Ethiopian Community Jeddah. በጅዳ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ

Ethiopian Community Jeddah. በጅዳ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Community Jeddah. በጅዳ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ, Community Center, Jeddah, Saudi Arabiya, Jeddah.

24/08/2026
በጅዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ የአሸንዳ በዓልን በደማቅ ሁኔታ አከበረ።( ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም፤ጅዳ) በጅዳ እና አካባቢው የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ነሐሴ ...
23/08/2026

በጅዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ የአሸንዳ በዓልን በደማቅ ሁኔታ አከበረ።

( ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም፤ጅዳ) በጅዳ እና አካባቢው የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. በጅዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጄኔራል ግቢ ውስጥ በሚገኘው የማህበረሰብ አዳራሽ በመሰብሰብ ዓመታዊውን የአሸንዳ ባህላዊ በዓል (ሻደይ፣ አሸንዲዬ እና ሶሌል በመባልም የሚታወቀውን) በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል።
በዝግጅቱ ላይ ዲፕሎማቶች፣ የቆንስላ ጽ/ቤት ሠራተኞች፣ የማህበረሰብ አመራሮች፣ የትግራይ ልማት ማህበር (ትልማ) ተወካዮች፣ ወጣቶች ፣ ሴቶች እና ልጃገረዶች ፣ የተገኙ ሲሆን፤ በዚህ ወቅት የሚያበስረውን የኢትዮጵያውያን ሴቶችን ውበት፣ ጥንካሬ እና ባህላዊ አስተዋፅኦ የሚያከብረውን ይህንን ድንቅ ባህል በጋራ ዘክረዋል።
የዝግጅቱ ዋና ዋና ሁነቶች እና የተደረጉ ንግግሮች፡-
• አቶ ሙሉጌታ አበበ (በጅዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጄኔራል ተወካይ)፦ በቆንስላ ጄኔራሉ ስም ያስተላለፉትን መልእክት አቶ ሙሉጌታ፣ በስደት የሚኖረው ዳያስፖራ ባህሉን እና ወጉን ጠብቆ ማቆየቱ ለሀገራዊ አንድነት እና ለትውልድ መስተጋብር ያለውን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ገልጸዋል።
• አቶ ሰመሩ ከድር (በጅዳ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ምክትል ሊቀመንበር)፦ በበኩላቸው በጅዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ እንዲህ ያሉ ባህላዊ ሁነቶችን በማዘጋጀት የዳያስፖራውን ህብረት እና ወንድማማችነት እንደሚያጠናክር ገልጸው፣ ዝግጅቱን ላስተባበሩት አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
• አቶ አብዱልቃድር አብራር (በጅዳ የትግራይ ልማት ማህበር ሊቀመንበር)፦ በዕለቱ ባደረጉት ንግግር የአሸንዳ በዓል በኢትዮጵያውያን ዘንድ ያለውን ሁለንተናዊ ባህላዊ እሴት ያብራሩ ሲሆን፣ የእንኳን አደረሳችሁ የደስታ መግለጫቸውን አሰምተዋል፣
• አቶ ሚካኤል አፅብሃ (በጅዳ የትግራይ ልማት ማህበር ምክትል ሊቀመንበር እና የዝግጅቱ አስተባባሪ)፦ የአሸንዳ በዓል የሰላም፣ የፍቅር እና የሴቶች ክብር መግለጫ መሆኑን በመጠቆም፣ በጄዳ የሚኖሩ ወጣቶች ከባህላቸው ጋር ያላቸውን ቁርኝት ለማጠናከር የተደረገው ጥረት ፍሬ ማፍራቱን አብራርተዋል።
ባህላዊ ትርኢቶች እና የወጣቶች ተሳትፎ
በዕለቱ ወጣት ልጃገረዶች እና ሴቶች በጥልፍ ሀገር ልብስ አምረው እና አጊጠው ከበሮ እየመቱ ባህላዊ ዜማዎችን እና ወካይ ጨዋታዎችን አቅርበዋል። በዓሉ በውጭ ሀገር ለተወለዱና ላደጉ ወጣቶች ከወላጆቻቸው ባህል፣ እሴት እና ወግ ጋር እንዲገናኙ ትልቅ ድልድይ ሆኖ አገልግሏል።
ሥነ-ሥርዓቱ በባህላዊ ዝግጅት እና በህብረት መግለጫዎች በታላቅ ደስታ ተጠናቋል።

