20/09/2023
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ባለሙያዎች እና ሀላፊዎች የክልሉ የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር እና የኣሪ ዞን ዋና ከተማ ጂንካ በሰላም ገቡ።
ጂንካ፤ መስከረም 9/2015 ዓ.ም (ኣዞመኮ)፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ባለሙያዎች እና ሀላፊዎች የክልሉ የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር ከተማ ጂንካ በሰላም ገብተዋል። የቢሮ ሠራተኞች ወደ ጂንካ ከተማ ሲገቡ የኣሪ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ አብርሃም አታ፣ የጂንካ ከተማ ከንቲባ አስፋው ዶሪ እና ሌሎች የዞኑ እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች አቀባበል አድርገዋል።
እንግዶችን ተቀብለው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኣሪ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ አብርሃም አታ፤ የኣሪ ዞን መቀመጫ ከተማ ጂንካ ህብረብሔራዊት እና ፍጹም ሰላማዊ ከተማ መሆኗን ጠቅሰው መልዕክት አስተላልፈዋል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ የፋይናንስ እና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታምሩ ከዚህ ቀደም የጂንካ ከተማን የሚያውቁ እንደሆነ በመጥቀስ ከቢሮ ሰራተኞች ጋር ተዋውቀው የክልል ሰራተኞችን በማስተባበር ስሰሩ የቆዩ ኮሚቴዎች እና ከጂንካ ከተማ ኮሚቴዎች ጋር በመሆን ለሰራተኞች ማረፊያ የማመቻቸት ስራ እንደሚከናወን ገልጸዋል።
በስተመጨረሻም የኣሪ ዞን የሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ማታዶ በርቢ እንግዶች ምናልባት ያልታሰበ ችግር ከገጠማቸው በ 0467750036 ወይም 0928738371 በቀጥታ ለዞኑ ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ በመደወል ጥቆማ ማድረስ የምችሉ መሆኑን ገልጸዋል።
Ussa laq'mi h'adetee
እንኳን ደህና መጣችሁ፤
"እውነኛ እና ትክክለኛ መረጃ ለዘላቂ ልማት እና ዕድገት"
በሁሉም የትስስር ገጾቻችን ቤተሰብ ይሁኑ
Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61551460769490
Telegram: https://t.me/aarizonecommunicationaffairs
Twitter: https://x.com/
Email: [email protected]