Kehos Charity Association ኬሆስ በጎ አድራጎት ማህበር

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • Kehos Charity Association ኬሆስ በጎ አድራጎት ማህበር

Kehos Charity Association ኬሆስ በጎ አድራጎት ማህበር ካለን አካፍለን አቅመ ደካሞችን እንርዳ
1000570917408 CBE
Zebiba Aklilu Buzayehu
0911234070/0912496222
(1)

ወላይታ ዲቻ ተጨማሪ ሁለት የነባር ተጨዋቾች ውል አራዝሟል!!የክለባችን ተጨዋቾች ያሬድ ዳርዛና ቢኒያም ገነቱ ለተጨማሪ ዓመት የሚያቆያቸውን ኮንትራት ከክለባችን ወላይታ ዲቻ ጋር ተፈራርመዋል።...
13/08/2025

ወላይታ ዲቻ ተጨማሪ ሁለት የነባር ተጨዋቾች ውል አራዝሟል!!

የክለባችን ተጨዋቾች ያሬድ ዳርዛና ቢኒያም ገነቱ ለተጨማሪ ዓመት የሚያቆያቸውን ኮንትራት ከክለባችን ወላይታ ዲቻ ጋር ተፈራርመዋል።

መልካም የውድድር ዘመን ይሁንላችሁ💪

 #ተለቀቀ 💪💪💪❤❤
09/05/2025

#ተለቀቀ 💪💪💪❤❤

BUZE BUCHE _Magilalan_Dir_ new Ethiopian Wolaita music 2025@yadistudio@Didigagamusic ...

 'sነዳጅ ለመቅዳት ወረፋ ይዤ የሆነ ወጣት ልጅ እድሜው ወደ 25 አካባቢ የሚመስል ቀጥ ብሎ ወደኔ ቀረብ አለኝና  "እህቴ ከነጋ እህል አልቀመስኩም አለኝ" አፉ ደርቋል ዓይኖቹ ብዙ ድካም አ...
04/03/2025

's
ነዳጅ ለመቅዳት ወረፋ ይዤ የሆነ ወጣት ልጅ እድሜው ወደ 25 አካባቢ የሚመስል ቀጥ ብሎ ወደኔ ቀረብ አለኝና
"እህቴ ከነጋ እህል አልቀመስኩም አለኝ"
አፉ ደርቋል ዓይኖቹ ብዙ ድካም አስተናግደዋል።

ተመሳሳይ ልመናዎች ቢያጋጥሙኝም አንጀቴን በላኝ። አነጋገሩና ሁኔታው እውነተኛነቱን ምለው የሚናገሩ ነው የሚመስለው።

ጥቂት የማፅናኛ ቃላትንና መፍትሄ ብዬ ያሰብኳቸውን ሃሳቦች ነገሬው የጠየቀኝን ያህል ሰጠሁት።

"አመሰግናለሁ " ብሎኝ ከሄደ በኃላ በክላክስ ጠርቼው የተወሰነ ጨመርኩለት። በጣም አመስግኖኝ ሄደ።

ሌሎቹን መኪናዎች ሳይጠይቅ ቀጥ ብሎ ሄደ። ይበልጥ አሳዘነኝ ግምቴ ትክክል ነበር። ልመናን ሥራዬ ብሎ የያዘ ሳይሆን ኑሮ ገፍትሮ አውጥቶት የሰው ፊት ያሳየው ወጣት ነው ማለት ነው።

በአይምሮዬ ብዙ ሃሳቦች ወጡ ወረዱ። አደባባይ ባይወጣም በየአካባቢያችን ያሉትን እንርዳ። ቢያንስ በቀን ለአንድ ሰው እንድረስ።
በስውር የምንሰራውን በግልፅ የሚከፍል አምላክ አለ። ፎቶ ማንሳትም ሆነ መቅረፅ አስፈላጊ ነው ብዬ አላስብም። ግዴታ ካልሆነ በቀር። ይህ መልዕክት ለእኔም ጭምር ነው።

ተባረኩ
አስቴር

07/01/2025
27/11/2024

Keho's በጎ ማህበር አባላት አድስ እቅድ አውጥተናልና በቅርቡ ወደ ስራ እንገባለን።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ካዎ ዳጋቶ ኩምቤ እና የመስሪያ ቤቱ ባልደረቦች በጎፋ ተገኝተው ሀዘን ተጋርተዋል!ኮሚሽኑ ከተከሰተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት ከደረሰው አደጋ...
02/08/2024

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ካዎ ዳጋቶ ኩምቤ እና የመስሪያ ቤቱ ባልደረቦች በጎፋ ተገኝተው ሀዘን ተጋርተዋል!

