Kambata Development Association/KDA/ የከምባታ ልማት ማኅበር/ከልማ/

  • Home
  • Ethiopia
  • Durame
  • Kambata Development Association/KDA/ የከምባታ ልማት ማኅበር/ከልማ/

Kambata Development Association/KDA/ የከምባታ ልማት ማኅበር/ከልማ/ WELCOME, This is the real page of Kambata Development Association

19/06/2026

A destination of natural beauty and healing hot springs, thoughtfully developed by the Kambata Development Association/KDA/ የከምባታ ልማት ማኅበር/ከልማ/ to promote wellness and sustainable tourism.

Come and experience the refreshing charm of Gemesha Hambericho Hot Springs.

የሕጋ ሞዴል አዳሪ ትምህርት ቤት ተጀምሮ የቆመውን የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃ ለማስቀጠል የዝግጅት ምዕራፍ መጠናቀቁ ተገለፀ::የከምባታ ህዝብ ልማት ማኅበር ከሕጋ ሞዴል አዳሪ ትምህርት ቤት መም...
11/06/2026

የሕጋ ሞዴል አዳሪ ትምህርት ቤት ተጀምሮ የቆመውን የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃ ለማስቀጠል የዝግጅት ምዕራፍ መጠናቀቁ ተገለፀ::

የከምባታ ህዝብ ልማት ማኅበር ከሕጋ ሞዴል አዳሪ ትምህርት ቤት መምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች ጋር በመሆን ግንባታው ተቋርጦ የቆየውን የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃ ለማስቀጠል ያለመ ውይይት ማካሄዱ ተገለፀ። በውይይቱ የግንባታ ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ የትብብር እና የሀብት ማሰባሰብ ስልቶች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።

በውይይቱ ላይ እንደተገለፀው፣ የሕጋ ሞዴል አዳሪ ትምህርት ቤት በዞኑ ውስጥ የልዕቀት ማዕከል በመሆኑ ለተማሪዎች ምቹና ዘላቂ የመማሪያ እና የመኖሪያ አካባቢ መፍጠር ተቋሙ የሚያተኩርበት ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑ ተጠቁሟል። በዚህም መሠረት የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃውን ከማጠናቀቅ ባሻገር የመግቢያ በር ግንባታ እና በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ የውበት ማስጌጫ ሥራዎችን ለማከናወን ባለድርሻ አካላትን እና የከምባታ ዞን ተወላጆችን በማስተባበር በፍጥነት ሥራውን ለማጠናቀቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በመድረኩ ላይ የቀረበውን የፕሮጀክቱን ዲዛይን ወደ ተግባር ለመቀየር የትምህርት ቤቱ መምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች በጉልበት፣ በእውቀት፣ በገንዘብ እና በቁሳቁስ ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። እንዲሁም የሀብት ማሰባሰብ ሂደቱን በቅንጅት ለማስፈጸም የሚሰጣቸውን ኃላፊነት በመቀበል ከማኅበረሰቡ ጋር በመተባበር ሀብት የማሰባሰብ እና የህዝብ ንቅናቄ ሥራዎችን ለማከናወን ቃል ገብተዋል።

በውይይቱ መጨረሻ የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃ ግንባታን ጨምሮ ተያያዥ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ሁሉም አካላት በተቀናጀ መንገድ እንዲሰሩ በመስማማት መድረኩ ተጠናቋል። የከምባታ ህዝብ ልማት ማኅበር በቀጣይም ፕሮጀክቱን ወደ ፍፃሜ ለማድረስ ከባለድርሻ አካላት፣ ከተቋሙ ማኅበረሰብ እና ከዞኑ ተወላጆች ጋር በቅንጅት የሚሰራ መሆኑን አስታውቋል።

 #ገበታለሀምበሪቾ በኢፌዴሪ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ከፈለች ደምቦባ ለሀምበሪቾ የኢትዮጵያዊያን መንደር ግንባታ ፕሮጀክት 20,000 ብር አ...
10/06/2026

