Sidama National Regional State Women's, Youth and Social Affairs Bureau

  • Home
  • Ethiopia
  • Hawassa
  • Sidama National Regional State Women's, Youth and Social Affairs Bureau

Sidama National Regional State Women's, Youth and Social Affairs Bureau This is official Sidama National Regional State Women's, Youth and Social Affairs bureau

የክልሉ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አመራሮች ለሀዋሳ ሀይቅ ዳሪቻ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ አደረጉ።ሀዋሳ፡ ግንቦት ፣07/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ) የህ/ግን/ዳይረክቶሬትየሲዳማ ክልል ...
15/05/2026

የክልሉ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አመራሮች ለሀዋሳ ሀይቅ ዳሪቻ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ አደረጉ።

ሀዋሳ፡ ግንቦት ፣07/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ) የህ/ግን/ዳይረክቶሬት

የሲዳማ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አመራሮች በቅርቡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ለዳሞ በተገኙበት በይፋ የተጀመረውን የሀዋሳ ሀይቅ ዳሪቻ ልማት ፕሮጀክት ለመደገፍ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ሰጡ።

የቢሮው ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ እመቤት ኢሳያስ መንግሥት በክልሉ እየሰራ ያለው ልማት የህዝቡን የመልማት ፍላጎት መሠረት አድርጎ መሆኑን አንስተዋል።

እንደ ሀገር የተጀመረው የከተማና የገጠር ኮሪደርን ጨምሮ ለትውልድ የሚሆን ፕሮጀክት እንዲሁም የቱሪዝም ማዕከልን ለማስፋትም በጠቅላይ ሚንስተር አቅጣጫ በክልላችንም ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን የጠቀሱት ቢሮ ኃላፊ በሀዋሳ ከተማ በቅርቡ ይፋ የተደረገው የሀዋሳ ሀይቅ ዳሪቻ ልማትን ሁሉም መደገፍ እንዳለበት በመጥቀስ እንደ ቢሮም አመራሩ ይህንን ድጋፍ ማድረጉ ልማቱን መምራት ብቻ ሳይሆን መደገፍ እንደሚቻል ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።

Sidaamu Qoqqowi Meentu Federeeshiine 7ki Doycho Gobboomu Doorshi Lifixinoha Assate   Meentu Towaataanora  Qajeelsha Uytu...
14/05/2026

Sidaamu Qoqqowi Meentu Federeeshiine 7ki Doycho Gobboomu Doorshi Lifixinoha Assate Meentu Towaataanora Qajeelsha Uytu
‎‎*********************************
‎Hawaasa, Onkoleessa 06, 2018 (MWDH biiro)

Sidaamu Qoqqowi Meentu Federeeshine 7ki Gobbomu Doorsha lifixanna amanamme nooha assate federeeshinete tantano miillanna doorshu towaataanora qajeelsha uytino.

Battalate leelte afii-fanote hasaawa assitinoti Qoqqowu Meentu Federeeshine Pirezidaante Dukko Gennet Maarqoositi ise widoonni, maamaru addi addi handaarinni tantantino meentu miilla kamalinoha ikkasi kulte, meentu ikkadimma buuxisiisate addi addi qajeelsha uynanni keeshshinoha ikkanna 350 ikkitanno maamaru miillaranna hattono 22 addi addi poletiku paarte riqiwamaanora huwanyootenna dhuku kaajjishshi qajeelsha uynoonnita coydhino.

Ledoteno tantano hanqaafaancho ikkasenni bisu gawajjo noonsa meento taalo beeqqisiisate looso loossinota kulte tini towaataano Onkoleessa 24,2018 ha'rinsanni doorshi aana daragaho leelte taalcho laonni xaaddanno mitiimma federeeshinete rippoorte shiqisha hasiissannonsata xawissino.

Qoqqowu Meentu Federeeshiine Aaantaancho Pirezidaante Dukko Wogiayyehu Wondimmuti ise widoonni, qajeelaano adhitino qajeelshi barra leellite mallaande nookki garinni taalu illachinni towaattanno gede hincilaallote qajeelsha ikkinota coydhino.

