11/02/2026
የ20ኛ ዓመት የምስጋና በዓል የክብር ግብዣ
"ወደ ቤትችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ!"
(Welcome Back Home!)
ውድ የቀድሞ ተማሪያችን፣
ያደጋችሁበትና ለዛሬው ማንነታችሁ መሰረት የሆነው የሐረር ሉተራን ቤተክርስቲያን የሕፃናትና ወጣቶች ልማት ፕሮጀክት 20ኛ ዓመቱን ያከብራል። ትናንት በልጅነታችሁ የዘራነው ዘር ዛሬ እናንተን የመሰሉ ትልልቅ ፍሬዎችን አፍርቶ በማየታችን ታላቅ ኩራት ይሰማናል።
በዚህ ታሪካዊ ቀን ከእኛ ጋር በመሆን ትዝታን እንድታድሱና የደስታችን ተካፋይ እንድትሆኑ በአክብሮት ተጠርታችኋል።
የፕሮግራሙ ዝርዝር፦
ቀን፦ የካቲት7፣ 2018
ሰዓት፦ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ
ቦታ፦ ሐረር ሉተራን ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ
"እስከዚህም ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል።" (1ኛ ሳሙኤል 7፡12)