Menna elderly & mentally challenging support center

Menna elderly & mentally challenging support center Menna is a Non-governmental association committed and established to give care & support for the elderly, mentally ill who live on the streets of Gondar.

እንኳን አደረሳችሁ​ምስጋና ለጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት!​መና የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በማዕከሉ የሚኖሩ አረጋውያንን፣ ሕፃና...
09/04/2026

እንኳን አደረሳችሁ

​ምስጋና ለጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት!
​መና የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በማዕከሉ የሚኖሩ አረጋውያንን፣ ሕፃናትንና የአዕምሮ ሕሙማንን በምገባና በተለያዩ አገልግሎቶች በመደገፍ ላይ ይገኛል። ለነዚህ ወገኖቻችን የምገባ ፕሮግራም ዋነኛውና ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅብን የማገዶ እንጨት ግዢ ነበር።
​ይህንን ችግራችንን በመረዳት የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት በጠየቅነው ቅፅበት፣ እጅግ በሚያስደንቅ ፍጥነት ምላሽ በመስጠት ለማዕከላችን የሚሆን የማገዶ እንጨት በዛሬው ዕለት በድጋፍ አበርክቶልናል። ለዚህ አርአያነት ያለው በጎ ተግባራችሁ በማዕከሉ ስም ከልብ እናመሰግናለን!
​ሌሎች ተቋማትና በጎ አድራጊዎችም ይህንን ቅን ተግባር በመከተል፣ መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የግብዓት ድጋፎችን በማድረግ ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
​📍 አድራሻችን፦
ጎንደር ከተማ፣ ቀበሌ 15 (ከስታድየም ጀርባ ወይም ከቅርጫት ኳስ ሜዳ ጎን)
​🏦 የባንክ ሂሳብ ቁጥሮቻችን፦
​የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000089064868
​አማራ ባንክ፦ M1818
​📞 ለበለጠ መረጃና ድጋፍ፦
​WhatsApp፦ 0934641310 0934641309
​Telegram፦
​Facebook፦ መና የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል
​Email፦ [email protected]
​ #ሆሳዕና #ጎንደር #ትንሣኤ #ምስጋና

እነሆ፥ ከሰማይ እህልን እዘንብላችኋለሁ” (ዘጸአት 16:4)በዚህ የትንሳኤ በዓል፣ ልክ እንደ በምድረ በዳ እንዳልቆመ መና፣ የእንክብካቤ ማዕከላችንም ለአረጋውያንና ለአዕምሮ ህሙማን የርህራሄ ...
02/04/2026

እነሆ፥ ከሰማይ እህልን እዘንብላችኋለሁ” (ዘጸአት 16:4)

በዚህ የትንሳኤ በዓል፣ ልክ እንደ በምድረ በዳ እንዳልቆመ መና፣ የእንክብካቤ ማዕከላችንም ለአረጋውያንና ለአዕምሮ ህሙማን የርህራሄ መና ይሁን። ጌታ በሕይወት ተነስቶ፣ የሚያገለግሉትንም ሆነ የሚጠበቁትን በተስፋው ያጽና።

ለበጎ አገልግሎታችሁ የምስጋና ድጋፍ ሁሉ ይብራ!

​እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
​ፋሲካ የፍቅር፣ የደስታ እና የአዲስ ተስፋ በዓል ነው። በዚህ ታላቅ በዓል ላይ ማዕዳችንን ስንሰናዳ፣ ቤታችንን በሳቅና በደስታ ስንሞላ፤ አጋዥና ጠያቂ የሌላቸውን ወገኖቻችንን ማሰብ የትንሳኤውን በዓል ሙሉ ያደርገዋል።
​በመና የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የሚገኙ አባቶች፣ እናቶች እና ወንድሞቻችን የእናንተን ፍቅርና ደግነት ይሻሉ።
የእርሶ በረከት ለእነሱ የትንሳኤ ብርሃን ይሆናቸዋል!

​እንዴት መርዳት ይችላሉ?
#​በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ
#​የምግብ ቁሳቁሶችን በመለገስ ዘይት፣በርበሬ፣ሽንኩርት ፣በሬ፣ጤፍ
#​በዓሉን ከእነሱ ጋር በማሳለፍና ፍቅር በመስጠት
​የእርሶ ስጦታ ለአንድ አረጋዊ ፈገግታ፣ ለአንድ የአዕምሮ ህሙማን ደግሞ ተስፋ ነው!
​📌 ማዕከላችንን ለመደገፍና መረጃ ለማግኘት፦
ጎንደር ከተማ ቀበሌ 15 ከቅርጫት ኳስ ሜዳ ጎን ነው
📞 ስልክ፦ 0934641310/09
📱 Telegram: t.me/menacharity
🔵 Facebook: መና የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል
🎵 TikTok: mennaelderly

መና የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል   ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ።በዓሉ የሰላም ...
07/01/2026

መና የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ።በዓሉ የሰላም የጤና የፍቅር ይሁንልን።
ለአንድ_ሰው_ፈገግታ_ምክንያት_ይሁኑ

ይምጡና ይጎብኙን

አድራሻ፦ጎንደር ቀበሌ 15 ከቅርጫት ኳስ ሜዳው ጎን
📱09 34 64 13 09
📱09 34 64 13 10
የ ኢ.ን. ባንክ አካውንት
1000089064868

ለመላው ኢትዮጵያን  እንኳን ለ2018አዲስ አመት በሰላም አደረሳቹ።        ካለፈዉ መጥፎን እረስተን ጥሩ ነገሮችን እንዉሰድ አዲስ አመትን 🌼በአዲስ አስተሳሰብ እንቀበል🙏🌼 የኛን ድጋፍ ለ...
10/09/2025