ኮሚሽኑ ከተከሰተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት ከደረሰው አደጋ ለተረፉት ዜጎች ማቋቋሚያ የሚሆን 12,200,000.00( አሥራ ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺ ) ብር በጥሬ ገንዘብ እና 2,522,810.00 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሃያ ሁለት ሺ ስምንት መቶ አሥር ) ብር በላይ የሚሆን በአይነት ድጋፍ በድምሩ 14,722,810.00 (አሥራ አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃያ ሁለት ሺ ስምንት መቶ አሥር ሺ ብር) የኮሚሽኑ አመራሮች እና የክልል ኮሚሸነሮች አደጋው በደረሰበት ቦታ በአካል በመገኘት አስረክበዋል::

የመዲናዋ አስተዳደር ለመሬት መንሸራተት አደጋ ተጎጂዎች በ2ኛ ዙር ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ*************የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጎፋ ዞን በመሬት መንሸ...
29/07/2024

የመዲናዋ አስተዳደር ለመሬት መንሸራተት አደጋ ተጎጂዎች በ2ኛ ዙር ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ
*************

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ዜጎች ሁለተኛ ዙር ድጋፍ አደረገ።

አስተዳደሩ ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምግብ፣ አልባሳት እና ሌሎች ቁሳቁስን የሰጠ ሲሆን፤ በተጨማሪም የ6.6 ሚሊዮን ብር የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ለሁለተኛ ዙር ለዞኑ አስረክቧል።

ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ክስተቱ መላ ኢትዮጵያውያንን ያሳዘነ በመሆኑ የከተማው አስተዳደር እና ህዝብ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ፥ ኢቶዮጵያውያን ተጎጂዎችን ለመደገፍ ለሳዩት ርብርብ አመስግነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሁለተኛ ዙር ድጋፍ በማድረግ ላሳየው አርዓያነት አመስግነዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በመጀመሪያው ዙር ድጋፍ ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

በአስረሳው ወገሼ

28/07/2024

Gofa በናዳ የሞቱትን ሌቅሶ የጋሞ ህዝብ በባህላቸው ስያለቅሱ😭😭

❣️ አርቲስት ያሬድ ነጉ ደግ ልቡን ይዞ ጎፋ ደርሷልአርቲስት ያሬድ ነጉ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ ምክኒያት የደረሰውን አደጋ ለማቋቋም...
27/07/2024

❣️ አርቲስት ያሬድ ነጉ ደግ ልቡን ይዞ ጎፋ ደርሷል

አርቲስት ያሬድ ነጉ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ ምክኒያት የደረሰውን አደጋ ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ጎፋ ደርሷል።

🛑 ያሬድ ጓደኞቹን በማስተባበርም የተለያዪ ለድጋፍ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን እና ለምግብነት የሚውሉ ግብአቶችን በአይሱዙ አስጭኖ የአደጋው ስፍራ ድረስ በመገኘት በአስክሬን ፍለጋ ስራ ላይም እንደተሰማራ በስፍራው የተገኙ ምንጮች ገልጸውልናል።

ደራሽ ለወገኔ 🙏❤️

📌 ይህቺ ናት ኢትዮጵያ፤
ይህቺ ናት አገሬ

ለሁለተኛ ዙር ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ ከ300,000 ሺህ ብር በላይ የሰብዓዊ ድጋፍ አደረጉየወላይታ ዞን አስተዳደር "ለወገን ደራሽ ወገን ነው" በሚል ሀሳብ በጎፋ ዞን በድንገተኛ ናዳ ...
24/07/2024

ለሁለተኛ ዙር ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ ከ300,000 ሺህ ብር በላይ የሰብዓዊ ድጋፍ አደረጉ

