30/06/2026
**የምስራች ከአዊ ልማት ማህበር(አዊልማ)!
ንጹህ መጠጥ ውሃ ለጤናማና አምራች ማህበረሰብ!
የአዊ ልማት ማህበር የማህበረሰባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና መሰረታዊ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ሌት ቀን እየሰራ ይገኛል። ከነዚህም ዋና ዋና አንገብጋቢ የልማት ፍላጎቶች መካከል አንዱ የሆነውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ማህበራችን ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ነው።
ልማት ማህበሩ ለአገልግሎት የሚውል ንጹህ የመጠጥ ውሃ ጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ (Deep Borehole Drilling) ሥራ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ፍጥነትና ስኬት ላይ ይገኛል።
ይህንን እጅግ ከፍተኛ የቴክኒክ ብቃትና ጥንቃቄ የሚጠይቀውን የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ፕሮጀክት በውል ስምምነታችን መሠረት በግንባታው ዘርፍ ሰፊ ልምድ ያለው ዋተርሆ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (Waterho Trading PLC) ጨረታውን ተወዳድሮ በመሸነፉ ስራውን በግንባር ቀደምትነት እያሰረ ይገኛል።
በዚሁ መነሻነት በእንጅባራ ከተማ በስገነባው G+6 ሁለ ገብ ገቢ ማስገኛ ህንፃ ማለትም ለባንክ አገልግሎት , ሬስቶረንት , አልጋ አገልግሎት ለቢሮ አገልግሎት እና ለአደራሽ ኪራይ አገልግሎት እንዲሰጥ እና የለምንም የውሃ ችግር አግልግሎት እንዲያገኝ እና የአካባቢ ነዋሪ አገልግሎት ለመስጠት ተስቦ ውሃ እያስቆፈረ ይገኛል :: ማንኛውም አገልግሎት ፈለጊ በህንፃ ዙሪያ የውሃ ችግር እንደማይገጥማቸው እያሳወቅን ለአዲሰ አበባው ህንፃ ግንባታ structure የላቀ በመሆኑ ለfinishing ሁሉ የልማት ማህበሩ አባለትና ደጋፊዎች በገንዘብ እንድትደግፉና ለህዝባችን የልማት ተጠቃሚነት እንድነውላው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
ተግበራዊ ልማትና ለአጋርነት
ስኔ 23/2018