Hawaasi Quchumi Meentu Federeeshine Massagaancho Dukko Hiyiwet Beellamoti qajeelshu miilla adhitino qajeelshi wodhotenna lallawu garinninna doorshu ammanamino demokiraasennihanna keeraancho ikkannoha assate kaa'lanno ikkasi kulte riqinboommo dagara ammanamatenni loosa hasiissannotano qaagiissitino.

Barraho Qajeelshu beeqqaano hedonsa uytanni doorshu barra dargaho leellatenni xaadannore taalu garinni calla towaatate federeeshshinete rippoorte shiqishate qajeelshunni ikkado huwanyo afi'ransa coydhino.

በወጣቶች ስነተዋልዶ ጤና፣ በኤችአይቪና በፆታዊ ጥቃት መከላከለ እንዲሁም በወጣቶች ሰላምና ደህንነትና በዲጂታል ክህሎት ዙሪያ ግንዛቤ ተፈጠረ።ሀዋሳ፡ ግንቦት ፣07/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ) ...
12/05/2026

በወጣቶች ስነተዋልዶ ጤና፣ በኤችአይቪና በፆታዊ ጥቃት መከላከለ እንዲሁም በወጣቶች ሰላምና ደህንነትና በዲጂታል ክህሎት ዙሪያ ግንዛቤ ተፈጠረ።
ሀዋሳ፡ ግንቦት ፣07/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ) የህ/ግን/ዳይረክቶሬት

የሲዳማ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በወጣቶች ሰነተዋልዶ ጤና፣ በኤች አይ ቪ፣ የማህፀን ጫፍ ካንሰር በመከላከል፣ በፆታዊ ጥቃት መከላከል፣ በወጣቶች ሰላምና ደህንነት፣ በአዕምሮ ጤናናና በዲጂታል ክህሎት ዙሪያ ለትክቶኬሮች ግንዛቤ ተፈጥሯል።

በመድረኩ የቢሮው ም/ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ደስታ ለገሠ ወጣቱን በሁሉም መንገድ ተጠቃሚና ተሳታፊ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ አንስተው በክልሉ ሰፊውን ወጣት ለመድረስ ከአዳራሽ ስልጠና ባሻገር በዲጂታል አውታሮችን በመጠቀም በቲክቶከሮች አማካኝነት ለወጣቱ ግንዛቤ መፍጠር በማስፈለጉ ወጣቱ ጤናው እንዲጠብቅና ጤናማ ዜጋ እንዲፈጠር የቤተሰብ እቅድ ከወዲሁ ግንዛቤ እንዲያገኝና ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታ እንዲከላከል በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ቲክቶከሮቹ የራሳቸውን ኮንተንት ከመሥራት ባለፈ በትውልድ ላይ ለመሥራት መግባባት ላይ ተደርሷል።

አክለውም ወጣቱ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በመጠበቅ የሀገሪቱን ልማት ከመደገፍ አልፈው በሴት እህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃትን በመከላከልና በማጋለጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉና ወጣቱ ዘመኑን አስድሞ በመገንዘብ ለዲጂታል ዘመን ክህሎቱን ለማሳደግ የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በመውሰድ እራሱን እንዲያበቃ በርካታ ወጣቶች በቲክቶክ ግንዛቤ ማግኘት እንዳለባቸው አሳውቀዋል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ የቢሮ የወጣቶች ተሳትፎ፣ ማብቃትና ንቅናቄ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን ዶሎ በበኩላቸው በዚህ ጊዜ አብዛኛውን ወጣት ለማግኘት ቲክቶክ ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን ጠቅሰው ቲክቶኬሮች ከራሳቸው ከተለመደ ሥራ በተጨማሪ እንደዚህ ለወጣቱ የሚሆን ትምህርታዊ ሥራዎች መሥራት እንዳለባቸው አንስተዋል።

ቲክቶኬሮቹ በቀረበው ሰነድ ላይ ሀሳብ ሰጥቶ አብሮ ለመሥራት ውል በመግባት ተጠናቋል።

በይርጋለም ሀምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል ለታካሚዎች ድጋፍ ተደረገ።==================================የሲዳማ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በሀዋሳና በይርጋለም ሀ...
11/05/2026

በይርጋለም ሀምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል ለታካሚዎች ድጋፍ ተደረገ።
==================================

