Kaffa zone Gesha woreda REDD+ investment program DD project

Kaffa zone Gesha woreda REDD+ investment program DD project Gesha District

23/12/2025
በጌሻ ወረዳ የሬድ ፕላስ (REDD+) ፕሮጀክት ለአሳታፊ ደን አስተዳደር ማህበራት የ400,000 (አራት መቶ ሺህ) ብር የድጎማ በጀት አጠቃቀም ላይ ያተኮረ መድረክ አካሄደ!ጌሻ/ደካ - ህዳር...
30/11/2025

በጌሻ ወረዳ የሬድ ፕላስ (REDD+) ፕሮጀክት ለአሳታፊ ደን አስተዳደር ማህበራት የ400,000 (አራት መቶ ሺህ) ብር የድጎማ በጀት አጠቃቀም ላይ ያተኮረ መድረክ አካሄደ!

ጌሻ/ደካ - ህዳር 21/2018 ዓ.ም

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን የጌሻ ወረዳ ሬድ ፕላስ (REDD+) ኢንቨስትመንት ፕሮጀክት፤ በወረዳው የተፈጥሮ ደንን በመጠበቅና በመንከባከብ ለተደራጁ የአሳታፊ ደን አስተዳደር ማህበራት የተፈቀደውን የድጎማ በጀት አጠቃቀም አስመልክቶ ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫና የውል ስምምነት መድረክ በዛሬው ዕለት በስኬት ተጠናቀቀ፡፡

በዚህ ወሳኝ መድረክ ላይ የወረዳው ስቲሪንግ ኮሚቴ አባላት፣ የቴክኒክ ቡድን አባላት እንዲሁም የድጋፉ ተጠቃሚ የሚሆኑት የአሳታፊ ደን አስተዳደር ማህበራት የበላይ አመራሮችና የባንክ ሂሳብ ጣምራ ፈራሚዎች ተገኝተዋል፡፡

የበጀት ድልድሉን በተመለከተ፡-
በመድረኩ በይፋ እንደተገለፀው፤ ማህበራቱን በገንዘብና በቁሳቁስ አቅማቸውን ለመገንባት እንዲቻል ለዚህ ዙር አጠቃላይ ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ ብር) በጀት ተፈቅዷል። ይህ በጀት በወረዳው ለተመረጡ አራት (4) የአሳታፊ ደን አስተዳደር ማህበራት (ባትዳቺ፣ ሹኒቲ፣ ሻዎዶ እና የሽቶየሪ/ኪጮ) በእኩል መጠን ለእያንዳንዳቸው ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል።

በጀቱ ለምን ተግባር ይውላል?
ለእያንዳንዱ ማህበር የተመደበው 100 ሺህ ብር በታቀደለት አግባብ ስራ ላይ እንዲውል የተዘጋጀው የተግባር ዕቅድ (Action Plan) በዝርዝር የቀረበ ሲሆን፣ በጀቱ በዋናነት፡-

የቢሮ ማደራጀት፡ ማህበራቱ የራሳቸው ቢሮ ኖሯቸው አስፈላጊ የሆኑ የቢሮ ቁሳቁሶችን (ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ሸልፍ) እንዲያሟሉ፣

የደን ጥበቃ: ለደን ድንበር ጥበቃ፣ ለምልክት ስራዎችና ለጥበቃ ግብዓቶች፣

የአሠራር ስርዓት: የፋይናንስ ሥርዓታቸው ግልጽነት እንዲኖረውና በውጫዊ ኦዲት እንዲመረመር፣ እንዲሁም

ክትትልና ድጋፍ: የማህበሩ አመራሮች የደን ጥበቃ ሥራውን በቅርበት እንዲከታተሉ ለማስቻል ታቅዶ የተፈቀደ መሆኑ ተብራርቷል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎችም ይህ የገንዘብ ድጋፍ የማህበራቱን ተቋማዊ አቅም ከመገንባት አኳያ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልጸው፤ እያንዳንዱን ሳንቲም በታቀደለት የህጋዊ አሠራር (Rules and Regulations) መስመር ብቻ ለመጠቀም ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በመጨረሻም፤ በቀጣይ ቀናት ከወረዳው ግብርና/አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት እና ከፋይናንስ ጽ/ቤት ጋር ህጋዊ የውል ስምምነት በመፈራረም የተፈቀደው 400,000 ብር ወደ አራቱም ማህበራት የባንክ ሂሳብ ተላልፎ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል፡፡
(REDD+)_ኢንቭስትመንት_ፕሮግራም

