14/04/2026
ትላንት ሰኞ፣ የFICDO የበጎ ፍቃድ ሰራተኞች፣ በአካል ሶሳይቲ ግቢ በሚገኘው አዲሱ ቢሮአችን ሊመጡ የቻሉ አረጋዊያን ጨምሮን በድርጅታችን የታቀፉ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ጋር የአመት በአል የምሳና የህብረት ግዜ አሳልፈዋል።
ይህ እውን እንዲሆን በራሳችሁ ተነሳሽነት ድጋፍ ላደረጋችሁ የመስከረም አፈወርቅ ቤተሰብ፣ ዮሓንስ ማሞ፣ አርቲስት አብርሃም ወልዴ፣ የደበሌ ፈይሳ ቤተሰብ ፣ ሚኪያስ መስፍን፣ ጌትዬ ግርማ፣ ዘላለም ብርሃኑ፣ ተስፋዬ ፍቃዱና ስማችሁን ሳትጠቅሱ የለገሳችሁ በሙሉ በምናገለግላቸው ማህበረሰባችን ስም ልናመሰግናችሁ እንወዳለን። እጅግ አስፈላጊ ለሆኑ ማህበራዊ አገልግሎቶቻችን በቓሚነት ድጋፍ እያደረጋችሁ ያላችሁም ሁሉ፣ ፍቅርን በተግባር አሳይታችኋል። እግዚአብሔር በእጥፍ ይባርካችሁ።
ያለምንም ክፍያ ይህን ሁሉ ለምታቀናጁ የበጎ ፍቃድ ሰራተኞች፣ በተለይም ለአቶ ሃብታሙ ሃይሌ፣ ቀሲስ አናንያና ሌሎቻችሁም እግዚአብሔር ብድራታችሁን ይክፈል። ደሞዛችሁ ከላይ ነው።
ፍቅር የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት
1000287498474 ንግድ ባንክ፤ ቱሉ ሰላሌ ቅርንጫፍ