Spreading Hope

Spreading Hope this is non profit organization and youth peer group for humanitarian activities

13/03/2026
ጫማ ጠራጊው ሙሳ  ሰምኑን ሜቄዶኒያ ወደተባለችው ሀገር ተጉዤ ዋና ከተማዋ ስኮፒዬን እየጎበኘሁ በሀውልቶች የተከበበችው ይህቺ ከተማ ላይ ይህንን የጫማ ጠራጊ ሀውልት አይቼ ቀልቤን ስቦት ወደ ...
06/01/2026

ጫማ ጠራጊው ሙሳ

ሰምኑን ሜቄዶኒያ ወደተባለችው ሀገር ተጉዤ ዋና ከተማዋ ስኮፒዬን እየጎበኘሁ በሀውልቶች የተከበበችው ይህቺ ከተማ ላይ ይህንን የጫማ ጠራጊ ሀውልት አይቼ ቀልቤን ስቦት ወደ ሀውልቱ ተጠጋሁ ሀውልቱ ሙሳ የተባለ በከተማዋ ይኖር የነበረ ጫማ ጠራጊ ነበረ። ከሁሉም ጋር ተግባቢ ተወዳጅ ከ 30 አመት በላይ በከተማዋ የኖረ እንደሆነ አስጎብኚዬ ነገረኝ። " እኛ ሀገር ምሁሩ ፖለቲከኛው እና ተዋጊው ብቻ አይደለም እኮ ሁሉም ሰው የራሱ ታሪክ አለው" አለኝ። እውነት ነው ሁሉም የራሱ ታሪክ አለው።

ጫማ ጠራጊውም ታሪክ አለው ስንቱ ወደ እጮኛው ሲሄድ ጫማውን አሳምሮ ሸኝቷል ስንቱ ሀላፊ ወደ ቢሮው ሲገባ ጫማውን አስውቧል የስንቱን ጫማ ሰፍቷል በስንቱ ተመስግኗል። ስንት የተበሳጨ ሰው ጫማ እያስጠረገ ብሶቱን ነግሮታል ስንቱ በንቀት አይቶታል ስንቱ አባሮታል ስንቱን አመስግኗል ብዙ ብዙ ሁሉም ታሪክ አለው። ሀገረ ሜቄዶኒያ በዋና ከተማዋ ስኮፒዬ የተመሰገነውን ተወዳጁን ሙሳ በህይወት ባይኖርም እንደ ምልክት በማድረግ ጫማ ጠራጊዎችን ሁሉ የሚወክል ይህንን ሀውልት አቁማለች ።

ብዙ ሀገራት ተጉዣለሁ በሺ የሚቆጠሩ ሀውልቶች አይቻለሁ ሁሉም ማለት በሚያስደፍር ሁኔታ መሪዎችን ተዋጊዎችን ታሪካዊ ክስተትን የሚዘክሩ ናቸው። ይህንን ስመለከት ታዋቂው አሜሪካዊ ጸሐፊና አስተማሪ ቡከር ቲ የተናገራት ትዝ አለቺኝ "ግጥም በመጻፍ በመዋጋት ሀገራ በመምራት ውስጥ እንዳለው ሁሉ በማንኛውም የጉልበት ሥራ ውስጥም እኩል ክብር እንዳለ እስካልተረዳን ድረስ እንደ ሕዝብ መቆም አንችልም።" እውነት ነው እንደ ሙሳ የሰፈራችን ድምቀት የሆኑ ስንት ሰዎች አሉ ብዙ ።

አመሰግናለሁ!
አቤል ብርሀኑ (የወይኗ ልጅ)
የጉዞ ማስታወሻዬ
ሰሜን ሜቄዶኒያ 2018 ዓ.ም

21/12/2025
31/12/2024
ልብህ ንፁ ይሁን ነገን ትወርሳለህ❤❤❤
23/10/2024

ልብህ ንፁ ይሁን ነገን ትወርሳለህ❤❤❤

61.2K likes, 1492 comments. “አካውንቴ ተመቷል ሼር አድርጉት ውዶችዬ ”

