07/11/2025
የሐዘን መግለጫ
በሐረር ስካውት ካውንስል ታሪክ አንጋፋና ቀደምት ከሚባሉ የስካውት አባሎች እና አመራሮች ስማቸው የሚጠቀሰው አቶ አያሌው ዘውዴ ቀዳሚ ናቸው .
አቶ አያሌው ዘውዴ በስካውት ትልቅ ቦታ ያለውን የ አመራርነት ስልጠና በስካውት wood badge የተሰኘውን ስልጠና በቀዳሚነት የወሰዱና ለሐረር ስካውት ካውንስል ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ያሉ አመራር እንደነበሩም ይታወቃል አቶ አያሌው የ ሐረር ስካውት ካውንስል በሚፈልጋቸው ወቅት ሁሉ ከጎን በመሆን በሙሉ አቅማቸው ሲያግዙ እንደነበርና ክልላችን 8 ኛውን የኢትዮጵያ ስካውት ጃምቡሬ ሲያዘጋጅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ትልልቅ ሓላፊነቶችን ወስደው ካውንስሉ ፕሮግራሙን በተሳካ ሁኔታም እንዲያልቅ ያደረጉና አሁንም በካውንስሉ ውስጥ የአደልት ስካውት አመራር በመሆንና በመከታተል ላይ የሚገኙ ለካውንስሉ ትልቅ አቅም እና ብርታት የሚሰጡ አባታችን ነበሩ ቢሆንም ግን የፈጣሪ ትዛዝ ነውና አቶ አያሌው ዘውዴን ትላንት ጥቅምት 26-2018 አ.ም ምሽት በድንገተኛ ህመም አጥተናቸዋልና ለመላው የካውንስሉ አመራርና አባላት ለሚያውቋቸውና ለወዳጅ ዘመድ ሁሉ መፅናናትን እየተመኘን የአባታችንን ነብስ በአፀደ ገነት እንዲያሳርፍልን እንመኛለን ::
ጥቅምት 2-2018 አ.ም
ነብስ ይማር