WOFA WULA charity Development association/ ወፍ ውላ በጎ ልማት ማህበር

  • Home
  • Ethiopia
  • Gofa (1)
  • WOFA WULA charity Development association/ ወፍ ውላ በጎ ልማት ማህበር

WOFA WULA charity Development association/ ወፍ ውላ በጎ ልማት ማህበር Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from WOFA WULA charity Development association/ ወፍ ውላ በጎ ልማት ማህበር, Charitable organisation, Gofa (1).

27/07/2024
01/11/2023
wofa WULA charity Development association
20/10/2023

wofa WULA charity Development association

የባናካ ተራራ ፕሮጀክት ታሪካዊ አመጣጥ 🤟ባናካ ተራራን ቀደምት አባቶቻችን ዳና አሌ ክቤ ባናካ ብለው ጠርተዉታል ።ታሪኩን ስናይ በድሮ ጊዜ አሪ ብሔረሰብ የጎፋን አከባቢ እስከ ሎጤ ጎይሮ ወን...
20/10/2023

የባናካ ተራራ ፕሮጀክት ታሪካዊ አመጣጥ 🤟

ባናካ ተራራን ቀደምት አባቶቻችን ዳና አሌ ክቤ ባናካ ብለው ጠርተዉታል ።

ታሪኩን ስናይ በድሮ ጊዜ አሪ ብሔረሰብ የጎፋን አከባቢ እስከ ሎጤ ጎይሮ ወንዝ ደረስ ስለተቆጣጠሩ ካዎ ቡራቃ ናአ ኦሌ ክቤ እና ካዎ ቡራቃ ናአ ጋሞ ፃንጋ በጋራ በመሆን በመዋጋት የአሪ ብሔረሰብ የጎፋን አከባቢ ለቀዉ አሁን ወደሰፈሩበት አከባቢ እንድሄድ አድርገዋል ።

በመሆኑ በዉጊያዉ በጣም ስለደከሙ ማረፊያ ቦታ አድርገው የመረጡት አራቱን አቅጣጫ ለመቆጣጠር እና ለማየት ምቹ የሆነ ነፋሻማ ቦታ ነዉ ብለዉ ባናካ ተራራን መርጠው እዚያው አርፈዉ እንደነበር ቀደምት አባቶቻችን ይናገራሉ ።

ስለሆነም ባናካ ተራራ ካዎ ኮራ ወይም ጋጶ ተብሎ ይጠራል ፤ በሌላ በኩል ካልሣ ሉፃ ፣ ሉፄ ቶጋ ፀራ እና ፀራ ዜማ የተባሉ ኤራ ካዎዎች ዝናብ እንዲዘንብ ወደ ፈጣርያቸው ምማፀኑበት ታሪካዊ ተራራ ነው ።

ከዚህ ታሪካዊ ቅርስነት በተጨማሪ ባናካ ተራራ በከተማችን ካሉ ቦታዎች እጅግ በጣም ነፋሻማና ንፁህ አየር ያለበት ለመዝናኛ ምቹ ቦታ ከመሆኑም በላይ በተራራው አናት ላይ ሆኖ የከተማውን ሙሉ ገፅታ ማየት የሚቻልበት ሁኔታ ስላለ ለተመልካች ልዩ የመንፈስ እርካታን ይፈጥራል ።

በሌላ በኩል ከተራራው አቀማመጥ አንፃር የከተማውን ሥነ ምህዳር ለማስጠበቅ እና የጎርፍና የናዳ አደጋዎችን ለመከላከል ተራራዉን በአረንጓዴ ልማት ማስዋብ የህልውና ጉዳይ ስለሆነ ባናካ ተራራ ከሌሎች በተለየ መንገድ እንድመርጥ ምክንያት ሆኗል ።

የፕሮጀክቱ ዓላማ የባለ ድርሻ አካላትንና የህዝብ ተሳትፎ በማጎልበት አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን መሠረት ያደረገ የከተማዋን ሁለንተናዊ ብልጽግና ከማረጋገጥ ባሻገር አስተማማኝ የመዝናኛ ፓርክ በመገንባት በከተማችን ለኑሮ ፣ ለአገልግሎት ፣ ለንግድ ፣ ለመዝናኛ ፣ ለተለያዩ ፕሮግራሞች እና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው ።

የፕሮጀክቱ ያካተታቸው አገልግሎቶች መዝናኛ ማዕከላት ፣ የህፃናት መጫወቻ ቦታ ፣ ለሰርግ ለልደትና ለስብሰባዎች የሚሆኑ ቦታዎችና መለስተኛ አደራሽ እና አንድ ነጥብ አምስት (1.5) ኪ.ሜ የሚሸፍን የአስፋልት መንገድና የመሳሰሉት በዉስጡ ያካትታል ።

ባናካ ፕሮጀክት በሕዝባችን የ ጋለ ተሳትፎ ተጀምሯል በፍጥነትና በጥራት ይጠናቀቃል ።

መረጃውን ከባናካ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ነው ያገኘነው ።

Address

Gofa (1)

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WOFA WULA charity Development association/ ወፍ ውላ በጎ ልማት ማህበር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share