ለመላው ኢትዮጵያን እንኳን ለ2018አዲስ አመት በሰላም አደረሳቹ።
ካለፈዉ መጥፎን እረስተን ጥሩ ነገሮችን እንዉሰድ አዲስ አመትን 🌼በአዲስ አስተሳሰብ እንቀበል🙏🌼 የኛን ድጋፍ ለሚሹ ሁሉ ምርኩዝ ሁነን በደግነት አዲሱን አመት እንቀበል🌻🌻🌻
ይምጡ አዲሱን አመት በመና የአረጋዉያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከሚገኙ ህፃናትና አረጋዉያን ጋር ያሳልፉ🙏
🌻🌻🌻🌻

!!!
🌻🌼
የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ብቅ ይበሉ...

ይጎብኙን! ።

🌻ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት
🌻ስልክ
+251582111718 +33664495674
+251934641309 +14257800316
+251934641310 +15713989298
Email:
[email protected]
በድህረ-ገፃችን
http://mennacenter.com
የ ኢ.ን. ባንክ አካውንት
1000089064868
አድራሻ
ጎንደር ቀበሌ 15 ከቅርጫት ኳስ ሜዳ ጎን

📍ስለ ህይወት 💡አንድ አባባል አለ በጣም የምወደው ''ቁም ነገሩ ምን ያህል እድሜ ኖረሀል ሳይሆን ምን አይነት ህይወት አሳልፈሀል'' ብዙዎቻችን ካለፍንባቸውን ህይወቶች የምንማረው እሩጫችንን ...
17/05/2025

📍ስለ ህይወት

💡አንድ አባባል አለ በጣም የምወደው ''ቁም ነገሩ ምን ያህል እድሜ ኖረሀል ሳይሆን ምን አይነት ህይወት አሳልፈሀል'' ብዙዎቻችን ካለፍንባቸውን ህይወቶች የምንማረው እሩጫችንን ከጨረስን በኋላ በእርጅና ትናንትን ስንመለከት ነው። በወጣትነታችን ያለፍንባቸውን የህይወት ዱካዎች አስተውለን ማጥናት ምንችል ቢሆን ግን ነጋችንን ብሩህ የማድረግ ትልቅ እድል ይኖረናል።

💡በዚህ አለም ላይ ቋሚ ነገር የለም።
ትላንታችን እንዳይቆጨን ዛሬአችንን አድምቀን የነጋችንን ስንቅ ለመሰነቅ ወደ መና የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ብቅ ይበሉ...

ትላንታቸው የደመቀ ዛሬ ቀን ገፍቶ ጧሪ ቀባሪ የሌላቸው አረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን እንዲሁም ህፃናትን የተጠለሉበት የህሊና መና የሚሸምቱበት ድንቅ ቦታ...

ይጎብኙን!

ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት
ስልክ
+251582111718 +33664495674
+251934641309 +14257800316
+251934641310 +15713989298
Email:
[email protected]
በድህረ-ገፃችን
http://mennacenter.com
የ ኢ.ን. ባንክ አካውንት
1000089064868
አድራሻ
ጎንደር ቀበሌ 15 ከቅርጫት ኳስ ሜዳ ጎን

መና የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል   ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ።
19/04/2025

መና የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ።

19/04/2025
ሰላም እንዴት ሰነበታቹ ውድ የማዕከላችን ቤተሰቦች ዛሬ 16-02-2017 ዓ/ም እለተ ቅዳሜ የእናታቸውን እሙሃይ ማንጠግቦሽ ፈለቀ(አመተሚካኤል)የነብስ ይማር(የፍታት) ኘሮግራማቸውን በማዕከላች...
26/10/2024

ሰላም እንዴት ሰነበታቹ ውድ የማዕከላችን ቤተሰቦች ዛሬ 16-02-2017 ዓ/ም እለተ ቅዳሜ የእናታቸውን እሙሃይ ማንጠግቦሽ ፈለቀ(አመተሚካኤል)የነብስ ይማር(የፍታት) ኘሮግራማቸውን በማዕከላችን ውስጥ የምሳ ኘሮግራም ሙሉ በሙሉ በማድረግ ያከናወኑ ሲሆን ከዚህ በተጨማረ የወር አስቤዛ እና የአልባሳት ድጋፍ እንዲሁም 10000(አስር ሺ ብር) በጥሬው ድጋፍ አድርገውልናል።
የእናታችንን ነብስ በአፀደ ገነት ያኑርልን ለቤተሰቦቻቸውም አምላክ ከክፉ ነገር ይጠብቅልን እመብርሃን ዋስ ጠበቃ ሁና ትቆምላቹ እግዚአብሔር ይስጥልን።
እናንተም ውድ ቤተሰቦቻችን እንደዚሁ ተዝካር፣ክርስትና፣ልደት፣ቀለበት፣ሰርግ፣እንዲሁም ህዝባዊ በአላትን በማዕከላችን ማክበር እንደምትችሉ እንገልፃለን።
መና የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል
አድራሻ:ጎንደር ቀበሌ 15 ከቅርጫት ኳስ ሜዳው ጎን
ስልክ ቁጥር:0934641309
0934641310
0582111718
የኢ/ን/ባ:1000089064868
ለአንድ ሰው ፈገግታ ምክንያት ይሁኑ

Address

Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Menna elderly & mentally challenging support center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Menna elderly & mentally challenging support center:

Share