ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር/hafa charity association

  • Home
  • Ethiopia
  • Durame
  • ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር/hafa charity association

ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር/hafa charity association Charity

ጥር 08/2018 ዓ.ምዱራሜሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶለታል።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ''በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ ፬ '' በሚል...
16/01/2026

ጥር 08/2018 ዓ.ም

ዱራሜ

ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶለታል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ''በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ ፬ '' በሚል መሪ ቃል የተከናውን 2017 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የ2018 ዓ.ም የበጋ ወራት በጎ ፍቃድ ስራ ባስጀመረው ክልላዊ መድረክ ለሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር ላከናወናቸው ተግባራት ክልላዊ የዕውቅና ሰርተፍኬት አበርክቷል። ይህ ዕውቅና የሁሉም ቀና አሳቢ የሀፋ ቤተሰቦች ነውና እንኳን ደስ አላችሁ!!

መልካምነት ይቀጥላል!!

የእርዳታ ጥሪአንብቦ ሼር ማድረግም መልካምነት ነውዳንኤል ከበደ ወረቲ ይባላል የዳምቦያ 01 ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን በሙያው የጤና ባለሙያ ነው። በዳምቦያ ወረዳ ለዓመታት በጤናው ዘርፍ ገጠር ከተማ...
05/11/2025

የእርዳታ ጥሪ

አንብቦ ሼር ማድረግም መልካምነት ነው

ዳንኤል ከበደ ወረቲ ይባላል የዳምቦያ 01 ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን በሙያው የጤና ባለሙያ ነው። በዳምቦያ ወረዳ ለዓመታት በጤናው ዘርፍ ገጠር ከተማ ሳይል ህብረተሰቡን በታታርነት ያገለገለ አንጋፋ ባለሙያ ነው። ከአመታት በፊት መንግስታዊ ባልሆነ በጤናው ዘርፍ በሚሰራ ድርጅት በተለያዩ ክልልሎች ማ/ሰቡን አገልግሎ ድርጅቱ የስራ ጊዜው በማብቃቱ በጣነ ከመታመሙ በፊት በግሉ ፋርማሲ ከፍቶ እየሰራ ነበር።

ዳኒ በአሁኑ ሰዓት የደም ከንሰር ታማሚ ሆኖ ሆስፒታል ይገኛል። የደም ከንሰር ህክምና (blood cancer chemotherapy) በከፍተኛ ወጭ እየታከመ ይገኛል።

ዳኒ አቅም በፈቀደ ሁሉ በዳካሞች ጎን ሁሌም የሚቆም ቅን ሰው ነው። የሰውን እርዳታ የማይሻም ነበር። አሁን ግን ከብዶታል፤ቤተሰቡም ከአቅሙ በላይ ሆኖበታል። ፋርማሲውም አካውንቱም ባዶ ሆኗል። ቤተሰቡም ያለውን ጨርሷል። ልጆቹና ባለቤቱም እጅግ ተጨንቀዋል። ድረሱልን እያሉ ነው። ዳኒም ወገኖቼ እርዱኝ የሚል ጥሪ ባባለቤቱ በኩል አድርሶልናል።

የቀድሞ የሥራ ባልደረቦቼ፣ወዳጆቼና ሌሎችም ቅን አሳቢዎች አቅም የፈቀዳውን ሁሉ በማድረግ እርዱኝ ብሏል ወንድማችን ዳኒ።

እርዳታው የሚደረገው በባለቤቱ አካውንት ነው

የእርዳታ አካውንት:- 1000064756153 (አበበች ታጰኖ ወንታሞ)

ስልክ 0926549365 ( አበበች)

ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር የምስጋና የምስክር ወረቀት  ተበርክቶለታል።"ለተፋጠነ ሀገራዊ ዕድገት ለዜጎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በቅንጅት መስራት" በሚል መሪ ሀሳብ የከምባታ ዞን ሠራተኛና ማህ...
30/10/2025

ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።

"ለተፋጠነ ሀገራዊ ዕድገት ለዜጎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በቅንጅት መስራት" በሚል መሪ ሀሳብ የከምባታ ዞን ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርት፣ የክረምት በጎ ማጠቃለያ ሪፖርትና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ግብ ስምምነት ዙሪያ ባካሄደው የሴክተር ጉባኤ ለሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር በተለያዩ በጎ አድራጎት ስራዎች ላበረከተው አስተዋጽኦ የምስጋናና የምስክር ወረቀት ስጦታ አበርክቷል።

ይህ የዕውቅና ሰርተፍኬት የብዙ ደጋግ የኢትዮጵያ ልጆች ውጤት ነውና መላው የሀፋ ቤተሰቦች እኳን ደስ አላችሁ። በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያላችሁ ሙልካም አሳቢዎች ድካማችሁ ሁሌም ፍሬያማ ነውና ውጤቱ የጋራችን ነው። በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ።

መልካምነት ሁሌም ይቀጥላል፤ቅን እናስብ መልካም እንስራ!!

ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር!!

በዳምቦያ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያሽድጋፍ ተደረገጥቅምት 07/2018 ዓ.ም ዳምቦያሀፈ በጎ አድራጎት ማህባር ዘር፣ኃይማኖትና ብሄር ሳይለይ የተለያዩ ቀ...
17/10/2025

በዳምቦያ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያሽድጋፍ ተደረገ

ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም

ዳምቦያ

ሀፈ በጎ አድራጎት ማህባር ዘር፣ኃይማኖትና ብሄር ሳይለይ የተለያዩ ቀና አሳቢዎችን በማስተባበር ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖችን እየደገፈ እንደሆነ ይታወቃል። እንደከምባታ ዞን ትምህርት እሴታችን ነው በሚል መርህ የትምህርት ስራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል።

በመሆኑም ይህንን የትምህርት ስራ በትንሹም ቢሆን ለመደገፍ በማሰብ ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር በትናንትናው ዕለት በዳምቦያ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ለሶስቱም 1ኛ ደረጀ ት/ቤቶች የቾክና ስክብሪቶ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉም ለእያንዳንዳቸው 60 ግሮስ ቾክና 2 ፖኬት ስክፕርቶ ሲሆን የሶስቱም ት/ቤት ርዕሳነ መምህራን ተረክበዋል!! በመርሃ ግብሩ ላይም የዳምቦያ ከተማ አስተዳደር ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቴ ታምሬ ዶጀሞና የትምህርት ዩኒት ባለሙያዎች እንዲሁም የ1ኛ ሩብ ዓመት የትምህርት ስራ ግምገማ መድረክ ላይ የተሳተፉ የትምህርት ቤት አመራሮችና የዞን ደጋፊ ባለሙያ ተገኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ የነበሩ የክላስተሩ አስተባባሪ አቶ ታምሬ ዶጃሞ ማህበሩንና ማህበሩን የሚደግፉ ወገኖችን አመስግነዋል።

በጎ እናድርግ መልካም እናስብ!!

ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር!!

ጉብኝት #2እናታቸውን በተወለዱ 12ኛ ቀን በጨቅላ ዕድሜያቸው  መስከራም12/ 2015 ዓ.ም በሞት የተነጠቁ ሁለቱም መንታ ሴት ህፃናት መስከራም አበራ እና መስቀሌ አበራ እና  3 ዓመት ከ1 ...
16/10/2025

ጉብኝት #2

እናታቸውን በተወለዱ 12ኛ ቀን በጨቅላ ዕድሜያቸው መስከራም12/ 2015 ዓ.ም በሞት የተነጠቁ ሁለቱም መንታ ሴት ህፃናት መስከራም አበራ እና መስቀሌ አበራ እና 3 ዓመት ከ1 ወር ሆኖኣቸዋል