ነሐሴ 15ቀን 2018 ዓ/ም በጅዳ ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ የጅማ ከተማ የልማት ገቢ ማሰባሰቢያ የመዝጊያ መርሃ ግብር በልዩ ድባብ ተካሄዷል     በእለቱ የገቢ ማሰባሰቢያው የመዝግያው ፕሮግ...
23/08/2026

ነሐሴ 15ቀን 2018 ዓ/ም በጅዳ ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ የጅማ ከተማ የልማት ገቢ ማሰባሰቢያ የመዝጊያ መርሃ ግብር በልዩ ድባብ ተካሄዷል
በእለቱ የገቢ ማሰባሰቢያው የመዝግያው ፕሮግራም ላይ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር በሳዑዲ አረቢያ የኢፌድሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣንና በሳቸው የተመራ የሪያድ ልዑካን ቡድን በጅዳ የኢፌድሪ ቆንሲል ጀኔራል ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ የቆንሲላው ጽ/ቤት ድፕሎማቶችና የአስተዳደር ሰራተኞች የተለያዩ አደረጃጀት ተወካዮች የልማት ማህበር አመራሮች የኢትዮጵያ ት/ቤት ቦርድ አመራር የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝቷል
በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ መሀመድኑር ሀሰን ለእንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ስሆን ዛሬ የተሰባሰብንበት የጅማ ከተማን የኤሌክትሪክ የውኃ እና የጎዶሏትን መሠረተልማት በጋራ ሆነን ለማሟላት በኮርደር ልማትና በመሳሰሉት በማስዋብ የቱሪዝም መዳረሻ ምቹ ከተማ ለመፍጠር ህዝባዊ ሀላፊነታችንን እንድንወጣ አደራ ብሏል
ቀጥሎ ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ የሞቲ አባጅፋር ሀገር የክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ እና የቀድሞው የኦሮሚያ ፕሬዝዳንትና ም/ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት የአምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር ከተማ የሆነውን ጅማ ለልማት የቀረበውን ጥሪ በመቀበል የጅዳና አከባቢው ማህበረሰብ እንደ ሁልግዜው ለጥሪው ትኩረት ሰጥተው ላሳየው ከፍተኛ ተሳትፎና ተባብሮ መቆምን በማድነቅ ደስታቸውን ገልጿል
ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድርም በበኩላቸው የጅዳ ማህበረሰብ ከዚህ በፊት የህዳሴ ግድብንና በሀገራችን በተገነቡት ትላልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች ውስጥ የናንተ አሻራ ያላረፈበት የለም ዛሬም የጅማ ከተማን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የተሳተፋችሁ የቻላችሁትን አስተዋዕፆ ያደረጋችሁ እና በሥፍራው ተገኝታችሁ ድጋፋችሁን ለገለፃችሁ ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ ብሏል
ለጥቆ ለጫረታ ከቀረቡት በጅማ ታሪካዊ ቅርሶች ዕድሜ ጠገቡን ከ250 ዓመት በላይ የኖረውን አፉርተማ መስጊድና የሞቲ አባጅፋር ምስል ለጫረታ ቀርበው ሁሉም ማህበረሰብ በአቅሙ የተሳተፈ ሲሆን በመጨረሻ በአልሸነፍም እልህና ቁጭት አንገት ለአንገት ተናንቀው የዘለቁት በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሠራተኞች የጅዛን ኮሚኒቲ የአርጎባ ልማት ማህበር ቄሮ ጅዳና ሸነን ግቤ ሲሆኑ የጅዛን ኮሚኒቲ በ24,650 ሳ.ሪ የጫረታውን ድል በመቀናጀት አሸናፊ ሆኗል
ይህ ድል የአንድ ቡድን ወይም የጥቂት ግለሰቦች ውጤት ሳይሆን የማህበረሰቡ አንድነት ተሳትፎና በጋራ ለመሥራት ለመልማት ያለው ፍላጎት የተገለጠበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነበር
በመጨረሻም በዚያች ምሽት ለጅማ ከተማ ከ142,000 ሳ.ሪ በላይ መሰብሰቡ ታውቋል ።