የሲዳማ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በሀዋሳና በይርጋለም ሀምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል በመገኘት በበሽታው ተጠቅተው በህክምና ላይ የሚገኙ ሴቶችን በመጠየቅ የተለያዩ ጥቃቶች ደርሶባቸው በሴቶች ማረፊያ ውስጥ የሚገኙ ሴቶችንና ህፃናትን በመጎብኘት የተለያዩ የገንዘብና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

ሀዋሳ፡ ግንቦት ፣ 03/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ) የህ/ግን/ዳይረክቶሬት

የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሴቶችና ህፃናት ዘርፊ ኃላፊ የተከበሩ ወ/ሮ ፍጹም በላይነህ በመሆን በይርጋለም ሀምሊን ፊስቱላ ሆስፒታ፣ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በአውሳዲ ሴቶች ማረፊያ እና በሀዋሳ ጣሊታ ሴቶች ማረፊያዎች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችና ህፃናት በአካል በመኘት ከመጠየቁም በላይ የተለያዩ የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።

የቢሮ ምክትል ኃላፊዋ በቦታው ተገኝተው ጥቃት ደርሶባቸው በሁለቱም ማረፊያዎች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችንና ህፃናት እንዲሁም በሀምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል በመገኘት በህክምና ላይ ለሚገኙ የተለያዩ ድጋፎችና ሴቶች ንጽሕና መጠበቂያ ማቴሪያሎችን ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት ስናገሩ እንደዚህ አይነት ድጋፎችን ቢሮው የተለያዩ አካላትን በማስተባበር በየጊዜው እያደረገ የቆዩ መሆኑን ገልፀው ለወደፊትም ድጋፊ ለሚሹ ወገኖቻችን ድጋፊ ማድረግን እንደሚቀጠሉ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በዕለቱ ለዳራ ወረዳ ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ለተጋላጭ ሴት ተማሪዎችና ልጃገረዶች የሚሆን የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና ለትምህርት ቤት ሴት ተማሪዎች የሚሆን ዲግኒቲ ኪት ከነቦርሳ ርክክብ ተደርጓል።

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችም ስተደረገላቸዉ ድጋፍ ቢሮውን አመስግነዋል የተረከቡትን የንጽህና ቁሳቁሶችን ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እንደሚያሰራጩ ገልፀዋል።

"ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል ለማህበራዊ ቁ-5 ብልፅግና ህብረት ስልጠና ተሰጠ።ሀዋሳ፡ ሚያዚያ ፣30/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ) የህ/ግን/ዳይረክቶሬትየሲዳማ ክልል ሴቶች፣ ...
08/05/2026

"ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል ለማህበራዊ ቁ-5 ብልፅግና ህብረት ስልጠና ተሰጠ።

ሀዋሳ፡ ሚያዚያ ፣30/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ) የህ/ግን/ዳይረክቶሬት

የሲዳማ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለማህበራዊ ቁ-5 ለብልፅግና ህብረት በብልፅግና ማኒፌስቶና ሌሎች የምርጫ ስነምግባርና እስካሁን ያለውን የምርጫ አፈፃፀምና እቅድ ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።

በመድረኩ የቢሮ ም/ኃላፊና ፋይናንስና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ሾንኮራ ሾዴ 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ገለልተኛና ሰላማዊ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንዳለባቸው ገልፀው የብልፅግና አባላት ፓርቲው እየሰራ ያለውን ልማት ለማስቀጠልና በምርጫው አሸንፎ መንግሥት እንድመሰርት የአካባቢው ሰላምን በመጠበቅ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው ተናግሯል።

አክለውም ብልፅግና ፓርቲ ግልፅ የመወዳደሪያ ማኒፌስቶ አዘጋጅቶ መንግሥት ለመመስረት ዝግጁ መሆኑን ገልፀው 7ኛ ሀገራዊ የምርጫ ስነምግባር ደንብ ሁሉም በመተግበር የድርሻቸውን መወጣት አለበት ብለዋል።

