Wolita sodo city Lasho Town Municipality

Wolita sodo city  Lasho Town Municipality work for good goverenance

06/09/2024
14/08/2024
በወላይታ ሶዶ ከተማ የተካላሉ ቀበሌያት ከሚመሩ አመራሮች ጋር ትውውቅና የቀጣይ የሥራ ስምርት ዙሪያ ውይይት ተካሄደወላይታ ሶዶ: ነሐሴ 7/2016ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ የተካለሉ ቀበሌያት ...
14/08/2024

በወላይታ ሶዶ ከተማ የተካላሉ ቀበሌያት ከሚመሩ አመራሮች ጋር ትውውቅና የቀጣይ የሥራ ስምርት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

ወላይታ ሶዶ: ነሐሴ 7/2016ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ የተካለሉ ቀበሌያት ትራስፎርሜሽን እና የፓርቲ ተግባራትን ለማሳለጥ ከቀበሌ አስተዳዳሪዎችና የማዘጋጃ ሥራ አስኪያጆች ጋር መድረክ ተካሄደ።

የወላይታ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መመሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት በመድረኩ እንደገለጹት በየደረጃው ያለው አመራር ተግባራትን አቀናጅቶ በመምራት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ ልሠራ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ጀገና አይዛ አመራሩ የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን እና በንቅናቄ የሚመሩ ሥራዎችን በጊዜ የለኝም መንፈስ በመሥራት ውጤታማ ልያደርግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

አክለውም በየአካባቢው የፀጥታ ሥራዎችን በማጠናከር የህብረተሰቡ የጸጥታ ባለቤት እንዲሆኑ አደረጃጀቶችን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚካኤል ሳኦል አመራሩ በመንግስታዊና በፓርቲ ሥራዎችን ለማሳለጥ የተግባር እና የአስተሳሰብ አንድነት በመላበስ ተግባራትን አቀናጅቶ እና ተግባብቶ ልሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
https://www.facebook.com/profile.php?id=100067551376751

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ በማዋል ለሠላም፣ የህዝቦችን አብሮነትና አንድነት በሚያጠናክር መልኩ መጠቀም ይገባል፦ አቶ ሳሙኤል ፎላወላይታ ሶዶ፤ሰኔ 26/2016 የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ...
04/07/2024

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ በማዋል ለሠላም፣ የህዝቦችን አብሮነትና አንድነት በሚያጠናክር መልኩ መጠቀም ይገባል፦ አቶ ሳሙኤል ፎላ

ወላይታ ሶዶ፤ሰኔ 26/2016 የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ እና የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል "ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማና ለገዢ ትርክት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል ለሚዲያና ኮሚኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሰጠ ባለው አቅም ግንባታ ስልጠና ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ በመዋል የህዝቦች አንድነትና አብሮነትን ማጠናከሪያና ማቀራረቢያ መሳሪያ በማድረግ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

ሚዲያ መንግስትና ህዝብ የሚያገናኝ ትልቅ ድልድይ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎቻችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም አመላክተዋል።

ከሚዲያ ተቋሞቻቸው ብዙ ስራ ይጠብቅባቸዋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ለህብረተሰቡ ትክክለኛውን መረጃ ተደራሽነት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ማረምና መታገል ያስፈልጋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ጥላቻን በጥላቻን ሳይሆን በበጎ ሀሳብና በሀሳብ የበላይነት ማሸነፍ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

አሁን አለም የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ዲጂታል ሚዲያን በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ሚዲያ በአግባቡ በመጠቀም ፓርቲያችን አንግቦ የተነሳውን ራዕይን ለማስረጽ እና ገዢ ትርክትን መገንባት እንደሚቻልም ጠቁመዋል።

እየተደጋገፈንና እየተጋገዘን የምንመኘውን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ለማድረግ ሁላችንም በተሰማራንበት ዘርፍ መትጋት አለብን ብለዋል።

ማህበራዊ ሚዲያን ወንድማማችነትን ሊያጎለብት በሚችል መልኩ እንዲሁም ህዝብን ከህዝብ ጋር በሚያቀራርብ መልኩ ሁሉም ዜጋ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል በበኩላቸው በእውቀትና በክህሎት የታገዘ የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ማህበራዊ ሚዲያውን መግራት፣ በአግባቡ ማስተዳደር እንዲሁም ለበጎ አላማ ማዋል እንደሚገባ አመላክተዋል።

ሚዲያን በአግባቡ ከተጠቀምን ጥላቻ ነቅለን ፍቅር መትከልና ለውጥ ማምጣት እንችላለን ያሉት አቶ ዘውዱ ለዚህም በአስተሳሰብና በአመለካከት ስራ መስራት እንደሚጠይቅም አስገንዝበዋል።

