Wolayta 888

Wolayta 888 Latitude 6° 51' 36" (6.86°) North
Longitude 37° 45' 41.7" (37.7616°) East
Average elevation 2,045 meters (6,709 fee

14/01/2026

እንግሊዘኛ ቋንቋ ዕውቀት ያለው colonized.
እንግሊዘኛ ቋንቋ ዕውቀት የሌለው uncolonized.
የተኛው ጥሩ ነው ቤተሰብ?

13/01/2026

የወላይታ ማህበረሰብ ከ 8,000 ዓመት በፊት የነበረ ማህበረሰብ ነው።።

23/11/2025

የሰሞኑ ወላይታ ሶዶ ከተማ ማሪያም ቤተክርስቲያን አጥር ጩህት በአንድ ሃይማኖት ሲበዛ ጠርጥረናል። አላማው ልማት ፍለጋ ሳይሆን ፀረ ልማት ኃይሎች እና ኦርቶዶክስ ጥላቻ እንደሆነ ያስታውቃል። በሀሰተኛ ምስል የቤተክርስቲያን አጥር ገፊዎች እጃችሁን አንሱ።

የጦር መሳሪያ ዝውውር ከደቡብ እስከ ሰሜንመቶ አለቃ መልካሙ እዮኤል ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ንግድና  ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዝውውር ከደቡብ እስከ ሰሜን የብልፅግናን መንግሥት ለመጣል ...
09/10/2025

የጦር መሳሪያ ዝውውር ከደቡብ እስከ ሰሜን

መቶ አለቃ መልካሙ እዮኤል ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ንግድና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዝውውር ከደቡብ እስከ ሰሜን የብልፅግናን መንግሥት ለመጣል በሰፊው ከሚያከናወኑት ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው።

መቶ-አለቃ መልካሙ እዮኤል በህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ንግድ ላይ ተሰማርቶ ከብላቴ የማሰልጠኛ ጣቢያ ወታደሮች እንዲኮበልሉ እያደረገ እና ከወለይታ ሶዶ ክ/ከተማ ህገወጥ መታወቂያ ለወታደሮች እያሰወጣ የጦር መሳሪያዎች በቀላሉ መገኘትና የህብረተሰቡ ጦር መሳሪያ የመታጠቅ ፍላጎት እያሟላ ይገኛል።

ከመቶ-አለቃ መልካሙ እዮኤል ጋር የአገሪቱን መረጋጋት የማይፈልጉ ሃይሎች በዚህ ዝውውር ውስጥ አሉበት። የቁጥጥር ማነስ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በስፋት እንዲስፋፋ እያደረገ ነው፡፡

በወለይታ ዞን እና አጎራባች ዞናች ላይ ከህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ጋር በተያያዘም ወንጀሎች እየተሰሩ ስለመሆናቸውም ነው ህብረተሰቡ የሚገልጸው፡፡ ከመቶ-አለቃ መልካሙ እዮኤል ከዚህ ቀደም የኢሐዴግ ሰላይ መሆኑንና በፎረጂ ትመህርት ማሰረጃ እንደሚሰራ መዘንጋት የለበትም።

መቶ-አለቃ መልካሙ እዮኤል በህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ንግድ ላይ ተሰማርቶ ከብላቴ የማሰልጠኛ ጣቢያ ወታደሮች እንዲኮበልሉ እያደረገ እና ከወለይታ ሶዶ ክ/ከተማ ህገወጥ መታወቂያ ለወታደሮች እያሰወጣ የጦር መሳሪያዎች በቀላሉ መገኘትና የህብረተሰቡ ጦር መሳሪያ የመታጠቅ ፍላጎት እያሟላ ይገኛል።

10/08/2025
08/08/2025

የደቡብ ክልልል ሁለቱ መንቲያ አጆራ ፏፏቴዎች

08/06/2025

ያም ሆነ ይህ ዋንጫው የድቻ ነው። ወላይታ ዲቻ 4:0 ሲዳማ ቡና

08/06/2025

ዓለም 120.000 ደጋፊዎችን የሚያዝ ስታዲየም ሰርቶ ካለምንም ኮሽታ ታላላቅ የእግርኳስ ሁነቶችን አስተናግዶ በሰላም ይቋጫል፥ እኔ ሀገር ግን መዲናዋ የእግርኳስ ደዌ ተጠቂ ሆና እንድትቀር ይመስል ከኳስና ተመልካች ተኳርፋ ዓመታት ሄደዋል።

የአንድን ሀገር እግርኳስ በበላይነት የሚመራ አካል እንዴት ምንም አይነት የሽብር እንቅስቃሴ ሳይሸተው፥ ኳሱን የሚያስተጓጉሉ ፈታኝ ክስተቶች ሳያጋጥሙት ከምንም ተነስቶ ኋላቀርና ምክንያት አልባ በሆነች "ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት" በምትል ቃል የደጋፊዎች ሞራል ላይ ውሃ ይቸልስበታል?😏😏

ወላይታ ዲቻና ሲዳማ ቡና ነውጠኛ ደጋፊዎችን በውስጣቸው ይዘው የሚገዳደሉ ክለቦች አይደሉም በርካታ መሸናነፎችን አይተው አሳልፈዋል ከ9ዐደቂቃ ውጤት በኋላ ደጋፊዎቻቸው ወደየጉዳያቸው ሲያመሩ ነው ያየነው የምን ከንቱ ስጋት ፈጥራችሁ ነው ኳስ የሚያቀነጭር የኋልዮሽ ዳዴ የጀመራችሁት?