የ7ኛ ሀገራዊ ምርጫ የእስካሁኑ አፈፃፀምና እቅድ ግምገማዊ ሰነድ ያቀረቡት የቢሮ ም/ኃላፊና የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ፍፁም በላይነህ በበኩላቸው አደረጃጀትን በማጠናከር የምርጫውን ሂደት ማቀላጠፍና አባላቱ የወሰደውን ካርድ በምርጫ ዕለት በአግባቡ በአደረጃጀት ተጠርንፎ መምረጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የህብረቱ ሰብሳቢ አቶ ቦቼ ፀጋዬ አባላቱ በምርጫ ምዝገባ ወቅት ፓርቲያቸው ለመምረጥ ካርድ መውሰዱን ገልፆ ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ጊዜና ከምርጫ በኋላ አባላቱ የሚኖራቸው እንቅስቃሴ በምርጫ ስነምግባርና ደንብ መሠረት መሆን እንድሆን ገልጿል ።

የሀዋሳ ሞዴል የወጣቶች ማዕከል በቢሮ ኃላፊ ጉብኝት ተደረገበሲዳማ ብ/ክ/መ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ስር የሚገኘው የሀዋሳ ሞዴል የወጣቶች ስብዕና ግንባታ ማዕከል በቢሮ ኃላፊ በ...
08/05/2026

የሀዋሳ ሞዴል የወጣቶች ማዕከል በቢሮ ኃላፊ ጉብኝት ተደረገ

በሲዳማ ብ/ክ/መ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ስር የሚገኘው የሀዋሳ ሞዴል የወጣቶች ስብዕና ግንባታ ማዕከል በቢሮ ኃላፊ በክብርት ወ/ሮ እመቤት ኢሳያስ ጉብኝት ተደርጓል።

ሀዋሳ፡ ሚያዚያ ፣30/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ) የህ/ግን/ዳይረክቶሬት

በጉብኝቱ ወቅት ቢሮ ኃላፊ ወጣቱ አልባሌ ቦታ እንዳይውል የወጣቱ ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በክልላችን በብዛት እንደሚገኙ ጠቅሰው ይህ ሞዴል የወጣቶች ማዕከል ሰፊ ቁጥር ያላቸውን ወጣቶች ተጠቃሚ የሚያደርግና የወጣቱን ስብዕና ለመገንባት ትልቁ የወጣቱ ሀብት ነው ብለው ፓርቲያችን ብልፅግና ለወጣቱ ከሚሰጠው ትኩረት በቀጣይም ይህንን ማዕከል ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን መንግሥት አቅዶ እየሰራ እንደሆነ አንስተዋል።

የቢሮ ም/ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደስታ ለገሠ በበኩላቸው በክልሉ ለሚገኙ ማዕከላት ይሄኛው ሞዴል መሆኑን ጠቅሰው ማዕከሉ ከሚሰጣቸው አገልግሎት ላይብረሪ፣ ICT፣ ጂም ቤቶች፣ ተኳንዶ፣ እግር ኳስ፣ የሻውር፣ ካፊቴሪያና የDstv አገልግሎት እና ወዘተ ወጣቱ በስፋት እየተጠቀሙ ስብዕናቸው እየገነቡ እንደሆነ አንስተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና የማዕከሉ ስ/አስኪያጅ ጨምሮ ሌሎችም ተገኝተዋል።

‎የተሟላ የህፃናት የቅድመ ልጅነት እድገት ስራን ማጠናከር ይገባል - ክብርት ሂክማ ከይረዲን ********************ሀዋሳ፡ ሚያዚያ ፣21/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ) የህ/ግን/ዳይረክ...
30/04/2026

‎የተሟላ የህፃናት የቅድመ ልጅነት እድገት ስራን ማጠናከር ይገባል - ክብርት ሂክማ ከይረዲን
********************

ሀዋሳ፡ ሚያዚያ ፣21/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ)
የህ/ግን/ዳይረክቶሬት

በፌዴራል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባባሪነት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የቅድመ ልጅነት ዕድገት (ECD) Steering Committee አባላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱም በዋናነት ብሔራዊ ቅድመ የልጅነት እድገት መዳበር እና ትምህርት ፖሊሲ ማዕቀፍ ፣ ከቅድመ-ወሊድ ጀምሮ ዕድሜያቸው እስከ ሰባት ዓመት በሚሆናቸው ሕፃናት ላይ ያተኮሩ ፖሊሲዎችን ጨምሮ በዚህ የሕይወት ደረጃ ውስጥ ያሉ ሁሉም ሕፃናት ጥራት ያለው ቀዳማይ የልጅነት እድገት፣ መዳበር እና የቅድመ-መደበኛ ትምህርት እንዲያገኙ በማስቻል ፣ አካላዊ ፣ ሥነ-ልቦናዊ ፣ አእምሯዊ እና ማህበራዊ እድገታቸውን እንዲጠናከር ለማድረግ እንደሚረዳም ተነስቷል።

