South Ethiopia chess

South Ethiopia chess this page is to give info how chess sport is going on in South Ethiopia and promote chess sport bene

የኢትዮጵያ ቼስ ፌዴሬሽን ለዩኒቨርስቲ መምህራን የ1ኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ስልጠና ግንቦት 6 /2018 ዓም በጅማ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሁኔታ አስጀመረ።በመክፈቻ መርሀ ግብሩ  የስልጠናው ዓላማ ...
17/05/2026

የኢትዮጵያ ቼስ ፌዴሬሽን ለዩኒቨርስቲ መምህራን የ1ኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ስልጠና ግንቦት 6 /2018 ዓም በጅማ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሁኔታ አስጀመረ።

በመክፈቻ መርሀ ግብሩ የስልጠናው ዓላማ በፌዴሬሽኑ ባለሙያ ገለፃ ከተደረገ በኋላ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት የፅሁፍ መልዕክት በንባብ በማስተላለፍ በይፋ ተጀምሯል ።

በስልጠናው ከ13 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 30 በላይ መምህራን እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

16/05/2026
ሀገር አቀፍ የግል የበላይነት ቼስ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ።ሚያዚያ 24፣ 2018ዓ.ም አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ቼስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የ2018 ለሁሉም ክፍት የሆነው የቼስ የግል ...
02/05/2026

ሀገር አቀፍ የግል የበላይነት ቼስ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ።

ሚያዚያ 24፣ 2018ዓ.ም አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ቼስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የ2018 ለሁሉም ክፍት የሆነው የቼስ የግል የበላይነት ሻምፒዮና ተጠናል።

በሻምፒዮናው ሀና ሙሉጌታ፣ ነፃነት ሉቃስ፣ አስቴር መለሰ በሴቶች ከ1-3 ያለውን ደረጃ በመያዝ የሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።

ለብሔራዊ ቡድንም የሜዳሊያ አሸናፊዎቹን ጨምሮ ሰላማዊት ስለሽንና ሲና ታደሰ ተመርጠዋል።

በወንዶች ለይኩን መስፍን፣ ፍላወር ሀብቱ እና ሮቤል ብርሃነ የወርቅ፣ የብርና የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ናቸው።

በተመሳሳይ ለብሔራዊ ቡድን ሚልኪ አብድሳ እና ጴጥሮስ ኦላና ጨምሮ የሜዳሊያ አሸናፊዎች ተመርጠዋል።

የኢትዮጵያ ቼስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ተሾመ በቀለ ሻምፒዮናው ተተኪ ስፖርተኞችን ማግኘት የተቻለበት እንደሆነ በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ገለፀዋል።

በሻምፒዮናው አሸናፊ የሆኑ ስፖርተኞች በቀጣይ ሀገራቸውን ወክለው በአለም አቀፍ መድረክ ይሳተፋሉ ብለዋል።
ፌዴሬሽኑ በቀጣይ ስልጠናዎችንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሬዚዳንቱ አክለዋል።

ለሁሉም ክፍት በሆነው የግል የበላይነት ሻምፒዮና ከ142 በላይ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል።

You can view and join right away.

21/03/2026
21/03/2026

ሁሉንም ህብረተሰብ ክፍል እንደ ፍላጎቱና ችሎታው በስፖርት ማሳተፍ የሀገራችን ስፖርት ፖሊሲ ዋና የትኩረት አቅጣጫ ነው።

መጋቢት 11፣ 2018ዓ.ም አዲስ አበባ

ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ የዜጎች መሰረታዊ መብት መሆኑን የሀገራችን ስፖርት ፖሊሲ ሲደነግግ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እንደ ፍላጎቱና ችሎታው በስፖርት መሳተፍ እንደሚችል ያስረዳል።

በዚሁ መሠረት በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት የፌዴራል መስሪያ ቤቶች የሚሳተፉበት የስፖርት ለሁሉም ውድድርና ፌስቲቫልን መጀመሩ ይታወሳል።