"ዶሳይስ" መጽሐፍን  ያላገኝፕ ያግኛት “ዶሳይስ” ከደራሲና ገጣሚ ኩሪ አየለ ኃይሌ ከሰሞኑ ለአንባቢያን የቀረበ ምርጥ የመጽሐፍ ጦማር ነው። ከዚህ ቀደም የግጥም መድብሏን ጨምሮ ሁለት መጻሕፍ...
26/07/2024

"ዶሳይስ" መጽሐፍን ያላገኝፕ ያግኛት

“ዶሳይስ” ከደራሲና ገጣሚ ኩሪ አየለ ኃይሌ ከሰሞኑ ለአንባቢያን የቀረበ ምርጥ የመጽሐፍ ጦማር ነው። ከዚህ ቀደም የግጥም መድብሏን ጨምሮ ሁለት መጻሕፍትን ያበረከተችልን ደራሲዋ ለሦስተኛው በዶሳይስ መጥታለች።

የአሁኑ ዶሳይስ መጽሐፏ በአጫጭር ልቦለዶች ታሪክ ተሰባጥሮ የቀረበ ባለ ብዙ የሀሳብ ጅማት ነው። ማኅበራዊ ማኅብረሰብ፣ ሀገራዊ ሀገርና ሕዝብን ጨብጦ የያዘ የንቃት መንገድና መንገደኛም ነው።
በማኅበረሰባችን ውስጥ ያሉትን ህጸጾች በተለያዩ መንገዶች እየነቀሰ የመመለሻውን ፍኖት ያንጸባርቃል። ምናልባትም የደራሲዋን ውስጣዊ ስብዕናና የአመለካከት ጮራዎቿን የሚፈነጥቅም ዓይነት ነው። በቅርቧ ሆኖ የሚያውቃት አንድ አንባቢ ምናልባትም ከእርሷ ጋር እያወጋ ያለ ያህል መስሎ ሊሰማው ይችላል። የምረቃ ስነ ስርዓቱ ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 በብሔራዊ የቲያትር አዳራሽ ውስጥ በጉምቱ የጥበብ ባለሙያዎችም ተመርቋል።

ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ የተወሰደ
****

‹‹ዶሳይስ›› አሁን በመነበብ ላይ፡፡ከረምቱ ‹‹ከዶሳይስ›› ጋር ---፡ የት እናግኛት የምትሉ

1/ Addis Ababa University Book Center- አዲስ አበባ ዩነቨርስቲ ውስጥ
2/ ኢማና- የመጽሐፍት ማዕከል ፡- ጌት ኮሜርሺያል የገበያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ -ሜክሲኮ
3/ ጃፋር- የመጻሐፍት ማዕከል:-ሜክሲኮ እና አራት ኪሎ
4/ ዓይናለም የመጽሐፍ መደብር ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ጎን
5/ ሀሁ- የመጽሐፍ መደብር-ሜክሲኮ -ደብረወርቅ ህንጻ -ከቡና እና ሻዪ ፊትለፊት እና አራት ኪሎ
6/ ኮሜርሺያል- መጽሐፍ መደብር-ሜክሲኮ

**********//**********
የ ‹‹ዶሳይስ ›› የመጽሐፉ ብርቱ ገጽታዎች ….
በየሻው ተሰማ (የኮተቤው፤ በሥነጽሑፍ ረዳት ፕሮፌሰር)
>
የሻው ተሰማ (የኮተቤው፤ በሥነጽሑፍ ረዳት ፕሮፌሰር) ከሰጡት አስተያየት ተቀንጭቦ የተወሰደ
* **

23/07/2024
Exactly I am an eye witness
07/07/2024

Exactly I am an eye witness

የራዲዮሎጂ ስፔሻሊስት ዶ/ር ቤቴልም ገርማሞ ጋኔቦ ህይወትን እንታደግ😭ዶ/ር ቤቴ የደም ካንሰር (leukemia )በሽታ የተገኝባት ስለሆነ የጥቁር አንበሳ ሜዲካል ቦርድ አፋጣኝ የሆነ የመቅኔ ...
30/04/2024