የመልጋዊ ቀበሌ ቤሞየሪና አሳታፊደን አስተዳደር ማህበር የምስረታ እና የውክልና ውል ስምምነት ፊርማ ስነስርዓት ተካሄደ።መስከረም 23/2017 ዓ.ም በREDD+ ፕሮጀክት ድጋፍ 78 ወንዶቸና 2...
03/10/2024

የመልጋዊ ቀበሌ ቤሞየሪና አሳታፊደን አስተዳደር ማህበር የምስረታ እና የውክልና ውል ስምምነት ፊርማ ስነስርዓት ተካሄደ።
መስከረም 23/2017 ዓ.ም በREDD+ ፕሮጀክት ድጋፍ 78 ወንዶቸና 23 ሴቶች በድምሩ 101 አባላትን አሳትፎ የተቋቋመው የመልጋዊ ቀበሌ ቤሞየሪና አሳታፊ ደን አስተዳደር ማህበር 184.116 ሄክታር ጫጂ ደን የ10 ዓመት ወክልና ውል ሰነድ ከጌሻ ወረዳ ግብ/አካ/ጥ/ኀ/ሥ/ል/ጽ/ቤት ፈርሞ ተረክቧል።
የውል ሰነዱን ያረካከቡት የጌሻ ወረዳ ፊትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሩ ከበዴ በዚህ የውል ስምምነት ሰነድ የተካተቱትን የሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች ግዴታቸዎችን በመወጣት ደኑን ማቆየትና ለትውልድ ማሸጋገር እንደሚገባቸው አሳስቧል። በተጨማሪም የጌሻ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድማሱ የጫጂ ደን ከዚህ በፊት የቆየ ታርክ ያለውና ለአካባቢ ህብረተሰብ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ስሰጥ የቆየ መሆኑን አስታውሰው አሁን እየደረሰበት ያለውን ጫና በመቀነስ መጠበቅና ማልማት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ሰለሞን አበቶ ህብረተሰቡ ከመንግስት የተረከበውን ደን በባለቤትነት በመጠበቅ በማልማትና በመጠቀም ፕሮጀክቱ ለኑሮ ማሻሻያ የሚያቀርባቸውን አማራጮችንም በአግባቡ በመጠቀም ደኑን ከጉዳት መታደግና የራሳቸውን ኢኮኖሚ እያያሻሻሉ የደን ሀብቱን በዘለቃኒነት እንዲያቆዩ መክረዋል። አቶ ታደሴ ተካ የወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ የውል ሰነዱን ፈርመው ከተረካከቡ በኃላ ፕሮጀክቱ ያቀረበውን ዕድል በመጠቀም እየጠፋ ያለውን ደን በመጠበቅ ማልማትና በአግባቡ እየተጠቀሙ የሚያቆዩበትን ምክረ ሀሳብ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ከቀበሌ በተመረጡ የሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት ከተደረገ በኃላ ለማህበሩ ይፋዊ ዕውቅና በመስጠት የዕለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል።
ዘገባው የጌሻ ወረዳ REDD+ ፕ/ት ማስ/ሪያ ነው።

Gesha woreda finance accountant Exam Result
20/08/2024

Gesha woreda finance accountant Exam Result

📢 **Attention Accountants!** 📢This is a reminder for all candidates who applied and were selected by the Region Finance ...
16/08/2024

📢 **Attention Accountants!** 📢

This is a reminder for all candidates who applied and were selected by the Region Finance Bureau for the Accountant position (Job Vacancy Announcement Ref. No. 8246, Date: 29/09/2016 E.C) in the Gesha Woreda REDD+ Program.

