የጎንደር ከተማ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ Gondar Cultural tourism & sport department

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • የጎንደር ከተማ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ Gondar Cultural tourism & sport department

የጎንደር ከተማ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ Gondar Cultural tourism & sport department ስፖርት ለሁሉም በሁሉም ቦታ፤

በጎንደር ከተማ አስ/ባ/ቱ/ ስፖርት መምሪያ ከጥር 30 እስከ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም በመካሄድ ላይ የነበረው ሮድ 2028 የእግር ኳስ ጨዋታ ፍፃሜውን አግኝቷል።የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ የጎ...
07/06/2026

በጎንደር ከተማ አስ/ባ/ቱ/ ስፖርት መምሪያ ከጥር 30 እስከ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም በመካሄድ ላይ የነበረው ሮድ 2028 የእግር ኳስ ጨዋታ ፍፃሜውን አግኝቷል።

የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ የጎንደር ከተማ አስ/ባ/ቱ ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ማርያም ካሳሁን ባስተላለፉት መልዕክት አገራችን ኢትዮጵያ የአፍሪካን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከመሰረቱት አገራት መካከል የምትገኝ ሲሆን በዘርፉ ያላትን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱ የሚታወቅ ነው፡፡

ለዚህም እንደ ምክንያት ከሚነሱት መካከል የስፖርት ማዘውተሪያ እጥረት ሲሆን ይህን ችግር ለመፍታት ከኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ በከተማችን ጎንደር የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እግርኳስ፤ ቅርጫት ኳስ ፤ ግራውንድ ቴንስ፤እና ሌሎች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራወች ተገንብተዋል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ሀገራት ለላቁ ስፖርተኞች ልማት የተለየ ትኩረት በመስጠት ከታዲጊ ወጣቶች መሠረታዊ የስፖርት ስልጠና ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የስፖርት ስልጠናዎች ድረስ ሀገራዊ ስትራቴጂዎችን እና ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ከፍተኛ የመንግስት በጀት መድበው ሲንቀሳቀሱ ይስተዋላል፡፡

የተተኪ ስፖርተኞች ልማትን በማጠናከር የአሸናፊ አገርን ግብ ለማሳካትና ስኬቱን ለማስቀጠል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ቢደረጉ በሚፈለገው መጠን ውጤታማ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ክቡር የኢ.ፌ.ዳ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠትና በተለየ አግባብ (Intervention) በመውሰድ የተተኪ
ስፖርተኞች ልማት ስራን በተለይም በእግር ኳስ ስፖርት በአገሪቷ ያለውን የህዝቡን ፍላጎት እና ኢትዮጵያን የሚመጥን ውጤት በአህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ መድረኮች ላይ ለማስመዝገብ በእርሳቸው ተነሳሽነት (Initiative) ልዩ ስልት በመቀየስ ከመላ አገሪቱ በተወጣጡ አሳታፊ በሆነ መንገድ እና ልዩ እምቅ አቅም ያላቸውን (Talent) ታዲጊዎች በስፋት በመምመልና ልዩ ስልጠና በመስጠት አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መፍጠርን ያለመ ልዩ ፕሮግራም መሆኑን ገልፀዋል።

በውድድሩ ከ13 ዓመት በታች 27 ቡድን
ከ 15 ዓመት በታች 14 ቡድን
በአጠቃላይ 41 ቡድኖች 74 ጨዋታዎች በማድረግ ከ13 ዓመት በታች የቆየ ተስፋ 2 ለ 0 አራጋው ከ 15 ዓመት በታች ጎንደር ዮኒቨርስቲ 3 ለ 0 ጌች ማድሪድን በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤ ሆነዋል።

ለአሸናፊዎች ዋንጫ ለኮከብ ተጫዋቾች፣ግብ አግቢዎች፣አሰልጣኞች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ብዛት ያላቸው ታዳሚዎች ፕሮግራሙን ተከታትለዋል።

ዘንድሮው ሰኔ 4 በሚጀመረው  የ2026 የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላለፉት በርካታ አሥርተ ዓመታት ስንመለከተው የነበሩ አሰራሮች ዘንድሮ አይደገምም።የዓለም እግር ኳስ ማህበር ፊፋ የ2026 የዓለ...
06/06/2026

ዘንድሮው ሰኔ 4 በሚጀመረው የ2026 የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላለፉት በርካታ አሥርተ ዓመታት ስንመለከተው የነበሩ አሰራሮች ዘንድሮ አይደገምም።