21/08/2026

🌸 ኣከባብራ በዓል ኣሸንዳ
ማሕበር ልምዓት ትግራይ ጅዳ ከምቲ ዓመት ዓመት እንገብሮ ንማሕበረሰብ ትግራይ ኣብ ጅዳን ከባቢኣን ፌስቲቫል ኣሸንዳ ንምብዓል ምድላዋት ዛዚሙ ኣሎ።
ስለዚ በዓል ኣሸንዳ ምስ ኩሎም ኢትዮጵያውያን ሓቢርና በዚ ኣብ ታሕቲ ተጠቒሱ ዘሎ ዕለት አብ አዳራሽ ኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ጅዳ ንምኽባር ምድላው አሎ።ኣሸንዳ በዓል ባህሊ፣ ልምድን ሕውነትን እዩ። ኣብዚ ውቁብ ባህላዊ ፈስቲቫል ብምስታፍ ባህልና ከነብዕልን ሓድነት ኢትዮጵያ ክንጠናኸርን ኩልኹም ብኽብሪ ንዕድም።
ዕለት➣ ነሓሰ 16, 2018 (ነሓሰ 22/2026)
ሰዓት➣12፡00 ምሸት (6፡00 pm)
ቦታ➣ ኣዳራሽ ማሕበረሰብ ጅዳ ኢትዮጵያ
ካብ ጨንፈር ማሕበር ልምዓት ትግራይ
ጅዳ

21/08/2026

🌸 የአሸንዳ በዓል የጋራ ክብረ በዓል
በጅዳ የትግራይ ልማት ማህበር በሳዑዲ አረቢያ ጅዳና አከባቢዋ ለሚገኘው የትግራይ ማህበረሰብ ቀደም ስል በየአመቱ እንደምያደርገው የአሸንዳ በአልን ለማክበር የዝግጅት ሥራውን አጠናቋል
በመሆኑም የአሸንዳ በዓልን ከታች በተጠቀሰው ቀን ከመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ጋር በጋራ በጅዳ ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ለማክበር ተዘጋጅተናል
አሸንዳ የባህል፣የወግና የእህትማማችነት በዓል ነው በዚህ ውብ የባህል በዓል ላይ በመገኘት ባህላችንን በጋራ እንድናከብርና የኢትዮጵያዊ አንድነታችንን እንድናጠናክር ሁላችሁንም በአክብሮት እንጋብዛለን
ቀን➣ ነሐሴ16 ቀን 2018(aug 22/2026)
ሰዓት➣ከምሽቱ 12:00( 6:00pm)
ቦታ➣በጅዳ ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ
ከትግራይ ልማት ማህበር ቅርንጫፍ
ጅዳ

20/08/2026

Sirna Cufiinsa Sagantaa Galii Misooma Magaalaa Jimmaa
Hawaasni Itiyoophiyaa magaalaa Jiddaa fi naannawa ishee Sa'udii Arabiyaa misooma Magaalaa Jimmaa cimsuuf sagantaa galii walitti qabuu qopheessee jira. Sirni cufiinsaa Jimaata Hagayya 15, 2018 (AUG 21/2026) Galma Hawaasa Jiddaatti ni gaggeeffama.
Sirna cufiinsaa kana irratti keessummoonni kabajamoo biyyaa fi biyya alaa irraa ni argamu.
Isaanis: Kantiibaa Magaalaa Jimmaa, Kabajamoo obbo Taha Qamar fi waahillan isaani.
Kabajamoo Dr. Ambaasaaddar Muktaar Kedir, Sa'udii Arabiyaatti Aangoo Guutuu Mootummaa Federaalaa Itiyoophiyaa.
Qoonsilaa Jeneraalaa Jiddaa, Ambaasaaddar Tafaa Tuluu fi dippilomaatota.
Akkasumas bakka bu'oonni jaarmiyaa hawaasaa fi abbootii amantaa Jiddaa fi naannawa ishee, waamicha manguddoota biyyattii. Sirni cufiinsaa bakka keessummoonni affeeraman argamanitti ni gaggeeffama
Sagantaan kun aadaa wal hubannaa fi tumsa hawaasa diyaaspooraa keenyaa fi biyya gidduu jiru, misooma bira darbee, akkasumas hirmaannaa inni guddina biyyaa keessatti qabu agarsiisudha. Hundi keessan miseensonni hawaasa keenyaa guyyaa fi sa'aatii beellamame irratti akka argamtan kabajaan isin gaafanna.
Waldaa Hawaasa Itoophiyaa irraa
Jiddaa

