Eastern Development Initiative

Eastern Development Initiative Eastern Development Initiative (EDI) is a nationally registered Ethiopian civil society organization, established in 2008 and headquartered in Dire Dawa.

EDI works across peacebuilding, education, health, livelihoods and climate resilience

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉየኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ ማንኤጅመንትና መላው ሰራተኞች እንኳን ለ1447 ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መ...
26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ
የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ ማንኤጅመንትና መላው ሰራተኞች እንኳን ለ1447 ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን በደስታ ይገልፃሉ።
ኢድ ሙባረክ

የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ (EDI) ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢንስቲትዩት ኣለም አቀፍ ድርጅት(LPI) ጋር በመተባበር በ2018 ዓ.ም.በሚያከናውነው ማህበረሰብ መር ሰላምን ለማፅናት  እና ...
26/05/2026

የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ (EDI) ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢንስቲትዩት ኣለም አቀፍ ድርጅት(LPI) ጋር በመተባበር በ2018 ዓ.ም.በሚያከናውነው ማህበረሰብ መር ሰላምን ለማፅናት እና ተሳትፎን መሰረት ያደረገ ተግባር ተኮር ምርምር ፕሮጀክት በድሬደዋ ከተማ በስድስት ወረዳዎች የመጀመሪያ ዙር የማህበረሰብ ውይይት ተካሄደ።
የማህበረሰብ ውይይቱ የተካሄደባቸው ወረዳ 1፤2፤4፤5፤8 እና 9 ሲሆኑ የወጣቶች ቡድንና የሴቶች ቡድኖች በየወረዳዎቹ በሰላም ዙሪያ የመጀመሪያውን ዙር የማህበረሰብ ውይይት አካሄደዋል።

የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ (EDI) ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢንስቲትዩት ኣለም አቀፍ ድርጅት(LPI) ጋር በመተባበር በ2018 ዓ.ም.በሚያከናውነው ማህበረሰብ መር ሰላምን ለማፅናት  እና ...
21/05/2026

የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ (EDI) ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢንስቲትዩት ኣለም አቀፍ ድርጅት(LPI) ጋር በመተባበር በ2018 ዓ.ም.በሚያከናውነው ማህበረሰብ መር ሰላምን ለማፅናት እና ተሳትፎን መሰረት ያደረገ ተግባር ተኮር ምርምር ፕሮጀክት በድሬደዋ ከተማ በስድስት ወረዳዎች በሰላም ዙሪያ ስለሚከናወኑት ተግባራት ከባለድርሻ አካላት ጋር የመጀመሪያ ዙር የውይይት መድረክ(Review meeting) አካሄደ።
የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግርማ ቱፋ ለመድረኩ ተሳታፊ የባለድርሻ አካላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ በ2017 ዓ.ም. ፕሮጀክቱ በሰላም ዙሪያ የተከናወኑትዝርዝር ተግባራትና የተገኙትን ውጤቶች ሪፖርት የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ የፕሮጀክት ግምገማና ክትትል ኦፊሰር አቶ ብርሀኑ ፈንቴ አቅርበዋል።
ፕሮጀክቱ ውጤታማነት እና ዘላቂነት እንዲኖረው ከማን ምን ይጠበቃል በሚለው ሀሳብ ላይ የባለድርሻ አካላቱ በሶስት ቡድን ተከፍለው ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ በሰጡት አስተያየት
• በፕሮጀክቱ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑት ተግባራት እና እስካሁን ባለው ሂደት ለማህበረሰቡ ያስገኘው ውጤትና ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን በማድነቅ ፕሮጀክቱ በከተማ ብቻ ሳይወሰን ወደ ገጠርም እንዲሰፋ
• በፕሮጀክቱ በሰላም ዙሪያ ውይይት ማድረግ ብቻ ሳይሆን ማህበረሰቡ አንድነቱንና ማህበራዊ ትስስሩን እንዲያጠናክር ማስቻሉ፤
• በማህበረሰቡ ውስጥ ያስገኘው ለውጥ የራሱን ችግር ተወያይቶ የመፍታት ልምድ ማዳበሩ፤
• በሰላም ግንባታው ሂደት ህብረተሰቡ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት መጨመሩ የሚሉትን አስተያየታቸውን በመስጠት በቀሩት ስራዎች እና የፕሮጀክቱ ቀጣይነት የሚያረጋግጡ አቅጣጫዎችን በመጠቆም የዕለቱ የውይይት መድረክ (Review meeting) ተጠናቋል።

የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ (EDI) ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢንስቲትዩት ኣለም አቀፍ ድርጅት(LPI) ጋር በመተባበር በ2018 ዓ.ም.በሚያከናውነው ማህበረሰብ መር ሰላምን ለማፅናት  እና ...
12/05/2026

የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ (EDI) ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢንስቲትዩት ኣለም አቀፍ ድርጅት(LPI) ጋር በመተባበር በ2018 ዓ.ም.በሚያከናውነው ማህበረሰብ መር ሰላምን ለማፅናት እና ተሳትፎን መሰረት ያደረገ ተግባር ተኮር ምርምር ፕሮጀክት በድሬደዋ ከተማ ስድስት ወረዳዎች ማህበረሰቡን በሰላም ዙሪያ ለሚያወያዩ የማህበረሰብ ውይይት አመቻቾች ጋር የመጀመሪያ ዙር የውይይት መድረክ(Quareterly review meeting) አካሄደ።

የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግርማ ቱፋ ለማህበረሰብ አወያዮች ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ የመክፈቻ ንግግር በየወረዳው የሚካሄደው የማህበረሰብ ውይይት በስድስት ወረዳዎች መሆኑንና በእያንዳንዱ ወረዳ ሀያ(20)አባላት የሚወያዩበት ሁለት ቡድኖች(የወንዶችና የሴቶች) አንደዚሁም በከተማ ደረጃ ከአረጋዊያንና ሀይማኖት አባቶች የተውጣጡ ሀያ አምስት(25) አባላትን ያቀፈ አንድ ቡድን በሰላም ዙሪያ ለስድስት ዙር የማህበረሰብ ውይይት እንደሚያደርጉና የማህበረሰብ አወያዮች ከምንጊዜውም በላይ ጠንክረው እንዲሰሩ የማበረታቻ ንግግር አድርገዋል።

ወ/ሮ መቅደስ ካሳሁን የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ ፕሮጀክት ኦፊሰር ለማህበረሰብ አወያዮች በተዘጋጀው የውይይት መድረክ(Review meeting) ላይ የሚከተሉትን አጀንዳዎች ለውይይት አቅርበዋል።
--Introducing the concept of the Project
--Negative and posetive peace
--Skils of dialogue
--Conflict Sensitivity
--Inclusivity of womens,Youths,Peoples with disabilities,
--Gender sensitivity
--Gender based violence
--How to prepare report,minutes and documetation. ከላይ በተዘረዘሩት አጀንዳዎች ላይ ወ/ሮ መቅደስና አቶ ብርሀኑ ፈንቴ የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ ፕሮጀክት ግምገማና ክትትል ኦፊሰር ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ ካደረጉ በኋላ ውይይቱን በመምራት ተወያዮች በእያንዳንዱ አጀንዳ ላይ የቡድንና የጋራ ውይይት አድርገዋል።
ከውይይቱ የተገኙ ጠቀሜታዎች
• የተካሄደው የውይይት መድረክ(Review meeting) የመጀመሪያ እንደመሆኑ የማህበረሰብ አወያዮች እርስ በእርስ በመተዋወቅ ልምዶችን የተለዋወጡበትና የስራ ግኑኝነታቸውን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ነበረው።
• የማህበረሰብ አወያዮች ማህበረሰቡን ሲያወያዩ የተለያዩ የጋራና የቡድን ውይይቶችን በማድረግ ችሎታቸውንና ክህሎታቸውን ማዳበር እና መማማር የሚያስችላቸውን ልምድ ቀስመዋል።።
• የማህበረሰብ ተወያዮችን እንዴት አድርገው መመልመል እና ውይይቱን መምራት እንደሚገባቸው በቂ ግንዛቤ አግኘወተዋል።