የዓለም እግር ኳስ ማህበር ፊፋ የ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ደጋፊዎችን እና ተጫዋቾችን ይበልጥ የሚያቀራርብ ፍፁም አዲስ የጨዋታ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ይፋ አድርጓል።

• እነዚህም ተጫዋቾች ከጨዋታ መጀመሪያ በፊት በሁለት ትይዩ መስመሮች ተሰልፈው መቆም ቀርቷል።

• ሁለቱም ቡድኖች፣ ተቀያሪ ተጫዋቾችን ጭምር በማካተት በየራሳቸው የሜዳ ክፍል ውስጥ ክብ በመስራት ይቆማሉ።

• የሀገራት ብሔራዊ መዝሙር በሚዘመርበት ወቅት፣ በሁለቱም የሜዳ ክፍሎች ላይ የሁለቱን ተጋጣሚ ሀገራት ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማዎች በሜዳው ላይ በስፋት ይዘረጋሉ።

ይህ አዲስ አሰራር በቡድን አባላት መካከል ያለውን አንድነት ከማሳየቱም በላይ፣ በስታዲየም ውስጥ የሚገኙትን ደጋፊዎች ስሜት የሚያነቃቃና ለዓለም ዋንጫው ጨዋታዎች ልዩ ድምቀት የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል ።

የጎንደር አብያተ መንግስታት አስተዳደር መዋቅር ጥናት ለውይይት ቀረበ።የጎንደር ከተማ ዓለማቀፍ ቅርስ የሆነው የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስታት ቅጥር ግቢ አጠቃላይ ጥገና በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስ...
26/05/2026

የጎንደር አብያተ መንግስታት አስተዳደር መዋቅር ጥናት ለውይይት ቀረበ።

የጎንደር ከተማ ዓለማቀፍ ቅርስ የሆነው የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስታት ቅጥር ግቢ አጠቃላይ ጥገና በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ተነሳሽነት ከተጠገነ በኋላ

ቅርሱን እና በውስጡ የፈሰሱ መዋለ ሀብቶች፣ የተክኖሎጅ ግብዓቶ እና የዱር እንሰሳትን የማስተዳደር አቅም የሚፈጥር የሰው ሃይል ጥናት ለውይይት ቀርቧል።

በአብክመ ባህል፣ቱሪዝምና ሰፖርት ቢሮ፣ አማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲና በጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ በኩል የተዘጋጀው ይህ ጥናት ከብርት ም/ከንቲባ ወ/ሮ ደብሬ የኋላ፣ የባህልና ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ማሪያሟ ካሳሁንና በተከማው ውስጥ የሚገኙ የባህልና የቱሪዘም ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችና በላድርሻ አካላት በተገኙበት መድረክ በቀረበ ጥናት።

በጎንደር ከተማ ውስጥና አካባቢው የሚገኙ የአብያተ መንግታትና ልዩ ልዩ ቅረሶችን በዘላቂነት ለማሰተዳደር የገቢ ምንጭ ለማሰደግና ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል አደረጃጀት መፈጠር እንዳለበት በጥናቱም ከ96 ላይ የሰው ኃይል እንደሚያስፍልግ ቀርቧል።

ክብር ም/ከንቲባ ወ/ሮ ደብሬ የኋላ ለቀረቡ ጥያቄዎች እና ሃሰቡች ምላሽ የሰጡ ሲሆን የሰው ሃይሉ ቅርሶቻቸን በዘላቂት ለመጠበቅና ለመከባከብ እንዲሁም በማስተዋወቅ የኢኮኖሚ ፋይዳቸውን በማሳደግ የሚጫወተው ሚና ጉልህ መሆኑን ጠቁመዋል።

የጎንደር ከተማ የባህልና ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ማሪያም ካሳሁን ተነሳሽነቱን ወድሶ ጥናቱን በማስጠናት ተግባራዊ እንዲሆን የክልሉን የባህልና ቱሪዝም ስፖርት ቢሮ እንዲሁም አመራሩን የሚያደርገው ድጋፍ ካመሰገኑ በኋላ ጥናቱ ዳብሮ በሥራ ላይ እንዲውል እንደ መምሪያ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚደርሱ አሳስበዋል።

ጎንደር - የመናገሻ ከተማ!በሕይወት ዘመን የግድ ሊጎበኙ ከሚገቡ ቦታዎች መካከል ጎንደር አንዷ ናት፡፡ ጎንደር ረቂቅ ጥበብ ያረፈባቸው አብያተ መንግሥታት፣ ከፍተኛ ሀይማኖታዊ ፋይዳ ያላቸው ቀ...
25/05/2026

ጎንደር - የመናገሻ ከተማ!

