ERCS Harari Regional Branch

ERCS Harari Regional Branch ERCS Harari Regional Branch is the first branch established in 1974 during Ethio-somali conflict.

Following the war Harari Regional branch provides humanitarian assistance for war victims by opening the office in harar town.

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ  የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ቀንን በታላቅ ድምቀት አከበረ።በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአለም አቀፍ ደረጃ "ትብብር ለሰብ...
10/05/2026

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ቀንን በታላቅ ድምቀት አከበረ።

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአለም አቀፍ ደረጃ "ትብብር ለሰብአዊነት "በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ቀንን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የባርድ አባላት፣ ሰራተኞች ፣ ወጣት በጎ ፍቃደኞች በጋራ በመሆን የተለያዩ የሰብአዊ ተግባራትን በማከናወን በታላቅ ድምቀት አክብረዋል።

የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ሀላፊ የሆኑት አቶ አስፋው ስንበቶ የእንኮን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል ። በማስከተል የቀይ መስቀል ወጣቶች ቀኑን የሚያወሳ ስነግጥም ፣ ትያትር እና የደም የመለገስ ተግባር አድርገዋል።
በመጨረሻም የቦርድ ሊቀመንበሩ ኢንጂነር አቶ ነቢል የሱፍ የመዝጊያ ንግግር እና አራት አመት ቅ/ጽ/ቤቱን አገልግለው ለተሰናበቱ የቦርድ አባላት ሽኝት በማድረግ ኘሮግራሙ ተጠናቆል።

ግንቦት 1/2018 ዓ/ም

ለሰብአዊነት እንኖራለን!!
---------------

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ  መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ የቦርድ አባላት ምርጫ አደረገ።በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስራ ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በማ...
23/04/2026

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ የቦርድ አባላት ምርጫ አደረገ።

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስራ ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩ የቦርድ አመራሮችንና አባላትን ሚያዚያ 14/2108 ዓ/ም በሐረር ከተማ መርጧል፡፡

በማኅበሩ የቅርንጫፎችና ሎካላይዜሽን ምክትል ዋና ጸሀፊው አቶ መሐመድ ጀማል በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕት፤ አባላትን ከማፍራት አኳያ ከፍተኛ ስራ መሰራት እንዳለበት የጠቆሙ ሲሆን የክልሉ መንግስትም በየደረጃው ማኅበሩን የመደገፍ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

የዕለቱ የክብር እንግዳ እና የሀረር ከተማ ከተማ ዋና ሀላፊ አቶ ካሊድ አብዲ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር በቀጣይ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጋር በተሻለ ትብብር እንደሚሰሩና ድጋፋቸውን በተሻለ ሁኔታ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የቦርድ ሊቀመንበር ኢንጂነር ነቢል ዩሱፍ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕት አስተላልፈዋል።

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሀላፊ የሆኑት አቶ አስፋው ሰንበቶ የአራት ዓመታት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትና የሁለት ዓመት የወደፊት እቅድ ለጠቅላላ ጉባኤው አቅርበዋል ።

በመጨረሻም ጉባኤው ኢንጂነር ነቢል የሱፍን የቦርድ ሊቀመንበር፣ አቶ አብይ አበበን ምክትል ሊቀመንበር እንዲሁም ወ/ሮ ኮኮቤ ሙላትን ዐቃቢ ነዋይ አድርጎ የመረጠ ሲሆን አቶ ፈቲህ መሀዲ፣ አቶ ያሲን አብዱላሂ፣ ዶ/ር ባህር አደም እና ወ/ሮ የኔነሽ ጥላሁን አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ሚያዚያ 15/2015 ዓ/ም

ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
---------------

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በመላው የሀገራችን ክፍሎች ከ የካቲት 14 እስከ መጋቢት 13 /2018 ዓ/ም የሚቆይ የሀብት ማሰባሰብ ዘመቻ በማረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል ።የሀረሪ ክልል ቅ/ፅ...
15/03/2026

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በመላው የሀገራችን ክፍሎች ከ የካቲት 14 እስከ መጋቢት 13 /2018 ዓ/ም የሚቆይ የሀብት ማሰባሰብ ዘመቻ በማረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል ።

የሀረሪ ክልል ቅ/ፅ/ቤትም ይህንን ዘመቻ በሰፊው ከበጎ ፍቃደኞቹ ፣ ሰራተኞቹ እና ከአባሎቹ ጋር በጋራ በመሆን ይህንን ተግባር በሰፊው በክልሉ ላይ በማከናወን ይገኛል።
።።።።።።።።።።።።።።
ይህንን መልካም ሀሳብ ተቀብላቹ ድጋፋችሁን ማድረግ የምትፈልጉ ማንኛውም ቀና ልብ ያላችሁ የክልላችን ነዋሪዎች ድጋፍችሁን
* በጥሬ ገንዘብ ።።።
*ምግብ ነክ በሆኑ እና ምግብ ነክ ባልሆኑ ቁሳቁሶች ።
በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኝት እንዲሁም በቅ/ፅ/ ቤቱ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000017625687 ማድረግ ይችላሉ ።
መጋቢት 5/2018 ዓ/ም

ለሰብአዊነት እንኖራለን!!

10/03/2026
01/03/2026

90 ብር ለ90 ዓመታት የሰብዓዊ አገልግሎት!
የእርስዎ ድጋፍ የብዙዎችን ህይወት ይታደጋል!

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበርን ይደግፉ!

ለሰብዓዊነት እንኖራለን!
---------------
90 Birr for 90 Years of Humanitarian Service!
Your support will save many lives!

Support the Ethiopian Red Cross Society

We Live for Humanity!
--------------------
በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለ ኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማኅበር ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇
For up-to-date information about the Ethiopian Red Cross Society on various social media options👇
📌Website: https://redcrosseth.org/
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/ethiopian-red-cross-society/
📌YouTube: https://www.youtube.com/
📌X(Twitter): https://x.com/EthioRedCross
📌Telegram: https://t.me/ERCSHQ
📌 Tiktok: https://www.tiktok.com/
📌 Flickr፡- 137615657@N05/" rel="ugc" target="_blank">https://www.flickr.com/photos/137615657@N05/

01/03/2026

Address

Shenkor
Harar
57

Telephone

+251256660527

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ERCS Harari Regional Branch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ERCS Harari Regional Branch:

Share