Ethiopian Sports and Culture Federation in UK

  • Home
  • Ethiopian Sports and Culture Federation in UK

Ethiopian Sports and Culture Federation in UK Ethiopian Sports and Culture Federation in UK (ESCFUK)

31/05/2026

የኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በዩኬ - ESCFUK ድርጅቱን በህገ ወጥ መንገድ ስለመያዙ በሚመለከት Thursday 4th June 2026 የቀጥታ ስርጭት TikTok ይኖረናል። በመሆኑም የፌዴሬሽኑ ባለድርሻ አካላት ፣ የስፖርት ቤተሰብ፣ ደጋፊዎች እና መላው ማህበረሰባችን እንድተከታተሉ ተጋብዛችኋል:: ጥያቄዎች ካላችሁ ለመጠይቅ ዕድል ይሰጣል፤ የፌዴሬሽኑ ጉዳይ በተወሰነ ደረጃ ውስብስብ በመሆኑ በሶስት ቀናት ተከፋፍሎ ለእናንተ ይደርሳል። ተዘጋጁ።
Date: Thursday, 4th June 2026
Time: 7:30pm
Venue: Live on TikTok live tiktok.com/ በቀጥታ ይከታተሉ
ተሾመ አለሙ ቦጋለ

ከኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በዩኬ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ቀን፣ December 13, 2025ለኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በዩኬ ደጋፊዎች፣ የስፖርት ቤተሰብ ፣ ባለድርሻ አካላት...
17/12/2025

ከኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በዩኬ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ቀን፣ December 13, 2025

ለኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በዩኬ ደጋፊዎች፣ የስፖርት ቤተሰብ ፣ ባለድርሻ አካላት እና ለመላው ኢትዮጵያውያን፤

በፌዴሬሽናችን ላይ የተፈጸመውን አስተዳደራዊ፣ መዋቅራዊ እና ድርጅታዊ አሰራርን በማፍረስና የድርጅቱን ሁለንተናዊ ቁመና ብሎም አቋም በመናድ ድርጅቱን በህገ ወጥ መንገድ ከያዙ በኋላ በሽምግልና ሰበብ ህጋዊ ለማድረግ የሚደረገውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ ፌዴሬሽናችን በጥብቅ እንደሚያወግዝና ህገወጦችን እንደመተባበር አድረጎ ይመለከተዋል።
በህጋዊ መንገድ የተመረጠውን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተሾመ አለሙ ቦጋለ በተከፋይ ሚዲያዎቻቸው ( ትግስት ንጉሱ ውቤ - TGS Entertainment እና ዘውዱ መንግስቴ - Zewdu Show) አማካይነት ከባድ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ አስደረገው እንዲሁም ድርጅቱን በህገ ወጥ መንገድ አግተው ከያዙ ግለሰቦችን ጋር ምንም ዓይነት ድርድር እንደማንቀበልና ጉዳዩም እልባት የሚያገኘው በሀገሪቱ እና በድርጅቹ ህገና አሰራር ብቻ እና ብቻ መሆኑን እንገልፃለን።

ደርጅታችን ከተመሰረተ 2011 ጀምሮ ማኅበረሰባችን በማንቃት፣ በማገናኘት እንዲሁም የኢትዮጵያ ባህልን በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሚና መወጣቱን ይታወቃል። ነገር ግን ድርጅቱ ከምሰረታው ጀምሮ በመስራቾቹ መካከል በነበረው አለመግባት ፣ የድርጅቱን የገንዘብ አቅም አለመረጋጋት፣ ብዙሃን ኢትዮጵያውያን መድረስ አለመቻል፣ የድርጅቱን የውስጥም ሆነ የውጭ ህጎች እና ደንቦች አለማክበር እና ማስከበር ችግር ገጥሞት ከተመሰረተ 9ኛው ዓመት ዓመታዊ ዝግጅት በኋላ ድርጅቱ ሙሉ ለሙሉ በአዲስ ሰው እንዲተካ በአጠቃላይ ጉባኤ በቀረበው ረቀቅ መሰረት፣ ሚዲያ ባለበት ፣ የሀይማኖት አባቶች በተገኙበት፣ ባለድርሻ አካላት ፣ የስፖርት ቤተሰብ በተገኘበት ብሎም ብዙ ኢትዮጲያውያን በተገኙበት February 17, 2019 ለአዲስ ኮሚቴ አስረክበዋል። ነገር ግን እነዚህ መስራች ነን የሚሉ ሰዎች በ9 ዓመት በድርጅቱ የገንዘብ ካዝና የተገኘው £8,000 መሆኑን በስፖርት ቤተሰብ በኩል ትልቅ ቅራኔ ብሎም ግርምት ፈጥሮ ቆይቷል።