የራዲዮሎጂ ስፔሻሊስት ዶ/ር ቤቴልም ገርማሞ ጋኔቦ ህይወትን እንታደግ😭

ዶ/ር ቤቴ የደም ካንሰር (leukemia )በሽታ የተገኝባት ስለሆነ የጥቁር አንበሳ ሜዲካል ቦርድ አፋጣኝ የሆነ የመቅኔ ንቅለ ተከላ (Bone Marrow Transplant) ከሀገር ውጭ እንዲደረግላት ወስኗል።

ስለዚህ አቅማችን የፈቀደውን በማድረግ የዶ/ር ቤቴን ህይወት እንታደግ
CBE-1000105102384 Bethel Germamo Ganebo
1000156496317-Mengistu Tumea Madalcho
Dashen-2939236369311- mengistu Tumea madalcho

17/03/2024

በዎላይታ ዞን "ያለልዩነት የተነሳውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ይደግፋሉ" የተባሉ ግለሰቦች እየታሰሩ ስለመሆኑ ተገለፀ።

የዜጎች ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ ተፈጥሯዊና ህገመንግስታዊ መብት ተጠቅሞ በዎላይታ ዞን ውስጥ የሚስተዋለውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መናገር፣ መንግስታዊ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ማጋለጥ እንዲሁም በአከባቢው መንግስታዊ መዋቅር በአቤ-ልጅ ኔትወርክና ጥቅም ላይ መመስረቱን በተመለከተ በአሁኑ ወቅት ያለልዩነት የተነሳውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ይፋ ለማድረግ የሚሞክሩና በእንቅስቃሴው ተሳትፈው አላቸው የተባሉ ግለሰቦች ከያሉበት ያለምንም ህጋዊ መጥሪያና አሰራር እየታሰሩ ስለመሆኑ ከየስፍራው የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ወጣቶቹና የመብት ተሟጋቾች የጅምላ እስራትና አፈሳ ለቤተሰቦቻቸው ጭምር እንዳይነገር ተብሎ በማስፈራራት በአረካ፣ ክንዶ ኮይሻ፣ ዳሞት ወይዴ፣ ሶዶ፣ ቦዲቲ ከተማ እንዲሁም ሌሎች መዋቅሮች ላይ የተጀመረ ሲሆን አንዳንድ የታሰሩ ግለሰቦች የሚያርፉበት እስርቤት ከመደበኛ ፓሊስ ጣቢያ ውጪ ስለመሆኑም ከአይን እማኞችና በአከባቢው ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል ምንጭ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያስረዳው።

በትናንትናው ዕለት "ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና" በሚል መሪህ ቃል በዞኑ በሁሉም ቀበሌዎች በተካሄደው ህዝባዊ ኮንፈረንስ ላይ አባላቱ የዎላይታ ህዝብ በሌብነትና በጥቅም ትስስር በተደራጀው ኔትወርክ ምክንያት ከፍተኛ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እጦት እንዲሁም በደል እየደረሰበት በመሆኑ በዞኑ "ፓርቲያችን ከሚከተለው ዕሳቤና አሰራር ውጭ የተዘረጋው መዋቅር በአስቸኳይ እንዲፈርስ፤ በአስናዋሪ ድርጊታችሁ በመንግስት ላይ እምነት ለመጣል እንኳን እየተቸገርን ነውና የፓርቲውንም መልካም ስም የሚያጎድፍ የግለሰቦች ኔትወርክ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ እርምት እርምጃ እንዲወስድ" በሚል የዎላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አባላት ያለልዩነት በይፋ መጠየቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በተቃራኒው በአከባቢው ባልተለመደ ሁኔታ አባላት ጠንከር ያለ ትችትና ቅሬታ በተለይም የዎላይታ አመራር ምደባ ስርዓት ብልጽግና ፓርቲ ከሚከተለው ዕሳቤና አሰራር ውጭ ዞኑ ለተለያዩ ችግሮች ስለመጋለጡ ተጨባጭ ማብራሪያ በማሰማታቸው አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከኮንፈራንስ አዳራሽ በማውጣት ማሳር፣ ማስፈራሪያና ዛቻ ማድረግ እንዲሁም በአመራሮችና ፀጥታ አካላት ተገደው ይቅርታ ጠይቀው ከእንደገና ለተሰበሰቡ አባላት "ባለፉት ጊዜ በአካባቢያችን አስደማሚ ለውጥ ተመዝግቧል" ብለው እንዲያወሩ ከማድረጋቸው ባሻገር በዛሬው ዕለት ደግም "ለምን እንደዛ ተናገራችሁ ? " ተብሎ እስርና እንግልት እየደረሰባቸው ስለመሆኑ ከተለያዩ ምንጮች እየደረሰ የሚገኘው መረጃ ያመለክታል።