የአበራ ሎምቤቦን ልጆች አስታወሳችሁ 2015 ዓ.ም በወርሀ መስከራም እናታቸው ከወለደቻቸው በኋላ በ12 ቀን ዕድሜ ነበር ጨቅላ ህፃናት በሞት የተለየችው።

መስከራም አበራና መስቀሌ አበራ የተወለዱት በዳምቦያ ወረዳ ሄባ ዳቶ ቀበሌ ሲሆን የእናታቸውን እቅፍ እንደጀመሩ ነበር ከእናታቸው የተለያዩት።

በወቅቱ ይህንን ክስተት የሰመው ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር ከፈጣሪ በታች የህፃናቱን ህይወት ለመታደግ ደጋግ የኢትዮጵያን ልጆች በማስተባበር ወተት፣አልጋ፣ፍራሽ፣አልጋ ልብስ፣የንፅህና መጠበቂያዎች፣ቢምቢ መከላከያ አጎበር፣ የህፃናት ልብስ፣ለአባታቸው አልባሳትና የቀለብ ቦቆሎ ማበርከታችን ይታወሳል።

በዛው ዓመት የዳምቦያ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ያለውን ችግር ለዞን በማሳወቅ በክልል በጀት አሁን ያሉበት 42 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት ተሰርቶላቸዋል።

በተጨማሪም ሀፋ በጎ አድራጎት በየጊዜው ህፃናቱን በመከታተልና ድጋፍ በማድረግ ግዴታውን እየተወጣ ነው።

ዛሬ ደግሞ መስከራም 06/2018 ዓ.ም ማህበሩ ህፃናቱን በቤታቸው በመገኘት ጉብኝት በማድረግ የአልባሳትና ለተወሰና ቀን የሚሆን ቀለብ ድጋፍ አበርክቷል። ማህበሩ የደጋግ ኢትዮጵያውያን ልፋት ፍሬ አፍሪቶ ዕድሜያቸው 3 ዓመት ከ 1 ወር ሆኖ ትልልቅ ሆነው እያወሩ እየተጫወቱ በማየቱ እጅግ ደስተኛ ሆኗል። ደጋጎች ይህንን ፍሬ በማየታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ። ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ክብሩን ይውሰድ። ቀጣይም ከጎናቸው ሆነን ዕድሜያቸው ለትምህርት ስደርስ እናስተምራቸዋለን።

መደገፍ ለምትፈልጉ በሩ ክፍት ነው።

መልካምነት ይቀጥላል!!

ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር

እግዚአብሔር ሆይ ስራህ ድንቅ ነው፤ተመስገን።እናታቸውን በተወለዱ 7ኛ ቀን በጨቅላ ዕድሜያቸው  ሚያዚያ 2014 ዓ.ም በሞት የተነጠቁ ሁለቱም መንታ ህፃናት ዬጋ አብርሃም እና ማሳ አብርሃም 3...
16/10/2025

እግዚአብሔር ሆይ ስራህ ድንቅ ነው፤ተመስገን።

እናታቸውን በተወለዱ 7ኛ ቀን በጨቅላ ዕድሜያቸው ሚያዚያ 2014 ዓ.ም በሞት የተነጠቁ ሁለቱም መንታ ህፃናት ዬጋ አብርሃም እና ማሳ አብርሃም 3 ዓመት ከ7 ወር ሆኖኣቸዋል

የአብርሃም ግፋቶን ልጆች አስታወሳችሁ 2014 ዓ.ም በወርሀ ሚያዚያ እናታቸው ከወለደቻቸው በኋላ በሳምንት ዕድሜ ነበር ጨቅላ ህፃናት በሞት የተለየችው።

ዬጋ አብርሃምና ማሳ አብርሃም የተወለዱት በዳምቦያ ወረዳ ቦንጋ ቀበሌ ጮጭንጋ ሲሆን የእናታቸውን እቅፍ እንደጀመሩ ነበር ከእናታቸው የተለያዩት።

