Hakimichu Health Tips

Hakimichu Health Tips This page posts health related topics and issues
Telegram: https://t.me/Sidama_Health

26/11/2025

ጤናባለሙያው የህይወት ዋጋ እየከፈለ ነው

ምን ማለትዎ ነው?
20/11/2025

ምን ማለትዎ ነው?

ወገን መንግስት ለገጽታ ምናምን እያለ ሊፈጀን እንዳይሆን
19/11/2025

ወገን መንግስት ለገጽታ ምናምን እያለ ሊፈጀን እንዳይሆን

(መሠረት ሚድያ)- ባለፉት ጥቂት ቀናት ጂንካ አካባቢ በተከሰተ አጣዳፊ በሽታ ስድስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን መዘገባችን ይታወሳል። የጤና ሚኒስቴር ይፋ ያረገው መረጃ በሽታው የማርበር.....

💥ሰበር‼️የጂንካ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ከስራ ተባረሩ !መርበርግ የተባለ አደገኛ ቫይረስ የ6 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈ ማግስት የሆስፒታሉ ሜዲካል የዳይሬክሩ መባረር አነጋጋሪ ሆኗል።ሜዲካ...
15/11/2025

💥ሰበር‼️

የጂንካ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ከስራ ተባረሩ !

መርበርግ የተባለ አደገኛ ቫይረስ የ6 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈ ማግስት የሆስፒታሉ ሜዲካል የዳይሬክሩ መባረር አነጋጋሪ ሆኗል።

ሜዲካል ዳይሬክተሩ የተባረሩትም አለማቀፉ ሚድያ በቫይረሱ የሞቱ ዜጎች መኖራቸውን በማረጋገጣቸው እንደሆነም የውስጥ ምንጮች ነግረውናል።

ከሰሞኑ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ የ 6 ሰዎች ህልፈትን ተከትሎ የማህበራዊ ሚድያዎች ትኩረት በጂንካ ሆስፒታል ላይ አነጣጥሯል።

ቫይራል ሄሞሬጅክ ፌቨር የተሰኘው አደገኛ የቫይረሶች ቡድን ተከተሰተ መባሉን ተከትሎ በተደረገ የሟቾች የደም ናሙና ምርመራ ውጤት ማርበርግ የተሰኘ አደገኛ ወረርሽኝ መከሰቱ ተሰምቷል።

የሟቾቹ የናሙና ምርመራ ውጤትን መነሻ በማድረግ በፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና በኢትዮጽያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት በኩል የወረርሽኙን ክስተት ያረጋገጡ መግለጫዎችም በማህበራዊ ሚድያ ገጾቻቸው ያሰራጩ ሲሆን አለም ዓቀፉ የጤና ድርጅትም አፋጣኝ የገንዘብ፣ የሙያተኛና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ ከጀርመን ድምጽ ራድዮ ጣቢያ ዶቼቬሌ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የጂንካ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ቢኒያም አስራት የወረርሽኙ ክስተት ሞት ማስከተሉን ያረጋገጡበትን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ 4 ታካሚዎችና የህክምና እርዳታ ያደረጉላቸው 2 ሀኪሞች፤ 1 ዶክተርና 1 ነርስ ህይወት ማለፍን ያረጋገጡት ሜዲካል ዳይሬክተሩ የሟቾችን ቁጥር መግለጻቸው ተከትሎም ሜዲካል ዳይሬክተሩ ከስራቸው መባረራቸው ተሰምቷል።

የቀረበው ውንጀላም ለአለማቀፉ የሚድያ ተቋም DW የተከሰተውን ሃቅ ያረጋገጠ መረጃ ሰጥተሃል በሚል ውንጀላ መሆኑንም ከሆስፒታሉ የመረጃ ምንጮች ለማረጋገጥ ችለናል።

የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት በሰጡት በመግለጫ በሆስፒታሉ በቫይረሱ የተጠረጠሩ ሰዎችን እንጂ የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን ያልገለጹ ቢሆንም ዳይሬክተሩ ይህንኑ ይፉ ማድረጋቸውን ተከተሎ ከስራ መታገዳቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ደርሷቸዋል።