የዎላይታ ዞን ከየትኛውም አከባቢ በላይ ሚዲያዎች፣ ህዝብ ውግንና ያላቸው አመራሮች፣ የመብት ተሟጋቾች እንዲሁም ወጣቶች ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ ተፈጥሯዊ እና ህጋዊ መብት ተጠቅመው በአከባቢው የሚስተዋሉ መንግስታዊ አሰራርና ብልሽት ላይ በሰላማዊ መንገድ ትችት በሚያደርጉበት ወቅት በህገወጥ መንገድ በማፈን፣ በማሰር፣ ያለጥፋታቸው ፍርድቤት እንዲመላለሱ በማድረግ እንዲሁም በስደት ከአከባቢው እንዲሸሹ የሚያስገድድ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለፃችን ይታወሳል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በአከባቢው ዜጎች ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ ተፈጥሯዊና ህገመንግስታዊ መብት ተጠቅሞ ህገወጥ አደረጃጀትን ለመታገል በአሁኑ ወቅት ያለልዩነት የተነሳውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ላይ ለመሳተፍ በሚሞክሩ ግለሰቦች ላይ የሚደርሰውን የትኛውንም ጫና እንዲሁም አጠቃላይ ሂደት በተመለከተ ተከታትሎ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ሰፊ ሽፋን የሚሰጥ ሲሆን የትኛውም ጠቃሚ ጥቆማዎች ካሉ ማድረስ እንደሚቻልም በዚህ አጋጣሚ እንገልፃለን። Wolaita Times

17/03/2024

በአንድ ሰፈርና ጥቅም ተጋሪዎች እየተመራ የሚገኘው የመላው ዎላይታ ህዝብ ማህበር ቀጣይ ሳምንት ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚያካሂድ ተገለፀ።

የህዝብ ውግንና ባላቸው ግለሰቦች ተመስርተው የመላው ህዝብ ኩራት የነበረው የዎላይታ ልማት ማህበር 23ኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤ በመጭው ቅዳሜ መጋቢት 14/2016 ዓ.ም እንደሚያካሄድ ተነግሯል።

ልማት ማህበሩ በአዲስ መልክ ከተቋቋመበት ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ከመላው ዎላይታ ህዝብ፣ ከአባለት በሚሰበሰብ ሀብት፣ ከረጂ ድርጅቶች በሚያገኘው ድጋፍና ከገቢ ማስገኛ ተቋማት በሚሰበስበው ገቢ በዞኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ ያሳረፈው አሻራ እጅግ በጣም የሚደነቅና ለሌሎች አከባቢ ልማት ማህበራትም ተምሳሌት እየሆነ የመጣ በአጭር ጊዜ ተቋቁመው ውጤታማ የሆነ የሚሊዮኖች ሀብትና ኩራት ቢሆንም አሁን አሁን የፓለቲካ ማሽን የሌቦች ዋሻ በመሆን የተጀመረውን ዋና መስሪያቤት ህንፃ ግንባታ በሙስና በጅምር በማቆም ለሰራተኞቹ እንኳን ደሞዝ በጊዜ ለመክፈል እየተቸገረ ስለመሆኑ ማህበሩን በቅርበት የሚያውቅ ምንጭ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድቷል።