በወቅቱ ይህንን ክስተት የሰመው ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር ከፈጣሪ በታች የህፃናቱን ህይወት ለመታደግ ደጋግ የኢትዮጵያን ልጆች በማስተባበር የፋብሪካ ወተት፣አልባሳት፣ፍራሽ፣የወተት ላም፣ለአሳዳጊዋች ቀለብ እንዲሁም መኖሪያ ቤት የመገንባት ተግባር ማከናወኑ እንዲሁም 1ኛ ዓመት ልደታቸውን ጭምር ማክበሩ ይታወሳል።

በተጨማሪም ሀፋ በጎ አድራጎት በየጊዜው ህፃናቱን በመከታተልና ድጋፍ በማድረግ ግዴታውን እየተወጣ ነው።

ዛሬ ደግሞ መስከራም 05/2015 ዓ.ም ማህበሩ ህፃናቱን በቤታቸው በመገኘት ጉብኝት በማድረግ የአልባሳትና ለተወሰና ቀን የሚሆን ድጋፍ አበርክቷል። ማህበሩ የደጋግ ኢትዮጵያውያን ልፋት ፍሬ አፍሪቶ ዕድሜያቸው 3 ዓመት ከ 7 ወር ሆኖ ትልልቅ ሆነው እያወሩ እየተጫወቱ በማየቱ እጅግ ደስተኛ ሆኗል። ደጋጎች ይህንን ፍሬ በማየታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ። ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ክብሩን ይውሰድ። ቀጣይም ከጎናቸው ሆነን ዕድሜያቸው ለትምህርት ስደርስ እናስተምራቸዋለን።

መደገፍ ለምትፈልጉ በሩ ክፍት ነው።

መልካምነት ይቀጥላል!!

ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር

ካንተ_ጋር_ልብላ አንዲት የጎዳና ህፃን ለአንድ ቢሊዮነር ባለሃብት ያቀረበችው ጥያቄና...ብዙዎችን በእንባ ያራጨ ንግግር ነውበአንድ ቀዝቃዛ የጥቅምት ምሽት፣ ሪቻርድ ኢቫንስ በአንድ ደረጃውን ...
11/10/2025

ካንተ_ጋር_ልብላ

አንዲት የጎዳና ህፃን ለአንድ ቢሊዮነር ባለሃብት ያቀረበችው ጥያቄና...ብዙዎችን በእንባ ያራጨ ንግግር ነው

በአንድ ቀዝቃዛ የጥቅምት ምሽት፣ ሪቻርድ ኢቫንስ በአንድ ደረጃውን በጠበቀ የችካጎ ሬስቶራንት ውስጥ ተቀምጦ ነበር። ጠረንጴዛውን የእራት ሻማ ተለኩሶበት ልዩ ድባብ የሰጠው ሲሆን ስለ ስኬቱ እና ስለደረሰበት ደረጃ እያሰላሰለ ነበር።

ሪቻርድ ያዘዘውን ጣፋጭ ስቴክ ሊያጣጥም ሲዘጋጅ አንዲት በባዶ እግሯ የምትሄድ ትንሽዬ ልጅ "ጋሽዬ ካንተ ጋር ልብላ" አለችው። የህፃኗ አይን በርሃብ ፍዝዝ ብለው እና ልመናዋን ስታቀርብ የሚንቀጠቀጥ ድምጿን ሲሰማ አንጀት ትበላለች....

የሬስቶራንቱ ሰዎች እያዳፉ ሊያባርሯት ሲሉ አስቆማቸው እና ፈገግ ብሎ "ማነው ስምሽ" ሲል ጠየቃት።

"ኤምሊ እባላለሁ...ከአርብ ጀምሮ ምግብ አልቀመስኩም..." አለችው።

ወንበር ላይ አስቀምጧት ጥሩ እራት አበላት፤ ትኩስ ወተትም አጠጣት። እራቱን ስትመገብ ምግቡ ድንገት እንዳይጠፋባት የፈራች ይመስል በስስት ምግቡን እያየችው ነበር.....