#ገበታለሀምበሪቾ

በኢፌዴሪ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ከፈለች ደምቦባ ለሀምበሪቾ የኢትዮጵያዊያን መንደር ግንባታ ፕሮጀክት 20,000 ብር አበርክተዋል።

ገበታ ለሀምበሪቾ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000746464871
:1000761497848
አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር: 013201588434000
ዳሸን ባንክ ሂሳብ ቁጥር: 5351865591021
ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ: 1049200203855
ብርሃን ባንክ: 1030986710069

ከላይ የቀረቡ የባንክ ሒሳብ ቁጥር አማራጮችን በመጠቀም "የጋራ ቤትዎን በጋራ ይገንቡ!!"

የተፈጥሮ እና የባህል መገናኛ—ውቡ የሀምበሪቾ 777 ኢኮቱሪዝም መንደር!ከተራሮች ግርማ ሞገስ ስር፣ በአረንጓዴ ምንጣፍ ከተሸለመው ማራኪ ተፈጥሮ ጋር ተስማምተው የተገነቡት ውብ ጎጆዎች የአካባ...
09/06/2026

የተፈጥሮ እና የባህል መገናኛ—ውቡ የሀምበሪቾ 777 ኢኮቱሪዝም መንደር!

ከተራሮች ግርማ ሞገስ ስር፣ በአረንጓዴ ምንጣፍ ከተሸለመው ማራኪ ተፈጥሮ ጋር ተስማምተው የተገነቡት ውብ ጎጆዎች የአካባቢውን ጥንታዊ የሕንጻ ጥበብ ያሳያሉ።

የሀምበሪቾ 777 ኢኮቱሪዝም መንደር ተፈጥሮን ከባህላዊ ማንነት ጋር አጣጥሞ የያዘ፣ ንጹሕ አየር የሚተነፍሱበት እና የኢትዮጵያን እውነተኛ መስተንግዶ የሚያዩበት ልዩ ስፍራ ነው። 🛖⛰

የቱሪዝም ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Tourism-Ethiopia

የሞዴል ወጣት አርሶ አደር አቶ አብነት ዴላም የዕውቅናና የ"አሻም" መርሀ ግብር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እና የከምባታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በሀሚዶ ጎፎሮ ቀበሌ አብነት ዴላሞ ...
08/06/2026

የሞዴል ወጣት አርሶ አደር አቶ አብነት ዴላም የዕውቅናና የ"አሻም" መርሀ ግብር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እና የከምባታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በሀሚዶ ጎፎሮ ቀበሌ አብነት ዴላሞ መንደር ተካሔደ።

የሞዴል አርሶ አደር አብነት የዕውቅናና የ"አሻም" መርሀ ግብር በከምባታ ዞን የንግዱ ማኅበረሰብ፣ በአዲሎ ዙሪያ ወረዳ ሕዝብ እና በቀበሌው ነዋሪዎች አነሳሽነት የተሰናዳ ሲሆን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮን ጨምሮ የከምባታ ዞን አስተዳደር፣ የከምባታ ሕዝብ ልማት ማኅበር፣ የዱራሜ፣ የሺንሽቾና የሀደሮ የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የአዲሎ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር፣ የአዲሎ ዙሪያ ወረዳ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት፣ በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳና በሀላባ ከተሞች የሚኖሩ የአብነት ወዳጆች እና ሌሎችም የዓይነትና የገንዝበ ስጦታ ለሞዴል አርሶ አደር አብነት አበርክተዋል።

በከምባታ ዞን አዲሎ ዙሪያ ወረዳ ሀሚዶ ጎፎሮ ቀበሌ በተካሔደው የሞዴል አርሶ አደር አብነት ዴላሞ የዕውቅናና የ"አሻም" መርሀ ግብር ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር፣ የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አረጋ እሸቱ፣ የከምባታ ዞን ዋና የመንግሥት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተክሌ ስዩምን ጨምሮ የክልል አመራሮች፣ የዞን አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ የከምባታ ዞን ካቢኔ አባላት፣ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

