15/07/2026
በክልሉ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የበሸታዎች መከላከልና የጤና ማጎልበት የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር እንዳሌ ሳህለ ገለጹ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የበሸታዎች መከላከልና የጤና ማጎልበት የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር እንዳሌ ሳህለ በሸኮ ወረዳ በሺሚና በግዝመሬት ቀበሌ ጤና ተቋማትን እና ሞደል ቤተሰብ መስክ ጉብኝት መልስ ማጠቃለያ ግብረ መልስ ሰጥቷል።
በማጠቃለያ መድረክ የመወያያ ሰነድ በበሽታ መከላከል እና በእናቶችና ህጻናት እንዲሁም በቤንች ማጂ ልማት ማህበር የተሰሩ ስራዎችን የሚዳስስ ሰነድ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል።
ዶ/ር እንዳለ ሳህሌ እንደተናገሩት፣የክልሉ ጤና ቢሮ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራም ይገኛል።
በወረዳው የዜጎችን ጤናን ለመጠበቅ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አመርቂ ውጤት መሆናቸውን የገለፁት ዶ/ር እንዳለ ይህንኑ ለማጠናከር ዘርፈብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ስለመሆናቸው ተናግሯል።
በዚህም የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን እና ግብዓቶችን የሟሟላት ስራን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት አሳስቧል።
ወረዳው በጤናዉ ዘርፍ ከዚህን ቀደሞ ሞደል እና ግንባር ቀደም በመሆን በፌደራል ደረጃ እዉቅና የነበረ ሞሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር እንዳለ አሁን ላይም ወደ ቀድሞ ለመመለስ በጤናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ጥሩ ነገር እንዳለ እና ድጋፍዊ ክትትል የሚፈልግ መሆኑንም ተናግሯል።
የወረዳዉ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ እናቶች በሰለጠነ የጤና ባለሙያ እንዲወልዱ በቂ ክትትል በማድረግና በልማት ቡድን ደረጃ ግንዛቤ በመስጠት እየተሰራ እንደሆነ ገልጻለች።
ቤንች ማጂ ልማት ማህበር እና jsi ድርጅት ጤናን ለማሳለጥ ባደረግነው ስራችን ላደረጉት ድጋፍ እጅግ ለቅ አድርገው ኃላፊዋ አምስግናለች።
በጤና ዘርፍ በቀጣይ ጊዜያት የተሻለ ስራ ለማከናወን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር መድረኩ ተጠናቋል።
ከሸኮ ወረዳ መንግስት ኮሚንኬሽን የተወሰደ