ፓርቲያችን ብልፅግና አንግቦ የተነሳውን ራዕይን ወደ ደር ለማድረስና የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በምናደርገው ጥረት ሚዲያ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ሚዲያን ለጥላቻና ለከፋፋይ አጀንዳ ከመጠቀም ይልቅ ለጋራ ሰላምና ዕድገት ብንጠቀም ትርፉ ሰላም፣ ፍቅር፣ መቻቻልንና አብሮ መበልፀግን እንደሆነም አስገንዝበዋል።

ስልጠኞች ከስልጠናው ያገኙት ዕውቀት ለበጎ ዓላማ በመዋል ሌሎችም ለበጎ ዓላማ እንዲጠቀሙ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል።
source from...
https://www.facebook.com/wolaitazoneprosperityparty Face book page

በቀን 22 /08 /2016 ዓ.ም ወላይታ ዞን ሶዶ ዙርያ ወረዳ ዋራዛ ላሾ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የ100 ቀን ዕቅድ ዙርያ ማዘጋጃ ቤታዊ አጠቃላይ ስራና አገልግሎት አስጣጥ ዙርያ ውይይት ተደረጉዋ...
01/05/2024

በቀን 22 /08 /2016 ዓ.ም
ወላይታ ዞን ሶዶ ዙርያ ወረዳ ዋራዛ ላሾ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የ100 ቀን ዕቅድ ዙርያ ማዘጋጃ ቤታዊ አጠቃላይ ስራና አገልግሎት አስጣጥ ዙርያ ውይይት ተደረጉዋል:- የወረዳ ደጋፊ አመራርና አድስ የተሾሙት የማዘጋጃ ቤት ስራ አስክያጅ አቶ አብዮት ወልደ ጋር አጠቃላይ ባለው ስራ ዙረያና እየተሰራ ባለው ፣ሊሰራ ያለው ጉዳይ ላይ የማዘጋጃ ቤት ሁሉም ዘርፍ ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሂዱዋል በመቀናጀት :በመናበብ እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል ውጤት እንድያስመዘግብም ከመድረኩ ተጠይቀውል።

በላሾ ከተማ  ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባ ሼድ ለ50 ዲግር ምሩቃን አገለግሎት እንድሰጥ ተደረገ :-ዋራዛ ላሾ  ፦ታኅሳስ 17/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋራዛ ላሾ...
27/12/2023

በላሾ ከተማ ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባ ሼድ ለ50 ዲግር ምሩቃን አገለግሎት እንድሰጥ ተደረገ :-

ዋራዛ ላሾ ፦ታኅሳስ 17/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋራዛ ላሾ ከተማ ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባ ሼድ ለ50 ዲግር ምሩቃን አገለግሎት እንድሰጥ ተደረገ ።

በተገነባው ሼድ 50 ለዲግር ምሩቃን ሥራ አጦች የሥራ አማራጭን በተለያዩ የንግድ ዘርፎች እንድሰማሩና ውጪው ሙሉ በሙሉ በማዘጋጃ ቤት የተሸፈነ ስሆን የተገነባው በ10 ሼድ መሰማረት ችለዋል።

በፕሮግራም ላይ የተገኙ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እስጢፋኖስ ዋቴ ሥራ ዕድልን ከመፍጠር ረገድ የወጣቱን እምቅ ችሎታን በመጠቀም በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችናን በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ራሱን ለመለወጥና ሌሎች ለማገዝ የሚታትር እንዲሁም የተለወጠና ለስራ የሚያነሳሳ ትውልድ መፍጠር ይገባል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ለዚህም ሁሉም ከፍተኛ ድርሻ የወጡ ባለድርሻ አካላት አመሰግነዋል።

አቶ እስጢፋኖስ የስራ አጥነትን ችግር ለመቅረፍ በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችና እምቅ አቅሞችን በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።

የወላይታ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራና እንተርፕራይዞች መምሪያ ም/ኃላፊና ማኑፋክቸርንግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማዬሁ ጎልዳ ወጣቱ ስራን የሚመረጥ ሳይሆን ስራንና ሀብት የሚፈጥር እንዲሆን በአመለካከትና በአስተሳሰብ ላይ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የወላይታ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች መምሪያ ም/ኃላፍ እና የማኑፋክቸርንግ ዘርፍ ኃላፍ አቶ አለማዬሁ ጎልዳ፥ የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ም/ኃላፍ የመሬት አስተዳደር ገጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል፥ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ እስጢፋኖስ ዋቴ፥ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ ጀማል ቦቼን ጨምሮ ለሎች ባለድርሻ አካላት መገኘት ችለዋል። SZA page.

