Mesewat

Mesewat MESEWAT is non religious,non racial,non political organization and it is an organization that advoc

26/07/2026
በኢትዮጵያ የስደት እና የግዳጅ መፈናቀል ምርምር ኮንፈረንስ ላይ የተደረገ ተሳትፎ እና የተቋማዊ ዕይታ።===========================================በመጀመሪያ ይህንን ...
18/06/2026

በኢትዮጵያ የስደት እና የግዳጅ መፈናቀል ምርምር ኮንፈረንስ ላይ የተደረገ ተሳትፎ እና የተቋማዊ ዕይታ።
===========================================
በመጀመሪያ ይህንን መሰል አገራዊ ፋይዳ ያለው መድረክ በሰኔ 17 እና 18/ 2026 በኢንተር ለግዠሪ ሆቴል ላዘጋጁት የአዲስ እበባ ዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት ሚኒስቴር መስዋዕት የበጎ አድራጎት ድርጅት የላቀ ምስጋናውን ያቀርባል። በኮንፈረንሱ ላይ የቀረቡት ሳይንሳዊ የምርምር ውጤቶች እና ማሳያዎች ከተቋማችን ስትራቴጂካዊ ዓላማ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚጣጣሙ በመሆናቸው፣ ከፍተኛ ተቋማዊ ግንዛቤ የተገኘበት መድረክ ሆኖም አግኝተነዋል።
==========================================
የኮንፈረንሱ አጠቃላይ ገጽታ እና ተሳትፎ
ይህ የሁለት ቀናት የምርምር ኮንፈረንስ ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የመጡ ልሂቃንን፣ የውጭ አገራት ምሁራንና ተመራማሪዎችን፣ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችን፣ ከስደት ተመላሾችን እና ስደተኞችን ያሳተፈ ነበር። በመድረኩ ላይ ስደትን፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ የአገር ውስጥ የግዳጅ መፈናቀልን እንዲሁም በአጎራባች አገራት የሚታዩ ቀጠናዊና አህጉራዊ ተግዳሮቶችን ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ያገናዘቡ ጥናቶች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
==========================================
ኮንፈረንሱ በስደት ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማትን እና የምርምር ስራዎችን በግልጽ ያሳየ ሲሆን፣ የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ተስተውለዋል፦
• የትኩረት አቅጣጫ መኖሩ፦ የስደተኞችን እንግልትና ስቃይ ለመቀነስ በትኩረት የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።
• የመረጃ ቅንጅትና ትስስር፦ በቀጣይ ስራዎች ላይ አወንታዊ ውጤት ለማስመዝገብ ከማን ጋር መተባበር እንደሚገባ ጠቋሚ የሆኑ ወሳኝ መረጃዎችና ግንኙነቶች ተፈጥረዋል።
• በምርምር ላይ የተመሰረቱ መፍትሔዎች፦ ለተለዩት ችግሮች የቀረቡት የመፍትሔ አቅጣጫዎች በተገቢው መንገድ ተግባራዊ ከተደረጉ ዘላቂ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ መሆናቸውን ለማየት ተችሏል።
==========================================
ስትራቴጂካዊ ምልከታዎች እና ምክረ-ሀሳቦች (Institutional Observations)
------------------------------------------------------------------------
የ«መስዋዕት» ማህበር ከተቀባይ አገራት ጀምሮ እስከ ላኪ አገር (ኢትዮጵያ) በነበሩት የሥራ ዓመታት ካካበተው ሰፊ ልምድ በመነሳት የሚከተሉትን ተቋማዊ ምክረ-ሀሳቦች ያቀርባል፦