በእለቱም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር ድኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን አምራችና በስነ ምግባር የታነፀ ዜጋን ለማፍራት የተሟላ የህፃናት የቀዳማይ ልጅነት እድገት ስራን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አፅኖት ሰጥተዋል።

ሚንስትር ዴኤታዋ አክለውም ጥራት ያለው የቀዳማይ የልጅነት እድገት መዳበር ላይ የሚደረግ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት በዘላቂነት ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልዩነቶችን ለመከላከል እንደሚያግዝና ሀገራችን ወደ ጀመረችው የብልፅግና ጉዞ ለመድረስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደደሚኖረውም ተናግረዋል።

የቅድመ ልጅነት እድገትና መዳበር ላይ መስራት የተለያዩ ሴክተሮችን ተሳትፎና ድጋፍ የሚፈልግ እንደሆነ የገለጹት ክብርት ሂክማ ባለድርሻ አካላትን በሰፊው በማካተት እና ከአለም አቀፍ እይታዎች ጋር በማስተሳሰር ስታንዳርዶችን የማሻሻል ስራ መስራት ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የተቋማት የህፃናት የቀን መንከባከቢያና ማቆያ (ዴይኬር) እናቶች ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ፣ ህፃናትም ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲያድጉ ከፍተኛ ሚናን እንደሚጫወት የገለፁት ክብርት ሂክማ ለመንግስት ሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ዴይኬርን ማስፋፋት፣ የተከፈቱትን ስታንዳርዳቸውን ማሻሻልና ማሳደግ ፣ማህበረሰብ አቀፍ የህፃናት ማቆያና መንከባከቢያን ማስፋፋት በማህበረሰቡ ውስጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙና በራሳቸው ጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ የሚሰሩ እናቶችን ለማገዝ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

በሲዳማ ክልል የቅድመ ልጅነት እድገት ፖሊሲ በአመራሩ እና በማህበረሰቡ ውስጥ አጀንዳ ተደረጎ መያዙ ጥሩ እንደሆነ አንስተው በቀጣይ ትግበራውም በተሻለ መንገድ መፈፀም እንዳለበት ከስትሪንግ ኮሚቴው ጋር ተግባቦት ተፈጥሯል::

በርሀግብሩም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉ የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ ፣የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ የጤና ቢሮ ኃላፊ ፣ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን በንግግራቸው ለህፃናት ትኩረት ሰጥቶ መስራት ለነገ ትውልድ ምሶሶነው ብለዋል።

‎ለውይይቱ መነሻ የሚሆን የህፃናት የቅድመ ልጅነት ዘመን ዕድገትና ትምህርት ፖሊሲ አተገባበርን አስመልክቶ የባለድርሻ አካለት ሚናና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ማድረግ ተችሏል።

‎በርሀግብሩም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉ የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ፣ የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ የጤና ቢሮ ኃላፊ፣ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

4.5 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የተስፋ ትውልድ የማህበረሰብ የቀን የህፃናት ማቆያና መንከባከቢያ ማዕከል /Day-Care/ በይፋ ተመረቀሀዋሳ፡ ሚያዚያ ፣21/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ) የ...
29/04/2026

4.5 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የተስፋ ትውልድ የማህበረሰብ የቀን የህፃናት ማቆያና መንከባከቢያ ማዕከል /Day-Care/ በይፋ ተመረቀ

ሀዋሳ፡ ሚያዚያ ፣21/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ)
የህ/ግን/ዳይረክቶሬት

የሲዳማ ክልል ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከኢፌዲሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በPFC በተደረገ ድጋፍ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በቱላ ክ/ከተማ በጨፌ -ኮቲጄቤሳ ቀበሌ የተገነባው የማህበረሰብ የህፃናት ቀን ማዋያና መንከባከቢያ ማዕከል ስራ በይፋ ተመርቋል።