ይህ ግዙፊ ተቁም የሚገኘው በኢትዮጵያ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወርዳ ዋራዛ ላሾ ቀበሌ ዉስጥ ይገኛል ይህ በ አፍሪካ ደርጃ 1ኛ ሲሆን አፍሪካ ዉስጥ ከዝህ ጋር በሁለት...
22/12/2023

ይህ ግዙፊ ተቁም የሚገኘው በኢትዮጵያ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወርዳ ዋራዛ ላሾ ቀበሌ ዉስጥ ይገኛል ይህ በ አፍሪካ ደርጃ 1ኛ ሲሆን አፍሪካ ዉስጥ ከዝህ ጋር በሁለት ቦታ ብቻ ይገኛል ይሁን እንጅ አፍርካ ዉስጥ አለው የሚባለው ይህንን አይደርስም ስም አጠራር ወላይታ ሶዶ ኮንቬርተር ስተሺን S**o converter station በዓለም ደርጃ ይታወቃል ይህ ስቴሽን ከገናሌ ዳዋ የሚመጣውን ኃይል ወደ ኃይልነት ይቀይራል ከዝህ ጣብያ ከኢትዮጵያ ከተማ #ሐዋሳ ኃይል ከዚህ ሲሆን ከዉጭ ኬንያ ከዝህ ኃይል ያገኛል በአጠቃላይ 400, 000 volt ኃይል የሚያመንጭ ሲሆን ጣብያዉ ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጅ የተደገፍ ነው በጣቢያ ዉስጥ የተለያዩ ቢሮችና room ይገኛል እንዴ ተቁሙ ከሆነ አብዝኛው ክፍሎች controlled ናቸው ለአብነት እዝህ ተቁም ዉስጥ ሆነው የኬንያን ያለው መብራት ኃይል ምን ያህል እንዴሆነና የተጠቀሙትን ኃይል ወደ ሂሳብ ቀይሮ በዶላር መጠን ያሳያል #በሁሉም ቦታ ያለውን ኃይል ሁኔታ በscreen ከዚህ ተቁም ክትትል ይደረጋል እንኩዋን በሕክምና ዓለም ስህተት ይፈጠራል ግን ከዚህ ተቁም ይህ አይታሰብም ይሁንና ቢሆን እንኩዋን second ዉስጥ power off አድርጎ ክስተቱን ያለ ምንም ሰው ንክክ ይቆጣጥራል ይህንና በዚህ ያልተካተቱ ብዙ የቴክኖሎጅ ይዘቶችህን ይህ ጣብያው ይዙዋል!!

በዋራዛ ላሾ ከተማ በተከታታይ ለሶስት ቀን ሲሰጥ የነበረው ከእዳ ወደ ምንዳ በሚል ርዕስ  የተዘጋጀው የአባላት ስልጠና በዛሬው እለት Ethio-Kenya power ኮንቨርተር ኃይል ማሰራጫ ጣቢ...
22/12/2023

በዋራዛ ላሾ ከተማ በተከታታይ ለሶስት ቀን ሲሰጥ የነበረው ከእዳ ወደ ምንዳ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የአባላት ስልጠና በዛሬው እለት Ethio-Kenya power ኮንቨርተር ኃይል ማሰራጫ ጣቢያ በመጎበኘ ት ተጠናቅቁል!!
ስለ converter ዝርዝር መረጃ ቦኃላ እናቀርባለን !!

  on our Area
20/12/2023

on our Area

በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋራዛ ላሾ ከተማ  ማዘጋጃ ቤት የ5ኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ ለአባላት መስጠቱ በይፋ ተጀምሯል።ዋራዛ ላሾ ፦ ታህሳስ 10/2016 ዓ....
20/12/2023

በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋራዛ ላሾ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የ5ኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ ለአባላት መስጠቱ በይፋ ተጀምሯል።

ዋራዛ ላሾ ፦ ታህሳስ 10/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ በሁሉም ቀበሊያትና ማዘጋጃ ቤት በተለያዩ ማህበራዊ ዘርፍ የ5ኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ ለአባላት መስጠቱ በይፋ ተጀምሯል።

በሁሉም ቀበሊያትና ማዘጋጃ ቤት የተመደቡ አመራሮች እንዳሉት በስልጠናዉ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ስልጠናው የአባላት አቅም ግንባታ የሚያጎልብትና የመፈፀም አቅም ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልፀዋል።

የስልጠናው አላማ አርሶ አደረ፥መንግስት ሠራተኛ፥ሴቶች፥ወጣቶች እና ለሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ተገንዝበው፣ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የማስፈፀም አቅም እንዲፈጥሩ ያለመ ነው መሆኑን ተገልጿል።

እንደ ሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋጥ በሚደረገው ትግል የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት ወሳኝ በመሆኑና በዝህ ስልጠና 30 ሺህ በላይ እንደሚሳተፉ ተገልፀዋል።

በሁሉም ስልጠና ማዕከላት የኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር በመዘመር ስልጠናውን በይፋ ተጀምሯል።

ስልጠናው ለአራት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንደምሰጥ ተገለፀ።
some informed from S**o zuria Administration office page.

Address

S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolita sodo city Lasho Town Municipality posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share