🗓 **Exam Date:** Tuesday, 14/12/2016 E.C
🕒 **Time:** 3:00 AM (Local Time)
📍 **Location:** Gesha Woreda Finance and Economy Development Office

Please make sure to attend on time. We wish you all the best in your exam!

Thank you!

ጌሻ:-ሴነ 14 ቀን 2016 ዓ.ም በREDD+ ፕሮግራም በደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀምን በማዘመን የወረዳችንን ማህበረሰብ ኑሮ ይበልጥ ማሻሻል አለብን:- አቶ ካሳሁን ገብሬ።የካፋ ዞን ጌሻ ወረ...
22/06/2024

ጌሻ:-ሴነ 14 ቀን 2016 ዓ.ም
በREDD+ ፕሮግራም በደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀምን በማዘመን የወረዳችንን ማህበረሰብ ኑሮ ይበልጥ ማሻሻል አለብን:- አቶ ካሳሁን ገብሬ።

የካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ሬድ-ፕላስ እንቨስትመንት ፕሮግራም የ2016 ዓ.ም በደን ጥበቃ ዙርያ ከህግ ባለሙያዎች እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋራ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የጌሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካሳሁን ገብሬ በመድረኩ በመገኘት እንደተናገሩት በዚህ ሬድ ፕላስ ፕሮጀክት ጋር በመደገፍ በደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀምን በማዘመን የወረዳችንን ማህበረሰብ ኑሮ ካለበት ይበልጥ ለማሻሻል ሁላችንንም በየደረጃው መስራት አለብንም ብለዋል።

አክለውም ፕሮጀክቱ የደን ሃብትን ተከትለው የመጣና የደን ሃብትን የመጠበቅና የጠፉት ላይ የመተካት፣የበካይ ጋዝ መከላከል እንዲሁም የማህብረሰብ ኑሮ ማሻሻል ዓላማ ሰንቀው እየሠራ የቆየና አሁንም በመሥራት ላይ ያለ ፕሮጀክት ስለሆነ የደን ሃብትን ለመጨር ችግኝ ጣቢያዎች በተለያዩ ቦታዎች በማቋቋም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን የችግኝ ዝሪያዎችን በማባዛት ለማህብረሰብ እያደለ ጭምር ይገኛልም ብለዋል።

በREDD+ ከደን ውድመትና መመናመን የሚለቀቅ በካይ ጋዝ ቅነሳ እና የማህበረሰብ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም ድጋፍ የዝሪያ ማሻሻያ ሥራ በፕሮጀክቱ የታቀፉ ቀበሌዎች ላይ እያከናወነ መገኘቱን ያሳሰቡት አቶ ካሳሁን ፕሮጀክቱ የደን ሃብትን ከማስጠበቅ ባለፈ የማህብሰቡን ኑሮ ለማሻሻል ትልቅ ዓላማ ይዘው እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

የጌሻ ወረዳ የፕሮጀክቱ እንቨስትመንት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ሰለሞን አበቶ የስልጠና ሰነዱን ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ስጋት የሆነዉን የአየር ንብረት መዛባት ወይም የካርበን ልቀትን ለመከላከል አልፎም ህብረተሰቡ በህጋዊ መንገድ የማስተዳደርና የመጠቀም መብቱን ለማረጋገጥ እንዲሁም ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በወረዳችን ከተቋቋመበት ግዜ አንስተው እሰከ አሁን ለብዙ ወጣቶች በቋምና በግዘያዊ ስራ እድል ተፈጥረዋልም ብለዋሉ።