 #ገበታለሀምበሪቾ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ የሩሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መሀሩ መናሞ ለሀምበሪቾ የኢትዮጵያዊያን መንደር ግንባታ ፕሮጀክት 5,000 ብር አበርክተዋል።ገ...
28/05/2026

#ገበታለሀምበሪቾ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ የሩሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መሀሩ መናሞ ለሀምበሪቾ የኢትዮጵያዊያን መንደር ግንባታ ፕሮጀክት 5,000 ብር አበርክተዋል።

ገበታ ለሀምበሪቾ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000746464871
:1000761497848
አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር: 013201588434000
ዳሸን ባንክ ሂሳብ ቁጥር: 5351865591021
ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ: 1049200203855
ብርሃን ባንክ: 1030986710069

ከላይ የቀረቡ የባንክ ሒሳብ ቁጥር አማራጮችን በመጠቀም "የጋራ ቤትዎን በጋራ ይገንቡ!!"

 #ገበታለሀምበሪቾ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት መብት ማስከበርና ሕገ መንግሥት ግንዛቤ መፍጠር ባለሙያ አቶ ዳንኤል ደገፋ ለሀምበሪቾ የኢትዮጵያዊያን መንደር ግንባታ ፕሮጀ...
28/05/2026

#ገበታለሀምበሪቾ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት መብት ማስከበርና ሕገ መንግሥት ግንዛቤ መፍጠር ባለሙያ አቶ ዳንኤል ደገፋ ለሀምበሪቾ የኢትዮጵያዊያን መንደር ግንባታ ፕሮጀክት 2ሺ 500 ብር አበርክተዋል።

ገበታ ለሀምበሪቾ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000746464871
:1000761497848
አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር: 013201588434000
ዳሸን ባንክ ሂሳብ ቁጥር: 5351865591021
ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ: 1049200203855
ብርሃን ባንክ: 1030986710069

ከላይ የቀረቡ የባንክ ሒሳብ ቁጥር አማራጮችን በመጠቀም "የጋራ ቤትዎን በጋራ ይገንቡ!!"

  መንደር ግንባታበማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የፎረንሲክ ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር አብርሃም ብርሃኑ 1,000 ብር አበርክተዋል።ገበታ ለሐምበሪቾ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:...
28/05/2026

መንደር ግንባታ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የፎረንሲክ ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር አብርሃም ብርሃኑ 1,000 ብር አበርክተዋል።

ገበታ ለሐምበሪቾ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000746464871
:1000761497848
አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር: 013201588434000
ዳሸን ባንክ ሂሳብ ቁጥር: 5351865591021
ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ: 1049200203855
ብርሃን ባንክ: 1030986710069

ከላይ የቀረቡ የባንክ ሒሳብ ቁጥር አማራጮችን በመጠቀም "የጋራ ቤትዎን በጋራ ይገንቡ!!"

 #ገበታለሀምበሪቾ ኦሞ ባንክ ለሀምበሪቾ የኢትዮጵያዊያን መንደር ግንባታ ፕሮጀክት 1,000,000 ብር (አንድ ሚሊዮን ብር) አበርክቷል።ገበታ ለሀምበሪቾ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000746...
25/05/2026

#ገበታለሀምበሪቾ

ኦሞ ባንክ ለሀምበሪቾ የኢትዮጵያዊያን መንደር ግንባታ ፕሮጀክት 1,000,000 ብር (አንድ ሚሊዮን ብር) አበርክቷል።

ገበታ ለሀምበሪቾ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000746464871
:1000761497848
አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር: 013201588434000
ዳሸን ባንክ ሂሳብ ቁጥር: 5351865591021
ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ: 1049200203855
ብርሃን ባንክ: 1030986710069
ኦሞ ባንክ: 1030410282570502

ከላይ የቀረቡ የባንክ ሒሳብ ቁጥር አማራጮችን በመጠቀም "የጋራ ቤትዎን በጋራ ይገንቡ!!"

Address

Durame

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kambata Development Association/KDA/ የከምባታ ልማት ማኅበር/ከልማ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Kambata Development Association/KDA/ የከምባታ ልማት ማኅበር/ከልማ/:

Share