ምግቡን ስትጨርስ ስለቤተሰቧ ጠየቃት። በሚያሳዝን ሁኔታ እንዲህ አለችው።

"አባቴ ሞቶብኛል፣ አያቴም ሞታለች፣ እናቴም ስላልቻለች ትታኝ ሄዳለች😭"

ሪቻርድ በሰማው አሳዛኝ ታሪክ ዝም ጭጭ ብሎ በፀጥታ ተዋጠ። እሱም በተመሳሳይ የህይወት መስመር አልፏል። ስኬታማ ከመሆኑ በፊት የጎዳናን ህይወት እና ረሃብን አሳምሮ ያውቀዋል። ከዛም ዝምታውን ሰበረ።

"ኤሚሊ ከኔ ጋር ወደ ቤት መሄድ ትፈልጊያለሽ❓ምቹ ምኝታ፣ በቂ ምግብ እና የትምህርት እድል ታገኛለሽ። ካንቺ አንድ ነገር እፈልጋለሁ...ትዕግስትና ጥረት።" አላት።

ከዛች ምሽት ጀምሮ ኤምሊ ረሃብን ተሰናበተችው። ድጋሜ ጭንቀት አልጎበኛትም፣ በትምህርቷም ጎበዝ ሆና ተማረች። ከኮሎምቢያ ዩንቨርስቲም ተመረቀች። በመጨረሻም "Can I eat with you?" " የተሰኘ የእርዳታ ድርጅት አቋቋመች። በዛ ድርጅት የተራቡ፣ ለጎዳና ህይወት የተጋለጡ እና የትምህርት ዕድል የተነፈጋቸውን ህፃናት መርዳት ጀመረች።

እናም አሁን ላይ October 15 ቀን ሪቻርድ ኢቫንስ እና ኤምሊ ወደዛ ሬስቶራንት እየሄዱ ልጆችን ምግብ ይመግባሉ።

እወዳችኋለሁ ❤ ከወደዳችሁት Mere Precious 👈follow

100,000 ብርከደቡብ አፍሪካ ሀፋ ቤተሰቦችከልጅነታቸው ቅንነትን ተያይዘው ያደጉ ቅን ወጣቶች ናቸው። መልካምነታቸው ሳይሸረሸር ከባህር ማዶ ዘልቋል። ጭቃውን፣ዝናቡን፣ፀሀዩንና ውርጩን ችለው ...
24/09/2025

100,000 ብር

ከደቡብ አፍሪካ ሀፋ ቤተሰቦች

ከልጅነታቸው ቅንነትን ተያይዘው ያደጉ ቅን ወጣቶች ናቸው። መልካምነታቸው ሳይሸረሸር ከባህር ማዶ ዘልቋል። ጭቃውን፣ዝናቡን፣ፀሀዩንና ውርጩን ችለው አስተባብረው ለበርካቶች ማረፍያ ቤት፣የእንጨት ድልድይ፣ማዕድ ማጋራት፣ቤቶችን መለጠፍ፣ከተማን ማፅዳትና ማስተባበር ሌሎችንም ስራዎች የሰሩና ያስተባበሩ ቅን የሀፋ መስራች አባላት ናቸው።

ዛሬም የምስኪኖች ጉዳይ እፎይ አላሰኛቸውም የእነዚህ ምስኪን እናቶች ፀሎትና ምርቃትም አልጣላቸውም። ባሉበት ሆነው ብዙዎችን አስተባብረው በሾፕ ቱ ሾፕ አካውንት ቀን ማታ አስተባብረው ለሀፋ ሼማታ 100,000 ብር ገቢ አድርገዋል።