ይህን መነሻ ያደረገው የኢትዮጵያ ቼስ ፌዴሬሽን 19ኛውን የስፖርት ለሁሉም የቼስ ስፖርት ውድድርን ዛሬ አስጀምሯል።

በሰፖርት ለሁሉም ውድድር ከተለያዩ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ የቼስ ስፖርት ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል።

የዓለም አቀፍ ቼስ ፌዴሬሽን ሴቶችን ለማበረታታት ወሩን በማስታወስ ባወጣው የውድድ መርሃ ግብር መሠረት ይህ ውድድር መካሄዱ ለየት ያደርገዋል።

የኢትዮጵያ ቼስ ፌዴሬሽን የመጀመሪያውን የሴቶች ልዩ ውድድር ቅዳሜ መጋቢት 12፣2018ዓ.ም እንደሚያካሄድም አስታውቋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚሰራበትና በሚማርበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል እየሰራ ይገኛል።

የስፖርት ለሁሉም ፕሮግራም ተቀርጾ ተግባራዊ እየሆነ ያለውም የዜጎችን በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የመሳተፍና ተጠቃሚ የመሆን መሰረታዊ መብት ለማረጋገጥ ነው።
ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር

ማስተዋል ቼዝ አካዳሚ በይፋ ተመረቀ! የልጆችንና የአዋቂዎችን የስትራቴጂያዊ አስተሳሰብ እና የፈጠራ አቅም ለማሳደግ ያለመው "ማስተዋል የአዕምሮ ማበልፀጊያ ተቋም" በአዲስ አበባ አያት አካባቢ...
15/02/2026

ማስተዋል ቼዝ አካዳሚ በይፋ ተመረቀ!

የልጆችንና የአዋቂዎችን የስትራቴጂያዊ አስተሳሰብ እና የፈጠራ አቅም ለማሳደግ ያለመው "ማስተዋል የአዕምሮ ማበልፀጊያ ተቋም" በአዲስ አበባ አያት አካባቢ ዘመናዊ የቼዝ አካዳሚ የካቲት 7/2018 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ አስመርቋል።

በአዳማ ከተማ በ2015 ዓ.ም የተመሠረተው ማስተዋል የአዕምሮ ማበልፀጊያ ተቋም አሁን በአዲስ አበባ ተመርቆ ስራ በጀመረዉ የቼዝ አካዳሚ እድሜዉ ከ8 አመት ጀምሮ ያለ ሰዉ መሰልጠን እንደሚችል ተገልጿል።

ቼዝ ተራ ጨዋታ ሳይሆን የአዕምሮ ስፖርት መሆኑን እና ተቋሙ ቼዝን እንደ መሣሪያ የመረጠዉ የፈጠራ አስተሳሰብን ስለሚያዳብር፣ትኩረትን እና ትዕግስትን ስለሚያስተምር፣ ለአዕምሮ ጤና እና ለማህበራዊ እሴት ግንባታ ወደር ስለሌለው እንደሆነ ተገልጿል።

የአካዳሚው መስራች አቶ ፈለቀ ጌታቸው፣ ዓላማቸው ከመላው ዓለም ሰልጣኞችን የሚቀበል በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ግዙፍ ተቋም መገንባት እንደሆነ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ቼዝ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ተሾመ በቀለ እንደገለጹት የነገ ግራንድ ማስተሮች መፍለቂያ ይሆናል ያሉት ይህ ተቋም ለሀገራችን የነገ የቼዝ ኮከቦችን (Grandmasters) ለማፍራት ትልቅ ተስፋ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል።

ማስተዋል የቼዝ አካዳሚ ትርፍን ብቻ ሳይሆን ማህበረሰባዊ አገልግሎትንም ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ እና ለተለያዩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ነፃ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።

ተቋሙ በአካባቢ ደረጃ ብቻ ሳይወሰን፣ በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ እና ከመላው ዓለም ሰልጣኞችን ተቀብሎ የሚያስተናግድ ግዙፍ የቼዝ ማዕከል የመሆን ራዕይ እንዳለዉም በመክፈቻዉ ተገልጿል።
#ድሬቲዩብ

Address

Piassa
Hawassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia chess posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share