በፈዴራል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ህፃናት ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ወ/ሮ ሂክማ ኬይረዲን የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር በዛሬዋ ህፃናት ለይ በሚገባ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ህፃናት ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ምቹ የሆነ የጤና የትምህርትና የመጫወቻ ስፍራ መፍጠር ዴይ-ኬር አስፈላጊነቱ የላቀ ነው ብለዋል።

የሲዳማ ክልል ሴቶችና ህፃናት ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ እመቤት ኢሳይያስ የነገዋን ሀገር የሚረከቡ ህፃናትን ዛሬ ላይ መብታቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲያድጉ መሰረታቸው ላይ በማተኮር በእንክብካቤ እንዲያድጉ ዴይ-ኬር ተቋም ትልቅ ሚና እንዳለው ገልፀዋል ።

ይህ ተቋም ህፃናት ጤናቸው ተጠብቆ እንድያድጉና እንድማሩ እንዲሁም ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ የነገዋ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማነፅ ጉልህ ሚና እንዳለው ነው ሀላፊዋ የገለፁት።

በከተማ ደረጃ የመጀመሪያና ሞዴል ተቋም ስሆን ይህም ለህፃናት ክብር ባለው መልኩ ነው የተሰራው ብለዋል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እንደ ሀገር ብልፅግናችን ሰው ተኮር ሰራ የሚተገብር ሲሆን ይህም ከህፃናት እስከ አዋቂ ባለው የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ ተግባራዊ የሚደረገው መሰል አገልግሎት ነው ብለዋል።

ከንቲባው አክለው የነገ ተተኪ በሆኑ ህፃናት ላይ ትኩረት የተሰጠበት ስራ ሲሆን እናቶች ያለምንም ችግር ልጆቻቸውን የሚያሳድጉበትና እድል ያገኙበትን አጋጣሚ በመሆኑ ይሄንን ሞደል አድርጎ በመውሰድ በስፋት ተደራሽ እንዲሆን እንደሚሰራ አስረድተዋል።

አቶ ጥራቱ በየነ ለዚህ ስራ ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ለPFC ተቋምና ለተሳተፉ አካላት የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የPFC ስራአስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ብርክት ተቋሙ የህፃናት ቅድመ ልጅነት ላይ መስራት የጀመረ መሆኑን ገልፀው በዋነኝነት ከዜሮ እስከ 4 አመት ባሉ ህፃናት ልጆች በእንክብካቤ እንዲያድጉና እንዲማሩ የማቋቋም ስራ እንደሚሰሩ አስረድተዋል ።

ስራ አስኪያጇ ሐዋሳ ከተማ ከወትሮ በማደግ ለይ ያለች ከተማ ስትሆን 4.5 ሚልዮን ብር ወጭ ተደርጎ የተገነባውን ተቋም ዛሬ ርክክብ በማድረግ በቀጣይም በስፋት የሚሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በፕሮግራሙ የፈዴራል፣ የክልል፣ የከተማና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የክ/ከተማው አመራርና ነዋሪዎች ተገኝተዋል

ለዚህ ስራ ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የዕውቅናና ሰርተፍኬት ተሰጥቷል።

በአማራጭ ህፃናት ድጋፍና ክብካቤ በተቋማት አድገው የወጡና አገልግሎቱን በማግኘት ላይ ያሉ  ታዳጊ ወጣቶችን  የተሳታፍነትንና  የተጠቃሚነት መብታቸውን ከማረጋገጥ አኳያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካ...
26/04/2026

በአማራጭ ህፃናት ድጋፍና ክብካቤ በተቋማት አድገው የወጡና አገልግሎቱን በማግኘት ላይ ያሉ ታዳጊ ወጣቶችን የተሳታፍነትንና የተጠቃሚነት መብታቸውን ከማረጋገጥ አኳያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በሀዋሳ ከተማ በሴንተራል ሆቴል ተካሂዷል።

መድረኩ የተካሄደው ከአማራጭ ‎ድጋፍ ክብካቤ አድገው የወጡ ማህበራት ጥምረት ከሲዳማ ክልል ሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር ነው።