በሕይወት ዘመን የግድ ሊጎበኙ ከሚገቡ ቦታዎች መካከል ጎንደር አንዷ ናት፡፡ ጎንደር ረቂቅ ጥበብ ያረፈባቸው አብያተ መንግሥታት፣ ከፍተኛ ሀይማኖታዊ ፋይዳ ያላቸው ቀደምት አብያተ - ክርስቲያናት እና የሌሎችም ባህላዊና ተፈጥሯዊ መስህቦች መገኛ ናት ፡፡

ከጎንደር ህያው ቅርሶች መካከል አብያተ መንግስታት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡ የጎንደር ዘመን አብያተ መንግስታት በአንድ የሚገኙበት የአጼ ፋሲል ግቢ ስፋት 70,000 ካሬ ሜትር ይሆናል፡፡ ግቢው ከ17ኛውና 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ መሪዎች ከነበሩ ነገሥታት መካከል የስድስቱን አብያተ መንግስታትና ሌሎች በርካታ የሕንፃ ፍርስራሾችን ይዞ ይገኛል፡፡ በአሁን ሰዓት በፋሲል ግቢ የሚገኙ አብያተ መንግስታት እና ሌሎች የግብር ሕንጻዎች እድሳት ተጠናቆ ጎብኝዎችን በአዲስ መንፈስ በማስተናገድ ላይ ይገኛል፡፡

በጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ስፖረት መምሪያ እና በአቡነ ሳሙኤል ት/ቤት በትብብር ያዘጋጁት 2nd Grand Samuel school Champion cup ውድድር  ፍፃሚውን አግንቷል...
18/05/2026

በጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ስፖረት መምሪያ እና በአቡነ ሳሙኤል ት/ቤት በትብብር ያዘጋጁት 2nd Grand Samuel school Champion cup ውድድር ፍፃሚውን አግንቷል።

ግንቦት 09/2018 ዓ.ም በዚህ ውድድር ላይ
አቡነ ሳሙኤል 1ኛ እና 2ኛ ደረጀ ት/ቤት
ብሪጅ 1ኛ እና 2ኛ ደረጀ ት/ቤት
ጃፓን 2ኛ ደረጀ ት/ቤት
ፋሲለደስ ጥቁር 2 2ኛ ደረጀ ት/ቤት
ቅዱስ ጊዮርጊስ 1ኛ ደረጀ ት/ቤት
ጎንደር አካዳሚ ት/ቤት ት/ቤት ተሳተፊ መሆናቸው ይታወቃል።

በፍፃሜው ጨዋታዎች የ1ኛ ደረጃ የት/ቤቶች የዋንጫ ጭዋታ ቅዱስጊወርጊስ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 1 አቡነ ሳሙኤል 0 በሆነ ውጤት አሽናፊ በመሆን ቅዱስጊወርጊስ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የ🏆ተሻላሚ ሆናል።

በፍፃሜው ጨዋታዎች የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች
አቡነ ሳሙኤል2ኛ ደረጃ ት/ቤት 7 ብሪጅ ት/ቤት 0 በሆነ ውጤት አሽናፊ በመሆን አቡነ ሳሙኤል2ኛ ደረጃ ት/ቤትየ🏆ተሻላሚ በመሆን ፍፃሜውን አግንቷል።

በመርሃ ግብሩ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኃላን ጨምሮ ሌሎች የመምሪያ ኃላፊዎች ተገኝተው ለአሸናፊዎች የ🏆ለኮኮብ ተጫዋቾችና ግብ አግቢዎች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት አበርክተዋል።

በጎንደር ከተማ ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ሲካሄድ የቆየ የእግር ኳስ ውድድር ተጠናቀቀ ።7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ በጎንደር ከተማ ሲካሄድ የቆየው የብልጽግና አመራሮች  የእግ...
18/05/2026

በጎንደር ከተማ ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ሲካሄድ የቆየ የእግር ኳስ ውድድር ተጠናቀቀ ።