09/05/2026

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የታዛቢነት ዕውቅና የሰጣቸውን 55 ድርጅቶች ይፋ አደረገ
****
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫን ለመታዘብ ካመለከቱት የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች ውስጥ በሕጉ ላይ የተቀመጠውን መሥፈርት አሟልተው ዕውቅና የሰጣቸውን 55 ድርጅቶች ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ድርጅቶቹም በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የሚያሠማሯቸው 60 ሺህ 277 ወኪሎች ማስመዝገባቸውን እና የወኪሎቹ ቁጥር ከዚህ ሊጨምር እንደሚችል ከቦርዱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡።

የመታዘብ ዕውቅና ያገኙ ድርጅቶችን ዝርዝር ከታች ያገኛሉ፡-

1. ሆሊስቲክ ዴቭሎፕሜንት ኢንሼቲቭ አሶሴሽን
2. መሸሩመ ኢንተግረትድ ደቨሎፕመንት ኦርጋናይዘሽን
3. ምስራቃዊ ዕድገት ፋና
4. ሲራድ የምርምር እና የልማት ተቋም
5. ሳውዝ ዌስት በጎ አድራጎት ድርጅት
6. ሴንተር ፎር ኢምፓወርመንት ኢትዮጵያ ማህበር (ሲኢኢ)
7. ስቲም ፕላስ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት
8. ስታንድ ፎር ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት ኢትዮጵያ
9. ቃል የተቀናጀ የማህበረስብ ልማት ድርጅት
10. ቦሮ ሺናሻ ልማት ማህበር
11. ተስፋብርሃን ትግራይ በጎ ኣድራጎት ማህበር
12. ትምራን
13. አክሽን ፎር ሬዚሊያንስ
14. አፍርካ ሥራ ፈጠራና ዘላቂ ልማት የበጎ አድራጎት ድርጅት
15. አዲስ አበባ ሴቶች ፌደረሽን
16. የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት(ኢሰመድህ)
17. የኢትዮጵያ ሴቶች ልማት ድርጅት
18. የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት
19. ኦሮሚያ ሴቶች ማህበር
20. የመብቶቸ እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕክል
21. ኮሚዩኒቲ ሳስቴይነብል ዴቬሎፕሜንት ኤይድ(ኮስቲዳ)
22. የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር
23. የአማራ ክልል ወጣቶች ማህበራት ፌዴሬሽን
24. የአማራ ወጣቶች ማህበር
25. የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር
26. የኢትዩጰያ ወጣቶች ምክር ቤት
27. የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ማዕክላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ
28. የኢትዮጵያ ሰላም ፣ ልማት እና ብልፅግና ድርጅት
29. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ
30. የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፎረም
31. የኢትዮጵያ ሴቶች ፌደሬሽን
32. የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን
33. የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን
34. የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ(ኅብረት ለምርጫ)
35. ነርቸር ኢጁኬሽን ኤንድ ዴቭሎፕመንት
36. የኢትዮጽያ ሴት አካል ጉዳተኞች ብሄራዊ ማህበር
37. የኦሮሚያ ወጣቶች ማህበር
38. የኦሮሚያ ወጣቶች ፌዴሬሽን
39. የጎንደር ልማትና ሰላም ማኅበር ወይም ጎልሰማ
40. ደቡብ ምክክርና ልማት ፎረም
41. ድሬ የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት
42. ጥላሁነን የበጎ አድራጎት ማህበር
43. ፊውቸር ጀነሬሸን ሆፕ ፎር ቨልነረብል ችልድሬን ኦርጋናይዘሽን
44. ፕሮጃይኒስት
45. ኦሮሚያ ሴቶች ፌዴሬሽን
46. መስጠት በጎ አድራጎት ድርጅ
47. ራምኖን ኢትዮጵያ የዕውቀት ፓርክ ማህበር
48. ሰኔ አስራ ስድስት የሰላምና የለዎጥ ተምሳሌት የበጎ አድራጎት ማህበር
49. ሶሻል አሊያንስ ቻሪቲ አሶስዬሽን
50. የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር
51. ነፃ ትውልድ ሲቪክ ማህበር
52. አዎንታዊ ሰላም ለኢትዮጵያ
53. የተጋሩ የሰላምና ተሃድሶ ንቅናቄ ለኢትዮጵያ ማህበረ
54. የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማሕበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ)
55. የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች    እንኳን ለ2018 ዓ.ም ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል በሠላም አደረሳችሁ በማለት የኢስተርን ደበቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ ማንኤጅመንትና ...
12/04/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለ2018 ዓ.ም ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል በሠላም አደረሳችሁ በማለት የኢስተርን ደበቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ ማንኤጅመንትና ሰራተኞች መልካም ምኞታቸውን በደስታ ይገልፃሉ።

የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን ተመልካች በድሬዳዋ ስታዲየም ተገኝቶ እንዲከታተል ተገለፀ መጋቢት 22/2018 ከቀኑ 10 ሰዓት የኢትዮጵያ እና ሳኦቶሜ ጨዋታ በዝግ እንዲካሄድ ካፍ ውሳኔ አሳል...
31/03/2026

የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን ተመልካች በድሬዳዋ ስታዲየም ተገኝቶ እንዲከታተል ተገለፀ

መጋቢት 22/2018 ከቀኑ 10 ሰዓት የኢትዮጵያ እና ሳኦቶሜ ጨዋታ በዝግ እንዲካሄድ ካፍ ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በስታዲየሙ ዙርያ የተሰጡ የግምገማ አስተያየቶችን መሰረት በማድረግ በፍጥነት ለማስተካከል በወሰደው እርምጃ እንዲሁም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታው ለተመልካች ክፍት እንዲሆን ባደረገው ከፍተኛ ጥረት የካፍ ሴኪዩሪቲ ኦፊሰር በአካል ተገኝተው ከገመገሙ በኋላ በላኩት ሪፖርት መሰረት ካፍ 10,000 ተመልካች በስታዲየም ተገኝቶ እንዲከታተል ውሳኔ ማስተላለፉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሳወቋል ።በዚሁ መሰረት ደጋፊዎች እስቴድየም በመግባት ብሄራዊ ቡድናቾንን እንዳደግፉ ጥሪ ቀርቧል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉየኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ ማንኤጅሜንትና ሠራተኞች ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉእንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጢር በዓል በሰላም...
20/03/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ

የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ ማንኤጅሜንትና ሠራተኞች ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጢር በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ይገልፃሉ ።

በዓሉ ለመላው ኢትዮጵያኖች የመረዳዳት የሰላም፣ የደስታ እና የጤና እንዲሆንልን እንመኛለን።

ዒድ ሙባረክ

እንኳን ለመላው ጥቁር ህዝቦች ኩራት ምንጭ ለሆነው 130ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሠላም አደረሳችሁ።ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች የድል ዓርማ  ነው!መልካም በዓል!
02/03/2026

እንኳን ለመላው ጥቁር ህዝቦች ኩራት ምንጭ ለሆነው 130ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሠላም አደረሳችሁ።
ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች የድል ዓርማ ነው!
መልካም በዓል!

Address

Dire Dawa, Dire Mall
Dire Dawa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eastern Development Initiative posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share