የጌሻ ወረዳ ግብ/ደ/አ/ጥ/ህ/ሥ/ልማት ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ ታደሴ ተካ በወረዳችን ይህ ፕሮጀክት ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በድሀ ማህበረሰብ ኑሮ ለማሻሻል መሬት ላይ በተሰሩ ስራዎች እጅግ አስደሳች ውጤት መመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።

የጌሻ ወረዳ ብልፅግና ፓርት ቅ/ጽ/ቤት የመንግስት ዋና ተጠረ አቶ አንድሰው ዓለማየሁ መድረኩን በጋራ የመሩ ስሆን በበኩላቸው እንደተናገሩት በፕሮጀክቱ በማስደገፍ የሥጋና የወተት እንዲሁም ሌሎች የእንስሳት ተዋፅዎችን በማስፋት ሀገራዊ ፕሮጀክት የሆነውን "የሌማት ትሩፋት" ሥራን በወረዳው በማስፋት አሁንም ፕሮጀክቱ ድጋፉን እንዲያጠናክር ማህብረሰቡ ደንን የመከባከብ፣ የመጠበቅና የመተካት ሥራዎችን አጠናክረው እንዲሠሩ ስሉም በጥብቅ አሳስበዋል።

🙏ዘውትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን🙏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዘገባው:-የጌሻ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው።

Gesha woreda REDD+ project coordination office:ኢትዮጵያ ከኖርዌይ ጋር የ75 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የካርቦን ሽያጭ ስምምነት ተፈራረመች****ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ...
27/02/2024

Gesha woreda REDD+ project coordination office:
ኢትዮጵያ ከኖርዌይ ጋር የ75 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የካርቦን ሽያጭ ስምምነት ተፈራረመች
****

ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ የ75 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የካርቦን ሽያጭ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የኖርዌይ የአየር ንብረት ለውጥ የአከባቢው ሚኒስትር አንደርሰን ኤሪክሰን ናቸው።

ስምምነቱ እ.አ.አ እስከ 2027 ድረስ የሚቆይ ነዉ ተብሏል።

ስምምነቱ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በማጠናከር የአየር ንብረት ለዉጥ የሚያስከትላቸውን ተፅዕኖዎችን ለመቀነስ እንደሚያገዝ ተጠቅሷል።

የዛሬው ስምምነት ኢትዮጵያ እየሰራች ያለዉ ዘላቂ የአረንጓዴ ደን ልማት ውጤታማ መሆኑን ማሳያ እንደሆነም ነዉ የተገለፀው።

ከካርበን ሽያጭ የሚገኘው ገቢ እንደ ሀገር የተሰሩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ለማጠናከር አንዲሁም አዳዲስ የደን ልማት ስራዎችን ለመስራት ይውላል ተብሏል።

በላሉ ኢታላ

Ethiopia and Norway signed a $75 Million Partnership Agreement.

February 27, 2024

Addis Ababa University, Ras Mekonen Hall
****®*****
In a landmark move, the Government of Ethiopia and the Royal Norwegian Government have forged a monumental partnership agreement, totaling a staggering $75 million. This historic accord, signed amidst great anticipation, marks a significant milestone in bilateral relations between the two nations.

Under the terms of the agreement, both parties have committed to a wide array of collaborative initiatives aimed at fostering sustainable development in “Reducing emissions from deforestation and forest degradation, conservation of forest carbon stocks, sustainable management of forests and enhancement of forest carbon stock and on promoting sustainable development and climate resilience within the context of Ethiopia’s Nationally Determined Contributions, The Climate resilient green economy strategy( CRGE), and the long term-Low emissions strategy (LT-LEDS) ”.

The partnership holds immense promise for Ethiopia's forest Spector development through offering access to Norway's expertise, technology, and financial resources to propel the nation's development agenda forward. Moreover, it underscores Norway's commitment to supporting Ethiopia's journey towards prosperity and self-reliance.

Speaking at the signing ceremony, H.E. Dr. Girma Amente, Minister of Ethiopi

Address

Mesan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kaffa zone Gesha woreda REDD+ investment program DD project posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share