09/06/2024
Atileetoonni Filataman maaliif ummataaf ifa gochuu qabdu.
የፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፤
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ግንቦት 14/2016፣ ማርዮት ሆቴል
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች የተከበሩ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት፣ ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ዶ/ር ኤደን አሸናፊ፣ አቶ ዳዊት አስፋው፣ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ እና አቶ ቢልልኝ መቆያ የኢትዮጵያ የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክን ጨዋታዎች ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫውን በጋራ ሰጥተዋል።
በዚህም መሠረት አሁን ላይ አትሌቶች ከሚያዝያ 28/2016 ጀምሮ በተመረጠው ቤልቪው ሆቴል ገብተው ጠንካራ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን
እስከ አሁን በሰባት ክልሎች የኦሎምፒክ ችቦ እየተዟዟረ እንደሚገኝ እና በቀሪ ጊዜም በቀሪዎቹ ሰባት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚካሄድ በመግለጫው ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በፓሪስ ኦሎምፒክ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያሳተፈ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።እንዲሁም ከ200 ሺህ በላይ ዲያስፖራዎች በዉድድሩ ስፍራ እንዲገኙ በፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በቅርበት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በፓሪስ ኦሎምፒክ በማራቶን ኢትዮጵያን የሚወክሉ የመጨረሻ ተወዳዳሪዎች ከነተጠባባቂ ተመርጠውና ካምፕ አድርገው ልምምምድ የጀመሩ ሲሆኑ
በሌሎች የውድድር ተግባራት የመጨረሻ ተሰላፊዎች ዝርዝር ለሚኒማ ማምጫው በተቀመጠው ቀነ ገደብ መሠረት የሚታወቁ ሲሆን ጁን 14/2024 በስፔን ማላጋ በሚከናወነው የማጣሪያ ዉድድር የ10000 ሜትር ተወዳዳሪዎች እንደሚለዩ ተጠቁሟል ።