14/04/2026
የዲላ ከተማ ጤና ስፖርት ማህበር የፋሲካን በዓል ምክንያት በማድረግ ለወገኖቹ የማዕድ ማጋራት ሥራ አከናውኗል ።
የኛን ሞት ገድሎ ህይወትን አበረከተልን በመስቀሉ ሰላምን ሰጠን ፣ ዘላለማዊ ፍቅርን አሳየን ፣ ተበድሎ ይቅር ማለትን አስተማረን ባስተማረን ትህትናና ፍቅር የማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች ባደረጉት ድጋፍ ለ50 የሚሆኑ አቅመ ደካሞች ወገኖቻችን ከ100 ሺህ ብር በላይ በማውጣት የማዕድ ማጋራት ድጋፍ ተደርጓል ።
ይህን የበረከት ሥራ በመልካም እንዲከናወን በገንዘብ፣ በጉልበት በሃሳብና ቦታ በመስጠት ለተባበራችሁን ሁሉ ክብረት ይስጥልን ።
በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የይቅርታ ይሁንልን !!
የዲላ ከተማ ጤና ስፖርት ማህበር !!