7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ በጎንደር ከተማ ሲካሄድ የቆየው የብልጽግና አመራሮች የእግር ኳስ ውድድር በ“መደመር” ቡድን አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

ከግንቦት 05 እስከ 09/2018 ዓ.ም ድረስ በጎንደር ከተማ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ በ4 ቡድኖች ተከፍሎ በመምሪያዎችና በክፍለ ከተሞች መካከል ሲካሄድ የነበረው የእግር ኳስ ውድድር ዛሬ ተጠናቋል።

በመርሃ ግብሩም ብልጽግና ፓርቲ በስፖርቱ ዘርፍ ያስመዘገባቸው ስኬቶች ወደፊትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

በውድድሩ ኮከብ ተጫዋች በመሆን ከ“መደመር” ቡድን ነፃነት መንግስቴ የተሸለመ ሲሆን፣ ኮከብ ግብ አግቢ ደግሞ እያንዳንዳቸው 4 ግብ በማስቆጠር ታዘባቸው ነጋ ከ“መደመር” እና አድኖ አያና ከ“ስንዴ ነዶ” ቡድን በጋራ ተሸላሚ ሆነዋል።
ለአሸናፊዎቹም የተዘጋጀ ሽልማት ተበርክቷል።

“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!”

የጎንደር ከተማዋ አስተዳደር ባ/ቱ/ስፖርት መምሪያ ወርሀዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከተለያዩ የስፖርት ማኅበራት...
16/05/2026

የጎንደር ከተማዋ አስተዳደር ባ/ቱ/ስፖርት መምሪያ ወርሀዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

ግንቦት 08/2018 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከተለያዩ የስፖርት ማኅበራት የተውጣጡ የከተማዋ ነዋሪዎች የጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሐግብር አካሂደዋል።

ከስፖርታዊ እንቅስቃሴው በተጨማሪም ብልጽግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ እጩ ትውውቅ እና ቅስቀሳ አካሂዷል።

‎በጋራ ስፓርታዊ እንቅስቃሴው የተለያዩ የከተማዋ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

‎በመርሐ ግብሩ የተገኙት የጎንደር ከተማ ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ማርያም ካሳሁን ጤናን ለመጠበቅ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ልምድ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል። ስፖርቱን የበለጠ ለማበረታታት በከተማዋ የሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች እየለሙ መኾኑን ገልጸዋል።

‎ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ ሰርከስ እና መሰል የቤት ውስጥ እንቅስቃሴዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መኾኑንም አንስተዋል።

‎በተካሄደው የጋራ ስፖርት የተሳተፉ የስፖርት ማኅበሩ እና የብልጽግና ፓርቲ አባላት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር ለሰላም እና ለአንድነት የጎላ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።

‎በከተማዋ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግሥት እየሠራቸው ያሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ዘርፉን የሚያጠናክሩ መሆኑን በተሳታፊዎች ተጠቅሷል።

የጎንደር ከተማ አሰተዳደር ባ/ቱ ስፖርት መምሪያ በአገልግሎት አሠጣጥና የደንበኞች አያያዝ ለተቋሙ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ ።ግንቦት 07/2018 ዓ.ም ስልጠናው በአገልግሎት አሠጣጥና የደንበኞ...
15/05/2026

የጎንደር ከተማ አሰተዳደር ባ/ቱ ስፖርት መምሪያ በአገልግሎት አሠጣጥና የደንበኞች አያያዝ ለተቋሙ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ ።

ግንቦት 07/2018 ዓ.ም ስልጠናው በአገልግሎት አሠጣጥና የደንበኞች አያያዝ፣ ኢኮኖሚዊ ጠቀሜታ ላይ ያተኮረ ሲሆን።

የስልጠናው ዓላማ በባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የሚሠጡ አገልግሎቶችን በእውቀት ላይ ተመስርቶ በመስጠት የውስጥና የውጭ ደንበኞች ለማርካት በማለም የተዘጋጀ ነው

የመጀመሪያውን ስልጠና እንዳልካቸው ኪዴ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማርኬቲንግ ት/ት ክፍል መምህር ።

ሁለተኛውን ርዕስ በዶ/ር ስመኝ ብርሃን የኢኮኖሚክስ ት/ት ክፍል ተመራማሪ አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን

በስልጠናው የተሳታፊዎች ከባ/ቱ/ስፖርት መምሪያ ከ4ቱም ቡድኖች የተውጣጡ 18 ሙያተኞች የተሳተፉ ሲሆን

መድረኩን በማመቻቸት አቶ አይቸው አዲሱ ሃላፊነት የወሰዱ ሲሆን ስልጠናውን የከፈቱት የመምሪያው ተወካይ አቶ ጌታሁን ስዩም እንዲሁም 2 የሲቪል ሰርቢስ ሙያተኞች በመታደም አዎንታዊ ድጋፋቸውን ስጥተዋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር /ባ/ቱ/ስፖርት መምሪያ ግንቦት 03/2018 ዓ.ም የስፖርት አበረታች ቅመሞች( ዶፒንግን)የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና  ተሰጠአበረታች ቅመሞች ጉዳይ የኢትዮጵያን ብቻ ...
11/05/2026

የጎንደር ከተማ አስተዳደር /ባ/ቱ/ስፖርት መምሪያ ግንቦት 03/2018 ዓ.ም

የስፖርት አበረታች ቅመሞች( ዶፒንግን)
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

አበረታች ቅመሞች ጉዳይ የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የዓለም ስፖርት ላይ ስጋት እንዲያንዣብብ አድርጓል።

ስፖርቱ በጣም እያደገ እና እየዘመነ፣ በቴክኖሎጂ እየታገዘ ሲሄድ አበረታች ቅመሞች ጉዳይም በዚያው ልክ እየተወሳሰበ ነው።

ይሁን እንጅ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የተከለከሉ ጸረ-አበረታች መድሃኒቶችን መጠቀም አሁንም የዘርፉ ትልቅ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል።

ይህ ችግር በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን ስፖርተኞችም ጭምር ተስተውሏል።

ከዚህ አኳያ ስፖርተኞችም፣አሰልጣኞች እና የሚመለከተው የስፖርት ፣ አስተዳደር ባለሙያዎች እነዚህ ፀረ-አበረታች ቅመሞች

በአትሌቶች ላይ ከሚያስከትሉት ከባድ ቅጣት በተጨማሪ የአገርንም ገፅታ በመጥፎ ጎን የሚያጠለሹ በመሆኑ ስልጠናዎችና ውድድሮች ከእነዚህ መድሃኒቶች የፀዱ ሆነው እንዲካሄዱ።

የከተማች የተለያዩ የስፖርት አይነቶች አሰልጣኞች ግንዛቤ ኑሯቸው ታዳጊ ወጣቶችን እንዲያሰለጥኑ ይህ የግንዛቤ መድረክ ተዘጋጅቷል።
ስልጠናውን ጎንደር ዮኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ ት/ት ክፍል መምህር ኤፍሬም ታምራት ዶ/ር ስልጠናውን ሰጠዎል።

የብልፅግና ፓርቲ እና የተፎካካሪ ፓርቲዎች የወዳጅነት የእግር ኳስ ውድድ በጎንደር ከተማ  አካሄዱ። የእግር ኳስ ውድድሩ በተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት በትብብርና በመተሳሰብ...
10/05/2026

የብልፅግና ፓርቲ እና የተፎካካሪ ፓርቲዎች የወዳጅነት የእግር ኳስ ውድድ በጎንደር ከተማ አካሄዱ።

የእግር ኳስ ውድድሩ በተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት በትብብርና በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ያስችላል ተብሏል።

በውድድሩ ላይ የተገኙት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ እና የብልፅግና ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ ቻላቸው ዳኘው

የእግር ኳስ ውድድሩ በተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል መካሄዱ በተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል መቀራረብን በመፍጠር በሀገረ መንግስት ግንባታ ጉልህ ሚና የሚጫወት መሆኑን ገልጸዋል ።

በህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የባህር ዳር ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ መኮነን ቢራራ ደግሞ የተካሄደው የእግር ኳስ ጨዋታ በተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል ወንድማማችነትንና በመደጋገፍ የጋራ ስራዎችን በጋራ ለመስራት መሰረት መሆኑን ተናግረዋል።

በዕለቱ በተካሄደው የእግር ኳስ ውድድር ብልፅግና ፓርቲ 8 ለ4 በሆነ ውጤት የተፎካካሪ ፓርቲዎችን የእግር ኳስ ቡድን አቸንፎ የተዘጋጀለትን ዋንጫ ወስዷል።

Address

Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጎንደር ከተማ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ Gondar Cultural tourism & sport department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share