አዲሱ በተመሰረተው ኮሚቴ በሁለት ዝግጅቶች ( በ2022 እና 2024) ብቻ £32,000 የተጠራ ገቢ የድርጅቱ ካዝና ውስጥ አስገብቷል በአጠቃላይ የድርጅቱ ካፒታል ወደ £40,000 አድርሶታል። ይህንን ተከትሎ idle ሆነው የነበሩት ድርጅቱ ላይ ምንም ዓይነት ተሳትፎ ያልነበራቸው መስራች ነን የሚሉ አካላት ብቅ ብቅ ማለት ጀምረው በድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ተሾመ አለሙ ቦጋለ ያው በለመዱት መንገድ ስም በመለጠፍ ምርመራ ብለው የራሳቸው ጓደኞች በመሰብሰብ ጉዳዩን ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው በማድረግ በለመዱት ሴራ መሰረት፣ የድርጅቱን ገንዘብ ያባከኑ ግለሰቦችን ሆነ ብለው በመተው በህገ-ወጥ መንገድ ጥሩ ስራ ሰርቶ በህዝቡ ዘንድ ቅቡልነት ያገኘውን አዲሱ የስራ አመራር ኮሚቴ ለማንሳት ሀሳብ ያቅርባል። አዲሱን የስራ አመራር ኮሚቴ በማንሳት ብሎም ድርጅቱን ለመንጠቅ መጀመሪያ ዋና ስራ አስኪያጅን የሆኑትን ተሾመ አለሙ በሰበብ አስባብ ለማንሳት ውሳኔ አቀረቡ ያው “ መንጋው ለመበተን እረኛውን መምታት” ይባል የለ።እነዚህ ግለሰቦች በ2024 በተዘጋጀው የፌዴሬሽኑ አመታዊ ፌስቲቫል ላይ የተገኘውን ገቢ £10,000 ከድርጅቱ አካውንት ማውጣታቸውን ቀጥሎም በ2025 በተደረገው የፌዴሬሽኑ ፌስቲቫል ላይ ምንም ዓይነት የፋይናንስ ሪፖርት ይፋ አለመደረጉን መታወቅ አለበት። እነዚሁ ግለሰቦች ናቸው ዋና ስራ አስኪያጅን አቶ ተሾመ አለሙ በ2024 የፌዴሬሽኑ ዝግጅት ላይ £100,000 ዘርፏል ብለው በተከፋይ ሚዲያዎቻቸው በኩል ስም ሲያጠፉ ከርመው በዘንድሮው (2025) አመታዊ ዝግጅት ላይ ተመሳሳይ የመግባቢያ ዋጋ እና የታዳሚው ቁጥር ተመሳሳይ ስለነበር በዝግጅቱ ላይ £100,000 ገቢ ተገኝቷል ማለት ነው ስለዚህ የፋይናንስ ሪፖርት ይፋ አለማድጋቸው የተለመደ ተግባር መሆኑን ይታወቃል።
በ2022 ዓመታዊ ዝግጅት ብቻ በአቶ ተሾመ አለሙ መሪነት £25,000 የተጣራ ገቢ ለድርጅቱ ገቢ መደረጉ ይታወሳል። የዚህን ያህል ትርፍ መገኘት መስራች ነን የሚሉ አካላት የ9 የዓመታት ጠቅላላ ገቢ (£8,000) ብቻ ስለሆነ በ2022 ፌስቲቫል የገባውን ገቢ ያልተዋጠላቸው እነዚህ የድርጅቱ መስራች ነን የሚሉ አካላት በአንድ አመት ፌስቲቫል ይህን ያህል ገቢ መገኘቱን ስማችን ሊጠፋ ይችላል በሚል በስራ አስኪያጁ ላይ የገንዘብ ምርመራ እንዲደረግ ከዚያም የቻሉትን የስም ማጥፋት እስከ action fraud ድረስ ሄደው ሳይበቃቸው በመጨረሻው ክስ መስርተው ከፍተኛ ፍርድ ቤት (12 September 2024) ቆመው ለ4 ሰዓታት ክርክር ከተደረገ በኋላ ለአቶ ካሳ ታደሰ፣ ነቢል ዮኑስ ፣ አለሚቱ ረታ እና አቶ ንጉስ ተመስገን ፊት ለፊት ደኛውም እንዲህ አላቸው “እናንተ የድርጅቱን ገንዘብ አክሰስ ብቻ ነው የምትፈልጉት” ብሎ ቅስማቸውን ሰብሮ አባራቸዋል።

በከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሸንፈው እንኳን ለሰላም ፣ ለአንድነት እንዲሁም ለስፖርት ቤተሰቡ ሲባል በአቶ ካሳ ታደሰ የተመራው ተሸናፊ ቡድን በ24/10/2024 አብሮ ለመስራት ስምምነት ተደረጎ የድርጅቱን ንብረት ከተረከቡ በኋላ የለመዱትን ክህደት ፈጸመው የስምምነቱ መፍረስ ምክንያት ሆነዋል።
በAugust 2024 ጀምሮ ድርጅቱን በህገ ወጥ መንገድ የያዘውም አካል ዋና ስራ አስኪያጅ ተሾመ አለሙን በድጋሚ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት በ15/10/2025 አቁመውት በካውንቲ ኮርት ለሁለተኛ ጊዜ የሽንፈት ዕዋቸውን ተጎንጭቷል። ማነው ሌባው? ማነው በፌዴሬሽኑ የዝግጅት ቀን (July 15 2024) የፌዴሬሽኑን Sumup አካውንት በራሱ የግል አካውንት login አድረጎ የመግቢያ ገንዘብ ወደ ራሱ personal account ውስጥ እንዲገባ ተደረጎ እጅ ከፍንጅ የተያዘው?

የ2022 የውስጥ ነውጥ ተከትሎ ምርመራዬን ስላላጠናቀቅኩኝ የ2023 ዝግጅት አቶ ዮሐንስ መሰለ ይምራው የሚል የመርማሪው ቡድን መሪ ነኝ የሚለው ግለሰብ ሃሳብ አቅርቦ ነገር ግን ከ2023 ዝግጅት በኋላ ምርጫ እንደሚደረግ ተናግረው (የእነርሱ ዘመን ማታለያ ወይም ሽንገላ አቅርበው) ዝግጅቱን እንዳይቋረጥ እና የስፖርት ቤተሰቡንም እንዳያዝን ሲባል የ2023 ፌስቲቫል አቶ ዮሐንስ መሰለ እንዲመራው ተደረጎ ዝግጅቱን ቀጠለ፤ ፌስቲቫሉም ተጠናቀቀ። ነገር ግን በ2023 ዝግጅት £1,000 እንኳን ለድርጅቱ ገቢ አልገባም በመሆኑም ይህንን ተከትሎ ዋና ስራ አስኪያጁን አቶ ተሾመ አለሙ ቦጋለ በ2022 ዓመታዊ ፌስቲቫል ላይ £25,000 የተጠራ ገቢ ለድርጅቱ ገቢ ያስገኘው ሰዉ ሲመረምር የቆየው ቡድን አቶ ዮሐንስ መሰለን ለድርጅቱ £1,000 እንኳን ያላሰገኘው ሰዉ እንዲመረምር ጥያቄ ቢቀርብለትም ጆሮ ዳባ አለ። ያው “ ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች” እንደሚባለው አቶ ዮሐንስ መሰለ አሁንም የ2025 ፌስቲቫል የገቢ ሪፖርት ይፋ አላደረገም።
መላው ማህበረሰቡ እና የስፖርት ቤተሰቡ እንዲረዳው የምንፈልገው ድርጅቱ ምሰረታ 2011 ጀምሮ እስከ 2019 ድረስ ፌዴሬሽኑን የመሩት አቶ ንጉስ ተመስገን፣ አቶ ዮሐንስ መሰለ እና አቶ ካሳ ታደሰ ናቸው ስለዚህ በ9 ዓመት ፌዴሬሽኑ ካዝና ውስጥ የተገኘው £8,000 ብቻ መሆኑን እንዲታወቅ እንፈልጋለን። አሁንም ከፊት ሆነው ድርጅቱን እያመሱት ያሉት እነዚሁ ሰዎች ናቸው።
በጣም የሚገርመው አሁን ድርጅቱን በጉልበት እና በህገ ወጥመንገድ የያዘው አካል የፌዴሬሽኑ የስራ አመራር ኮሚቴ በጠቅላላ ነው አግጃለሁ ብሎ አካኪ ዘራፍ ሲል የሚውለው።

በመሆኑም ከተጠያቂነት ለማምለጥ ወቅት እናጊዜ እየጠበቁ ጉዳዮችን በማድበስበስ በሽምግልና ባህል ተከልሎ የሚያልፍ ነገር እንደሌለ ማሳወቅ እንወዳለን ።

ተሾመ አለሙ ቦጋለ - ዋና ስራ አስኪያጅ
የኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በዩኬ

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Sports and Culture Federation in UK posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your organization to be the top-listed non profit organization?

Share