በሁለቱም በሀፋ መስራች አባላት አስተባባሪነት በቅን የኢትዮጵያ ልጆች ለጋስነት 100ሺ ብር ገቢ ሆኗል።

ይህንን ያስተባበሩ ቅን አሳቢ የሀፋ መስራች ቤተሰቦች ረደሀኝ መነዶና በረከት ደረበ ናቸው። ምስጋናችን ከልብ ነው።

ለነዚህ ቅን ልቦች በመታዘዝ ካላችሁ ትንሽም ሆነ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ብድራቱን ከፈጣሪ ተቀበሉ። ባላችሁበት ፈጣሪ ይጠብቃችሁ።

መልካም መሳላ!!

ድጋፍ ማድረግ የምትሹ 1000666950608 ንግድ ባንክ

ሀፋ የሁሉም ጥላ!!

17/09/2025

የ2018 ዓ.ም የመሳለ በዓል ደረሷል
የሀፋ ሼማታ ድጋፍ ቤተሰቦች የተለመደው ትብብራችሁ ይቀጥል

በዳምቦያ ከተማ ከ200 በላይ ሰዎች ማዕድ የማጋራት ፕሮግራም ተካህዷል።ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ከተማ  ከሚገኝ  አንድ ቤተሰብ ጋር በመተባበር የ2018 ዓ.ም አዲስ...
12/09/2025

በዳምቦያ ከተማ ከ200 በላይ ሰዎች ማዕድ የማጋራት ፕሮግራም ተካህዷል።

ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ከተማ ከሚገኝ አንድ ቤተሰብ ጋር በመተባበር የ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከዳምቦያ ከተማና ከዳምቦያ ወረዳ ለተወጣጡ ከ200 በላይ አቅመ ደካሞች ማዕድ የማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል።

በዝግጅቱ ላይም የከተማ አስተዳደሩ ካንቲባ ክቡር አቶ ሰለሞን ገመስቀል፣የከተማ አድተዳደሩ ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ታምሬ ዶጀሞ፣የዳምቦያ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተሾመ ዮሐንስ፣ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ አዛዥ ኮ/ር ተክሌ ሆብቾ፣የከተማ አስተዳደሩ ማህበራዊ ክላስተር ባለሙያዎችና የሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር አባላት ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙ የድራ ኃላፊዎች ይህንን ቀና ስራ የሰሩ ቤተሰቦችና የሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር አባላትን አመስግነዋል።

ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበርም ለዚህ ቀና ስራ ትብብር ያደረጉ ቤተሰቦችን እጅግ አድርጎ ያመሰግናል።

መልካም አዲስ ዓመት

መስከራም 01/2018 ዓ.ም

ዳምቦያ

11/09/2025

መልካም አዲስ ዓመት!
Happy New Year!

መሳላ በዓልን ምንም ከሌላቸው እናት፣አባት፣እትና ወንድሞቻችን ጋር አብረን ማዕድ በመጋራት እናሳልፍ።ደቡብ አፍሪካ ያላችሁ ቀና አሳቢ ወዳጆቻችን የተለመደ ትብብራችሁን ከታች ባለው shop to...
02/09/2025

መሳላ በዓልን ምንም ከሌላቸው እናት፣አባት፣እትና ወንድሞቻችን ጋር አብረን ማዕድ በመጋራት እናሳልፍ።

ደቡብ አፍሪካ ያላችሁ ቀና አሳቢ ወዳጆቻችን የተለመደ ትብብራችሁን ከታች ባለው shop to shop በመጠቀም ስልፕ በውጥ መላክ ትችላላችሁ።

ለምታደርጉት ቀና ትብብር ከወዲሁ እናመሰግናለን።

ሀፋ የሁሉም ጥላ!!

Address

Right Side
Durame
YES

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር/hafa charity association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ሀፋ በጎ አድራጎት ማህበር/hafa charity association:

Share