የተከሰተው ቫይረስ እጅግ አደገኛና ገዳይ መሆኑ እየተገለጸ የሟቾችን ቁጥር መደበቅ ለምን እንደተፈለገ የታወቀ ነገር ባይኖርም ሃቁን ባለመደበቃቸው የተወነጀሉት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቢኒያም አስራት አደገኛ ዛቻና የእስር ማስፈራሪያ እየደረሱባቸው መሆኑንም ለማረጋገጥ ችለናል።

ከስራ የተባረሩበት ደብዳቤ የደረሳቸው ሜዲካል ዳይሬክተሩን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም በዚህ ጉዳይ ምንም አስተያዬት ለማንም መስጠት እንደማይፈልጉ በመግለጽ ስልካቸውን ዘግተዋል።

ሆኖም ግን የእገዳ ደብዳቤው በክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ ጫና አድራጊነት የተጻፈባቸው መሆኑን ከሆስፒታሉ የውስጥ ምንጮች ለማረጋገጥ ችለናል።

በስራው ታታሪና ትጉህ የሆነው የጂንካው ተወላጅ ዶ/ር ቢኒያም ሆስፒታሉን ለማሻሻል እየተጋ ቢሆንም በተደጋጋሚ ጫና ውስጥ መቆየቱን ጠቁመው እውነተኛ መረጃ መስጠት ኃላፊነቱን በመወጣቱ ሊመሰገን ሲገባው ከስራ መታገዱ ተገቢ አይደለም ብለዋል።

በአለማቀፉ የጤና ተቋም ተረጋግጦ በመንግስት መግለጫ በተሰጠበት ጉዳይ መረጃ ምንም አይነት ክልከላ በሌለበት፤ ዶ/ሩ መባረር እውነታን ለመደበቅ የሚፈልግ አካል ሴራ ሊሆን ይችላል የሚሉት ምንጮቹ ሃቀኛ መረጃ እንዲሸፈን የተፈለገበት ምክንያት ግን ምን ሊሆን እንደሚችል አናቅም ብለዋል።

via EHPM- Ethiopian Health Professionals Movement

https://www.facebook.com/61574891082699/posts/122167910204829702/

Urgent!ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት  በወቅታዊ የጤና ጉዳይ የተሰጠ  መግለጫ
12/11/2025

Urgent!
ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በወቅታዊ የጤና ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ እየተፋጠነ እንደሆነ  ተዘገበ። የኦክስጅን ማምረቻ ፋብርካው ከዚህ በፊት በኦክስጅን እጦት ለአላስፈላጊ ወጪና...
28/10/2025

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ እየተፋጠነ እንደሆነ ተዘገበ።

የኦክስጅን ማምረቻ ፋብርካው ከዚህ በፊት በኦክስጅን እጦት ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ሲዳረጉ የነበሩ ህሙማንን ችግር እንደሚያቃልል ተስፋ ተጥሎበታል

via ማለዳ_ሚዲያ

የፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ አስከሬን ሽኝት በጥቁር አንበሳ ተካሂዷል : ቀብራቸው ነገ ሐዋሳ ይፈፀማል::via Hakim
16/10/2025

የፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ አስከሬን ሽኝት በጥቁር አንበሳ ተካሂዷል : ቀብራቸው ነገ ሐዋሳ ይፈፀማል::

via Hakim

‎አሳዛኝ መረጃ ከወደ አሜሪካ 😭‎ባልታወቀ ሰዎች በጥይት ተመቶ ህይወቱ አለፈ‎ዶ/ር ዳራራ ብዲሶ ቦሮጄ (የስነ አዕምሮ ዶክተር ፣ Psychiatrist) በቅርቡ ሳብ ስፔሻላይዝድ እያደረገ የነ...
05/10/2025

