chelsea, MA
09330933

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Digital weyane movement posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share