• የምርምር ውጤቶችን ወደ ተግባር መለወጥ፦ እስካሁን በስደት እና ስደተኞች ዙሪያ በርካታ ጥናቶች ቢደረጉም፣ አብዛኛዎቹ በጥናት ደረጃ ተከማችተው የሚቀሩ እንጂ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ ሲቀየሩ አይታዩም። በመሆኑም በላኪ እና በተቀባይ አገራት መካከል ያሉ ችግሮችን ያገናዘቡ ጥናቶች ተቀናጅተው ለዘላቂ መፍትሔ ቀርበው መገልገያ መሆን ይኖርባቸዋል።
• የተመላሾችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መልሶ ማቋቋም፦ በስደት የሚገኙ ዜጎች ወደ አገራቸው ሲመለሱ ቀላል በሆነ መንገድ ቋሚ ገቢ የሚያስገኙ የሥራ ዕድሎች ወይም ተቋማዊ አደረጃጀቶች ተመቻችተውላቸው፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወታቸው ከዜሮ እንዳይጀምር ለማድረግ ከመንግስት መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የለፉበትን ገንዘብ አጠቃቀማቸውን እንዲያስተካክሉ ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ እና ይህንን ክፍተት ለመሙላትም ቀላል እና ተመላሹ ከመመለሱ በፊት ራሱን እና ቤተሰቡን ብሎም ማህበረሰቡን ሊጠቅም የሚችልበትን የፖሊሲ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥረት ቢደረግ።
• የዜጎችን የመደራጀት አቅም ማሳደግ፦ መንግሥትና የሚመለከታቸው አካላት በተቀባይ ሀገራት ላይ ጠንካራ የሰው ኃይል አደረጃጀት በሌለባቸው የተቀባይ አገራት አካባቢዎች ኢትዮጵያውያን በህጋዊ መንገድ እንዲደራጁ ማገዝ የሚቻልባቸውን ዘዴዎችና አሰራሮችን መቀየስ።
• የጠንካራ መዋቅር ምስረታ ልምድ መውሰድ፦ አገራችን በተቀባይ አገራት ካሉ የሌሎች አገራት ጠንካራ የዜጎችን መብትና ጥቅም የማስከበር ልምዶች በመቅሰም አፋጣኝ ለውጦች እንዲመጡ መስራት።(እስከዛሬ ምንም የለም ማለት ያለመሆኑ ይታሰብ)
• የአገልጋይነት ስነ-ልቦና፦ የዲፕሎማሲና የመንግሥት ተወካዮች ከዜጎች ጋር ያላቸውን ጥምረት በማጠናከር፣ የኢትዮጵያዊ ስደተኛ ኃይል ለአገር ኢኮኖሚና ለፖለቲካ ዲፕሎማሲ የበላይነት አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት ማድረግ የሚቻልበት መንገድ ቢቀየስ በአገር ውስጥ ብቻ የሚደረጉትን ጥረቶ በእጥፍ በማሳደግ በአጭር ግዜ ችግሮቻችንን ልንቀንስ እንችላለን።
==========================================
ማጠቃለያ
------------------------------------------------------------------------
ይህ የሁለት ቀናት ኮንፈረንስ የበጀት ማሟያ መድረክ ብቻ ሳይሆን፣ ለቀጣይ ተጨባጭ ለውጦች መነሻ ምክንያት እንዲሆን ተስፋ እናደርጋለን። የቀረቡትን የምርምር ውጤቶች መሠረት በማድረግ፣«መስዋዕት» ከተመራማሪዎችና ከመንግሥት አካላት ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ያረጋግጣል።

ሳሙኤል ተስፋዬ

መስዋዕት ይህህን ብሏል።  ይህንን እድል እናንተ አግኝታችሁት በሆነ ምን ትሉ ምን እውነትን ታስተላልፉ ነበር?
27/04/2026

መስዋዕት ይህህን ብሏል።
ይህንን እድል እናንተ አግኝታችሁት በሆነ ምን ትሉ ምን እውነትን ታስተላልፉ ነበር?

187 likes, 3 comments. "EMS “ሙዚቃውን እያለቀስን ሰማነው” “አረብ ሀገር መምጣትልጅነትን መጨረስ ነው” Apr 2026"

16/02/2026

Celebrating my 8th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

Address

Beirut

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mesewat posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Mesewat:

Share