12/08/2026
በሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በወንዶ ገነት ወረዳ ተካህዷል::
==========================
በተከላ መረሃግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያድረጉት የቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና እንደተናገሩት በሀገር ደረጃ እንዲሁም በክልል ደረጃ የተጀመረው ንቅናቄ አካል እንደሆነ ገልፆዎ በቢሮ በኩል አጠቃላይ ሰራተኞችና አመራር ተሳትፎ በማድረግ አሻራቸውን እንዲያኖሩ ታሳብ የተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል::
በሀገር ደረጃ የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ለምግብነት እና ለኢኮኖሚ ጥቅም የሚውሉ የፍራፍሬ፣ ቡና እና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብት ተክሎች ላይ በማድረጉ ቀጥተኛ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ይበልጥ ማረጋገጥ እየተቻል እንደሆነ ገልፆዋል።
በደን መመናመን ምክንያት እየደረሰ ያለውን ጉዳትን ለመቀነስ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሶ አመራሩና ሰራተኞች በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይፋ ከተደረገ አንስቶ ተሳትፎ በማድረግ የዜግነት ግድታቸውን እየተወጡ እንደሆነ ተናግሯል::
ችግኝ መትከል ለነገ ትውልድ ተስፋን መትከል በመሆን ከመትከል ባሻገር በየጊዜው እንክብካቤ በማድረግ የፅድቀት መጠኑን ለማሳደግ ይበልጥ መስራት እንደሚገባ ገልፆዋል::
ዛሬ የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ መኮትኮትና እንዲያድጉ ማድረግ የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አከባቢን ለመፍጠር እጅግ ወሳኝ መሆኑ ገልፆዎ በተፈጥሮ በተዋበች የወንዶ ገነት ወረዳ በመገኘት አሻራ ማሳረፍ መቻሉ የታሪክ አካል መሆን የሚያስችል ነው ተብለዋል::
በመረሃግብሩ ላይ የተገኙት የወንዶ ገነት ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ሃማሮ ሀይሶ እንደገለፁት በቢሮ በኩል የወንዶ ገነት ወረዳን መርጣችሁ የአረንጓዴ አሻራ ለማሳረፍ መምጣታችሁ ለነገ ትውልድ የሚሆን ተስፋን በወረዳችን ማሳረፋችሁ የወንዶ ገነት ወረዳን ይበልጥ በደን ሽፋን እንዲትሽፈን ከማድረግ ባሻገር በእለቱ የተተከለው የአቭካዶ ችግኝ በመሆኑ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ አብራርቷል::
በመረሃ ግብሩ ላይ የቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና ;የቢሮ ምክትል ኃላፊዎች ;የወረዳ አስተዳዳሪ አመራሮች እንዲሁም የቢሮ ሰራተኞች በሙሉ ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል::
===========================
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ሐምሌ, 06/2018 ዓ.ም
ወንዶ ገነት ሲዳማ
============================