በአሁኑ ወቅት በማህበሩ ስር የሚመሩ በርካታ ዳሞታ ኮንስትራክሽን ጨምረው ያሉት በተዋቀረው በሌብነት፣ በአከባቢያዊና ጥቅም አደረጃጀት፣ በተሰራው ሴራ የአባላት ድጋፍና እምነት ማነስ፣ ከዚህ በፊት የሚሰሩ አጋር ድርጅቶች መቀነስ እንዲሁሂ ልምድና እውቀት ያላቸው ሰዎች ተገፍተው ከማህበሩ መልቀቅ ምክንያት እንደ ከ1970ዎቹ ጀምሮ እስከ 1993 ዓ.ም በማህበሩ የተደቀነው አይነት በአንድ ሰፈር ልጆች እንዲመራ ተደርጎ ህዝቡ "ማህበሩ የሁሉም አይደለም" በሚል ድጋፍ እንዲያቆም ድብቅ ሴራ በመኖሩ የመፍረስ አደጋ እንደተጋረጠበትም አክሎ ጠቁሟል።

"አንጋፋው የዎላይታ ልማት ማህበር በሰው ሀብት ልማት፣ በዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ፣ በትምህርት እና በተቀናጀ ጤና የትኩረት አቅጣጫ ዘርፎች በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች ከራሳቸው በላይ ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ በሚሰጡ ታታሪ አመራሮችና ሰራተኞች ተዋቅሮ የመላው ህዝብ ኩራት የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ያ አመራርና አብዛኞቹ ሰራተኞች እንዲወጡ በማድረግ እስከ ቦርድ ሰብሳቢ ድረስ በአንድ ሰፈር፣ ትውውቅና ጥቅም እንዲደራጅ በመደረጉ ልማት ማህበሩ የነበረውን ግርማ ሞጎስ እያጣ ነውና ብቸኛው የህዝብ ሀብት የሆነውን ለመታደግ ሁሉም ዎላይታ ያለልዩነት መረባረብ እንዳለበት" ጥሪ አቅርቧል።

ማህበሩ ከ1957 ዓ.ም ጀምሮ በዎላይታ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ተሰማርቶ አያሌ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ከቆየ በኋላ ከ1970ዎቹ ጀምሮ እስከ 1993 ዓ.ም ባለው ጊዜ አሁን ላይ በማህበሩ የተደቀነው አይነት በአንድ ሰፈር ልጆች እንዲመራ ተደርጎ ህዝቡ ማህበሩ የሁሉም እንዳይልና ድጋፍ እንዲያቆም ድብቅ ሴራ በመኖሩ፣ ለልማት የሚሰበሰብ ገንዘብ ግለሰቦች ተከፋፍለው ስለበሉ እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች በማህበሩ ላይ ህዝቡ የእኔነት ስሜት እንዲያጠፋ በመደረጉ ተዘግቶና ተዳክሞ የቆየ ቢሆንም ያለልዩነት ከሁሉም አከባቢዎች የመላውን ህዝብ ጥቅም መነሻ ባደረገ መንገድ የተሰባሰቡ የህዝብ ልጆች በ1993 ዓ.ም ዳግም በአዲስ መልክ እንዲዋቀር በማድረግ ስራውን ጀምሮ በአጭር ጊዜ አስደማሚ ለውጦችን ማስመዝገቡን በርካቶች ይመሰክራሉ።

ባለቤትነቱ የመላው ህዝብ የሆነው ማህበሩ የዘንድሮውን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ከላይ የተዘረዘሩ ጥቂት ግለሰቦች የፈጠሩት ዘርፈብዙ ችግሮች ጫናና የመፍረስ አደጋ በተጋረጠበት በዚሁ ወቅት ለ23ኛ ጊዜ ከፌደራል ጀምሮ በተለያዩ የመንግስት መዋቅሮች ያሉ የልማት ማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች፣ ከልማት ማህበሩ ጋር የሚሰሩ አጋር ድርጅቶች ተወካዮች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በቀጣዩ ቅዳሜ 14 መጋቢት 2016 ዓ.ም በዎላይታ ሶዶ ከተማ ጉተራ አዳራሽ እንደሚያካሂድ ከስፍራው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል። Wolaita Times

Address

Wolaita S**o
S**o

Telephone

+251465513074

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Spreading Hope posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share