Boditti Times 360

Boditti Times 360 Mind set; to spread Positive vibe for humanbeing and to let them logical for decision

እንኳን ደስ አላችሁ የድቻ ደጋፊዎችየ2024/25 የናይጄርያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ወላይታ ድቻን ለመቀላቀል ከስምምነት ደረሰ።በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በአልጄርያው ክለብ ጄኤስ...
12/08/2026

እንኳን ደስ አላችሁ የድቻ ደጋፊዎች

የ2024/25 የናይጄርያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ወላይታ ድቻን ለመቀላቀል ከስምምነት ደረሰ።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በአልጄርያው ክለብ ጄኤስ ሳውራ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ በሀገሩ ክለቦች ናሳራዋ እና ዊኪ ቱሪስትስ መጫወት የቻለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ከ23 ዓመት በታች እና ዋናውን የናይጄርያ ብሔራዊ ቡድን አገልግሎ በቻን አፍሪካ ዋንጫ መሳተፍ ችሏል።

የዘመናት የጎል ጥማታችን ሊረካ ነው👍

😂 ልጅትዬ፣ ነገሩን አበላሽተሽዋል! 😅🔥
11/08/2026

😂 ልጅትዬ፣ ነገሩን አበላሽተሽዋል! 😅🔥

ያኔ በደጉ ጊዜበ10 ሳንቲም ምን ገዛችሁ ❓
09/08/2026

ያኔ በደጉ ጊዜ
በ10 ሳንቲም ምን ገዛችሁ ❓

‎ውስብስብ ሀገራዊ ፈተናዎችን እና ዘላቂ መፍትሔ የሚሹ ጉዳዮችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ታስቦ የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር እነሆ ዛሬ በየ500 ቡድን የመጨረሻ ምክረ ሀሳብ ቀርቦ በማጠቃለያ ...
08/08/2026

‎ውስብስብ ሀገራዊ ፈተናዎችን እና ዘላቂ መፍትሔ የሚሹ ጉዳዮችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ታስቦ የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር እነሆ ዛሬ በየ500 ቡድን የመጨረሻ ምክረ ሀሳብ ቀርቦ በማጠቃለያ 4000 ላይ ለውሳኔ የሚቀርቡ ለቀጣይ ትውልድ ዘላቂ የመፍትሄ ሀሳብ እንድሆን እኛም በየቡድናችን ጠንካራ የሀሳብ መግት በማድረግ የሕዝባችንን አንገብጋቢ አጀንዳዎችን ከኢትዮጵያ ሀገራችን መጻኢ ዕድል ጋር እንድታይ በአጽኖት አስመዘግበናል ..💪

‎ከአጀንዳዎች መኃል እነዚህን በዋናነት አስመዘግበናል👇

‎1. ☞ ታላቁ የዎላይታ ሕዝብ ለሀገር ግንባታ ባለፉት ጊዜያቶች ለሀገርቱ አንድነት፥ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ የከፈለው ውድ ዋጋ አንጻር የሕዝባችን ታርክ በኢትዮጵያ ታርክ ውስጥ በተገቢይው አልተቀመጠምና በቀጣይ በሚዘጋጀው በጋራ ኢትዮጵያ ታሪክ ላይ የሕዝባችን ታርክ በጉልህ እንዲመዘገብ በ500 ቡድን አጽድቀን ለማጠቃለያው ለ4000 ብድን አሸጋግረናል።

‎2. ☞ ከደቡብ እስከ ሞያሌ በከፍል የሚደመጥ ቋንቋችን #ዎላይትኛን ስድስተኛ የሀገሪቱ የሥራ ቋንቋ እንድሆን አጄንዳ አስዘናል፤

‎3. ☞ ኢ_ህገመንግስታዊ በሆነ መንገድ የተነጠቅነውን ዎላይታ ብሔራዉ ክልላዊ መንግስትን የመመስረት መብት በመሆኑ ለታላቁ ዎላይታ ህዝብ መብቱ ልከበርለት ይገባል።

‎4. ☞ ለአራት /ለ4 አመታት በመዋቅራዊ ሴራ በዎላይታ ህዝብ እየደረሰ ያለው ኢ-ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል፣ ኢ-ፍታሃዊ የፖለቲካና የማህበራዊ ውክልና በአስቾካይ ቆሞ በሁሉም ዘርፍ ትክክለኛ ፍታሃዊነት በተገቢይው ይረጋገጥ።

‎5. ☞ በተለያዩ ኃላፊነት ደረጃ ላይ እያሉ የህዝብን ውስን ሀብት እና የመንግስትን በጀትን በተደራጀ ሌብነት በማጥፋት ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲማረር በሚያደርጉ ባለስልጣናት ላይ የተጠናከረ ክትትልና አስተማሪ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ በዋናነት በምክክሩ ካስመዘገብናቸው እና ወደ ቀጣዩ መጨረሻ ዙር ካሸጋገርናቸው አጀንዳዎች አንኳሮች ናቸው።


‎ #ማሳሰቢያ፦ ይህ የዛሬ ለዛውም የአሁኑ በመሆኑ ዶ/ር ወልደማሪያም ሊሳኑ ታስሯል የሚባለው የሟርት መረጃ አሉባልታ በመሆኑ በዚህ አጋጣም እንድታውቁ ጭምር እናሳስባለን 🤓