የወላይታ ዞን አስተዳደር "ለወገን ደራሽ ወገን ነው" በሚል ሀሳብ በጎፋ ዞን በድንገተኛ ናዳ አደጋ ለደረሰባቸው ህብረተሰብ ክፍሎች ሀብት እያሰባሰበ ባለው ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ 300,015 ሺህ ብር የሰብዓዊ ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

ኢንጂነር ብርሃነመስቀል በትናንትናው ዕለት በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች የተሰማቸውን ልባዊ ሀዘን በመገለጽ 200,000 ሺህ ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለት የወላይታ ዞን አስተዳደር ለተጎዱ ወገኖቻችን ድጋፍ ለማድረግ ባቀረበውን ጥሪ ተቀብሎ 300,015 ሺህ ብር የሰብዓዊ ድጋፍ አድርገዋል።

የተቸገሩ ወገኖቻችንን ፈጥኖ ለማገዝ ሆነ ለመስጠት የማይሰስቱ፣ በተለያዩ ጊዚያት ልማት አጋር የሆኑ እና ሰብዓዊነት አሟልተው የተላበሱ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ናቸው ኢንጂነር ብርሃነመስቀል።

በአጠቃላይ ከ500,000 ሺህ ብር በላይ ለጎፉ ዞን በድንገተኛ አደጋ የተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።

ከልብ እናመሰግናለን🙏

 አሁን ባለው ሁኔታ አደጋው የተከሰተበት ቦታ አስቸጋሪ በመሆኑ አስክሬን በሰው ኃይል ለማንሳት አስቸጋሪ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመላክታል። #ሂሊኮፍተር እና  #ኤክስካቫተር ማሽኖች ...
23/07/2024



አሁን ባለው ሁኔታ አደጋው የተከሰተበት ቦታ አስቸጋሪ በመሆኑ አስክሬን በሰው ኃይል ለማንሳት አስቸጋሪ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

#ሂሊኮፍተር እና #ኤክስካቫተር ማሽኖች በአከባቢው በአስቸኴይ መድረስ አለበት❗️
ህብረተሰቡ በዶማ ነው ሬሳ እያፈላለገ ያለው🥹

⛔️በአደጋው

▶️ከወለደች ገና ወር ያልሞላት እናት ጨቅላ ህፃኗን ቤት ጥላ በወጣችበት የቀረችበት፤

▶️አባት እና እናት ሁለቱንም ያጡ ህፃናት ቁጥራቸው ከፍተኛ መሆኑ፤

▶️ከአንድ ቤተሰብ 13 ሰው የሞተበትና ብቻውን አንድ ሰው የቀረበት፤

▶️ልጅ ያጡ ወላጆች ከአንድ እስከ ሦስት ከአንድ ቤት የሞተ፤

▶️ከተለያዩ የመንግሥት መስርያ ቤት የተጎዱትን ለማገዝ የመጡ ፖሊሶች፣ የማዘጋጃ ቤት ሠራተኞች፣ የግብርና ባለሙያዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ መምህራን እና ርሰመምህራን፣ የቀበሌው ሊቀመንበር ጨምሮ የአደጋው ሰለባ የሆኑበት፤

▶️ከሁሉም ማሀበራዊ መሠረት የኃይማኖት አባቶች ቄስ፣ ፓስተር እና በቀበሌ ያሉ ተዕጽኖ ፈጣሪ አባቶች እና እናቶች ያለቁበት፤

▶️የሞቱና የጠፉ ሰዎች ቁጥር እስከ 300 የሚደርስ መሆኑና እጅግ አስደንጋጭ ቢሆንም እከአሁን 230 የሚጠጉ ሰዎች አስከሬናቸው ሲገኝ ሌሎች እስካሁን ፍለጋ ላይ መሆኑ ጉዳቱ የሁላችንንም ርብርብ ይጠይቃል❗️

እስካሁን 5 ሰው ከናዳው መሐል በሕይወት ተገኝተዋል።

ሼር በማድረግም ትብብር አድርጉ🙏🏿

Address

S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kehos Charity Association ኬሆስ በጎ አድራጎት ማህበር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Kehos Charity Association ኬሆስ በጎ አድራጎት ማህበር:

Share