በተለያዩ ከተማዎች የሚደረጉ ብዙ ዓይነት ውድድሮች በተሳካ መልኩ ፍፃሜያቸውን በሚያገኙበት ሃገር እንዴት ሃገር አምና የአስተዳደር ቁንጮ ላይ ያስቀመጠችው አካል ባንኩም ታንኩም በእጁ ሆኖ በቂ የፀጥታ አስከባሪ ሃይላትን መድቦ መርሃግብሩን ማስፈፀም እየቻለ ህዝብ ከመናቅ በመነጨ ውሳኔ ያውም ውድድሩ ከመካሄዱ 48ሰዓታት በፊት ማሳወቅ እያለበት የረፈደ ውሳኔውን በውድቅት ሌሊት ይወስናል?

የሸገር ደርቢዎቹ የኢት/ያ ቡናና የቅዱስጊዮርጊስ ህመም አሁን ይመመን ደርቢዎቹ ከተማቸው ላይ ሳይጫወቱ ዓመታት ተቆጥረዋል ምናልባት የነሱ ቁጭት እንዲቆጨን በሌላ መንገድ የተዘረጋልን ጥሩ አጋጣሚ ቢሆንስ?

ዓለም ዓቀፍ ቢሮዎች፥ የዲፕሎማቶች መቀመጫ፥ የቆንፅላ ፅ/ቤቶች መገኛ፥ የአፍሪካ ርዕሰ-መዲና፥ ቀደምትና አንጋፋ ከተማ፥ ከከተማነት ልቃ ሜትሮፖሊታን የሚል ማዕረግን የተጎናፀፈች አዲስአበባችን ሰላሳ ሺህ ህዝብ በቅጡ የማይሸክም ስታዲየም ላይ የሚካሄድን የፍፃሜ ውድድር ማስተናገድ እንዴት ያቅታታል?

በባሌም በቦሌም ብሎ ይሄ ክስተት ያቃጠረን አንድ እውነት አለ "እግርኳሱ ሊመሯት አቅም በሌላቸው ደካሞች እጅ ስር ወድቃለች"

ለመሆኑ የሰው ልጅ ሞራል ቢሸጥ ስንት ያወጣል? ከወራት በፊት ይሄን ፍፃሜ ቋምጠው የሚጠብቁ የሁለቱን ክለብ ደጋፊዎች እንጀራቸውን፥ ቤተሰቦቻቸውን፥ ሃብትና ንብረታቸውን ትተው ለኳሱ አዲስ ላይ ለፍፃሜው ከመሸጉ በኋላ "ዕቃቃ ፈረሰ፥ዳቦ ተቆረሰ" አይነት የልጅ ጨዋታ "ዝግ ስታዲየም የምትል የፈሪዎች ውስጠ ወይራ ቃል አድበስብሶ ማለፍ በውኑ ለኋላፊነታችሁስ ይመጥነዋልን?

በሉ እንግዲህ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያታችሁ ዝግ ስታዲየምን ውሳኔያችሁ ካደረጋችሁ የደጋፊዎችን

👉የትራንስፖርት ወጪ
👉የምግብና የአልጋ ወጪ
👉የውሎ አበል
👉በምንም ሂሳብ ልትከፍሉት የማትችሉትን የሞራል ካሳ ክፍያ ክፈሏቸው።

የሁለቱም ክለብ ደጋፊዎች ሸገር ድረስ ተጉዘው ክለባቸውን ሊደግፉ የተጓዙት መሄጃ ስላጡ ወይም ስራ ፈት ስለሆኑ አልነበረም በቃ ታስጠላላችሁ😏😏

ህዝብ አትናቁ ከትንንሽ መሰረተ ልማቶች እስከ ሀገር አቀፍ ታላላቅ ግንባታዎች ድረስ ካለ ህዝብ የናንተን አቅም ታውቁታላችሁና በግብርና መዋጮ ለምታሳብዱት ህዝብ ክብርና ሞራል ተጨነቁለት። ህዝብ የናቀ መንግስት ፍፃሜው ከናቡከደነፆር የተሻለ አይሆንምና።

ሀገሬ ለእግርኳሷ ትንሳኤ የሚዋደቁላትን አመራሮች እስክታገኝ ስንት ዓመታት ይፈጅባት ይሆን???

ለሰላማዊ እግርኳሳዊ ጦርነት የተሰደዱ የሁለቱን ደጋፊዎች የሞራል ካሳ የሚከፍል "እኔ ነኝ ተጠያቂው" የሚል አመራር የዛሬ ስንት ዓመት ይኖረን ይሆን???

በ ቼቼ ጳውሎስ

Address

S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolayta 888 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share