19/08/2026
የሀረሪ ሉኃ ሙዳይ ድርጅት ከአመሽና የወጣቶች በጎ አድራጎት ማህብር ጋር በመተባበር ለተማሪዎች የሐረሪ ቋንቋ ስልጠና ተሰጠ።
የሐረሪን ቋንቋ ለማሳደግ የሚሰራው «ሀረሪ ሉኃ ሙዳይ» ድርጅት ከአመሽና የወጣቶች በጎ አድራጎት ማህብር ጋር በመቀናጀት፣ በክረምት የበጎ አድራጎት መርሃ-ግብር ላይ የክረምት የማጠናከሪያ ትምህረት ለሼኽ አቡበከር ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሐረሪ ቋንቋ መሰረታዊ አጻጻፍ እና የቋንቋ አመሰራረት ስልጠና ሰጥቷል።
መጽሐፉ በትምህርት ቢሮ እውቅና አግኝቶ በበርካታ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በመሰራጨት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ደራሲው ከዚህ ቀደም 8 መጽሐፍት የፀፈ ሲሆን በተጨማሪ አሁን ለህዝብ ለመድረሰ 9ኛ መጽሐፋ ዚግጅት ለይ እንደሆነ ተገልጿል።
«ሀረሪ ሉኃ ሙዳይ» ድርጅት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በዋትሳፕ፣ በቲክቶክ እና በዩቲዩብ ቻናሎቹ አማካኝነት የቋንቋ ማዘመን ስራዎችን ከማከናወኑ ባሻገር፤ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመዘዋወር ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል።
ቀደም ሲልም ለመጀመሪያ ጊዜ የሐረሪ ቋንቋ የጥያቄና መልስ እንዲሁም የንባብ ውድድሮችን ማካሄዱ ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የስልጠና መርሃ-ግብር ላይ በርካታ ወጣቶችና ተማሪዎች ንቁ ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን፣ በስልጠናው መጨረሻም ከፍተኛ ተሳትፎ ላሳዩ ተማሪዎች የመጽሐፍ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በመጨረሻም ድርጅቱ ለትምህርት ቤቱ አመራሮች፣ ለመምህራን እንዲሁም ከጎኑ በመሆን መርሃ-ግብሩን ላስተባበሩት ከአመሽና የወጣቶች በጎ አድራጎት ማህብር አባላት የላቀ ምስጋናውን አቅርቧል።