19/08/2026

የጅማ ከተማ ልማት ማጠናከሪያ የገቢ ማሰባሰቢያ መሪሃግብር መዝጊያ ፕሮግራም
በሳዑዲ አረቢያ ጅዳና አከባቢዋ የሚገኙው የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ለጅማ ከተማ ልማት ማጠናከሪያ የሚውል ገቢ ለማሰባሰብ ሲያከናውን የቆየው መርሃግብር ነሐሴ 15 ቀን 2018(AUG 21/2026) የፊታችን ጁመዓ(አርብ) ምሽት በጅዳ ኮሚኒቲ አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ የመዝጊያ ፕሮግራም ይጠናቀቃል
በመዝጊያ መርሃ ግብሩም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር ተዋቂ እንግዶች ይገኛሉ
እነርሱም ፦ የጅማ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ጣሃ ቀመር እና ባልደረቦቻቸው
በሳዑዲ አረቢያ የኢፌዲሪ ባለ ሙሉ ስልጣን ክቡር ዶ/ር አምባሳደር ሙክታር ከድር
የጅዳ ቆንሲል ጀኔራል ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ እና ድፕሎማቶች
እንዲሁም የጅዳ እና አከባቢዋ ማህበረሰብ አደረጃጀት ተወካዮችና የሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የመርሃ ግብሩ መዝጊያ ይከናወናል
ይህ መርሃ ግብር ከልማት በላይ የድያስፖራው ማህበረሰባችን ከሀገር ጋር ያለውን ትስስር የመረዳዳት ባህልን እና ለሀገር ልማት ያለውን ተሳትፎ የሚያሳይ ታላቅ ተግባር ነውና ሁላችሁም የኮሚኒቲ ማህበረሰብ አባሎቻችን በተባለው ቀንና ሰዓት በክብር እንድትገኙ በአክብሮት እንጠይቃለን
ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር
ጅዳ

በጅዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ቆንስል ጄኔራል የሆኑት ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ በሳዑዲ ዓረቢያ፣ ጄዳ የነበራቸውን የሥራ ዘመን ማጠናቀቃቸው ምክንያት በማድረግ በጅዳና አካ...
16/08/2026

በጅዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ቆንስል ጄኔራል የሆኑት ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ በሳዑዲ ዓረቢያ፣ ጄዳ የነበራቸውን የሥራ ዘመን ማጠናቀቃቸው ምክንያት በማድረግ በጅዳና አካባቢዋ በሚገኙ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ደማቅ የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ተደረገላቸው።
በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ የጅዳና አካባቢዋ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት፣ ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ ለማኅበረሰቡና ለሀገራችን በከፍተኛ ቁርጠኝነት፣ ትጋትና ተቆርቋሪነት ላበረከቱት አገልግሎት የላቀ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅርና ክብር ለመግለጽ የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክተውላቸዋል።
በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ የማኅበረሰቡ አባላት ላደረጉላቸው ሞቅ ያለ ሽኝት ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ በቆይታቸው ወቅት ማኅበረሰቡ ላደረገላቸው ያልተቋረጠ ድጋፍና ትብብር ከፍተኛ አክብሮታቸውን ገልጸዋል።

Qonsilaa F.D.R.I Jiddaatti Hooganaa kan turan Ambasaaddar Xaafaa Tulluu, yeroo Turtii isaanii Sa’uudi Arabiyaa, Jiddaatti qaban xumuruu isaanii sababbeeffachuun Hagayya guyyaa 8/2018 hawaasni oromoo magaalaa jiddaa fi naannawa ishee qophii geggeessaa hoo'aa isaaniif taasisanii jira.
Sirna geggeessaa kana irratti, miseensonni hawaasa Oromoo Jiddaa fi naannawa ishee Ambaasaaddar XaafaaTulluu hawaasichaafi biyya keenyaa kutannoo olaanaa fi quuqama guddaan tajaajila turuu isaaniif galata guddaa dhiyeessuun, jaalalaafi kabaja guddaa isaaniif qaban ibsuuf kennaa garaagaraa gumaachaniifii jiru.
Dhumarrattis, Ambaasaaddar XaafaaTulluu miseensota hawaasaa geggeessaa isaaniif taasisaan galateeffachuun, yeroo turtiisaanitti hawaasichi deggersaa fi tumsa walirraa hin cinne taasisaa turuu isaanitiif kabaja olaanaa hawaasichaaf qaban ibsaniiru.

Address

Jeddah, Saudi Arabiya
Jeddah

Opening Hours

Monday 8am - 3pm
Tuesday 8am - 3pm
Wednesday 8am - 3pm
Thursday 8am - 3pm
Sunday 8am - 3pm

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Community Jeddah. በጅዳ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share