በዕለቱ በመድረኩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮ የሴ/ህ/መብ/ደህ/ማስ/ዳ/ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አክሊሉ አርጎ ስሆኑ በመልዕክታቸውም አንደ ቢሮው የህፃናትን መብትና ደህንነት እንዲሁም የተሳታፊነትና ተጠቃሚነት መብታቸውን ከማረጋገጥ አንፃር በርካታ ተግባር መፈጸማቸውን በመግለጽና ወላጆቻቸዉን ያጡና በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡ ህጻናትን በአማራጭ ህፃናት ድጋፍና ክብካቤ ሥራዎች በተለይ በተቋማዊ አገልግሎት(Institutional care) በርካታ ህፃናት ተጠቃም በማድረግ ላይ ይገኛል።

ነገር ግን ቀደም ሲል በአማራጭ ድጋፍና ክብካቤ አገሌግሎት አግኝተው ጨርሰዉ የሚወጡ ህፃናትን ተጠቃም የሚያደርግ ግልጽና ወጥ የሆነ የአሰራር ሥርዓት ባለመኖሩ ምክንያት ለሥነ ልቦናዊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በርካታ ታዳጊ ወጣቶች ለችግር ተጋላጭ መሆናቸውን አንስተው አሁን ደረጃውን የጠበቀ ግልጽና ወጥነት ያለው አገልግሎት መስጫ ስታንዳርድ በማዘጋጀት ከአማራጭ ክብካቤ የሚወጡ ታዳጊ ወጣቶች በዘላቂነት እራሳቻውን በማስቻል በተዘረጋው አሠራር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በተሠራው ሥራ በርካታ ወጣቶች ተጠቃም መሆን መቻላቸውን በመግለጽ አሁንም ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግስታዊ ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ማሳደጊያ ተቋማት የሥነ ልቦናና ምክር አገልግሎት እንዲሁም የሙያ ክህሎት ስልጠና፣ሥራ ማፈላለጊያና የሥራ ዕድሎችን በማመቻቸት ብዙ ሥራዎችን መሥራትና ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

አክለውም አቶ አክልሉ አርጎ ከአማራጭ ክብካቤ ጨርሰው የወጡ ወጣቶች በማህበር ደረጃ ተደራጅተው ሦስት ማህበራት ጥምረት ፈጥረው መብታቸውን ለማስከበር መንቀሳቀስ መጀመራቸው አመስግነው በሁሉም ህፃናት ማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ህፃናት የማህበሩ አባል በመሆን በጋራ ተደራጅተው መንቀሳቀስ እንደምገባቸው አሳስበዎል።

በመቀጠልም አቶ ደረጄ አበራ ‎የአማራጭ እንክብካቤ አድገው የወጡ ማህበራት ጥምረት ዋና ስራ አስኪያጅ በበኩላቸው ስለ ጥምረቱ ዓላማና አስፈላጊነት ዙርያ አጭር ገለፃ የሰጡ ስሆን ጥምረት በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸው በማጣት ከቤተሰብ ውጪ በሆኑ አማራጭ እንክብካቤዎች ውስጥ አድገው ለሚወጡና እና በተቋማት ደረጃ አገልግሎቱን በማግኘት ላይ ያሉ ወጣቶች መብት፣ ጥቅም እና ደህንነት ለማስከበር ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ ተሳታፊዎች ‎የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን የተነሱ ስሆን ሰፊ ውይይት በማድረግ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ምላሾችን በመስጠት የቀጣይ አቅጣጫ በመያዝ ውይይቱ ተጠናቀዎል።

የሴ/ወ/ማ/ጉ/የህ/ግን/ዳይ/ዳይሬክተር
ሀዋሳ

የሲዳማ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በሀዋሳ  ከተማ አስተዳደር ታቦር ክ/ከተማ በመገኘት የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ለጽ/ቤቱ ድጋፍ አድርገዋል።ሀዋሳ፡ ሚያዚያ ፣17/2...
25/04/2026

የሲዳማ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ታቦር ክ/ከተማ በመገኘት የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ለጽ/ቤቱ ድጋፍ አድርገዋል።

ሀዋሳ፡ ሚያዚያ ፣17/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ) የህ/ግን/ዳይረክቶሬት

የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ወ/ሮ እመቤት እሳያስ ከቢሮ ም/ኃላፊና የሴቶችና ህጻናት ዘርፍ ኃላፍ ጋር በመሆን በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ታቦር ክ/ከተማ ለሴቶችና ህፃናት ንጽህናቸውን እንዲጠብቁ የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