‎አሳዛኝ መረጃ ከወደ አሜሪካ 😭
‎ባልታወቀ ሰዎች በጥይት ተመቶ ህይወቱ አለፈ
‎ዶ/ር ዳራራ ብዲሶ ቦሮጄ (የስነ አዕምሮ ዶክተር ፣ Psychiatrist) በቅርቡ ሳብ ስፔሻላይዝድ እያደረገ የነበረ ሬዝዴንት ነበር።

‎አባቱ በቅርቡ ከሁለት አመት በፊት ያረፉ ታዋቂ ፖለቲከኛ እና የሲአን ታጋይ ነበሩ።

‎ነፍስ ይማር
‎መጽናናትን ለቤተሰቡ እና ለወዳጆቹ እንመኛለን

እናመሰግናለን !!በመምህር ዳንኤል ንጉሴለደሞዝ ማሻሻያዉ ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉ ሰራተኞችን እናመሰግናለን ። (የጤና ባለሞያዎቻችን ) ።የጤና ባለሙያዎቻችን ለዚህ ለዉጥ ታስረዋል፣ተሰደዋል፣ከስራ...
03/10/2025

እናመሰግናለን !!

በመምህር ዳንኤል ንጉሴ

ለደሞዝ ማሻሻያዉ ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉ ሰራተኞችን እናመሰግናለን ። (የጤና ባለሞያዎቻችን ) ።

የጤና ባለሙያዎቻችን ለዚህ ለዉጥ ታስረዋል፣ተሰደዋል፣ከስራ ተባረዋል ፣ ለመኖሪያነት የተሰጣቸዉ ቤት ተነጥቀዋል ፣ተሳደዋል ተዋክበዋል ።

ይህ የደሞዝ ማሻሻያ ዝም ብሎ በመንግስት በጎ ፍቃድ የተሰጠ አይደለም ።ይልቁንም ለጤና ባለሙያዎቻችን ከፍተኛ ምስጋና ይድረስ .....

የጤና ባለሙያዎች ከሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ሴክተሮች በተለየ ሁኔታ እየደረሰ ያለዉን የመኖር ህልዉና ፈተና ለማስከበር መታገል በጀመሩበት ሰዓት ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች ሆዳቸዉን እያከኩ ፤ ኑሮ ከብዷቸዉ እራሳቸዉን እስኪጠሉ ድረስ እያማረሩ ፤ እራሳቸዉን እና አኗኗራቸዉን እየኮነኑ ይኖሩ ነበር። በዛ ሰዓት ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች የሚያደርጉት ጠፍቷቸዉ ከፍተኛ ቁዘማ ዉስጥ ነበሩ።

ባጠቃላይ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች በልቶ ማደር ፣የቤት ኪራይ መፍፈል እና ልጆቻቸዉን አብልቶ ወደ ት/ቤት መላክ ከፍተኛ ፈተና እየሆነባቸዉ ባለበት ሰወቅት እና የሆነ መፍትሄ እያሰላሰሉ ባለቡት ሰዓት ለወትሮም በሙያቸዉ አቻ የማይገኝላቸዉና በሀገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ ሞያቸዉን ፈልገዉና መርጠዉ እያገለሉ ያሉ የጤና ባለሙያዎች በተለይም ዶክተሮች ያደረጉትን ትግል በታሪክ ተመዝግቦ አልፏል ።

ይህ የደሞዝ ማሻሻያ የመጣዉ በጤና ባለሙያዎች ከፍተኛ ተጋድሎ እና የተቃዉሞ እንቅስቃሴ መሆኑ እሙን ነዉ ። የእነርሱ እንቅስቃሴ" ወደ ሌሎች የስራ መስክ ባለሙያዎች የመዛመት ሁኔታ ይኖራል" በማለት የተሰጠ ግብረ መልስ መሆኑን እኔ በግሌ አምናለዉ።