 :- ‎ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም. የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከፍተኛ ዉጤት በማስመዝገብ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቀዳሚነቱን አስጠበቀ‎-------------------------...
04/08/2026

:- ‎ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም. የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከፍተኛ ዉጤት በማስመዝገብ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቀዳሚነቱን አስጠበቀ
‎-------------------------------------
‎ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም. የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉ ትምህርት ቤቶች መካከል የቀዳሚነት ደረጃዉን አስጠብቋል።

‎ትምህርት ቤቱ ለ2018 ዓ.ም. ክልላዊ ፈተና ያቀረባቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ በማሳለፍ 100% የማለፍ ውጤት አስመዝግቧል። በዚህም መሠረት በአራቱም ማዕከላት (ወላይታ ሶዶ፣ ቦዲቲ፣ አረካና ገሱባ) ለፈተና የቀረቡት 180 ተማሪዎች በሙሉ ወደ 9ኛ ክፍል ለመሸጋገር በቅተዋል።

‎ይህ ውጤት በልማት ማህበሩ ቁርጠኝነት፣ በትምህርት ቤቱ ጠንካራ የትምህርት አመራር፣ በመምህራን ትጋት፣ በተማሪዎች ጥረት እንዲሁም በወላጆች ተሳትፎ የተገኘ ውጤት ነዉ።

‎ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤቶች በደ/ኢትዮጵያ ክልል ከ1ኛ እስከ 9ኛ ካሉት ከፍተኛ ዉጤት ካስመዘገቡት ተማሪዎች ውስጥ በቁጥር ስምንት ተማሪዎችን አስገብተዋል፤ ከነዚህም በአንደኛ ደረጃ ያለዉ የትምህርት ቤቱ ተማሪ ነዉ።

‎በተጨማሪም ትምህርት ቤቱ በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ያስመዘገበውን የቀዳሚነት ክብር እስካሁን ለሌላ ትምህርት ቤት አሳልፎ አልሰጠም።
‎ይህም ትምህርት ቤቱ በተከታታይ ዓመታት የላቀ የትምህርት ጥራትና ውጤታማነት እያሳየ መሆኑን ያረጋግጣል።

‎ወላይታ ልማት ማህበር ለዚህ ክብር አስተዋጽኦ ላበረከቱ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ አጠቃላይ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ፣ ወላጆችና ለሁሉም አጋር አካላት ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል ።

‎ወላይታ ልማት ማህበር በሰዉ ሀብት ልማት የትኩረት አቅጣጫ ዘርፍ የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ፣ የሥነ ምግባር ዕድገትን በማጎልበትና ብቁ ዜጎችን በማፍራት ለሀገር ልማት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ወደፊትም አጠናክሮ ይቀጥላል።

Wolaytta Worqaa Mayzzana!

🚨💣 አርሰናል ከቪኒሲየስ ጁኒየር 🇧🇷 ጋር በግል ውል ላይ መርሃ ግብር ስምምነት ላይ ደርሷል።የተጫዋቹ ወኪል ድርጅት Roc Nation በፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮኖች ከቀረበው ግዙፍ የዝውውር ጥያ...
01/08/2026

🚨💣 አርሰናል ከቪኒሲየስ ጁኒየር 🇧🇷 ጋር በግል ውል ላይ መርሃ ግብር ስምምነት ላይ ደርሷል።

የተጫዋቹ ወኪል ድርጅት Roc Nation በፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮኖች ከቀረበው ግዙፍ የዝውውር ጥያቄ ጋር ወደ ሪያል ማድሪድ በይፋ የድርድር ሂደት ለመግባት በዝግጅት ላይ ነው።

አሁን ውሳኔው በቪኒሲየስ እጅ ነው፤ በሪያል ማድሪድ ይቆያል? ወይስ የአርሰናልን "ጋነርስ" ይቀላቀላል? 👀
(ምንጭ፦ )

🚨 ይፋ ሆኗል!የቀድሞው የወላይታ ድቻ በረኛ ቢኒያም ገነቱ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታላቅ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ በይፋ ፈርሟል።
30/07/2026

🚨 ይፋ ሆኗል!
የቀድሞው የወላይታ ድቻ በረኛ ቢኒያም ገነቱ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታላቅ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ በይፋ ፈርሟል።

29/07/2026

🚨 ጭምጭምታ | 500 ሚሊዮን ብር... ዎላይታ ሶዶን እያነጋገረ ያለው ጉዳይ! 👀አንድ የባንክ ኃላፊ ከግለሰቦች የሰበሰበውን ወደ 500 ሚሊዮን ብር ይዞ መሰወሩ ተሰምቷል።

ዳልቦ ቅዱስ ገብርኤል ወላይታ ሶዶ!  እንኳን አደረሳችሁ! በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በወላይታ ሀገረ ስብከተ የዳልቦ ደብረ ኃይለ ቅዱሰ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ላይ ዓመታዊ ...
26/07/2026

ዳልቦ ቅዱስ ገብርኤል ወላይታ ሶዶ! እንኳን አደረሳችሁ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በወላይታ ሀገረ ስብከተ የዳልቦ ደብረ ኃይለ ቅዱሰ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ላይ ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል በዓል እየተከበረ ይገኛል።

እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን!

19 ለዓመቱ በሠላም ያድርሰን🙏♥⛪

Address

Wolaita
S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Boditti Times 360 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Boditti Times 360:

Shortcuts

Share