የቢሮ ኃላፊዋ በክ/ከተማ ተገኝተው ለተቸገሩ ሴቶች ንጽሕና መጠበቂያ ማቴሪያሎችን ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት ስናገሩ እንደዚህ አይነት ድጋፎችን በየጊዜው እያደረገ የቆዩ መሆኑን ገልፀው ለወደፊትም ድጋፊ ለሚሹ ወገኖቻችን ድጋፊ ማድረግን እንደሚቀጠሉ ተናግረዋል።

የክ/ከተማ ጽ/ቤት አመራሮችም ስተደረገላቸዉ ድጋፍ ቢሮውን አመስግነዋል የተረከቡትን የንጽህና ቁሳቁሶችን ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እንደሚያሰራጩ ገልፀዋል።

የሲዳማ ክልል ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የወጣት አደረጃጀቶች ፎረም ውይይት ተካሄደሀዋሳ፡ ሚያዝያ ፣15/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ) የህ/ግን/ ዳይረክቶሬትየሲዳማ ክልል ሴቶች ወጣቶች...
23/04/2026

የሲዳማ ክልል ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የወጣት አደረጃጀቶች ፎረም ውይይት ተካሄደ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ ፣15/2018 ዓ.ም (ሴወማጉቢ)
የህ/ግን/ ዳይረክቶሬት

የሲዳማ ክልል ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በወጣቶች አደረጃጀቶች አቅም ማጠናከርና በሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ውስጥ የወጣቶች ተሳትፎ ማሳደግ ዓላማ በማድረግ የፎረም ውይይት አካሂዷል።

የፎረሙን ውይይት የመሩት የቢሮው ም/ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደስታ ለገሰ ሲሆኑ፣ በንግግራቸው ወጣቶች በዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ የሀገር ልማትና ሰላም መሠረት መሆኑን ገልጸዋል።

በፎረሙ ላይ የተነሱ አጀንዳዎች በተለይም በሰባተኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ዙሪያ በስፋት ውይይት ተደርጓል፤ ውይይቱም ወጣቶች በምርጫ ቀን ብቻ ሳይሆን ከምርጫ ቀድሞ የሚካሄዱ ዝግጅቶች እና ከምርጫ በኋላ የሚከተሉ ሂደቶች ላይ ንቁ ሚና እንዲወስዱ አስፈላጊነቱ ተገልጿል።

ወጣቶች በምርጫ ቀድሞ የሚካሄዱ የምርጫ ምዝገባ ላይ ያሳዩትን ተሳትፎ በምርጫ ቀን ሰላማዊና ህጋዊ ሂደት እንዲጠበቅ በንቃት መሳተፍ እና ሁኔታዎችን በሰላማዊ መንገድ ማስተካከል
በድህረ ምርጫ ወቅት ባሉ ጊዜያት ሰላምን በማጠናከር ረገድ ሚናቸዉን መወጣት እንዲችሉ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ተጨማሪም የወጣቶች አደረጃጀቶች መደበኛ ስራዎች በተደራጀ መልኩ እንዲከናወኑ በአባልነት ማጠናከር፣ በአመራር ብቃት ማሻሻል፣ የፕሮግራም እቅድ እና ክትትል ስርዓት ማበረታታት እንዲሁም ከተለያዩ አጋሮች ጋር ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ በውይይቱ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳቦችን እና ተሞክሮዎችን በመጋራት ወጣቶች በሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ውስጥ አግባብ ያለ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚያግዙ የተግባር አቅጣጫዎችን አቅርበዋል።

ፎረሙ በመጨረሻ የወጣቶች አደረጃጀቶች በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ እንዲሰሩ እና በሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ውስጥ የሚገባ ድርሻ እንዲወስዱ አጠቃላይ ግብዓቶችን በማስቀመጥ ተጠናቋል።

Address

Street Of South Star To Piasa, Infront Of Meskel Square
Hawassa

Opening Hours

Monday 08:30 - 05:45
Tuesday 08:30 - 05:45
Wednesday 08:30 - 05:45
Thursday 08:30 - 05:45
Friday 08:30 - 05:45

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidama National Regional State Women's, Youth and Social Affairs Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Sidama National Regional State Women's, Youth and Social Affairs Bureau:

Share