የጤና ባለሙያዎች የፈጠሩት መነቃቃት እና የከፈሉት መዋዕትነት ቀላል አይደለም ።
1.በተለይ ሬዝደንት የሆኑ ዶክተሮች በስራ ማቆም አድማ በማድረጋቸዉ የደረሰባቸዉ በደል መካከል ፦
ሀ.ከስራ የመታደግ
ለ. የመታሰር እና የመሳደድ፣
ሐ. ለመኖሪያ ቤትነት የተሰጣቸዉ ቤት የመነጠቅ ፣
መ. ባጠቃላይ ከፍተኛ የመዋከብና ያልተገባ የስም ማጥፋት ዘመቻ በወዶ ገብ ሚዲያዎች የተከፈተባቸዉ መሆኑን እና
ሠ.በእነሱ ህጋዊ ጥያቄ በብዙ አካባቢዎች በተለይ በአዲስ አበባ ፣ በድሬዳዋ፣በኦሮሚያ ክልል መምህራንን ስለ እነሱ እንቅስቃሴዎች ለማወቅና መረጃ ለመስበሰብ ብሎም ቀጣይ የመመምህራንን እንቅስቃሴ እቅድና ሁኔታ ለማወቅ ስብሰባ መጥራታቸዉ ጥሩ ማሳያ ነበር።

ለማንኛዉም ድል ያለ ትገል፤ነፃነትና ኃጢያት ያለ ስርየት አንደማይሆ ሁሉ ለተደረገዉ መሻሻል የጤና ባለሙያዎቻችንን አስተዋፅኦ ፈር ቀዳጅ መሆኑን መዘንጋት የለብንም!!!

ይህ የደሞዝ ለዉጥ መሻሻል ጠቀምም አልጠቀመም ፈር ቀዳጅ እንዲሆን ዋጋ ከፍለዉ እንዲሻሻል ያደረጉት ወይም መንግስት ደጋግሞ እንዲያስብ ያደረጉት የጤና ባለሙያዎች ተጋድሎ ብሎም ቁርጠኛ የተግባር እንቅስቃሴ እንደሆነ ይገባኛል ።

አሁንም ቢሆን ባለሙያዉ ህዝቡን በሞራልና እና በሙሉ ፍቃደኝት እንዲያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች የመኖሪያ ቤትና ሌሎች እንደ የዱቲ ፣ የተጋላጭነት ፣ የtop up፣ የትራንስፖርት እንዲሁም መሰል ጥቅማ ጥቅሞች ለጤና ባለሞያው በተለየ መልኩ ታይቶ የተሻለ ማስተካከያ ሊደረግ እና ጥያቄዎቻቸዉ ሊመለሱ ይገባልየሚል እምነት አለኝ።

እናመሰግናለን የጤና ባለሙያዎቻችን ።

via EHPM- Ethiopian Health Professionals Movement

‎ We're deeply saddened to hear about the passing of Lidiya Tadese, a dedicated midwife at Dale, Sidama who touched so m...
07/09/2025

‎ We're deeply saddened to hear about the passing of Lidiya Tadese, a dedicated midwife at Dale, Sidama who touched so many lives with her compassion and care.
‎Our heartfelt condolences go out to her family, friends, and all those who had the privilege of knowing her. May she rest in peace.

‎ዛሬ ወላይታ ሶዶ ኦቶና ሪፈራል ሆስፒታል በደረሰው እሳት አደጋ ለደረሰው ከፍተኛ ንብረት ውድመት የተሰማንን ሀዘን እንገልጻለን።‎አንጋፋውና 80 አመታትን ያስቆጠረው ከወላይታ ዞን አልፎ ለበ...
26/07/2025

‎ዛሬ ወላይታ ሶዶ ኦቶና ሪፈራል ሆስፒታል በደረሰው እሳት አደጋ ለደረሰው ከፍተኛ ንብረት ውድመት የተሰማንን ሀዘን እንገልጻለን።
‎አንጋፋውና 80 አመታትን ያስቆጠረው ከወላይታ ዞን አልፎ ለበርካታ ዞኖችና ክልሎች ህክምና ሲሰጥ የቆየው ተቋም እንደዚህ ሲቃጠል ማየት በጣም ያማል።

Address

Irgalem

Telephone

+251916826491

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hakimichu Health Tips posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share